TG Telegram Group Link
Channel: Walta Tv ዋልታ ቲቪ
Back to Bottom
የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጫካ ፕሮጀክት ላይ እየሠሩ ላሉ ሠራተኞችን፣ ለበዓል በተዘጋጀ የምሳ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው፣ የእንኳን አደረሳችሁ መልክት አስተላልፈዋል::
ዛሬ የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ከአገርበቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ አፈፃፀም ጋር የተያያዙ ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ያላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል። - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የሀገር ውስጥ ምርትን በመጠቀም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ማስቀጠል ይገባል - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ግንቦት 1/2016 (አዲስ ዋልታ) የሀገር ውስጥ አምራቾችን በመደገፍ እና የሀገር ውስጥ ምርትን በመጠቀም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ማስቀጠል አለብን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች በግብዓት፣ በኢነርጂ፣ በገበያ እና በሰው ሀይል ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በተሻለ ወደ ውጤት ለመለወጥ መትጋት ይኖርባቸዋል ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።
በኮርደር ልማት መልሶ የተገነቡ የኤሌክትሪክ መስመሮች አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

ግንቦት 2/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርደር ልማት የኤሌትሪክ መስመር ማዛወር እና መልሶ ግንባታ ስራ አጠናቆ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገለጸ፡፡

በመስመር ማዛወር ስራው ወቅት የልማት ተነሺ ለነበሩ 2 ሺሕ 700 ደንበኞች በአዲስ መልክ በሰፈሩበት አካባቢ አዲስ ኃይል የማገናኘት ስራ መከናወኑም ተገልጿል፡፡

የኃይል መስመር ማዛወር ስራው በአጠቃላይ 68 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን በቀጣይ የኃይል መቆራረጡን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ታሳቢ በማድረግ 50 ኪ.ሜ የመካከለኛ እና 18 ኪ.ሜ የዝቅተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ማሻሻያ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡
ዛሬ ለጽዱ ኢትዮጵያ 50 ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር ለማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን ይካሄዳል

ግንቦት 4/2016 (አዲስ ዋልታ) በዛሬው ዕለት ለጽዱ ኢትዮጵያ 50 ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር ለማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን ይካሄዳል።

በጋራ ትርጉም ያለው በጎ ተፅዕኖ እንዲፈጠር፤ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ግንቦት 4 የሚከናወነውን የ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካቶች በመቀላቀል ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።

በዚህ ንቅናቄ እስካሁን ድረስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ባለሃብቶች፣ የተለያዩ ተቋማት እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎች አቅማቸው የፈቀደውን ገንዘብ በመደገፍ ለዓላማው መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

በርካቶች እየተቀላቀሉት ያለውን ይህን ንቅናቄ ዜጎች እንዲሳተፉ ለማድረግም ዛሬ  በአንድ ጀምበር 50 ሚሊዮን ብር ዲጂታል ቴሌቶን ተሰናድቷል፡፡

ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዛሬው ዕለት በሚካሄደው ለ #ጽዱኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን ድጋፋቸውን በማበርከት እነዚህን ስኬቶች እንዲደግሙ ተጋብዘዋል።

ለ#ጽዱኢትዮጵያ
For a #CleanEthiopia
በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይቀላቀሉ።
በቱሪዝም ፣ በመስተንግዶ እና በሆቴል ኢንዱስትሪ ተመርቃችሁ መስራት ለምትፈልጉ!!!
የአፍሪወርክ ቴሌግራም ቻናልን በመቀላቀል በየቀኑ በዚህ ዘርፍ ከሚወጡ አዳዲስ ስራዎች ተጠቃሚ ይሁኑ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑክ ጋር ተወያዩ

ግንቦት 8/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከትራንስፎርማቲቭ ግባችን አንዱ የሆነው የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶቻችንን በሚደግፉበት ዙሪያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የተንጸባረቀው ሀሳብ የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለበት ያልተጠየቀ ምክር ለመምከር የሞከረ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ግንቦት 8/2016 (አዲስ ዋልታ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የተንጸባረቀው ሀሳብ ሀሰተኛና ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በትናንትናው ዕለት ያደረጉት ንግግር በተረጋገጠ መረጃ ላይ ያልተመሰረተና በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣን መንግስት እንጥላለን በሚል የሚንቀሳቀሱ፣ ንጹሃንን ከሚያግቱና ከሚያሸብሩ አካላት ጋር መንግስትን መጥቀሳቸው ተገቢ አለመሆኑን አስታውቋል፡፡

የአምባሳደሩ ንግግር የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቷን እንዴት መምራት እንዳለበት ያልተጠየቀ  ምክር ለመምከር የሞከረ፤ ከሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ወዳጅነት ላይ ከተመሰረተው ግንኙነት የተቃረነ እንደሆነም ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነታቸውን አጠናክረው በመቀጠል በብሔራዊ፣ ቀጣናዊና የጋራ በሆኑ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራታቸውን እንደሚሰሩ ጠቅሶ ኢትዮጵያ የሰላምና የጸጥታ ጉዳዮችን ጨምሮ ከአሜሪካ ጋር ለመስራት ያላትን ዝግጁነት ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ ከሚገኘው ኤምባሲ ጋር በመስራት የተፈጠረውን ስህተት እንዲታረም የሚያደርግ መሆኑን አመልክቶ የተፈጸመውን ዲፕሎማሲያዊ ስህተት ማረም እንደሚገባ አሳስቧል።

ኢትዮጵያ በመከባበር ላይ የተመሰረተ የሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር እንዲኖር ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጧል።
ቦይንግ ኩባንያ የአፍሪካ ዋና ጽሕፈት ቤትን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው

ግንቦት 14/2016 (አዲስ ዋልታ) ግዙፉ የአሜሪካ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ የሆነው ቦይንግ የአፍሪካ ዋና ጽሕፈት ቤትን በአዲስ አበባ ሊከፍት ነው፡፡

ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የአቪዬሽን ጉባኤ ላይ እየተካፈለች ትገኛለች። በመድረኩ ላይ ኩባንያው በሚቀጥለው ዓመት ቢሮውን በአዲስ አበባ ለመክፈት ማቀዱ ተገልጿል፡፡

ኩባንያው ይህን ውሳኔ ያስታወቀው በአፍሪካ ከግዙፍ አየር መንገዶች መካከል ተጠቃሽ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 65 አውሮፕላኖቹን በቦይንግ እንደሚተካ ማስታወቁን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

በሚልኪያስ አዱኛ
"ዛሬ በአዋሬ አካባቢ ከስድስት አመታት በፊት በጀመርነው የዝቅተኛ ወጪ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንቅስቃሴ ምናልባትም የመጨረሻው ስፍራውን ለግንባታ ዝግጁ የማድረግ ስራ ተሰርቷል። የመኖሪያ ሁኔታዎቹ ችግር የበዛባቸው ነበሩ።  እጅግ ያረጁ፣ የተጠባበቁ፣ መፀዳጃ የሌላቸው መኖሪያዎች ነበሩ። ምቹ የመኖሪያ እና አረንጓዴ አካባቢ የሚያካትተው አዲሱን የመኖሪያ ህንፃ ግንባታ በመጪው መስከረም ወር ለማጠናቀቅ ዛሬ አስጀምረናል።

ይህ ስራ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ህይወት ብቻ ሳይሆን የሪል ስቴት አልሚዎችንም የጠቀመ ነው። በዚህ ፕሮጀክት የቀጣይነት መንፈስ አይተንበታል። አፅንተንበታልም። አዋሬ ቀጣይነት ያለው ያላሰለሰ ጥረት የመኖሪያ አካባቢዎችን ሊለውጥ የነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ እና ተስፋ ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ማሳያ ምልክት ነው። የዚህ አመቱ የዝቅተኛ ቤቶች ግንባታ ወጪ በከፊል በቪዛ ፋውንዴሽን (VISA Foundation) ተሸፍኗል። ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች እና በጎ አድራጊዎች ለዜጎች ህይወት እና ከባቢ መለወጥ ያለመታከት ልግስናቸውን እንዲዘረጉ ጥሪዬን አቀርባለው።"

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ ሲ ቲ ፍጻሜ ውድድር አሸነፉ

ግንቦት 19/2016 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ ሲ ቲ ፍጻሜ ውድድር ሶስተኛውን ሽልማት አሸነፉ።

ኢትዮጵያን ወክለው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ አይ ሲ ቲ ውድድርን በቻይና ሼንዘን ከተማ በኮምፒውቲንግ ትራክ የተሳተፉት 3 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሶሰተኛውን ሽልማት ከማሌዢይ፣ ሜከሲኮ እና ኬንያ ቡደን ጋር መጋራታቸው ተጠቁሟል።

ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሶስት የውድድር ትራኮች (Innovation, Network and Computing) ተካፋፍሎ የተካሄደ መሆኑም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ቡድን የተወከለው ከአርባ ምንጭና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በተገኙ ተማሪዎች መሆኑን አመላክቶ  በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ሶስተኛውን ሽልማት አሸንፎ ዛሬ ወደ ሀገሩ መመለሱም ተጠቁሟል።

ትምህርት ሚኒስቴር በተማሪዎቹ ውጤት የተሰማውን ደስታም በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

ወደፊትም የተማሪዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እድል የሚፈጥሩ ውድድሮች ላይ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ከመሰል ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
በቱሪዝም ፣ በመስተንግዶ እና በሆቴል ኢንዱስትሪ ተመርቃችሁ መስራት ለምትፈልጉ!!!
የአፍሪወርክ ቴሌግራም ቻናልን በመቀላቀል በየቀኑ በዚህ ዘርፍ ከሚወጡ አዳዲስ ስራዎች ተጠቃሚ ይሁኑ።
የቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ሲምፖዚየም ተጀመረ

ግንቦት 22/2016 (አዲስ ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ሲምፖዚየም አስጀምረዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኑ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና ዓለም አቀፉ ዲኤምጂ ኢቨንትስ ከግንቦት 22 እስከ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ “ኢትዮጵያን እንገንባ!” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጁት ነው፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መንግሥት የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማበረታታት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ዘርፍን ለመፍጠር፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን በማበረታታት ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ የቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኤግዚብሽንና ሲምፖዚየም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ልማት፣ እድገት እና ስኬት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

በዘርፉ የሚታዩ ማነቆዎችን ወደ ዕድል ለመቀየር እንዲሁም የፋይናንስ፣ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ድጋፍን ለማግኘት የሚረዳ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በሳሙኤል ሓጎስየቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ሲምፖዚየም ተጀመረ

ግንቦት 22/2016 (አዲስ ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽንና ሲምፖዚየም አስጀምረዋል፡፡
ባለማሲንቆው ‘ጋርዲዮላ’ 

እግር ኳስ ላይ የነገሰ ማስተር ማይንድ ይሉታል፤ በየጊዜው በሚቀያየር በድንቅ የአጨዋወት ፍልስፍናው ያለፉትን ተከታታይ አራት አመታት ሀያሉን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለማንም አላስነካም፡፡ ከስፔን እስከ ጀርመን፤ ከጀርመን እስከ እንግሊዝ በቀጠለው ጉዞ ውስጥ ዋንጫን ሲጠራርግ ለነገ አይልም፡፡ ጆሴፍ ጋርዲዮላ ሳላ ወይም ፔፕ ጋርዲዮላ፡፡

ታዲያ ይህ ዓለም ያደነቀውን የሚመስል ግለሰብ ከሰሞኑ ማሲንቆ ይዞ ሲጫወት የተነሳ ምስል በማኅበራዊ ትስስር ገፅ ላይ በስፋት ተሰራጭቷል፡፡ ሰውዬው ‘ጋርዲዮላ በመስታወት’ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በአቋምም በመልክም ራሱ ጋርዲዮላን የመሰለ የሀገር ልጅ፡፡

ተኽሊት ተስፋይ (አታክልቲ)፡፡ በአዲሱ ስሙ ደሞ “ባለማሲንቆው ጋርዲዮላ፡፡” ትውልድና እድገቱ ከወደ ትግራይ ነው፡፡ ላለፉት 20 አመታት ደግሞ በአዲስ አበባ በሚጫወታት ማሲንቆ ይተዳደራል፡፡ ማሲንቆዋን ወርቅነሽ ሲል ይጠራታል፡፡ ወርቅ ስለምታመጣልኝ ነው ይላል፡፡ ታዲያ አታክልቲ ሰርግ ላይ እየተዟዟረ ማሲንቆ ከመጫወት በዘለለ ስለ ኳስ ጨዋታ የሚያቀው ነገር የለም፡፡ አዳራሽ ውስጥ ማስጨፈር እንጂ ስታዲየም ገብቶ መጨፈር ልምዱ አይደለም፡፡ ሙሽሮችን ማጋባት እንጂ እገሌ የተባለ ተጫዋች ጎል አገባ ስለሚል ጉዳይ አውርቶ አያውቅም፡፡ አርሰናል? ማንችስተር? የሚባሉ ክለቦች ማናቸው ተብሎ ቢጠየቅ መልስም አልነበረው፡፡ በዚህ ደረጃ ከኳስ ጋር የተራራቀ ሰው ነበር፡፡ የቀድሞ ተኽሊት የአሁኑ ባለማሲንቆው ጋርዲዮላ፡፡
HTML Embed Code:
2024/06/02 17:06:11
Back to Top