TG Telegram Group Link
Channel: TIKVAH-MAGAZINE
Back to Bottom
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በአገልግሎት አሰጣጣችንና በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ ደንበኞቻችን ምስክሮች ናቸው።
ዛሬም ብዛት እንዲሁም ጥራት ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለ!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች፣ ወ.ዘ.ተ.

አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ! የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844
0928442662
0940141114

https://hottg.com/samcomptech
ኬንያ ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የገዛችው የኤሌክትሪክ ሀይል ከባለፈው አመት በ41 በመቶ ማደጉ ተገለፀ

ኬንያ ከፈረንጆቹ አዲስ አመት 2024 ጀምሮ ባሉት 3 ወራት ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የገዛችው የኤሌክትሪክ ሀይል ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ41 በመቶ ማደጉን ተገለፀ።

ኬንያ በተጠቀሰው ጊዜ ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ 408.78 Gigawatt-hour (GWh) የገዛች ሲሆን ይህም ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገዛው የ 288.3 GWh የኤሌክትሪክ ሀይል ግዢ በ41.7 የበለጠ መሆኑ ተጠቁሟል።

ለሀይል ግዢው ኬንያ ወደ 4.23 ቢሊየን የኬንያ ሽልንግ ያወጣች ሲሆን የሃይል አቅርቦቱ ርካሽ እንደሆነና ሀገሪቱ ጥገኛ የሆነችበትን የሙቀት ሀይል ማመንጫ ወጪን እየቀነስ መሆኑን ቢዝነስ ዴይሊ አስነብቧል።

@tikvahethmagazine
የኤሌክትሪክ ኃይልን ባሉበት በመሆን መሙላት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል ተባለ

ከ900 ሺህ በላይ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ በካርድ ብቻ ባሉበት ሆነዉ የኤሌትሪክ ኃይል መሙላት የሚያችላቸዉ ቴክኖሎጂ በተያዘው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ።

ቴክኖሎጂው ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ በኦላይን ወይም የካርድ ቁጥርን ከዲጅታል የክፍያ አማራጮች በመጠቀምና ግዢ በመፈፀም ወደ አገልግሎት መስጪያ ማዕከሉ መሄድ ሳይጠበቅባቸዉ ኃይል መሙላት የሚያስችላቸው መሆኑን የዘገበው ካፒታል ነው።

@tikvahethmagazine
የመንግስትን እና የሀይማኖት ተቋማትን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

መንግሥትና ሃይማኖት አንዱ በአንዳቸው ተግባርና እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ አይገቡም የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ፣ መንግሥት ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያለው ድንጋጌ ሃይማኖትና መንግሥት አይደራረሱም ማለት እንዳልሆነ ሲገለጽ በጋራ የሚሠሩባቸው ጉዳዮች መኖራቸውንና ሆኖም በሕገ መንግሥቱ ያለው ድንጋጌ ጥቅል መርሆዎችን የያዘ በመሆኑ፣ ይህን ለማብራራት ሕግ በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ተጠቁሟል፡፡

በዚህም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉባቸው ሦስት ጥናቶች ተካሂደው ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ከተወሰኑ ቤተ እምነቶች ጋር ውይይት የተጀመረ መሆኑን በሰላም ሚኒስቴር የሃይማኖት ጉዳዮች ዴስክ ተጠባባቂ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሀለፎም ዓባይነህ፣ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

@tikvahethmagazine
የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ እንዲፀድቅ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ ተነገረ

በሆቴሎች የሚሠሩ ሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች ከሀገሪቱ ባሕል ውጪ የሆነውን አለባበሳቸውን ለማስተካከል የሚያስችል የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ ተጠናቅቆ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

አሁን ላይ የመስተንግዶ ባለሙያዎች በተለይም ሴቶች በአንዳንድ ሆቴሎች አማካኝነት ሥነ-ሥርዓቱን ያልጠበቀ አለባበስ እንዲለብሱ ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን መመሪያው ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል በሆቴሎች የሚሠሩ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአለባበስ ኮድ እንዲከተሉ ይደረጋል ተብሏል።

መመሪያው በከተማዋ ካቢኔ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሲገለፅ ሕጉ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም ጭምር ያለው በመሆኑ መመሪያውን በሚተላለፉ ላይ ቅጣት እንደሚጣል የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሣው (ዶ/ር) መግለፃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

@tikvahethmagazine
በወር 15,000 ብር 💸💵💰💰 ማግኘት ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ
🚴‍♀️ ብስክሌት
🏍 ሞተር
🛵 E-bike ካልዎት ምን ይጠብቃሉ ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ።

💰ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን ብስክሌት ፥ ሞተረ እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል።

የስራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ

ለመመዝገብ:-


ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት

✴️https://hottg.com/DriversRegistration_bot

ወይም

☎️ 9533 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
TIKVAH-MAGAZINE
በኢትዮጵያ 68% የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51% የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ ተነገረ በኢትዮጲያ በተለያዩ የአንደኛ ደረጃ 168 ትምህርትቤቶች በሚገኙ በ 9,000 ተማሪዎች በተጠናዉ ጥናት መሰረት 2ኛ ክፍል ተማሪዎች 68% እና 3ኛ ክፍል ተማሪዎች 51% ያህሉ ማንበብና መጻፍ እንደማይችሉ ተገልጿል። የተማሪዎችን የትምህርት ዉጤት ለማሻሻል የትምህርት ስርአቱ የተናበበ እና የተቀናጀ…
በኢትዮጵያ የ2ኛ እና 3ተኛ ክፍል ተማሪዎች ከግማሽ በላዩ ማንበብ እንደማይችሉ ጥናት አመለከተ።

የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ንባብን መሠረት አድርጎ ባካሄደው ጥናት በኢትዮጵያ የሚገኙ የ2ኛ እና 3ኛ ክፍል ተማሪች #56_በመቶዎቹ ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ አመልክቷል።

👩‍🎓  በጥናቱ ምን ያህል ተማሪዎች ተሳተፉ?

በዚህ ንባብን መሠረት ባደረገ ጥናት ከ9 ክልሎች የተወጣጡ ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎች በዘፈቀደ (Random sampling ) ተመልምለው ተሳትፈዋል። ተማሪዎቹ ከ401 የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተመረጡ ናቸው።

🔍  ጥናቱ እንዴት ተካሄደ?

በጥናቱ የተመለመሉት ተማሪዎቹ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የተጻፉ 50 ቃላት ቀርበውላቸው ቃላቱን ያነቡ እንደሆነ ተጠይቀዋል።

በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በአፋርኛ፣ በሶማሊኛ፣ በሀዲይኛ፣ በወላይትኛ፣ በሲዳምኛ እና ቤንሻንጉል ውስጥ በሚነገረው በርታ ቋንቋ የሚማሩ ተማሪዎች በዚህ ጥናት ተሳትፈዋል።

ከጥናቱ የሚጠበቀውም ፊደልን የመለየት፣ ቃላት ወይም አጭር አንቀጽ የማንበብ እና የማድመጥ እና የመረዳት ችሎታቸውን መመዘን ነው።

📕 የጥናቱ ውጤት ምን ያመለክታል?

- በጥናቱ ከተሳተፉት የ2ኛ እና 3ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 56 በመቶ የሚሆኑት አንድም ቃል ማንበብ አይችሉም።

- በጥናቱ ከተሳተፉ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ቢያንስ አንድ ቃል ማንበብ የሚችሉት 37 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው። የተቀሩት 63 በመቶዎቹ አንድም ቃል ማንብብ የማይችሉ (Zero renderers) ናቸው።

- የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ 55 በመቶ የሚሆኑት ከየትኛውም ፊደል ጋር እንደማይተዋወቁ ጥናቱ ጠቁሟል።

- ጥናቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉ፤ በተለምዶ ታዳጊ የሚባሉ ክልሎች ላይ ትኩረት እንዲደረግ ምክረ ኃሳብ አስቀምጧል።

🌍 በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ ጥናቶች ምን ያመለክታሉ?

- በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ የሁለተኛ ክፍል ተማሪ በደቂቃ ቢያንስ 60፤ የ3ኛ ክፍል ተማሪ ደግሞ 90 ቃላትን እንዲያነብ ይጠበቃል።

- ከላይ በተነሳው ነጥብ መሠረት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሚማሩት የ2ኛ ክፍል ተማሪዎች ቢያንስ በደቂቃ 43 እንዲሁም የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች 53 ቃላትን እንዲያነቡ ይጠበቅ ነበር።

መረጃው የተወሰደው ከቢቢሲ አማርኛ ነው።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዩናይትድ ኪንግደም ከ150 አመታት በፊት ከአሻንቲ የተዘረፉ 32 የወርቅ እና የብር ቅርሶችን ለጋና በውሰት መለሰች

ዩናይትድ ኪንግደም ከ150 ዓመታት በፊት በብሪቲሽ እና ታዋቂ በነበሩት የአሻንቲ ህዝቦች መካከል በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ከአሻንቲ ንጉስ ፍርድ ቤት ተዘርፈው የተወሰዱ 32 የወርቅ እና የብር ቅርሶችን ለስድስት አመታት ውል በውሰት ለጋና መስጠቷ ተገለፀ።

ቅርሶቹ ሊመለሱ የቻሉት የወቅቱን የአሳንቲ ንጉስ የሆኑት "ኦቱምፉኦ ኦሴይ ቱቱ 2ኛ" የብር ኢዮቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሚቀጥለው ወር በአሻንቲ ክልል ርዕሰ መዲና በሚገኘው በማኒሺያ ቤተ መንግስት ሙዚየም ለእይታ እንዲቀርቡ ታልሞ መሆኑ ተጠቁሟል።

ዩናይትድ ኪንግደም እነዚህ ቅርሶች የመለሰችው የአውሮፓና የአሜሪካ ሙዚየሞችና ተቋማት እንደ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ቤልጂየም ባሉ ኃያላን አገሮች በቅኝ ግዛት ዘመን የዘርፏቸውን የአፍሪካ ቅርሶች እንዲመለሱ ግፊት እየተደረገባቸው ባለበት ወቅት መሆኑም ነው የተገለፀው።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update: በዲላ ከተማ ሚያዝያ 5 በጣለው ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በከተማው ሙሉ ለሙሉ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም መመለሱ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
በወር 15,000 ብር 💸💵💰💰 ማግኘት ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ
🚴‍♀️ ብስክሌት
🏍 ሞተር
🛵 E-bike ካልዎት ምን ይጠብቃሉ ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ።

💰ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን ብስክሌት ፥ ሞተረ እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል።

የስራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ

ለመመዝገብ:-


ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት

✴️https://hottg.com/DriversRegistration_bot

ወይም

☎️ 9533 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
ታላቅ ቅናሽ 📣📣📣📣📣

💵 ድርጅታችን ድሪም ቢዉልደርስ በካሬ 90,000 ሲሸጥ የነበረውን ውደ 79,900 ብር ቅናሽ  አድርጓል።

🕧በ10% ቅድመ ክፍያ፣ በ9 ዙር፣ በ2 አመት ከ6 ወር ከፍለዉ የሚጨርሱት።

📍 በ CMC የተሟላ የመኖርያ መንደር ከ ለሚ ኩራ ፓርክ ፊትለፊት

⛰️በ ተንጣለለ 23,000 ካሬ ላይ ያረፉ አፓርትመንቶች፣ ከተሟላ መገልገያዎች ጋር

🛏️ባለ 1 መኝታ  79.92ካሬ  91.56ካሬ 
🛏️ባለ 2 መኝታ 125.4ካሬ   127.44ካሬ 
🛏️ባለ 3 መኝታ  169.92ካሬ

☎️ ለበለጠ መረጃ ይደዉሉልን 0974388888
በአዲስ ከተማ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ 7 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታዉ ጠሮ መስኪድ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ የግንባታ ግብዓት አፈርና ድንጋይ ተደርምሶ በአቅራቢያው ያለ መኖሪያ ቤት ላይ በመናዱ በቤታቸዉ ተኝተዉ የነበሩ 7 ሰዎች ህይወታቸዉ አለፈ።

አደጋው የደረሰው በዛሬው እለት ሚያዚያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 11 :00 ሰዓት ላይ ነው። የሟቾቹን አስከሬን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አዉጥተዉ ለፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን የአደጋዉን መንስኤ ለማጣራት ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine
በኢትዮጵያ በገዳይነቱ የተመዘገበው የ 'ካላዛር' በሽታን ለማከም የሚውል መድኃኒት በሰዎች ላይ መሞከር ተጀመረ

የካላዛር ሕሙማንን ለማከም ለ17 ቀናት የሚሰጠውን የመርፌና የእንክብል መድኃኒት ሙሉ ለሙሉ በእንክብል ብቻ ለመተካት የሚያስችለው መድኃኒት፣ የዕድሜ ክልላቸው ከ18 እስከ 44 በሚደርሱ 52 ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን ላይ ሙከራው ተጀመረ።

በምርምሩ 15 የጤና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን፣ ፈውስ ትኩረት ለተነፈጉ በሽታዎች ኢኒሺዬቲቭ ወይንም ዲ ኤን ዲ የጤና ምርምር የተባለ ተቋም እና አጋሮቹ ለዚህ በሽታ የሚያደርጉት የመድሃኒት ፍለጋ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ ደረጃ መሸጋገሩ ተጠቁሟል።

በአፍሪካ አሁን እየተሰጠ የሚገኘው የካላዛር ህክምና ለ17 ቀናት የሚወሰድ ከፍተኛ ህመም የሚፈጥር ክትባት ሲሆን በኢትዮጵያ በምርምር ላይ የሚገኘው አዲሱ የ “LXE408” በአፍ  የሚወሰድ መድሀኒት አሁን ከሚሰጠው ህክምና የበለጠ ፈዋሽና እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል። በኢትዮጵያ በዓመት ከ2 እስከ 3 ሺ ሰዎች በካላዛር በሽታ ይያዛሉ ሲባል በበሽታው ተይዘው ሕክምና ካላገኙት ውስጥ 95 በመቶ ያህሉ እንደሚሞቱ ተጠቁሟል።

Credit: Sheger, reporter

@TikvahethMagazine
ኬንያ የፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል የፕላስቲክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያን መጠቀም ከለከለች

የኬንያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር የፕላስቲክ ብክለት እያስከተሉ ነው ያላቸውን ቆሻሻን ለመሰብሰብ እና ለማስወገድ የሚያገለግሉትን ፕላስቲክ ከረጢቶች መጠቀም የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እገዳውን በኤፕሪል 8 ያስተላለፈ ሲሆን ኬንያውያን ዜጎች የእገዳ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በ90 ቀናት ውስጥ መጠቀም ማቆም አለባቸው ተብሏል።

በመሆኑም ሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃን እና ጤናማ የቆሻሻ አወጋደድን ለማረጋገጥ በባህሪያቸው ሊበሰብሱ የማይችሉትን የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም በማቆም፣ ቆሻሻ አስወጋጅ ድርጅቶች ለደንበኞቻቸው ሙሉ በሙሉ ሊበሰብስ የሚችል ቆሻሻ ማጠራቀሚያ (biodegradable bags) ብቻ እንዲያቀርቡ መመሪያ መሰጠቱ ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። ዜጎችም ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ መመዝገብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በማስጀመር በወር በአማካይ 1 ሚሊየን ዜጎችን በመመዝገብ እስከ 2018 ዓ.ም ለ90 ሚሊየን ዜጎች አገልግሎቱን ለመስጠት ማቀዱም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
TIKVAH-MAGAZINE
ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። ዜጎችም ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ መመዝገብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በማስጀመር በወር በአማካይ…
#Update: እድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን እንደሚችሉ ተገለፀ

እድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማከናወን ይፋ በተደረጉት የኢትዮቴሌኮም  የአገልግሎት ማዕከላት በአካል በመገኘት፣ ማንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እንደ ፦

ቀበሌ መታወቂያ፣
የታደሰ የመንጃ ፈቃድ፣
ፓስፖርት የመሳሰሉ ሰነዶችን በመያዝ ወይም የሰው ምስክር በማቅረብ በነጻ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከሎቻችን የትኞቹ ናቸው?

በአዲስ አበባ፦ ውሃ ልማት (ሃያ ሁለት)፣ ልደታ፣ ስታዲየም፣ ቦሌ መድኃኔዓለም፣ ገርጂ፣ አያት፣ ስድስት ኪሎ፣ ጉርድ ሾላ፣ ሽሮሜዳ፣ ሳሪስ፣  ቃሊቲ፣ አቃቂ፣ ጀሞ፣ ለቡ፣ ቤተል፣ አራዳ፣ ኮልፌ፣ ቡራዩ እና ቲፒኦ (ጥቁር አንበሳ) ናቸው።

በሪጅኖች ደግሞ ፦ በሐረር፣ ደብረብርሀን፣ ፊቼ፣ ለገጣፎኣ፣ አምቦ፣ ሰበታ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሰመራ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ አዘዞ፣ መቀሌ(ሁለት)፣ ባሕርዳር፣ ዓባይ ማዶ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሐዋሳ(ሁለት)፣ ሻሸመኔ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ ጅማ፣ ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ጋምቤላ ነቀምቴ እና አሶሳ ናቸው።

ከከተማ እና የገጠር ነዋሪዎች በተጨማሪ የዩኒቨርስቲ፣ የከፍተኛ እና የብሔራዊ 2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ተፈታኞች፣ በተፈናቃዮች ጣቢያ የሚገኙ፣ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች እና በሀገራችን የሚገኙ ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሃገር ዜጎች ምዝገባ ማከናወን ይችላሉም ተብሏል።

@TikvahethMagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#Update በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተደረገ በረራ 1 ሺህ 71 ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ዛሬ የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ዘጠኙ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው። መረጃው የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ነው። @TikvahethMagazine
#Update: ከሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ ስራ እስካሁን ከ9ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተነገረ።

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 181 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሁሉም ወንዶች እንደሆኑና 4 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።

@TikvahethMagazine
ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን ይኖሩበት የነበረውን ቤትና የሥራ ስቱዲዮ ለመጠገን የስራ ርክክብ ተደረገ

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ይኖሩበት የነበረውን ቤትና የሥራ ስቱዲዮ ለመጠገን የሥራ ርክክብ መደረጉን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ የጥገና ሥራውን ለማከናወን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን፣ ቢዋይ ኤምቲ ኮንትራክተር እና ዳሎል አማካሪ ድርጅት የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ቅርሱ የነበረውን አሻራና ይዘት በመጠበቅ የቅርስ ጥገና መርሆዎችን ተከትሎ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት የጠቆሙ ሲሆን የጥገና ሥራውም በተቀመጠለት የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲከናወን አሳስበዋል፡፡

@TikvahethMagazine
HTML Embed Code:
2024/04/25 05:38:55
Back to Top