TG Telegram Group Link
Channel: Buy and sell online
Back to Bottom
#US

አሜሪካ መላ ዜጎቿን ለመግደል በቂ የሆነ " ፌንታሊን " የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ማያዟን አስታወቀች።

የአሜሪካ የዕጽ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን እየተጠናቀቀ ባለው 2022 መላውን የአሜሪካ ዜጋ ለመግደል በቂ የሆነ " ፌንታሊን " የተሰኘ አደገኛ አደንዛዥ ዕጽ መያዙን አሳውቋል።

ባለስልጣኑ፤ በአንዴ እንዲወሰዱ ተደርገው የተዘጋጁ እያንዳንዳቸው ሁለት ሚሊግራም የሚመዝኑ ገዳይ የሆኑ 379 ሚሊዮን ፌንታሊን የተሰኘ ዕጾችን ይዣለሁ ብሏል።

ይህ አደንዛዥ ዕጽ ከሄሮይን 50 እጥፍ በላይ ገዳይ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን "ፌንታኒል አሜሪካ በአሁኑ ወቅት የገጠማት ገዳይ ስጋት ነው " ሲል ገልጾታል።

ይኸው የዕፅ ተቆጣጣሪ መ/ቤት እንደሚለው፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ፌንታሊን ወደ አሜሪካ የሚገባው #ከሜክሲኮ ሲሆን ከ4 ሺ 500 ኪግ በላይ ፌንታሊንና 50.6 ሚሊዮን በእንክብል መልክ የተዘጋጁ ዕጾች ተይዘዋል።

በእንክብል መልክ የተዘጋጁት ዕጾች ህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች እንዲመስሉ መደረጋቸውን ተገልጿል።

እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት የተያዘው የዕጽ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ጨምሯል።

አንደ ባለስልጣኑ መረጃ፤ በአሜሪካ የሚያዙት ዕጾች " በሲናሎዋ እና ጃሊስኮ " ዕጽ አዘዋዋሪ ቡድኖች አማካይነት ሜክሲኮ ውስጥ በምስጢራዊ ስፍራ በሚገኙ ፋብሪካዎች ይመረታሉ።

"ፌንታሊን" እጅግ አደገኛ የሆነ ዕጽ ሲሆን የእርሳስ ጫፍ ላይ ልትቀመጥ የምትችል ትንሽ መጠን እንኳን የመግደል አቅም አላት።

ማጠቃለያ፦

- ባለፈው ዓመት 100 ሺ አሜሪካውያን ከመጠን በላይ ዕጽ ወስደው ሕይወታቸው አልፏል። ከዚህ ውስጥ ሁለት ሦስተኛው ሞት ከፌንታሊን ጋር የተገናኘ ነው።

- በዚህ ዓመት የተያዘው ፌንታሊን መጠን 330 ሚሊዮን የአሜሪካ ነዋሪዎች መግደል የሚችል ነው።

#BBC

@tikvahethiopia
#AmazonFashion

አማዞን ፋሽን ለሙሽራ ፣ ለሚዜ ፣ ለባንክ ቤት ሰራተኞች እና ለተመራቂ ተማሪዎች ‍የሚሆኑ ሱፎች፣ ሸሚዞች ፣ ጫማዎች ፣ ከረባቶች ፣ ኮቶች በብዙ አማራጭ እና እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርበንሎታል።

ለጨረታ እና በብዛት ፈላጊዎች ከ4000 ሺ ብር ጀምሮ ሙሉ ልብሶችን እናስረክባለን። በብዛት ለሚወስዱ የብድር አገልገሎት እንዲሁም በሚፈለገው ሳይዝ እናቀርባለን።

አድራሻ፦ ፒያሳ Down Town ህንፃ ምድር ላይ እና 2ኛ ፎቅ                                                            
ስልክ ፦ 0919339250 / 0923468025 

ቴሌግራም : https://hottg.com/+AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
#AddisAbaba

በRomal የክር ጥበብ(String Art) እና በአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አስተባባሪነት የተዘጋጀው የክር የስዕል ጥበብ አዉደ-ርዕይ ከታህሳስ 2 ጀምሮ ለተመልካች ክፍት ሆኖ እየተጎበኘ ይገኛል።

ይህን አውደ ርዕይ እስከ ፊታችን እሁድ ታህሳስ 16 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ በመሆኑ ታዳሚያን #በዲሊኦፖል ሆቴል ተገኝተው በነጻ እንዲጎበኙ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።

የክር ጥበብ(String Art) እንዴት ይሰራል ?

የክር ጥበብ ያለ ምንም ቀለም በተለያዩ የክር ውጤቶች፣ ጥቃቅን ሚስማሮችና መደብ የሚሆን እንጨተት (MDF) አማካኝነት የሚሰራ የጥበብ ውጤት ነው።

ለአብነት ያክል ከላይ በፎቶ የተያያዘው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ መልክ የተሰራው የጥበብ ሥራ ከ4000 በላይ ሚስማሮች(የባከኑትን ጨምሮ)፣ 9 አይነት የክር አይነቶች ጥቅም ላይ ውለዋል።

በተጨማሪም ሚስማሩን ቅርጽ አሲዞ ለመምታት ወደ 11 ሰዓታት የፈጀ ሲሆን ቀሪው በ4 ቀናት ውስጥ ሥራው ተጠናቋል።

ይህ የጥበብ ሥራ በዚህ የአውደ ርዕይ ወቅት የሚሸጥ ከሆነ አዘጋጆቹ 180 ሺ ብር ተመን አውጥተውለታል።

በአውደ ርዕዩ ከ50 በላይ የተለያዩ የጥበብ ውጤቶች የቀረቡ ሲሆን ሁለት ወጣቶች በዋነኛነት፤ በአጠቃላይ አራት ወጣቶች በሥራው ላይ ተሳትፈውበታል። በቀጣይ የተለያዩ ሥራዎችን አካተው የአርት ጋላሪ የመክፈት እንዲሁም በዲጂታል አማራጭ ሥራቸውን የመሸጥ ትልም አላቸው።

NB: ከላይ በፎቶ የምትመለከቷቸው የጥበብ ውጤቶች ሙሉ በሙሉ በክር የተሰሩ ሲሆኑ ክሮቹ ተጠላልፈው ከፈጠሩት ቀለም ውጭ ምንም አይነት ቀልም አልተጠቀሙም።

More : @tikvahethmagazine
#UPDATE

ዛሬ በጎረቤታችን ኬንያ ናይሮቢ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የህወሓት ተወካዮች ለ3 ቀናት የሚቆይ የምክክር ስብሰባ ማካሄድ መጀመራቸው ተሰምቷል።

እስከ አርብ ድረስ እንደሚቆይ የየተነገረው ይኸው ንግግር ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም፣ ደቡበ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ውስጥ የተፈረመውን ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ትግበራን የሚመለከት መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ስብሰባው ላይ ሁለቱ ወገኖች የትጥቅ ማስፈታቱ ሂደት ትግበራ፣ የአፍሪካ ኅብረት ለሚያካሂደው የስምምነቱ ትግበራ ቁጥጥር ማስፈጸሚያ ነጥቦች ላይ ውይይት በማድረግ ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ተወካዮች ምክክር እያደረጉ የሚገኘው ቀደም ሲል ናይሮቢ ውስጥ ድርድር በተደረገበት ስፍራ ሲሆን ምክክር ለሚዲያዎች ዝግ ነው።

ማጠቃለያው ላይ ግን መግለጫ እንደሚሰጥ ቢቢሲ ፅፏል።

Photo : Nuur Mohamud Sheekh (IGAD)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Qusaqus

እነዚህን እና ሌሎች አልባሳትን ከቁሳስ ገበያ ለልጆች ይሸምቱ ፤ ሚሊኒየም አዳራሽ የገና ባዛር ላይ ያገኙናል። ቋሚ አድራሻ ለቡ ቫርኔሮ ለቡ ኮሜርሻል ሴንተር 3ኛ ፍሎር።

ዋጋቸውን ለማየት ይቀላቀሉ https://hottg.com/+AAAAAFdSYGPj_KBJP_-vXA
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን: 0944032449/0941993049
" ... አንድ ተማሪ ከነልጇ ህይወታቸው አልፏል " - የቤኒሻንጉል  ጉሙዝ ትምህርት ቢሮ

የ2ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደሚፈተኑበት ተቋም እየገቡ እንደሆነ ይታወቃል።

ዛሬ ከወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሳዛኝ ዜና ተሰምቷል።

በ2ኛ ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን ከሚዢጋ ወረዳ ወደ አሶሳ ሲመጡ በነበሩ ተማሪዎች ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶ ነበር።

ከክልሉ ትምህርት ቢሮ በተገኘ መረጀ በደረሰው የተሸከርካሪ አደጋ ፤ አንድ ተማሪ ከልጇ ጋር ሕይወታቸው አልፏል።

በአምስት ተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

ምንጭ፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገፅ

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ስለ ዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ፦

(የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ)

- የዓይን ባንኩ ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው ሰዎች የማን እንደተሰራላቸው አያሳውቅም፤

- ባንኩ አስፈላጊውን ፍተሸ በማድረግ ለንቅለ ተከላ ማዕከላት ያሰራጫል፤

- የዓይን ባንኩ የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና ከሚሰሩ ተቋማት ጋር ይሰራል፤

- የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና የሚሰጠው የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ የሚሰራበቸው ማዕከላት ውስጥ ብቻ ነው እነዚህም ፦
👉 ዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕርሄንሲቭ ሪፈራል ሆሰፒታል
👉 ቅ.ጳውሎስ ሚሊኔም ኮሌጅ
👉 ጎንደር ስፔሻላይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል
👉 ጅማ ስፔሻይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል
👉 ሐዋሳ ስፔሻላይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል ናቸው።

በተጨማሪም አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የግል የዓይን ህክምና ጣቢያወች መካከል ፦
👉 ብሩህ ቪዢን ልዩ የዓይን ክሊኒክ
👉 ዋጋ ቪዥን ልዩ የዓይን ክሊኒክ
👉 አልአሚን የዓይን ህክምና ማዕከል
👉 ላቪስታ ስፔሻሊስት የዓይን ክልኒክ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዓይን ባንክን በምን ላግኛቸው ?

አድራሻ ፦ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ

ስልክ ፦
0111223838
0930006367
0930006368
Email [email protected]

#የኢትዮጵያ_ዓይን_ባንክ

@tikvahethiopia
Channel name was changed to «Buy and sell online»
Channel photo removed
HTML Embed Code:
2024/04/26 05:43:46
Back to Top