TG Telegram Group Link
Channel: Tikvah Ethiopia Aid
Back to Bottom
የእርዳታ ጥሪ!

ተወዳጁ ሙዚቀኛ ሙሌ ሐመልማሎ በተለይም ከኤፍሬም አማረጋ "ተሸንፊያለሁ" በሚለው ስራው በስፋት የሚታወቀው አርቲስት ሙሉአለም ወንድማችን ነው። ከጎን ለመቆም ሁላችንም ጊዜ አንጠብቅ
ዛሬ አሁን ለምንወደው ድምፃዊ እገዛችንን እናድርግ! ሙሌ #በኩላሊት ህመም #ዲያልሲስ ጀምሯል
ስልክ:- +251911572276
ንግድ ባንክ (CBE)
mulualem takele
1000182044184

ከፀሎት ጀምሮ ሁላችንም በምንችለው አቅም ከአርቲስቱ ጎን በመሆን እንርዳው....
አስቸኳይ እርዳታ የእገዛ መልዕክት!

😰አሞኛል😔

ማቲያስ እባላለሁ ከተወለድኩ 6 አመት ሆኖኛል ማለትም እናት እና አባቴን ማስቸገር እና ማስለቀስ የሰው ደጅ ለልመና ማስቆም ከጀመርኩ። አሞኛል አዎ በጣም አሞኛል ከኔም አልፎ ምንም አቅም የሌላቸውን ቤተሰቦቼንም አሟቸዋል። ገና ስወለድ ከተወሳሰበ የልብ በሽታ ጋር ነበር የተወለድኩት በዛ ብቻ ግን አላበቃም እያደኩ ስመጣ የልቤ ጉዳት አንደበቴን እና እግሬን አስረብኝ ለዛ ነው የተሰማኝን የማላወራው፣ ካሻኝ እሮጬ ከእኩዮቼ ጋር እንደልብ የማልቦርቀው። አዎ አቅቶኛል በልጅ አእምሮዬ ከምችለው በላይ ችግርን ተሸክሜ አለሁ፣ የሚያመኝን ተናግሬ ማስረዳት አልችልም፣ የእናቴን እንባ እና የአባቴን ስብራት በቃላት ማከም አቅቶኛል ። አዎ አነባለሁ ህመሜ ሲፀና፣ ቤተሰብ ሲሰቃይ ፣ የሚረዳኝም የሚረዳኝም ሳጣ አብዝቼ አነባለሁ😭እንኳንስ ልቦርቅ ልሯሯጥ ልጯጯህ ደጁን ማየት ሲሳነኝ አነባለሁ። እመኛለሁ በጣም እመኛለሁ ጤናዬ ተመልሶ የወልጆቼ እምባ ታብሶ ማየት በቤታችብ ደስታ ነግሶ። በእድሜዬ ትምህርት መጀመርን መድሀኒት ሳይሆን ደብተር እና እርሳስ ማስገዛትን እመኛለሁ። ህይወቴ በአንድ ክፍል ቤት እንዲወሰን ሳይሆን ከሀገርም እንዲሰፋ እመኛለሁ። እጄ ለመረዳት ሳይሆን ለመርዳት እንዲዘረጋም እሻለሁ።ለዘላቂ መፍትሄ ማለትም በህይወት ለመኖር ከሀገር ውጪ ሄጄ መታከም አለብኝ። ለህክምናውም 1.4 ሚሊዮን ብር ነው ሚያስፈልገኝ። ስለዚህ ህፃን፣ ወጣት ፣አዛውንት፣ ሽማግሌ ሳትሉ ሁላችሁም የአቅማችሁን ብትረዱኝ የኔን ህይወት አትርፋቹ ምኞቴንም አሳክታቹ ለራሳችሁም የህሊና እርካታ ታገኙ ዘንድ እማፀናለሁ🙏🙏🙏🙏
ንግድ ባንክ፦1000289124458
ስልክ፦ 0932275457
ስልክ፦ 0937678839
•ሳምራዊት አረጋ
•ምህረቱ መንግስቴ
•ካሊድ ኡመር

ታዳጊዎቹን እንታደጋቸው!
ለህክምና ወጪያቸው እገዛ እናድርግ!!

1000278664612 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

400,000 ብር(ለማሰባሰብ የታቀደው ገንዘብ)

በትንሹ 40 ሺ አባላት ተሳታፊ ብንሆን:

10 ብር*40,000 የtikvahethiopia አባላት= 400,000 ብር

የTikvah-Ethiopia ቤተሰብ አባላት ሁሌም ለመልካም እና ለበጎ ነገር ስለቆማችሁ ፈጣሪ ያክብራችሁ!!

የአካውንቱ ስም:

ኡመር መሀመድ(የካሊድ አባት)
ፍቃዱ(የምህርቱ ወንድም)
አረጋ(የሳምራዊት አባት)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ለወድማችን አብረሀም እንድረስለት!

ይህ በፎቶ ላይ የምታዬት ወንድማችን አብረሀም በአሁኑ ሰአት ሁለቱም ኩላሊቶቹ እጥበት ይገኛሉ በመሆኑም ወንድማችን አብርሀምን አብርሀምን በገንዘባችሁ በፀሎታች እንድትረድት በፈጣሪ ስም እለምናችሀለው መልካም እጆቻችሁ ለመልካም ነገር ይነሱ commercial bank of Ethiopia account (1000199023075 Tsega Bekele)

@tikvahethiopiafund
ወጣቷን ፅግሬዳ እናግዛት...!

እህታችን ተማሪ ፅጌሬዳ እሸቴ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የትያትር ተማሪ ናት አሁን ላይ ባጋጠማት #የልብ ህመም ምክንያት ጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል ትገኛለች ለህክምና ከ 800,000 ብር በላይ ተጠይቃለች፡፡ ገንዘብ ያለችሁ በገንዘብ የሌላችሁ በጸሎት ከጎኗ እንድትሆኑ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን ሲሉ ጓደኞቿ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የባንክ አካውንት ቁጥር 1000310743821 (ፅጌሬዳ እሸቴ)

@tikvahethiopiafund
የህክምና እገዛ ጥሪ ለቲክቫህ ቤተሰቦች!!

Name: Dessalew Adinnew Adimasu

Acc.#. 1000145144152

Commercial Bank of Ethiopia.

8,000 ዶላር እንደሚያስፈልጋቸው ነግረውናል!

ወድ ቤተሰቦቻችን የአቅማችሁ ታደርጉ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።

ቤተሰቦቹ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሊዲያ እንድረስላት!

ወጣት ሊዲያ ታፈሰ ትባላለች ያደገችው ጂማ ከተማ ቆጪ ሰፈር ሲሆን በአሁኑ ሰአት ከቤተሰቦቿ ጋር ሚዛን አማን ከተማ ላይ ነዋሪ ነች :: ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እና ማኔጅመት የትምህርት ዘርፍ ለአምስት አመት ተከታትላ በ2011 አም ተመርቃለች :: ብዙ መሰናክል ታልፋ የስኬት ምእራፍን ለመጀመር ስንጣደፍ ያልተጠበቀ ሌላ መሰናክል ሲገጥመን እና ብቻችንን መወጣት ሲያቅተን የሚሰማን የልብ ስብራት ብርቱ ነው።

ሊዲያም የገጠማት እንዲሁ ነው ገና የምርቃቷን ደስታ ሳታጣጥም ከፍተኛ የጤና ችግር የገጠማት ሲሆን ማለትም የጭንቅላት ውስጥ እጢ ተፈጥሮባት የማየት ችግር እና የማያቋርጥ ራስ ምታት ገጥሟት ከጂማ እስከ አዲስ አበባ ድርስ ህክምና ብትከታተልም ከሀኪሞች በአፋጣኝ ቀዶጥገና እንዲደረግላት የተወሰነ ቢሆንም ለቀዶ ጥገና የሚውለውን ወጪ ለመሸፈን ቤተሰቦቿ ምንም አቅም የሌላቸው በመሆናቸው የከተማዉችን ማህበረሰብ የልጅቷን ህይወት ለማትረፍ እየተረባረቡ ይገኛሉ።

አቅም ያለውችሁ ሰዎች የተቻላችሁን እንድታደርጉ አቅም የሌላችሁ ሰዎች ሼር በማድረግ እንድትረባረቡ በፈጣሪ ስም እንጠይቃልእን።

እውነት ለመናገር ሊዲያን ታክሞ በሚድን በሽታ ማጣት ልብ ይሰብራልና በህይወት ቆይታ በተማረችበት ሞያ ቤተሰቦቿንና ሀገርን እንድትረዳ እንረባረብላት::

ለሰው መዳኒቱ ሰው ነው !

የባንክ አካውንት ቁጥር
1000092879449(ሊዲያ ታፈሰ)
“አካሚውን እናሳክመው!”
ጤና ይስጥልኝ። ዶ/ር መስከረም አበባው እባላለሁ። በደ/ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ጠቅላላ ሀኪም ነኝ። ባለቤቴ ዶ/ር ንጉስ ሸጋው አውለውም ጠቅላላ ሀኪም ሲሆን ከባህር ዳር 43 ኪ.ሜ በምትገኝ አደት ሆስፒታል ይሰራ ነበር።
ሁለታችንም የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የ2010 ዓ.ም ተመራቂዎች ነን፡፡ በጓደኝነት ለጥቂት አመታት ቆይተን ከተጋባን ደግሞ የተወሰኑ ወራትን አስቆጥረናል።
"ሁሉ ነገሬ" ብዬ የምጠራው ባለቤቴ ዶ/ር ንጉስ በቅርብ ጊዚያት መለስተኛ የጤና መታወክ ይታይበት ነበር። ከ3 ቀናት በፊት ምርመራ ሲያደርግ Acute myeloid leukaemia (AML) የሚባል የደም ካንሰር አይነት እንዳለበት ተነገረው።
ሁሉ ነገሬ፣ ባሌ አሁን በጥቁር አንበሳ የደም ካንሰር ህክምና ክፍል ተኝቶ ህክምናውን በመከታተል ላይ ይገኛል። የባለቤቴ ሀኪም ጋር ባደረኩት ምክክር የመቅኔ ንቅለ ተከላ (hematopoietic stem cell) የሚባል ህክምና በውጭ ሀገር ማድረግ እንዳለበት ነገረኝ።
ነገር ግን ያለብን የኢኮኖሚ ውስንነት ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተጣምሮ ነገሮችን ከባድ አድርጎብናል። አጥብቄ እርዳታችሁን እፈልጋለሁ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለኛ ፈታኝ በሆነው ጊዜ በገንዘብ ፣ በሀሳብም ሆነ በፀሎት የእርዳታ እጁን እንዲዘረጋልን እጠይቃለሁ።
ህክምናውን በፍጥነት ማግኘቱ ለመዳኑ በጣም ወሳኝ ነው። በቶሎ ልትደርሱልኝ ይገባል፡፡
ባለቤቴ ሁሉ ነገሬ ነው። አባቴን በለጋነት እድሜ በህክምና እጦት ምክንያት እንዳጣሁት ሁሉ አሁን ደሞ ባለቤቴንም ካልታከመ አጣዋለሁ፤ ኢትዮጵያም አንድ ሐኪም ታጣለች። ስለዚህ እባካችሁን እርዱን!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጋራ የባንክ አካውንታችን
ዶ/ር ንጉስ ሸጋው እና/ወይም ዶ/ር መስከረም አበባው -1000323020349/ ወይም በ +251923065854 ደውሉልኝ። አመሰግናለሁ።
#TIKVAHAID

https://youtu.be/-STvdTHxWmk

እህታችን ሊሻን ተክሉ ጥሩነህ ትባላለች በከፍተኛ የኩላሊት ህመም #ዲያልሲስ በማድረግ ላይ ትገኛለች። እርዳታችሁን እሻለሁ ስትል ገልጻልናለች፡፡

ለጥያቄ እና ለመርዳት
ሊሻን ተክሉ ( 0913956906) እናቷ ወይዘሮ ፀሀይ (091 328 5177)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) 1000095728913 ሊሻን ተክሉ ጥሩነህ

@tikvahethiopiafund
* አስቸኳይ የእገዛ ጥሪ !

ለሐያት መዳን ምክንያት እንሁን 🙏

ሀያት ኢብራሂም ኡመር ትባላለች:: የ 11ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን እድሜዋ 17 ነው። በደረሰባት ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ህመም ዲያሌሲስ እየተደረገላት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ትገኛለች።

በበሽታው መጠቃቷ ከታወቀበት እለት ጀምሮ ከበሽታው ጋር በትግል ላይ የምትገኝ ሲሆን ይህም ከቀን ወደ ቀን ሰውነቷን እያደከመው ይገኛል።

ታዳጊዋ የቀድሞ ጤንነቷ እንዲመለስ ያለው ብቸኛ አማራጭ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ብቻ እንደሆነ ከህክምና ባለሙያዎች ተነግሯታል።

ለዚህ ህክምና ሁሉንም ሂደት (process) ጨምሮ እስከ 2,000,000 (ሁለት ሚሊየን) ብር ያስፈልጋታል!!!

ይህን ገንዘብ ለመሸፈን የሀያት ቤተሰቦች ወገኖቻችን እርዱን አግዙን እያሉ ወደ ህብረተሰቡ ጥሪ ያቀርባሉ።

ሐያት ወደ ሞት ስትሄድ እያያችሁ ዝም አትበሉኝ ለመዳኔ ምክንያት ሁኑ ትለናለች!

ከተረባረብን 2000 (ሁለት ሺህ) ሰው ሆነን 1000 (አንድ ሺህ) ብር ብልነግስ ልጃችን፣ እህታችን ድና ህልሟን ታሳካ ዘንድ ምክንያት እንሁናታለን። ሀያት ድና ትምህርቷን መቀጠል ትፈልጋለች። ደግሞ ለመዳኗ ሰብብ እንሆናለን።

የቻልነውን በሙሉ እህታችንን በገንዘብ እንርዳት፣ በገንዘብ ያልቻልን በፀሎት አብረናት እንሁን ፣ ሌላው ቢቀር መረጃውን ሼር በማድረግ ሊረዷት ወደሚችሉ ሰዎች አንድ እርምጃ እናቅርባት።

በገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ

የአካውንት ስም:— ሀያት ኢብራሂም ዑመር

የኢትዮጲያን ግድ ባንክ:— 1000353443147

አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ:— 01425853981500

ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ :— 1000089014135

የሀያትን ቤተሰቦች በስልክ ለማግኘት

0983676776
0920942369
0912823605

@tikvahethmagazine
HTML Embed Code:
2024/03/29 05:08:22
Back to Top