TG Telegram Group Link
Channel: ትምህርት በቤቴ®
Back to Bottom
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን ለሚወስዱ የተዘጋጀ መለማመጃ

በተቀመጠው መመሪያ መሠረት የኦንላይን ፈተናውን ይለማመዱ።

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ExitExam #ReExam

የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፤
ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ አምስት መቶ (500.00) ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፤
1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።
2. የድጋሚ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ አምስት መቶ ብር (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል። ( የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር)


❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"ዘንድሮ በወረቀት ከሚሰጠው ፈተና ጎን ለጎን ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መንግሥት በሚያዘጋጃቸው ኮምፒውተሮች ይከናወናል፡፡" - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት እንዲሁም በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይ የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች የራሳቸውን ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ ተወስኗሉ የሚሉ መረጃዎች ሲዘዋወሩ ታይቷል፡፡

"ይህንን በተመለከተ ለትምህርት ቤቶች የተላለፈ መልዕክት አለመኖሩንና ወላጆች ኮምፒውተር እንዲያዘጋጁ መጠየቃቸውም ተገቢ አለመሆኑን" የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

"ፈተናው መንግሥት በሚያዘጋጀው የኮምፒውተር አቅርቦት ይከናወናል" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ "ተማሪዎች አንብበውና በቂ ዝግጅት አድርገው የተመዘገቡበትን መታወቂያ ብቻ ይዘው መምጣት ነው የሚጠበቅባቸው" ብለዋል፡፡ "ሆኖም ትምህርት ቤቶችም ሆኑ ተማሪዎች የግል ኮምፒውተሮቻቸውን ለፈተናው መጠቀም ከፈለጉ እንደማይከለከሉ" ተናግረዋል፡፡

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በልምምድ ላይ እንደሚገኙ ያነሱት ኃላፊው፤ 156 የኮምፒውተር ባለሙያዎች ሰልጥነው በክልሎች ስልጠና እንዲሰጡ መሰማራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በዘንድሮው ፈተና ልምዶችን በመያዝ፤ በሚቀጥሉት ከ3 እስከ 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የመስጠት ዕቅድ መኖሩን ገልፀዋል፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሳይበር ጥቃት በመፈጸም ፈተናውን ለመስረቅ ጥረት አያደርጉም ብለን እንጠብቅም ፤ ያንን ለመከላከል ዝግጅት ተደርጓል 

በበይነ መረብ በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሳይበር ጥቃት እንዳይሰረቅ ዝግጅት መደረጉን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል ፤ " በዚህ ዓለም ምንም አይነት ችግር የሌለበት ነገር የለም። ሁሉም ነገር የራሱ የሆነ ችግር / ጉድለት ይኖረዋል ያለን ምርጫች ግን ችግሩን የመከላከል አቅም ጎን ለጎን መገንባት ነው " ብለዋል።

" በበይነ መረብ የሳይበር ጥቃት በመፈጸም ፈተናውን ለመስረቅ ጥረት አያደርጉም ብለን እንጠብቅም " ያሉት ዋና ዳይሬክቲ ፥ " የሳይበር ደህንነት (ሴክዩሪቲ) ስራዎች ፦
° ሞያው ባላቸው ፣
° መሳሪያዎች ባሏቸው
° አቅም ባላቸው ተቋማት በኩል ተገቢ የሆነ ዝግጅት አድርገን እየሰራን ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።

" በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ፈተናው ብዥታ ለመፍጠር የሚፈልጉ ፣ ፈተናው ላይ ጥቃት ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት ማወቅ ያለባቸው ይሄ #የፖለቲካ#የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም ማንም ወላጅ ልጁን አስተምሮ የሚያደርስበት ስለሆነ ሁለት ሶስቴ ማሰብ አለባቸው ፤ ተማሪዎቹ ነገ ለሀገር እዳ እንዳይሆኑ ማሰብ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

ከኦንላይን ፈተናው ጋር በተያያዘ ማንም አካል ወላጆችን " ኮምፒዩተር አቅርቡ " አላለም ፤ ሊጠየቁም አይገባም ከተጠየቅም ስህተት ነው ተብሏል።

ፈተና የሚሰጠው መንግሥት በሚያቀርበው አቅርቦት / ኮምፒየተር እንደሆነ ተመላክቷል።

ይህ ማለት የኮምፒዩተር አቅም ኖሯቸው ት/ቤታቸውን ማገዝ የሚፈልጉ ዜጎችን አይችሉም ማለት አይደለም ተብሏል።

የወረቅት ፈተናን በተመለከተ አሁን ላይ ህትመት ወደ መጠናቀቁ ሲሆን ፈተናው ልክ እንዳለፉት ፈተናዎች ደህንነቱ እንዲጠበቅ በቂ ዝግጅት መደረጉ፣ በክፍል ውስጥም ኩረጃ እንዳይኖርና ተማሪዎች በራሳቸውን ሰርተው እንዲያልፉ ካለፈው በጠነከረ ሁኔታ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገልጿል።

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገለፀ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ አምስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው ይህ የተገለፀው።

በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተሠራው የተቋማት ኦዲት ሪፖርት የ2014 በጀት ዓመት ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጣቸው 24 መሥሪያ ቤቶች ውስጥ 13 ተቋማት ላይ አስተደደራዊ ዕርምጃ መወሰዱን ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ለቋሚ ኮሚቴው ገልጸዋል፡፡

በዚህም የወላይታ ሶዶ፣ ጋምቤላ እና ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን ተናግረዋል።

ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መሠጠቱም ተገልጿል። #ሪፖርተር

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#የመውጫፈተና #ምረቃ

➡️ " ትምህርታችን በአግባቡ ብንጨርስም ለ8 ወራት ትዘገያላችሁ ተብለናል " - ተማሪዎች

➡️ " ይህ ውሳኔ የመጣዉ #ከትምህርት_ሚኒስቴር በመሆኑ ምንም ማድረግ አልቻልንም " -  የኮሌጅ አመራሮች

➡️ " የመጀመሪያ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች የተቋም ቆይታቸው ቢያንስ 4 ዓመት ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ከሰሞኑን በርካታ #የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከምረቃ እና ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቅሬታ መልዕክቶችን ልከዋል።

ቅሬታቸውን ከላኩት መካከል በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ ደሴ እና ሌሎች ከተማ የሚገኙ የኮሌጅ  ተማሪዎች ይገኙበታል።

ተማሪዎቹ " በ4 አመታት ውስጥ ማጠናቀቅ ያለብንን ትምህርታችን በአግባቡ ጨርሰን ፤ ክሊራንስም ሆነ የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ክፍያ ብንፈጽምም ድንገት ለ8 ወራት መቆየት አለባችሁ ተባልን " ሲሉ  ገልጸዋል ።

ቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎቹ ፦

° ከሌሎች ተመራቂ ተማሪዎች እኩል በሚባል ደረጃ ትምህርት እንደጀመሩ፤

° መወሰድ የሚጠበቅባቸው አስፈላጊውን ኮርስ ወስደው ማጠናቀቃቸውን፤

° የመዉጫ ፈተና የማዘጋጃ ቲቶሪያል መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

ይሁንና " የመዉጫ ፈተናዉን ልንወስድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩን የመመረቂያ ቀናችሁ ጊዜ በሚቀጥለዉ ዓመት ጥር ላይ ነው " በማለት የመውጫ ፈተናውን መውሰድ እንደማይጠቅመን እና የሀምሌ ወር ምረቃችን መሰረዙ ተነገረን ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ " ተመሳሳይ ባች ከሆኑ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እኛ በምን ተለይተን ነው ይሄ የተደረገው ? ለምን ሌላው ሊፈተን ሲዘጋጅ እኛ ግን ' ብትፈተኑም ጥቅም የለውም ቀጣይ ዓመት ጠብቁ ' ተባልን ? ይህ በፍጹም አግባብነት የለውም ፤ መፍትሄ እንሻለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከደረሱት ብዛት ያላቸው ቅሬታዎች በመነሳት ኮሌጆችን ለማነጋገር ጥረት አድርጓል።

ከነዚህም ውስጥ አንዱ የሆነዉ የኢንፎ ሊንክ ኮሌጅ ፥ ተማሪዎቹ የሚጠበቅባቸዉን ኮርስና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችን ማጠናቀቃቸዉን ልክ እንደሆነ ገልጿል።

ይሁንና የመመረቂያ ጊዜያቸዉ የተወሰነዉ ከትምህርት ሚኒስቴር በመጣ አቅጣጫ መሆኑን አስረድቷል።

ኮሌጁ ፤ ተማሪዎቹ #የተፈተኑበት_ጊዜ ምንም እንኳን 2012 ዓ/ም መሆኑን በወቅቱ ከትምህርት ሚኒስቴር በኩል ያገኙት 'የኦንላይን ዶክሜንት' ቢያሳይም በኋላ የመጣላቸዉ ኦሪጅናል ደግሞ 2013 ዓ/ም እንደሚል ገልጿል።

ይህም ደግሞ ተማሪዎቹን ወደኋላ እንደሚያቆያቸዉና ለሚቀጥሉት ወራት የተለያዩ ትሬኒጎችና የመዉጫ ፈተና መለማመጃዎች እየሰጡ ለማቆየት መታሰቡን አስረድቷል።

በሌላ በኩል ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ለተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ አንድ ደብዳቤ ተመልክተዋል።

ደብዳቤው ፦

በ2013 ዓ/ም ሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት የጀመሩ ተማሪዎች ለሰኔ ወር 2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ እንዲደረግላቸው የጠየቁ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳሉ ያስረዳል።

ነገር ግን የትምህርት ሥልጠና ፓሊሲው የመጀመሪያ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች የተቋም ቆይታቸው ቢያንስ 4 ዓመት እንደሆነ እንደሚደነግግ ይገልጻል።

አንዳንድ ተቋማት ህጋዊ ባልሆነ አግባብ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ መጠየቃቸውን በማንሳት ይህ የሚያስጠይቅ ነገር ስለሆነ ተቋማት ተማሪዎችን በአግባቡ በማብቃት የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ እንዲሰሩ አስጠንቅቋል።

❤️ @temhert_bebete
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ለ1 አመት የሚያገለግል ድምፅ አልባ ጄኔሬተር የፈጠረው የወለጋው ፌዴሳ ሹማ።

ፌዴሳ ሹማ ተወልዶ ያደገው በቄለም ወለጋ ሲሆን፣ በከተማው ውስጥ በኤሌክትሪክ ጥገና ሙያው ይታወቃል፡፡ ይህን የኤሌክትሪክ ጥገና ሥራውን የመብራት መጥፋት እና መቆራረጥ ብዙ ጊዜ አስተጓጉሎበታል።

"ችግር ብልሃትን ይወልዳል" እንዲሉ ወጣቱ ሥራውን በተደጋጋሚ ላስተጓጎለበት ችግር መላ መዘየድ እንዳለበት አሰበ፤ አስቦም ወደ ተግባር ገባ።

ከብዙ ጥረት በኋላ አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ እስከ አንድ ዓመት ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂ እውን አደረገ።

ወጣት ፌዴሳ ሹማ በኃይል አማራጭ ዘርፍ አብዮት ይፈጥራል ተብሎ የታመነበት መሣሪያ የፈጠራ ባለቤት ነው፡፡

ፈዴሳ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በሚመራው ልዩ የክረምት ወራት የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሀሳቦች ማበልፀጊያ መርሐ ግብር ተሳትፎው ባገኘው ስልጠና እና ሙያዊ ድጋፍም ቴክኖሎጂውን ይበልጥ አዘምኖ መሥራት ችሏል።

ቴክኖሎጂው የመብራት አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ለሞባይል፣ ለቴሌቭዥን፣ ለፍሪጅ እና የትኛውንም ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችን ቻርጅ የሚያደርግ፣ የሚያንቀሳቅስ እና በገመድ እና ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሠራ ነው።

አንዴ የያዘውን ኃይል ደጋግሞ እያደሰ (recycling) ራሱን ቻርጅ ከማድረግ አልፎ ለረዥም ጊዜ ኃይል ማመንጨት የሚችለው ይህ ቴክኖሎጂ በሀገራችን ብቻ ሣይሆን ምን አልባትም በዓለማችን ላይ በኃይል አማራጭ ዘርፍ አብዮት መፍጠር እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።

ከ300 ዋት ጀምሮ እንደ ተጠቃሚው አቅም እና ፍላጎት የሚዘጋጀው ይህ ድምፅ አልባ ጄኔሬተር አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ነው ወጣቱ ያረጋገጠው።

በዚህም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን በቤቱ መብራት የማይጠፋበት ብቸኛው ሰው መሆኑን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ የሚያመላክተው ሲል ኢቢሲ ዘግበዋል።

አሁን ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወጣቱ የራሱን ኩባንያ የሚከፍትበትን እና ቴክኖሎጂው በስፋት ተመርቶ ለህብረተሰቡ ማድረስ የሚቻልበትን ሁኔታ ላይ እየሠራ ይገኛል ተብሏል።

Via - fastmereja

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ2016 ዓ.ም ሞዴል ፈተና በመሰጠት ላይ መሆኑ ተገለጸ።


ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ለሚገኙ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ ከቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ሞዴል ፈተናው ተማሪዎቹ ለመደበኛው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ክልላዊ ፈተና በአግባቡ መዘጋጀት እንዲችሉ ቢሮው ከክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ጋር በጋራ በመሆን ስታንዳርዱን የጠበቀ ፈተና ማዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ገልጸው ሞዴል ፈተናው በአግባቡ እንዲሰጥ በየተቋማቱ ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች መመደባቸውን አስታውቀዋል።


❤️ @temhert_bebete
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በመጪው ሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ን በድጋሜ ለሚወስዱ ተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።

1ኛ. በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የነበረና አሁን በድጋሜ ለመፈተን ማመልከት ለሚፈልጉ፤

2ኛ. ከሰኔ 2015 ዓ.ም በፊት #የሕግ_መውጫ_ፈተና ወስደው የማለፍያ ነጥብ ያለገኙ አሁን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርስቲያቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የተላከላቸው አመልካቾች፤

ምዝገባው እስከ ግንቦት 25/ 2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ተፈታኞች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ ምዝገባውን እንዲያጠናቅቁ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ ፦

➡️ ከላይ ከተገለጸው ጊዜ ውጭ የሚቀርቡ የምዝገባ ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው አሳስቧል።

➡️ በሰኔ 2015 ዓ / ም እና በየካቲት 2016 ዓ / ም ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያልመጡ አሁን በድጋሜ መፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች የሚጠበቅባቸውን የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር ብቻ መፈጸም አለባቸው ተብሏል።

➡️ ከሰኔ 2015 ዓ/ም በፊት ለሕግ መውጫ ፈተና ተቀምጠው በድጋሜ ለመፈተን የሚፈልጉ አመልካቾች ስም ዝርዝራቸው ከቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው መላኩን በማረጋጥ የሚጠበቅባቸውን #የአገልግሎት_ክፍያ ለዚሁ ጉዳይ ብቻ በተከፈተው የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ➡️1000553176097 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን በግልፅ በሚታይ #ስካን_ኮፒ በማድረግ በ [email protected] ኢሜል አድራሻ እንዲልኩ ጥሪ ቀርቧል።

❤️ @temhert_bebete
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎቹን በት/ቤታቸው ለማስፈተን ምን ማሟላት አለባቸው?

ግንቦት 24/2016 ዓ.ም ( የትምህርት ሚኒስቴር) በዚህ አመት በኦንላይን የተዘጋጅውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ አገር አቀፍ ፈተናን ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ለማስፈተን ፍላጎት ያለው ማንኛዉም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት የተደራጀ የኮምፒዉተር ላብራቶሪ ሊኖረው ግድ ይለዋል። ይሄውም
1. ዴስክቶፕ ወይም ላፕቶፕ ኮምፒዉተሮች
2. የዉስጥ ኔትዎርክ ያለዉ (የገመድ) ኔትዎርክ/Local Area Network /
3. የኢንተርኔት መስመር ከበቂ ባንድዊድዝ ጋር እንደ የመፈተኛ ኮምፒዉተር ብዛት
4. የባክ አፕ ፓዎር (ጄኔሬተር)
ጋር አሟልተው መገኘትና ለትምህርት ቢሮዎች በማሳወቅ በቢሮዎች በኩል መሟላቱ ሲረጋግጥ የፈተና ማእከል በመሆን ተማሪዎቹን ማስፈተን እንደሚችሉ እያሳውቅን ለፈተና የሚዘጋጁት ዴስክቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒዉተሮች ማሟላት ያለበቸዉ ትንሹ ስፔስፊኬሽን እንደሚከተለው ቀርቧል።
1. RAM --------------- 4GB or higher
2. Storage --------------250GB or higher
3. Processor Speed -------- 2.5GHZ or higher
4. Processors ---------- Intel Core i3 or higher
5. OS --------------- Windows 10
6. Browsers ---------------Safe Exam Browser and other
7. Accessories ---------- Keyboards and Mouse for desktop computers.

❤️ @temhert_bebete
❤️ @temhert_bebete
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ተረጋግጧል!
ከ Notcoin Community በመብለጥ እና ህጋዊ ሆኖ የመጣው Hamster Kombat ሌላ ገራሚ የጨዋታ ፕላትፎርም ይዞ መጥቷል።

ለመጀመር ይህን ይጠቀሙ👇

https://hottg.com/hamSter_kombat_bot/start?startapp=kentId433177540

Play with me, become cryptoexchange CEO and get a token airdrop!
💸 2k Coins as a first-time gift
🔥 25k Coins if you have Telegram Premium

ጊዜ የለም እድሉ እዳያመልጣችሁ!
HTML Embed Code:
2024/06/01 15:25:40
Back to Top