TG Telegram Group Link
Channel: የኢትኤል ብዕሮች
Back to Bottom
ከራስህ ጀምር

የሚከተሉት ቃላት በአንድ ሰው መቃብር ላይ የተፃፋ ናቸው።

ወጣትና ነፃ ሳለሁ ና ምናቤ ገደብ በሌለው ወቅት አለምን ስለመለወጥ አልም ነበር። እያደግኩና እየበሰልኩ ስመጣ ግን እንደማትለወጥ አወቅኩ፣ ስለዚህ ምኞቴን አጠር አደረኩና ሀገሬን ለመለወጥ ወሰንኩ። ነገር ግን እሱም የሚሳካ አልመሰለኝም።ወደ መጨረሻ እድሜዬ እየደረስኩ ስመጣ በአንድ የመጨረሻ ተስፋ የመቁሩጥ ሙከራ ፣ የራሴን ቤተሰቤን ብቻ ፣ ለእኔ ቅርብ የሆኑትን ለመለወጥ ወሰንኩ ፤ እሱም አልሆነም።

እና አሁን በምሞትበት አልጋ ላይ ተጋድሜ ድንገት ይህንን አስተዋልኩ፤ ራሴን ለውጬ ቢሆን ኖሮ ፣ ምሳሌ በመሆን ቤተሰቤን መለወጥ እችል ነበር። ከእነርሱ ምሳሌነት ማበረታቻ የተነሳ ፣ ሀገሬን የተሻለ ማድረግና ማን ያውቃል አለምንም መቀየር እችል ይሆን ነበር።

#ሼር ይደረግ
የታላላቅ ሰዎች ምርጥ አባባሎች

ሰው የሚማረው አንድም በፊደል፣ አንድም በመከራ ነው፣ አንድም በሳር “ሀ” ብሎ፣ አንድም በኣሳር “ዋ” ብሎ።”
#ፀጋዬ ገ/መድህን

እውነት እርቃኑን በባዶው መራመድ ይችላል፡፡ ውሸት ግን ሁልጊዜ
አምሮና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል፡፡
#ካህሊል ጂብራን

የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ። ሁለቱም የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው።
#ዊሊያም ሼክስፒር

እምነት ባለዩት ነገር ማመን ሲሆን ሽልማቱም ያመንቱን ነገር ማየት ነው።
#ጳጳስ ኦገስቲን

ማለም የፈጠራ መነሻ ነው ፤ የምትፈልገውን ታልማለህ ፣ ያለምከውን ትመኛለህ ፤ በመጨረሻም የተመኘኸውን ትፈጥራለህ።
#ጆርጅ በርናንድ ሾው

ለመጀመር ስኬታማ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ስኬታማ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡
#ዚግ ዚግላር

በብርሃን ስትሆን ሁሉ ነገር ይከተልሃል:: ጨለማ ውስጥ ከሆንክ ግን ጥላህ እንኳን አይከተልህም።
#ሂትለር

ሳንቲም ብዙ ድምፅ ያሰማል:: ገንዘብ ግን ምንም አያሰማም:: ስለዚህ ዋጋህ ሲጨምር ወሬህን እየቀነስክ ና!
#ዊሊያም ሼክስፒር

ደሀ ሆነህ ብትወለድ ጥፋቱ ያንተ አይደለም ደሀ ሆነህ ብትሞት ግን ጥፋቱ ያንተ ነው።
#ቢል ጌትስ

ደካሞች ይቅር ማለት አይቻላቸውም። ይቅር ባይነት የጠንካሮች ብቻ ባህርይ ነው።
#መሀተመ ጋንዲ

በምድር ላይ የማያለወጠው ነገር ቢኖር ራሱ ለውጥ ነው።
#መሀተመ ጋንዲ

ቁንጅና ያለው ፊት ላይ አይደለም፡፡ ቁንጅና በውስጣችን የሚገኝ የልብ
ብርሃን ነው፡፡
#ካህሊል ጂብራን

በዓለም አንተ ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ ራስህ ኹነው።አለም ላይ ሰላም ፍቅር እንዲኖር ከፈለክ አፍቃሪ እና ሰላማዊ በመሆን ከራስህ ጀምር
#መሀተመ ጋንዲ
"አሳፋሪው ነገር መውደቅህ ሳይሆን ወደቀህ አለመነሳትህ ነው!!

‹‹በስኬቴ አትዳኙኝ፡፡ ይልቁንስ ምን ያህል ጊዜ ወድቄ ምን ያህል ጊዜ መልሼ እንደተነሳሁ አይታቹህ ፍረዱኝ (Do not judge me by my success, judge me by how many times I fell down and got back up again)›› ይላሉ፡፡

🌿አዎ! የአወዳደቅህ ሳይሆን የአነሳስህ ሁኔታ ያንተን ማንነት አጥርቶ ያሳያል፡፡ የወደቁ ሳይሆን ከውድቀታቸው የተነሱ አዕምሯቸው ሰፊ ስለመሆኑ ክርክር አያሻውም፡፡ በጠባቡ አስተሳሰባቸው ወድቀው በሰፊ አስተሳሰባቸው ሕይወታቸውን ያሰፉና ከውድቀታቸው የተነሱ ትንሳኤ ብሩሃን የሆኑ ሊደነቁ ይገባል፡፡ ምክንያቱም በመውደቅ መነሳታቸው መካከል ያገኙት ትምህርት እንዴት ከውድቀት መነሳት እንደሚቻል አዲስ ዕውቀት አስጨብጧቸዋል፡፡ ተስፋ ቆርጠው ወድቀው አለመቅረታቸው የሚያሳየው የአስተሳሰባቸው ጮራ ምን ያህል የበራ እንደነበረ የሚያሳይ ነውና፡፡

🌿አዎ! ዛሬ ዛሬ ብዙዎቻችን በተለያዩ ውድቀቶችና አወዳደቆች ተፍገምግመናል፡፡ የሚያሳፍረውና የሚያስፈራው ነገር ከውድቀታችን ለመነሳት ፍላጎቱም ሆነ ቁርጠኝነቱ የሌለን መሆኑ ነው፡፡ አንዳንዶች በዘረኝነት ወድቀዋል፣ ጥቂቶች በትእቢት በአፍጢማቸው ተተክለዋል፡፡ ቀላል ቁጥር የሌላቸው አወቅን ብለው ደንቁረዋል፤ ሰፋን ብለው ጠብበዋል፡፡ ሰለጠንን ያሉት እቡያን ሰይጥነዋል፡፡ ከዕድሜአቸው ያልተማሩ፤ ከብዝሃ ማንነታቸው ቀለም ያልቆጠሩ፣ መልካሙን ያልኮረጁ ቆመ-ቀሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ ከብዝሃ ማንነታቸው ያልተማሩ በአንዱ ማንነታቸው የሙጥኝ ያሉ አዲስ ሃሳብ ያስደነግጣቸዋል፤ ለውጥ ይቀፋቸዋል፤ አዲስ ማንነት ያስፈራቸዋል፡፡

🌿 አዎ! አንድ ሰው ብዙ ነው፡፡ ብዙነቱን ግን እውን የሚያደርገው በሰፊው አስተሳሰቡ ሲሰፋ ነው፡፡ ከተፈራረቁበት ማንነቶቹ ጠቃሚውን ማንነት ፈልቅቆ የሚያወጣ ብልህ ሰው ከብዙነቱ እልፍ ትምህርት ቀስሟል፡፡ ቅስሙን የሚሰብር ሳይሆን ቅስሙን በአዲስ አስተሳሰብ የሚጠግን ጀግና ካለፈው ሕይወቱ ብዙ የተማረ ነው፡፡ ከውድቀቱ የሚማር መላልሶ መነሳት አይቸግረውምና፡፡

🌿 ወዳጄ ሆይ… አንተ አንድ ሰው አይደለህምና እንደብዙ ሰው አስብ የዕለቱ መልዕክት ነው! መውደቅን አትፍራ! ነገር ግን እንዴት ከወደቅበት ቦታ መነሳት እንደምትችል አዕምሮህን አሰራ፡፡ መውደቅ በማንም ላይ የሚደርስ ነው፡፡ ከዛ ይልቅ ወድቆ መቅረት ነው አሳፋሪው ነገር፡፡
አሳዛኝ ዜና
ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ሲያገለግሉ የኖሩት ታላቁ አባት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ዐረፉ። ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ሲያገለግሉ የኖሩ ታላቅና ትሑት ነበሩ። በረከታቸው ትድረሰን።
ልብ እንበል !!!!!!!!!!!!! እረ የተወህዶ ልጆች እንቃ እባካችሁን እንቃ የአባቶቻችንን ትንቢት እንዳንረሳ አደራ አደራ አደራ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ተነገረዉ ትንቢት የሚያምን
anonymous poll

አዎን አምናለሁ – 11
👍👍👍👍👍👍👍 85%

አይ አላምንም – 2
👍 15%

👥 13 people voted so far.
እስቲ አላምንም ካላችሁ በዚህ ቦት ሀሳባችሁን አጋሩኝ📩📩📩📩📩📩@Tsegazagbot📩📩📩📩📩📩📩
~ ዜና ዕረፍት
ዋርካዎቻችን እየወደቁ ነው።
*~★★~*

#ETHIOPIA | ~ በረከታቸው ይደርብን !! አሜን።

… በዚያን ዘመን ክፍለ ሃገር በአሁኑ ዘመን ደግሞ ሃገር በሆነችው በኤርትራ በማዕረገ ጵጵስና ሐዋርያዊ ሥራቸውን የጀመሩት በቀደመ ስማቸው አባ ኢያሱ ገብሬ ኋላ ላይ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶክተር) ከረጅም ዘመን ሐዋርያዊ አገልግሎት በኋላ በሚወዷት ሃገራቸው በእናት ኢትዮጵያ ምድር በተወለዱ በ81 ዓመታቸው ዓርፈዋል።

… እንደ ሐራ ዘገባ ከካህን አባታቸው ከመምህር ገብረ ሕይወት እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብርነሽ በወሎ ክፍለ ሀገር በዋግ አውራጃ በ1932 ዓ.ም. የተወለዱት ብፁዕነታቸው፣ የወሎ ክፍለ ሀገር ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ ማዕርገ ዲቁናን፤ ሥርዓተ ምንኵስናን በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከቆሞስ ሊቀ ምርፋቅ ኤርሚያስ በ1958 ዓ.ም፤ ሥልጣነ ቅስናን ከወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በ1959 ዓ.ም ተቀብለዋል፡፡

•••
የቅኔንና የአገባብን ይትበሃል በሚገባ አጠናቀው በመምህርነት የተመረቁት የአቋቋም እና የትርጓሜ መጻሕፍት ዐዋቂው ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ በ1962 ዓ.ም. ወደ ቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረት ተልከው ከሌኒን ግራድ መንፈሳዊ ኮሌጅ የማስተር ኦቭ ዲቪኒቲ ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ውጤት አግኝተዋል፡፡

•••
የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በዚኹ መንፈሳዊ ኮሌጅ ቀጥለው እና በሚገባ ፈጽመው በትምህርተ ሥጋዌ ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል፡፡ ወደ ሰሜን አሜሪካ ዘልቀውም ከፕሪንስተን መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የማስተር ኦቭ ቴዎሎጂ ዲግሪ ጨምረዋል፡፡ የዶክትሬት ሥራቸው፣ ሞስኮ እና ኒውዮርክ በሚገኙት የዩኔስኮ የትምህርት ኮሚሽኖች ተመርምሮ ጸድቆላቸዋል፡፡

የብፁዕነታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ እሑድ፣ ኅዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከቅዳሴ ውጪ፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተጠቁሟል፡፡

… እንግዲህ እናስተውል። ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ ብቻ 8 ብፁዓን አባቶች አጥተናል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አምስቱን አባቶች ያጣናቸውና የተለዩን ባለፉት 7 ዋራት ውስጥ ነው። ልብ ያለው ልብ ይበል።

፩ኛ፥ ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ። ሰኔ/2010
፪ኛ፥ ብፁዕ አቡነ ገሪማ። ሚያዚያ/2011
፫ኛ፥ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ። ግንቦት/2011
፬ኛ፥ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል። ታኅሣሥ/2012
፭ኛ፥ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ። መጋቢት/2012
፮ኛ፥ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ጥቅምት/2013
፯ኛ፥ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ኅዳር/2013 ዓም
፰ኛ፥ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ኅዳር/2013 ዓመተ ምህረት ተለይተውናል።

… አስተውላችሁ ከሆነ ሰሞኑን በየፌስቡኩ ግድግዳ ላይ የመሞታቸው ዜና የሚለጠፍ የብዙ የሚያማምሩ አፍላ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ፎቶግራፍ ማየት እየበረከተ ነው። ያውም መታመማቸው ሳይሰማ ሞታቸው እየተነገረ ብዙዎች ሲደነግጡም እያየሁ ነው። ከአንድ ቤት በድንገት ሁለት ሦስት ሰው በአንድ ጊዜም እየተጠሩ ነው። ትናንት በሰላም በደህና አብራችሁ ስታወጉ፣ ስትጨዋወቱ ያመሻችሁት ሰው በማግስቱ የለም። እናም እናስተውል። መደንገጥ፣ መርበትበት ብቻውን መፍትሄ አይሆንም። ተዘጋጅተንም እንጠብቀው። በዙሪያችን እየሆነ ያለውን ነገር በሚገባ ጊዜ ሰጥተን መመርመሩም መልካም ነው። የወንድም እህቶቻችንንም ነፍስ ይማር።



… የብፁዓን አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን። አሜን።
በደንብ አስተዎሉ 🙏🙏🙏🙏🙏
🗣🗣🗣ጆሮ ያለው ይስማ : ልብ ያለው ልብ ይበል

ይህ የበረኸኞች ቅዱሳን አባቶቻችን የንስሐ ግቡ ጥሪ ነው።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቢያንስ ለ 21 የተዋህዶ ልጆች Share በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን እንወጣ

ነገ ከባድ የመከራ ጊዜ አለና ዛሬውኑ ንስሐ ገብታችሁ ተዘጋጁ።

2012፣ 2013፣2014፣ የኢትዮጵያ የምጥ ዘመናት ናቸው።

😭ንስሐ ያልገባ በቶሎ ንስሐ ይግባ። ንስሐ የገባ ደግሞ በየሳምንቱ ለነፍስ አባቱ ራሱን ያስመርምር
የመዳን ቀን ዛሬ ነውና

😴በስንፍና ነገ ንስሀ እንገባለን ያላችሁ ነገ አባቶችን ላታገኙቸዉ ትችላላችሁ እና እንዳይረፍድባችሁ

ሥጋወደሙ የተቀበሉ፣ ንስሐ የገቡ ሰዎች ብቻ ጨለማውን ይሻገሩታል። ንጉሡ ከመምጣቱ በፊት አባጣ፣ ጎርባጣው የግድ መስተካከል አለበት። ተራራው ዝቅ ማለት አለበት። ጉድባው ጉድጓዱ መሙላት አለበት። በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር እስከ 2014 መጨረሻ ድረስ መከራው እንዲሁ
ይቀጥላል። ዘመኑ የምንጣሮ ዘመን ነው። ከኢትዮጵያ መከራ
ፍጻሜ በኋላ የመላዋ ዓለም መከራ ደግሞ ከዚያ በኋላ
ይጀምራል።

🗣🗣በቶሎ ንስሐ ገብታችሁ የታዘዛችሁትን ቀኖና ፈፀሙ ።

ዜጎች ቀን በቀን ይታረዳሉ ። አለቃው ይበዛል። አዛዥ እንጂ ታዛዥ አይኖርም። ሁሉ አለቃ፣ ሁሉ አዛዥ ይሆናል። ፍትሕና ሕግ ስፍራቸውን ለቀው ይሰደዳሉ። ትርምስምሱ ይወጣል። የሚያዝ የሚጨበጠው ይጠፋል። ክስ አድማጭ አይኖረውም። ወታደር ግራ ይጋባል። ዜጎች አማራጭ ያጣሉ። የውስጥም የውጪም ጠላቶች መግቢያ ቀዳዳው ይሰፋላቸዋል።

በአራቱም አቅጣጫ ኢትዮጵያ ትወረራለች። ሰላም በማስከበር
በሚል ሰበብም በ2 ሃያላን ሀገራት የሚመሩ ሰባት የሙስሊም ሀገራት በኢትዮጵያ ምድር ላይ እሳት ያዘንባሉ። በአሰብ ወደብ ላይ በልዩ ሁኔታ የተከማቸው የጦር መሣሪያ በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንደበረዶ ይዘንባል። ብዙ ፍጅትም ይሆናል።
ኦርቶዶክሳውያን በያሉበት፣ በየተገኙበት እንደከብት ይታረዳሉ። የኢትዮጵያ ምድር በደም ትጨቀያለች። የደም ጎርፍ፣ የደም አበላ በምድሪቱ ላይ ይፈሳል ።

🗣🗣ንስሐ ግቡ : ንስሐ ግቡ : ንስሐ ግቡ

ክፉ ረሃብ በኢትዮጵያ
ይመጣል። የሚበላ የሚጠጣ ከምድሪቱ ይጠፋል። ከጦርነቱ
የተረፈውን ህዝብ ረሃብ ይፈጀዋል። በስደት ምክንያት የዐቢይ ጾም የማይጾምበት ጊዜም ይመጣል። በረሃቡ ጊዜ ግን ጥቂቶችን የመትረፊያ ገዳማት ግን አሉ። ሰው የሚተርፍባቸው ገዳማትና አድባራት አሉ። ታቦተ ኢየሱስ ያለባቸው ገዳማትና አድባራት በሙሉ ሰው ይተርፍባቸዋል። በጊዜው እስከ አሁን ዝግ
የሆኑ ዋሻዎች ይከፈታሉ። የሚተርፉ ኢትዮጵያውያንም በዚያ
ይጠለላሉ። ከአሁኑ ጨውና የማይነቅዙ እህሎች አከማቹ።

🗣🗣ንስሐ ግቡ : ንስሐ ግቡ : ንስሐ ግቡ

ከዚያም ክፉ በሽታ ይመጣል። ክፉ ወረርሽኝ ይከሰታል። ወረርሽኙ የ12 ሁለት ሰዓት ዕድሜ ብቻ የሚሰጥ ክፉ በሽታ ሲሆን ይኼም ጦርነቱንና ረሃቡን ተከትሎ ይመጣል።

🗣🗣መፍትሄው ንስሐ መግባት፣ ሥጋወደሙ መቀበል ነው።

አባቶች እንዲህ አሉ: ነገ ንስሐህን የሚቀበል ካህንም ላታገኙ
ትችላላችሁና ይሄን መልእክት የማንበብ ዕድል የገጠማችሁ
ልጆቻችን ሆይ ጨርቄን፣ ማቄን፣ ሳትሉ፣ ወገቤን ደረቴን ሳትሉ፣
ምክንያት ሳትደረድሩ፣ ዕለቱኑ ዛሬውኑ ንስሐ ግቡ።

🗣🗣ንስሐ ግቡ : ንስሐ ግቡ : ንስሐ ግቡ

2015 በዘመነ ሉቃስ ንጉሱ ይመጣል። ለሳምንት ዝናብ ይዘንባል። የፈሰሰውን ደም አጥቦ ያስወግዳል። ምድር ትባረካለች።
የተረፉት ሰዎች እርስ በእርስ ይፈቃቀራሉ። ጠማማ ሰው አይኖርም። ንጉሱ ቴዎድሮስ በፍቅር ለ40 ዓመታት ይመራል።

🗣🗣 በመላው ኢትዮጵያ የምትኖሩ ልጆቻችን ሆይ እነሆ አስቀድሞ በአባቶቻችን የተነገረው ሊፈፀም ግድ ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል። በሗለኛው ጊዜ አልሰማንም : አላየንም እንዳትሉ እነሆ ከመከራው አስቀድሞ ይህ መልዕክት ከብዙ በጥቂቱ ለአእምሮ በሚመጥን ልብን በሚገዛ መልኩ ለመላው ህዝበ ክርስቲያን አስተላልፈናል።

🗣በጸሎት የምንለምንና የምንማልድ ሁላችንንም በሰላም በመንፈስ ይጠብቀን ፍቅርንም ይስጠን ዓይነ ልቡናችንን ያብራልን ፈቃዱም ሆኖ ጸሎታችንን ይቀበል ዘንድ ቀርበን እግዚአብሔርን እንለምነው!
ዐውቀን በሃብቱ እናድግ ዘንድ በእርሱም ስም እንመካ
ዘንድ...በነቢያት በሐዋርያትም መሰረት ላይ እንታነጽ ዘንድ
እንግዲህ በመንፈስ ቅዱስ እንነሳ!
ቀርበን አምላካችን እግዚአብሔርን እንለምነው ወዶ ጸሎታችንን
ይቀበል ዘንድ። አሜን!

🗣🗣🗣ንስሐ ግቡ : ንስሐ ግቡ : ንስሐ ግቡ

ቅዱስ አባ ዘወንጌል፣ ፍካሬ ኢየሱስ፣ ራዕየ ባሮክ ፣
የአባቶች ትንቢት
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Share share share share share share

1 ሰው ለ 21 ምዕመን

ለመላው ህዝበ ክርስትያን መልዕክቱ እንዲደርስ በማድረግ የአባቶቻችንን አደራ እንወጣ

🗣ጆሮ ያለው ይስማ : ልብ ያለው ልብ ይበል

🗣መንግስተ ሰማያት ቀርባለች እና ንስሐ ግቡ

ውድድርሙኒ አስሙናኤል 21፣ ለምለምሊጊኖን 21 አካ ክስብኤል ቤቃ ጼቃ ሴቃ አልፋ ወኦ ቤጣ የውጣ ዮድ አህያ ሸራህያ ኤልሻዳይ ጸባዖት አማኑኤል እልመክኑን 21 .......

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Share share share share share share

ለ 21 የተዋህዶ ልጆች Share በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን እንወጣ
የኢትኤል ብዕሮች pinned «🗣🗣🗣ጆሮ ያለው ይስማ : ልብ ያለው ልብ ይበል ይህ የበረኸኞች ቅዱሳን አባቶቻችን የንስሐ ግቡ ጥሪ ነው። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ቢያንስ ለ 21 የተዋህዶ ልጆች Share በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ነገ ከባድ የመከራ ጊዜ አለና ዛሬውኑ ንስሐ ገብታችሁ ተዘጋጁ። 2012፣ 2013፣2014፣ የኢትዮጵያ የምጥ ዘመናት ናቸው። 😭ንስሐ ያልገባ በቶሎ ንስሐ ይግባ። ንስሐ የገባ ደግሞ በየሳምንቱ…»
Channel photo removed
#ታህሳስ 3
ባዕታ ለማርያም-
እመቤታችን ቤተመቅደስ የገባችበት ዕለት ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤልም እመቤታችንን የመገበበትና የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤ ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤ ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ፡፡›› በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን በቤተ መቅደስ በፍጹም በንጽሕናና በቅድስና ስለመኖሯ ሊቁ ቅዱስ አባ ሕርያቆስ ሲናገር ነው እንዲህ ያለው፡፡
በዓታለማርያም፡-የብርሃን እናቱ የድንግል ወላዲተ አምላክን የትውልዷን ነገር አስቀደመን እንናገራለን፡፡ ጥንተ ነገሩ እንዲህ ነው፡- ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ የከበሩ ደጋግ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው በሕገ እግዚአብሔር ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱም በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን መካን ስለ ነነበሩ የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውም፡፡
አንድ ቀን ጴጥርቃ ቴክታን እንዲህ አላት፡- ‹‹እህቴ ሆይ! ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን? ልጅ የለን የሚወርሰን፣ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ወንድሜ ሆይ! አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ›› ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳን ስላደርገው በልቦናዬም እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቃል›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም፣ ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማኅፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ፣ ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አየሁ›› አለችው፡፡ እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሔዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ ‹‹እግዚአብሔር በምሕረቱ አይቷችኋል፣ በሳህሉ መግቧአችኀል፣ 7 አንስት ጥጆች መውለዳችሁ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላችሁ፤ ከቤታችሁ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም›› አለው፡፡
ጴጥርቃም ሕልም ፈቺው የነገረውን ሁሉ ሔዶ ለሚስቱ ነገራት፡፡ እርሷም ‹‹እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል!?›› ብላ ዝም አለች፡፡ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት፤ ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች ፣በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት፡፡ ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደችና ቶና አለቻት፣ ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት፣ ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፣ ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት፣ ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሐናን ወለደች፡፡
ይህቺም ሐና በሥርዓት አድጋ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነ ቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም ጋር አጋቧት፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፡፡ እነርሱም እጅግ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድ ልጅ እንኳ ስላልነበራቸው እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ አጥብቀው ይለምኑት ነበር፡፡ መብዓ ይዘው ለሊቀ ካህኑ ሲሰጡት ሊቀ ካህኑም እንኳ ሳይቀር ‹‹እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ያለውን ሕግ በእናንተ ላይ እንዳይፈጸም አድርጎ ልጅ የከለከላችሁ ኃጢአተኛ ብትሆኑ ነውና መብዓችሁን አልቀበልም›› ብሎ በእጅጉ አሳዝኗቸዋል፡፡ በሊቀ ካህኑ እያዘኑና እየተከዙ ሲመለሱ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ዛፍ ሥር ተቀመጠው ሳለ እርግቦች ጫጩቶቻቸውን ሲያጫውቱ ተመልክተው ‹‹ለእነዚህ ወፎች እንኳ ልጆችን የሰጠህ አምላክ ለእኛስ መች ይሆን ልጅ የምትሰጠን?›› ብለው እጅግ አምርረው አለቀሱ፡፡
ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ ‹‹አቤቱ ጌታዬ ለዚች እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ?›› እያለችም ርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ውኃ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን›› ብለው ስዕለት ገቡ፡፡ ዘካርያስም ‹‹እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስዕለታችሁን ይቀበልላችሁ የልቦናችሁን ሀሳብ ይፈጽምላችሁ›› ብሎ አሳረገላቸው።
ከዚህም በኋላ ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩስ እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም ‹‹7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› አላት፡፡ ‹‹ወፍ›› የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው፤ ‹‹ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ››ማለቱ የኢያቄምን (የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው ዕወቅ ሲል ነው፡፡
7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባሕርይውም ልዕልናው ናቸው፡፡ ሐናም ‹‹እኔም ደግሞ አየሁ እንጂ›› አለችው፡፡ ‹‹ምን አየሽ?›› ቢላት ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ›› አለችው፡፡ ‹‹ርግብ›› የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፤ ነጭነቱ ንጽህናዋ ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡ ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ›› ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሷን ነው፡፡ ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው፡፡
እነርሱም እንዲህ ያለ ራእይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም ይልቁንም ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሔዋንን‹ ‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት›› ብሎ ያበሰረ አምላክ ለእኛስ ይልክልን የለምን?›› ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ‹‹‹ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ሥጋ ተገናኙ› ብሎሏችኀል ጌታ›› ብሎ መልአኩ ለቅድስት ሐና ነገራት፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አብርሃምን እና ሳራን የተመለከተ አምላክ በኢያቄምና ሐና አማካኝነት ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነችውን እና ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቦና ታስባ ትኖር የነበረች የተነገረላት ትንቢት ሊፈጸም የአባት የእናቷ የቅድመ አያቶቿ ራእይ ሊተረጎም ጌታ የፈቀደበት ጊዜ ሲደርስ እመቤታችን እግዝእትነ ማር
ያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን በ16 ዓ.ዓ ተፀነሰች፡፡
እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ፤ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት፡፡
ቅድስት ሐናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዯአት፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነሥቶ
"ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሐየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ" ብሎ ሰገደላት፡፡ አይሁድም ይህ ተአምር ሲደረግ ከዚያው ነበሩና "ምነው ሳሚና ስምን አየህ? ምን ትላለህ?" ቢሉት
"ከዚች ከሐና ማኅፀን የምትወለደው ሕፃን ሰማይ ምድርን አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማሁ" አላቸው፡፡
ዳግመኛም "እኔንም ያነሣችኝ የፈወሰችኝያዳነችኝ እርሷናት" አላቸው፡፡
አይሁድም "በል ተወው ሰማንህ" ብለው ቅናትጀመሩ፡፡ሐና በእርጅናዋ ጊዜ መፀነሷን የተመለከቱ ዘመዶቿና ያገሯ ሰዎች ተገርመው እየመጡ ይጠይቋት ነበር፡፡
እመቤታችን ማርያም በፅንስ እያለች ብዙ ታምራትን አድርጋለች። ከእነዚህም መካከል ዐይነ ስውር የነበረችው የአርሳ ባንልጅ ወደ ሐና መጥታ እውነትም ሐና መጸነሷን ለማረጋገጥ ሆዷን ዳሰሰቻት፡፡እርሷም ሳታስበው ዐይኗን ስትነካ ዐይኗ በራላት፡፡
እመቤታችንም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች፡፡ሦስት ዓመትም በሆናት ጊዜ እናትና አባቷ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስትሐ ና ስዕለታቸውን አስበው የአምላክ እናት ብፅዓት አድርገው ለእግዚአብሔር ይሰጧት ዘንድ በዛሬዋ ዕለት ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዷት፡፡

"ልመናዋ ይደረግልን አማላጅነቶ አይለየን"
HTML Embed Code:
2025/04/08 04:47:17
Back to Top