TG Telegram Group Link
Channel: መዝገበ ሃይማኖት
Back to Bottom
ወላጅነት ብዙውን ጊዜ ከማራቶን ጋር ይነጻጸራል፤ ትክክል ነው። ከወሊድ ክፍል ርቆ የሚሄድ፣ የማያቋርጥ ጥረት እና የማያወላውል ትጋት የሚጠይቅ ጉዞ ነው። ነገር ግን ከማራቶን በተቃራኒ ልጅ ማሳደግ የመጨረሻ መስመር የለውም። የወላጅነት ሚናችን መጠናቀቁን የሚያመላክት የመጨረሻ ነጥብ ወይም ስኬት የለም። ይልቁንም፣ ወላጅነት ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት፣ የህይወት ዘመን ትምህርት እና ዕድገት ነው። ታዲያ ይህን የወላጅነት ማራቶን ለማሸነፍ እንዴት እንሩጥ? ልጆቻችን ሕይወታቸውን ለመምራት አስፈላጊ የሆኑ ክህሎቶችን እና እሴቶችን ታጥቀው ስኬታማ ግለሰቦች ሆነው እንዲያድጉ እንዴት ማድረግ እንችላለን?

መልሱ ሁለንተናዊ ወላጅነት እና ሙሉውን ሕፃን ማሳደግ ነው::

ሁለንተናዊ የልጅ አስተዳደግ ሁሉንም የልጆች ዕድገት ገፅታዎች (አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ስሜታዊ፣ ማህበራዊ፣ ፋይናንሺያል እና መንፈሳዊ) በመንከባከብ እና በማሳደግ ላይ ያተኩራል።

ወላጅነት በእርግጥም የማጠናቀቂያ መስመር የሌለው የማራቶን ውድድር ነው። ለልጆቻችን ሁለንተናዊ እድገት የእድሜ ልክ ቁርጠኝነት እና ቀጣይነት ያለው ትጋትን፣ ጽናትን እና የማያቋርጥ ትምህርትን የሚጠይቅ ጉዞ ነው። የወላጅነት ማራቶንን ለማሸነፍ ቀጣይነት ያለው ራስን መረዳት፣ መላመድ እና በግል ሰብዕና ዕድገት ላይ የመስራት ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። ወላጆች እንደመሆናችን መጠን ልጆቻችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ እንዲዳብሩ ለማገዝ  ያለማቋረጥ መማር አለብን። ይህ ውጣ ውረድ የተሞላበት ፈታኝ ጉዞ ነው፣ ነገር ግን ጥረቱ በልጆቻችን ስኬት የማያጠራጥር ዋጋ ይከፍለናል።

እናም ኦሲስ የሥልጠና እና የማማከር አገልግሎት በዚህ ማራቶን ለማሸነፍ እንዲረዳዎት  ፓረንቶን (የወላጅነት ማራቶን) የሚል ስያሜ የተሰጠው የወላጅነት ሴሚናር አዘጋጅቷል። በዚህ ተከታታይ የወላጅነት ሴሚናር ወላጆች ይህንን የወላጅነት ማራቶን ለአሸናፊነት መሮጥ የሚችሉባቸውን በስነ ምግባር የታነፁ፣ ታታሪ፣ ችሎታ ያላቸው እና ደስተኛ ልጆችን ማሳደግ ዋና ግብ ያደረጉ የወላጅነት መንገዶችን እንቃኛለን። ስለዚህ የሩጫ ጫማዎን ይሰሩ፣ አይንዎን በዚሁ አድማስ ላይ ያድርጉ እና በቁርጠኝነት እና በፍቅር ወደዚህ የወላጅነት ማራቶን ይሳፈሩ።

ቅዳሜ ኅዳር 15፣ 2016 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 በኢትዬጲያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር አዳራሽ እንገናኝ!!
በ 0946444445 ይደውሉ።
2016 ኅዳር 12 ለሚከበረው ለታላቁ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ክብረ በዓሉን ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ጋር ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደ ሚከተለው ተዘጋጅቷል በፍጥረት #Share_Share ያድርጉ

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

✥ነግሥ / ለጒርዔክሙ /

ሰላም ለጒርዔክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ ፤ ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ ፤ እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤
ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ሥጋየ ጌሠ ፤
ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ዚቅ፦

አመ ይፈጥራ እግዚአብሔር ለምድር ፨ ኢዜነዎ ለሰማይ ፨ ወኢተማከረ ምስለ መላእክቲሁ፨ወተከለ ፫ተ ዕፀ ሕይወት በዲበ ምድር ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.


✥ነግሥ / ጎሥዓ ልብየ /

ጎሥዓ ልብየ ጥበበ ወልቡና፤ ለውዳሴከ ጥዑመ ዜና፤ ቅዱስ ሚካኤል ልማድከ ግብረ ትኅትና፤ አንተኑ ዘመራኅኮሙ ፍና፤ ወአንተኑ ለእስራኤል ዘአውረድከ መና ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ወረብ፦

አንተኑ ሚካኤል መና መና ዘአውረድከ፤
ወአንተኑ ለእስራኤል መና ዘአውረድከ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ዚቅ፦

አዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ፨ ፀዓዳ ከመ በረድ፨ ወርእየቱ ከመ ተቅዳ፨ ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ፨ አውኃዘ ሎሙ ማየ ህይወት፨ ዘትረ ኮኲሕ ፈልፈለ ነቅዕ ዘኢይነጽፍ፨ ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ ነግሥ / ዘመንክር ጣዕሙ /

ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ዚቅ፦

ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን፨ አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና ፨ እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት እኅቶሙ ለመላእክት ፨ አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ ለዝክረ ስምከ / መልክአ ሚካኤል /

ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ፤ ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ፤
ሶበ እጼውዕ ስመከ ከሢትየ አፈ፤
ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ፤ ለረዲኦትየ ነዓ ሰፊሐከ ክንፈ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ወረብ፦

ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል ረዳኤ ምንዱባን፤
በከመ ከመ ታለምድ ዘልፈ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ዚቅ፦

ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል፨ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ፨ ይስአል ለነ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፨ ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ወረብ፦

ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤
ይስአል ለነ አመ ምንዳቤነ ይስአል ሰፊሆ ክነፊሁ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ ለልሳንከ / መልክአ ሚካኤል /

ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተሀበለ፤
በእንተ ሥጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበሀለ፤ ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ፤ ቀዊምየ ቅድመ ሥዕልከ ሶበ አወትር ስኢለ፤
በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ወረብ፦

ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስኢለ፤
በብሂለ ኦሆ በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ዚቅ፦

ረሰዮ እግዚኡ ለውእቱ ሚካኤል ፨ እምኲሎሙ መላእክት ይትለዓል መንበሩ ፨ ስዩም በኀበ እግዚኡ ምእመን።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ወረብ፦

እግዚኡ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል፤
እምኲሎሙ መላእክት መላእክት ይትለዓል መንበሩ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ ለኅንብርትከ / መልክአ ሚካኤል /

ሰላም ለኅንብርትከ ኅንብርተ መንፈስ ረቂቅ፤ ዘቱሣሔሁ መብረቅ፤
ነግሀ ነግህ አንተ በአዝንሞ መና ምውቅ፤
በገዳም ዘሴሰይኮሙ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ፤
ሴስየኒ ሚካኤል ሕገከ በጽድቅ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.


✥ወረብ፦

በገዳም በገዳም በገዳም ዘሴሰይኮሙ፤
ለነገደ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ዚቅ፦

ባሕረ ግርምተ ገብረ ዓረፍተ ፨ ወበውስቴታ አርዓየ ፍኖተ፤፨ በእደ መልአኩ አቀቦሙ በገዳም ለሕዝቡ አርብዓ ዓመተ፨ ወሴሰዮሙ መና ሕብስተ ፨ ኪነ ጥበቡ ዘአልቦ መሥፈርተ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ወረብ፦

ባሕረ ግርምተ ዓረፍተ ገብር አርአየ ፍኖተ እግዚአብሔር
በእደ መልአኩ አቀቦሙ ለእስራኤል አርብዓ ዓመተ ለሕዝቡ በገዳም/፪/
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ አምኃ ሰላም / መልክአ ሚካኤል /

አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤
ለለ፩ዱ ፩ዱ ዘበበክፍሉ፤
ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤
ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤
ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ዚቅ፦

ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ፨ወስእለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ፨ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ወረብ፦

ተወከፍ ጸሎተነ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ፤
ወስእለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ ሊቀ መላእክት።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ አንገርጋሪ

ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል፤ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ ይስአል ለነ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ እስመ ለዓለም

ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ አስተምህር ለነ ሰአልናከ በ፲ ወ፬ ትንብልናከ፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ መኑ ከማከ ክቡር።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ አቡን በ፮ሃሌታ

ዝስኩሰ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ይስአል ለክሙ ኀበ ንጉሠ ስብሐት ስዮም በኀበ እግዚኡ ምእመን ፨ ረሰዮ እግዚኡ ለውእቱ ሚካኤል እምኲሎሙ መላእክት ይትለዓል መንበሩ፨ ስዮም በኀበ እግዚኡ ምእመን፨ በጽሑ መላእክት ወቦሙ መዘምራን ማእከለ ደናግል ዘባጥያተ ከበሮ ስዮም በኀበ እግዚኡ ምእመን።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ ዓራ

ሐመልማለ ወርቅ ልብሱ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቅ ሐመልማለ ወርቅ ክነፊሁ ዘእሳት አድኅን እግዚኦ ዛተ ሀገረ ወካልዓተኒ አህጉረ በሐውርተ በኃይለ መላእክቲከ እለ እምዓለም አሥመሩከ ረዳእየ አንሰ ኪያከ ተወከልኩ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ ቅንዋት

ሚካኤል ብሂል ዕፁብ ነገር መልአከ ኪዳኑ ለእግዚአብሔር ገብርኤል ብሂል ወልደ እግዚአብሔር ወዲበ ርእሱኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

✥ሰላም

መልአከ ሰላምነ ሉቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ።
👉hottg.com/mezgebehaymanot👈.

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት"   hottg.com/mezgebehaymanot 👈
 
በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇...  ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉hottg.com/mezgebehaymanot👈. ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

[email protected]


ወስብሐት ወለመስቀሉ
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
ለምንድን ነው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ወር በገባ በ12 የሚከበረው የሚታሰበው ? ህዳር 12 ቅዱስ ሚካኤል ያደረጋቸው ተአምራት በዝርዝር ከስር ያንብቡ👇👇

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)


እንኳን ለታላቁ፣  ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ
እንኳን አደረሳችሁ ፣ለታላቁ ሩህሩሁ መልአክ  ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ

  ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ' ካ-ከመ' ኤል- አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡
😘 @mezgebehaymanot 😍

      ስለዚህ ስለ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፤ ጠባቂነትና አማላጅነት ከአባቶቻቸው የተማሩትን በኑሮአቸው ያዩትን አባቶቻችን ጽፈዋል፡፡ ስለ ቅዱስ ሚካኤል ከጻፉት አባቶች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል፡-
+ ዮሐንስ አፈወርቅ
+ ኤዎስጣቴዎስ ዘአንፆኪያ
+ ቅዱስ መቃርዮስ
+ ቅዱስ ያሬድ
+ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
+ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባዲማቴዎስ ናቸው፡፡
😘 @mezgebehaymanot 😍

እኛም የአባቶቻችንን አንደበት አንደበታችን አድርገን በኅዳር 12 ክቡር ገናና የሆነ ቅዱስ ሚካኤል ካደረጋቸውና ከሠራቸው ብዙ ተአምራት ውስጥ የተወሰኑትን በመልአኩ ተረዳኢነት እንዲህ ብለን እንናገራለን አንጽፋለን፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ለምን ወር በ12 ይከበራል ? መልሱን ከስር👇👇👇

    በእስክንድርያ ሀገር ውስጥ ‹‹ሳተርን›› (ዙሐል) የተባለ ቤተ ጣዖት ነበራቸው። ይህን የንግስት ክሌዎፓትራ በእስክንድርያ(በግብፅ ) ‹‹ሳተርን›› (ዙሐል) ለሚባለው ጣዖት ቤተ ጣዖት ያሰራችለት እርሷ እንደሆነቸ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ ፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እስክንድርያው ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312 - 326/ ዘመን ድረስ ነበር፡፡ እለ እስክንድሮስ ሊያጠፋው ሲነሣ ሕዝቡ ከልቡ ገና የአምልኮ ጣዖት ስላልጣፋ 18 ፓትርያርኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት፡፡ እለ እስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት በነበረው በ12 ነው።  እስክንድሮስም ስአስተምሮ የሳተርን አጠፋው ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ሕዝብ በ12 በገባ ሳተርን›› (ዙሐል) እናከብር ነበር አንተ እርሱን አጠፋህብን ሰለዚህ የለመድ ነው እንዳይቀር አንድ ነገር አድርግልን አሉት እስክንድሮስም በ12 የቅዱስ ሚካኤልን በዓል እንዲያከብሩ አውጆ ቤተ ጣዖቱንም በቅዱስ ሚካኤል ስም ሰይሞ ቤተክርስቲያን አደረገው፡፡ ከዚህ በኋላ በቅዱስ ሚካኤልም ስም አብያተ ክርስቲያናት መታነጽ ጀመሩ  በዓሉ በዚህ ቀን እንዲከበር ተወስኗል፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ይህ ወደ እኛ የመጣው እስክንድሮስ ካረፈ በኋላ ቅዱስ አትናቴዎስ በተሾመ ጊዜ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ) ከኢትዮጵያ ሀገር ተልከው በእስክንድርያ ሀገር ጵጵስና ይዘው ሲመጡ ቅዱስ አትናቴዎስ ወር በገባ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል እንዲያከብሩ አስተምሯቸው አንድ ሕዝብ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን በአል ሲያከብሩ እግዚአብሔር ሲያመሰግኑ ተመልክተው ይህ ወደ ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው መተዋል አባቶቻችንም ወር በገባ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል እንዲ ዘከር እንዲከበር እንዲ ቀደስ በፍትሐ ነገስ ሥርዓት ሰርተውልናል።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ህዳር 12 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምን ምን ያደረገበት እንደሆነ እንመለከታለን።

ህዳር 12 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ምን ምን ያደረገበት እንየሆነ እንመለከታለን

1 .ቅዱስ ዱራታዎስ ቴዋብለት(ቴውብስታ) ቤት የተገለጠበት ቤታቸውን የባረከበት ዕለት ነው።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

      እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዋብለት ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያረጉ ነበር፡፡ ከዚህምወ በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ በዚህም የተነሳ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን አጡ፡፡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስን ወደ በጎች እንዲሔድና በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ አዘዘው፤ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሔዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ አዘዘው፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

መልአኩም ወደ ቤት ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አስጠነቀቀው፡፡ ወደ ባለ ስንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በእርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

      ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ፤ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደው አደረገ፡፡ የተራቡ ድሆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

      ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው ዱራታዎስንም የዓሳውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፤ በሰነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሳው ሆድ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዋብስታን እንዲህ አላቸው፡፡ ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሳውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ፤ እግዚአብሔር አስባችኋልና በጎ ሥራችሁን መስዋዕታችሁን ምጽዋዕታችሁን በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

በኋላኛውም መንግስት ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል፡፡›› ብሎ ባርኳቸው ከእንርሱ ተሰወረ።

2.የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በባህር ሲጓዙ የተጨረቁት የተራዳበት ዕለት ነው።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

በአንድ ዘመን ብዙ ሰዎች ከግብፅ አውራጃ መጥተው ወደ ባሕር ማዶ ሄዱ፡፡ ከባሕሩም በደረሱ ጊዜ በመርከብ ላይ ተሳፍረው ከየብሱ ጥቂት በራቁና ወደ ባሕሩ መካከል በደረሱ ጊዜ ጽኑ ነፋስ ተነሳባቸው ለመስጠም እስኪ ደርሱ ድረስ፡፡

👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈
የማዕበሉ ሞገድ እየጨመረ እየጸና ከፍ አለ፡፡ ታላቅም ማዕበል መጥቶ ሊገለብጣቸው ደረሰ፡፡ ፍጹም ጥፋትና ክፉ ሞት እንደ መጣባቸው ባዩ ጊዜ ጽኑ ሐዘን ያዛቸው፡፡ የሚያድናቸው የሚያጽናናቸው አጥተው ተስፋ ቆረጡ፡፡ ያን ጊዜ እንዲህ ብለው ጮኹ፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈
‹‹የመላእክት አለቃቸው ግሩም ገናና የምትሆን ሚካኤል ሆይ የተአምራትና የይቅርታ መልአክ ነህና፡፡ ልዑል ቸርነቱን የሚገልጥብህ መልአክ ሆይ! እግዚአብሔር ፍቅሩን የሚያስታውቅብህ መልአክ ሆይ ወደኛ ተመልከት እርዳን፡፡ የተጨነቅን እኛን አድነን፡፡ ከመጣብን ሞትና ጥፋት እንድን ዘንድ ስለኛ ወደ ፈጣሪህ ወደ ፈጣሪያችን ወደ እግዚአብሔር ለምንልን፡፡ አሁን የሞት መጋረጃ ዓይናችንን ሸፍኖታልና፡፡ ፍጹም የጥፋት ጥላንም አይተናታልና›› ብለው በፍጹም ልቦናቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡

👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈
በመርከብ ውስጥ ያሉት ሁሉ ጽኑ ለቅሶ እያለቀሱ መራራ እንባ እያፈሰሱ ጮኹ፡፡
ከባሕር ጽኑ ማዕበል ከሞት ያድናቸው ዘንድ ያን ጊዜ በዚያች ሰዓት እግዚአብሔር የልቦናቸውን ሐዘንና ልመናቸውን ሰማቸው፡፡ ያን ጊዜም ይገዳቸው ዘንድ ቸር መልአኩን ሚካኤልን ላከላቸው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወረደ መርከቡን በእጁ ይዞ ሳበው፡፡

👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈
በመርከቡ ውስጥ ያሉትንም ወደ የብስ አወጣቸው፡፡ በደኅናቸው ተሻገሩ፤ ክፉ ነገር ጥቂትስ ስንኳ ፈጽሞ አላገኛቸውም፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ገናና የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ልመናውና አማላጅነቱ ፈጽሞ ይጠብቀን፡፡ ከጽኑ ጠላት እጅ በክንፎቹ ጋርዶ ይሰውረን፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

3. በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል
ህዳር ፲፪ በዚህ እለት መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመበት እለት ነው፡፡

👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈
መጽሐፍ ቅዱስ  እንዲህ ይላል
ኢያሱ ወልደ ነዌ ሕዝቡን እየመራ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዐይኑን አንሥቶ ቢመለከት እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወደ እርሱም ቀርቦ «ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን?» አለው። እርሱም «እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወደ አንተ መጥቻለሁ» ብሎታል። ኢያ ፭፥፲፫-፲፭። ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስ ይሁዳ «የመላእክት አለቃ ሚካኤል» በማለት መስክሮለታል ይሁዳ ፩፥፱።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በደሴተ ፍጥሞ በግዞት ሳለ በተመለከተው ራእይ ሃላፊያትና መጻእያት ተገልጠውለት ስለነበረ «በሰማይም ሰልፍ (ጦርነት) ሆነ፤» ካለ በኋላ «ሚካኤልና መላእክቱም ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም ከነሠራዊቱ ተዋጋቸው። አልቻላቸውምም ከዚያም በኋላ በሰማይ ቦታ አልተገኘላቸውም። ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያቢሎስና ሰይጣን የሚባለው
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ ወደ ምድርም ተጣለ መላእክቱም (የዘንዶው ሠራዊት) ከእርሱ ጋር ተጣሉ፤» ብሏል። ራእ ፲፪፥፯-፱።ዳን ፲ ፡፲፫ " ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ" የመላእክት አለቃ መሆኑን መስክሯል በሌላ በኩል ዳንኤል እንዲህ ይላል ፡፡ ዳንኤል፦ «በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው (በአማላጅነት በተራዳኢነት የሚቆመው) ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል ሕዝብም በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤» ብሏል።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዳን ፲፪፥፩።ዩሐንስ በራእዩ ያየው " ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መላእክ ሲወርድ አየሁ ከክብሩም የተንሳ ምድር በራች ራይ ፩ : ፲፰  ብሎ የመላእኩን ክብረ ተናግሯል የመላእክት አለቃ መሆኑን መስክሯል ፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

4.እስራኤልን ከግብፅ እየመራ ወደ ሀገራቸው ያስገባበት ዕለት የሚታሰብበት እለት ነው
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጡትን ሕዝብ እግዚአብሔር ቀኑን በደመና ዓምድ ሌሊቱን ደግሞ በብርሃን ዓምድ መርቷቸዋል እስራኤል ዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው መና ከሰማይ ያወረደላቸው ተአምራትን ያደረገላቸው ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ርስታቸው የመራቸው  በደመና መጋረጃ የጋረዳቸውበክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይ የተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው። መላእኩ በዚሁ እለት የሰራውን ድንቅ ስራ እንመሰክራለን
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

★ ኅዳር አሥራ ሁለት ቀን በየዓመቱ በማኅሌት እና በቅዳሴ የምናከብረው  በዓለ ሹመቱን በማሰብ ቴዎብስታ ዱራታዎስ ያደረገው ታምረ እና በባህር የተጨነቁትን ያዳነበት በማሰብ  ነው።ሌላው እና ዋንኛው  የምናከብረው ይህ ለእስራኤል ዘሥጋ የተደረገውን የበለጠው ደግሞ እስራኤል ዘነፍስ ለምንባል ክርስቲያኖች ይደረግልናል። በዓሉን በታላቅ  ድምቀት ይከበራል ።

❤️መልካም ክብረ በዓል ❤️

❤️ ሰለ ማይንገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን❤️

አዘጋጅ በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አዲስ አበባ ጣፎ 2008 የተጻፈ ደጋሚ ተለጠፈ

╔​✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_ጾም_ይሁንልን
╚✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ  አንብቡት🙏🙏🙏

በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
 
በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇...  ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

hottg.com/mezgebehaymanot ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ኦ ሚካኤል
ዝማሬ ዳዊት
#ኦ_ሚካኤል

ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል/2/
ስንጠራህ ድረስልን ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል

ዘንዶው ጠላታችን ከፊታችን ቆሟል
ከባህር ሊጥለን አድፍጦ ያደባል
የመላዕክት አለቃ እርዳን በፀሎትህ
ጥበቃህ አይራቀን በቀን በሌሊት/2/

ክርስትና ኑሮ እጅጉን ከብዶናል
የጌታን ውለታ ፍቅሩን ዘንግተናል
አፅናኙ መልዐክ ከፊታችን ቅደም
በመንገድህ ምራን እንድንሆን ሰላም/2/

የጌታ ባለሟል የህዝብ እረኛ
ባህሩን አሻግረን ቅረበን ወደ እኛ
ከጌታህ አማልደን መልዐከ ራማ
የልጆችህን ቃል ድምፃችንን ስማ

በሚያስፈራው ዘመን ሰላም በሌለበት
ባስጨናቂው ጊዜ ፍቅር በጠፋበት
የፍቅርን ወንጌል ቃሉንም ስበከን
ሚካኤል ተራዳን ድረስም አፅናናን

ዘ/ዲ ሱራፌል ስዩም
╔​✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል_ይሁንልን
╚✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ  አንብቡት🙏🙏🙏


በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
╔​✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል_ይሁንልን
╚✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ  አንብቡት🙏🙏🙏


በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
Forwarded from መዝገበ ሃይማኖት (Belete Kebede)
#ፈተና_ቢገጥማት

ፈተና ቢገጥማት /2/ ቅድስት አፎሚያን
ሚካኤል /2/ ብላ ስትጣራ /2/

ፈጥኖ አዳናት ከጭንቅ ከመከራ /2/
ነውና እምነቷ /2/ ጽኑ በምግባሯ /2/
ሚካኤል መጣላት /2/ ተአምሩን ሊሰራ
ሚካኤል መጣላት /2/ ለአፎምያ ተአምሩን ሊሰራ

ፍጡነ ረድኤት /2/ መጣላት ገስግሶ /2/
እንደ ኃያልነቱ ኃይሉን አፈራርሶ /2/
በመጣበት አስሄደው መልሶ

በእምነት ስንጠራው/2/ ጸንተን በሃይማኖት /2/
ቶሎ ይደርስልናል ፍጡነ ረድኤት /2/
ሚካኤል ሊቀ መላእክት

ታላቁ ሚካኤል/2/ ተራዲኢው መልአክ
ምሕረት እንዲሰጠን ለምንልን ከአምላክ/2/
ሚካኤል ፀሎታችንን ባርክ
መዝሙረ ማኅሌት
hottg.com/mezgebehaymanot

አዘጋጅ በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል _❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
ናና ሚካኤል ናና
ዝማሬ ዳዊት
#ናና_ሚካኤል_ናና

ናና ሚካኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ሚካኤል ናና

የረዳህ አፎምያን ሚካኤል ናና
ሰይጣን ሲፈትናት ሚካኤል ናና
አንተነህ ያዳንከው ሚካኤል ናና
ባሕራንን ከሞት ሚካኤል ናና
ለእነርሱ እንደመጣህ ሚካኤል ናና
እኔንም ተራዳኝ ሚካኤል ናና
ሚካኤል ደግፈህ ሚካኤል ናና
ለመንግሥቱ አብቃኝ ሚካኤል ናና
ናና ሚካኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና

አዝ-------------

ናና ገብርኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ገብርኤል ናና

ዘመኑ ሲፈፀም ገብርኤል ናና
አምላክ መምጫው ሲደርስ ገብርኤል ናና
ገብርኤል አንተ ነህ ገብርኤል ናና
ያልካት ደስ ይበልሽ ገብርኤል ናና
ድምጽህን አሰማኝ ገብርኤል ናና
ነፍሴ ጽድቅን ትልበስ ገብርኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ገብርኤል ናና

አዝ-------------

ናና ዑራኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ዑራኤል ናና

ቆመህ ጽዋ ይዘህ ዑራኤል ናና
ለእዝራ ሱቱኤል ዑራኤል ናና
ጥበብ አጠጥተህ ዑራኤል ናና
ዕውቀት ስታድል ዑራኤል ናና
ተገለጠ ክብርህ ዑራኤል ናና
መልአኩ ዑራኤል ዑራኤል ናና
ድኜ በፀበልህ ዑራኤል ናና
በአውደ ምህረትህ ላይ ዑራኤል ናና
እኔም ዘመርኩልህ ዑራኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ዑራኤል ናና

አዘጋጅ በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል _❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
"ኦ ቅዱስ ሚካኤል"
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ኦ_ቅዱስ_ሚካኤል

ሚካኤል በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል
ለተጨነቀች ነፍስ ምህረት ይለምናል
ጨለማው እንዲሸሽ እንዲሆን ብርሃን
ኦ ቅዱስ ሚካኤል ሰዓለነ እንበል (2)

እረቂቁ መላዕክ መብረቅ ተጎናጽፏል
ለሰማይ ሰራዊት አለቃቸው ሆኗል
የምክሩ አበጋዝ ስሙ የተፈራ
እሱ ነው ሚካኤል ለሕዝቡ የሚራራ (2)
#አዝ
እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልፅበት
ፀሎት የሚያሳርግ የሚያሰጥ ምህረት
ስለ ትህትናው ከአምላክ የተሾመው
ቅሩበ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤል ነው (2)
#አዝ
እርህሩ ነው እና የነፍሳችን ወዳጅ
ለፍጥረቱ ሁሉ የታመነ አማላጅ
ከቅጥረ ፀሎቱ ነፍሳችን ትጠጋ
ተግቶ እንዲጠብቀን ሲመሽም ሲነጋ (2)
#አዝ
የነፀብራቅ ዝናር ሚካኤል ታጠቀ
በቅድመ እግዚአብሔር ሕዝቡን አስታረቀ
በእሳታዊው አክናፍ ከክፉ ጋረደ
ልጆቹን ሊባርክ ሚካኤል ወረደ (2)

ዘማሪ ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

አዘጋጅ በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል _❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
Forwarded from መዝገበ ሃይማኖት (Belete Kebede)
#ሊቀ_መላእክት

ሊቀ መላእክት(፪)
ሚካኤል(፪) ሐመልማለ ወርቅ(፪)

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
hottg.com/mezgebehaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

አዘጋጅ በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል _❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
✞ውእቱ ሚካኤል✞
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
#ውእቱ_ሚካኤል

ውእቱ ሚካኤል ውእቱ መልአከ ኃይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር
ይስሀል ለነ ይስሀል ለኢትዮጵያ ረዳኤ ይኩና አመ ምንዳቤ
#ትርጉም
መቀመጫው ከፍ ያለ ኃያል መልአክ
ሚካኤል በችግራችን ጊዜ ይለምንልን ረዳት ይሁነን(ለኢትዮጵያ ረዳት ይሁነን ይለምንልን)

hottg.com/mezgebehaymanot

አዘጋጅ በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል _❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
Forwarded from መዝገበ ሃይማኖት (Belete Kebede)
#ሚካኤል_አማልደን

ሚካኤል አማልደን ከአምላካችን
እንዳንጠፋ እንዳንሞት በነፍሳችን አደራህን ቁምልን ከፊታችን

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
hottg.com/mezgebehaymanot
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

አዘጋጅ በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አላቲኖስ

╔​✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል _❀
╚✞═┉✽🌹🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
#ጾመ_ነቢያት_የሚጀመረው_መቼ_ነው?በፍጥነት Share Share አድርጉ

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

#ሙሉውን_እንድታነቡት_በታላቅ_ትሕትና_እጠይቃለሁ_በፍጥነት_Share_Share_አድርጉ

✥የተከበራችሁ ክርስቲያኖች ፆመ ነቢያት መቼ ነው የሚጀምረው የሚል ጥያቄ እያነሣችሁ መሆኑ ይታወቃል። ብዙኃን መገናኛ በሆኑት ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ውዝግብ ሲነሳም ተመልክቻለሁ እስቲ መጽሐፍትን መሰረት አደረገን የአባቶቻችን የቅዱስ ሲኖዳስን ወሳኔ ምን እንደሚመስል እንመልከት ብዬ ይህቺን አጭር ጹሁፍ አዘጋጀሁ ወደ ሐሳባችንእስቲ እንዝለቅ ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

✥ የክርስቲያኖች ለፆም መቅናት ከአምላካችን ከእግዚአብሔር በረከት እንደሚያስገኝ ጥርጥር የለውም። ከዓመታት በፊት አንድ ጊዜ ኅዳር 14፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ኅዳር 15 ይጀመር ስለነበር ምእመናን ይወዛገቡ እንደነበር የሚታወቅ ነው።"" ጾመ ነቢያት በዘመነ ዮሐንስ የሚገባው ኅዳር 14 ነው፡፡ በ15
የሚገባው ለ3ቱ ዓመታት (በቅዱሳን ማቴዎስ፡ ማርቆስና ሉቃስ አዝማናት) ነው፡፡
ጾመ ነቢያት 44 ቀናትን ይይዛል፡፡
✥40 (ጾመ ነቢያት)
✥3ቱ (ጾመ ፊልጶስ ወአብርሃም ሶርያዊ . . .)
✥1ዷ (ገሃድ - ተውላጠ ልደት) ናት፡፡
✥ጾሙን ኅዳር 15 ስንጀምር ታኅሣሥ 29 እንፈታለን፡፡ በ14 ስንጀምር በ28 እንፈታለን። ቅዱስ ሲኖዶስ ምእመናን እንዳይወዛገቡ በማለት በ1980 ዓ.ም በረከታቸው ይደርብንና ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በጥቅምት ሲኖዶስ ላይ በአራቱም ዘመናት በ 15 እንዲጀምር አስወስነዋል፡፡ ስለዚህ እኛም የምንቀበለው አባቶቻችን በሲኖዶስ የወሰኑትን ነው።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

✥ጾሙ ኅዳር 15 እንዲጀመር ወስኗል። ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው መከበር ስለአለበት ኅዳር 15 ማለትም ሰኞ ጀምረን ብንፆም መልካም ነው። አድሉ ለፆም ነውና ከ14 ጀምረን እንፁም የሚሉ ወገኖ ካሉ ለጾም ማድላት ተገቢ ነው ነገር ግን እነርሱ በ14 ስለጀመሩ የአባቶችን የሰሩትን ቀኖናዊ ሥርዓት ተከትሎ የሚጾመውን መንቀፍ ተገቢ አይደለም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ሮሜ. ፲፬፥፫ "ወዘኒ ይበልእ ኢይመንኖ ለዘኢይበልእ ወዘኒ ኢይበልእ ኢይግዐዞ ለዘይበልእ እስመ ለኩሎሙ እግዚአብሔር አእመሮሙ"

[የሚበላ የማይበላውን "አይናቀው" የማይበላው በሚበላው "አይፍረድ" ከተባለና ሁለቱንም እግዚአብሔር እንደ እምነታቸው ከተቀበለ እኔ ምን ቤት ነኝ የሌላውን የምነቅፈው!

✥በ 14 የሚል ቢኖሩ እኛ መግለጥ የፈለግነው የዐዋጁን እና የቤተ ክርስቲያኗ የበላይ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውን ነው።

✥ስለዚህ በ14 ቅበላ ወይም ጾሙ የሚገባበት ዋዜማ እንጂ ጾሙ የሚገባበት አይደለም፡፡ ጾሙ ሕዳር 15 ቀን በእለተ ማግሰኞ ይገባል፡፡

✥በጾሙ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ስለ ምዕመናን ለእመቤታችን የአሥራት ሀገሯ እኛም የቃል-ኪዳን ልጆችዋ ስለሆንን ንጽሕት እመቤታችን እንድ ትለመነን ይህንን ታላቅ ጾም በጸሎት በስግድት ልናሳልፈውና ለሀገራችን ለቅድስት ቤተ ክርስትያናችን ለሕዝባችን ለሀገራችን ምሕረት እንዲወርድ የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባናል፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

✥ይህ ታላቅ ጾም ነብያት ጌታ ሥጋ ማርያምን ለብሶ ዓለምን ለማዳን እንደሚመጣ በጾም ሲጠባበቁበት የነበረው ጾም ነው፡፡ የነብያት ትንቢቱ ከፍጻሜ ደርሶ ጾማቸው ተሰምቶ የጌታም መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት በመሆኑ ነው ጾመ ነብያት የተባለው፡፡ ጾሙን ነብያት ስለጾሙት ብቻ ሳይሆን በጾሙ ስለተጠቀሙበትም ነው የምንጾመው፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

✥ሌላ የዚህ ጾም መጠሪያ ጌታችን ለአዳም የተናገረው የድህነት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ጾመ አዳም ይባላል፡፡ ሌላው ስለ እግዚአብሔር ወልድ ሰው መሆን በስፋት የሚሰበክበት ስለሆነም ጾመ ስብከት ወይም የስብከት ጾም ይባላል፡፡ ብዙዎቻችን የማናውቀው ይህ ጾም ጾመ ማርያም ይባላል፡፡ ይህም የሆነው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ባበሰራት ጌዜ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ጸንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ›› ብላ በትህትና ጾማዋለች፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

❖ ይህ ጾም በተመለከተ በ1980 ዓ.ም በረከታቸው ይደርብንና ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በጥቅምት ሲኖዶስ ላይ በአራቱም ዘመናት በ 15 እንዲጀምር አስወስነዋል

✥ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፊሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ በምዕራፍ 2÷20 ላይ ‹‹በሐዋርያትና በነብያት መሠረት ላይ ታንጻችኃል›› ብሎናል፡፡ ስለዚህ የሐዋርያት እና የነብያት መሠረት ምንድን ነው? ካልን መሠረታቸው ጾም ጸሎት ነው፡፡ ስለዚህ ሐዋርያት እና ነብያት አባቶቻችን የጾሙትን ጾም እኛም እንጾማለን፡፡
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

✥ አብዝቶ መፆም በረከት እንደሚያስገኝ ቢታወቅም በቅንነት መታዘዝም በረከት ያስገኛል። እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያኗ ቴሌቭዥን የሚያስተላልፈው መልእክት ካለም ሰምተን መተግበር ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው።ስለሆነም ጾሙ መጀመሪያ ኅዳር 15 መሆኑን ነው።
#መልእክቱን_ለሁሉም_ሕዝበ_ክርስቲያን_አዳርሱ

╔​✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_ጾም_ይሁንልን
╚✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
 
በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇...  ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

hottg.com/mezgebehaymanot ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❖የነቢያትን ጾም የተቀበልክ ቅዱስ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ 🙏

✥ጦርነት ተወግዶ ሰላም ሰፍኖ መርዶውን በብሥራት ፣ሃዘኑን በደስታ ፣ጥላቻውን በፍቅር፣ ስድብን በምስጋና ፣ የትዕቢት መንፈስን በትሕትና ፣ ቂሙን በይቅርታ የሰቆቃ የጦርነት ዜና ጠፍቶ በሰው ልጅ ላይ ፍቅር አብቦ በሀገራችንና በዓለማችን ላይ አምላካችን መድኃኔዓለም ደስ በሚሰኝ ሁኔታ ተዘጋጅተን ጾሙን ፈጽመን። እርሱ ባለቤቱ እንደ ቸርነቱ ጾማችን ተቀብሎ ተምኒተ ሕሊናችን ተሳክቶ ሰላሙን የድንግል ማርያም ልጅ ያስፍንልን🙏🙏

╔​✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_ጾም_ይሁንልን
╚✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot

ጸሎቴ ምኞቴ ነው 🙏 በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)
የኅዳር ጽዮን ክብረ በዓል ከሊቃውንቱ ጋር አብረን በወረብ ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ወረቡ ዚቁ ነግሥ መልኩ ተዘጋጅቷል #Share_ሼር_ይደረግ

አዘጋጅ በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)

ሥርዓተ ማኅሌት ዘኅዳር ጽዮን "ኅዳር ፳፩"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ፤ ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት፤ እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዚቅ
ዘዘካርያስ ተቅዋም ዘወርቅ፤ ዘሕዝቅኤል ነቢይ ዕፁት ምስራቅ፤ ለመሠረትኪ የኃቱ ዕንቊ፤ ሰአሊ ለነ ማርያም፤ በአሚን ንጽድቅ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ነግሥ
ነቢያተ ፳ኤል ጸሐፉ በመጽሐፎሙ እሙነ፤ ነገረ ሰቆቃው ወላህ በዘመኖሙ ዘኮነ፤ ለባቢሎን ውስተ አፍላጋ አመ በጼዋዌ ነበርነ፤ ውስተ ኲሃቲሃ ዕንዝራቲነ ሰቀልነ፤ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን እምነ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዚቅ
ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሀ ዚአነ፤ እንተ ረከበተነ በእንተ ጽዮን፤ ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን፤ ወሶበ ኢረሳዕናሃ ለኢየሩሳሌም።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወረብ
ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሀ ዚአነ እንተ ረከበተነ/፪/
ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ/፪/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

መልክአ ማርይም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዚቅ
እምነ ጽዮን በሀ፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ ሥርጉት በስብሐት፤ ዓረፋቲሃ ዘመረግድ፤ ሥርጉት በስብሐት፤ ወማኅፈዲሃኒ ዘቢረሌ፤ ሥርጉት በስብሐት፤ እምስነ ገድሎሙ ለሰማዕት፤ ሥርጉት በስብሐት፤ ታቦተ ሕጉ ለንጉሥ ዓቢይ፤ ሥርጉት በስብሐት፤ እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ፤ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
አንሶሱ ማዕከለ መርህብኪ፤ ይቤ ቅዱስ ፳ኤል፤ ተንሥኢ ተንሥኢ ጽዮን፤ ልበሲ ኃይለኪ፤ ጽዮንሃ ስመኪ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወረብ
እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ ፀሐየ ጽድቅ/፪/
ለሰማዕት "ሥርጉት በስብሐት"/፪/ /፪/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

መልክአ ማርያም
ሰላም ለአስናንኪ ሐሊበ ዕጎልት ዘተዛወጋ፤ ወመራዕየ ቅሩጻተ እለ እም ሕፃብ ዐርጋ፤ ማርያም ድንግል ለደብተራ ስምዕ ታቦተ ሕጋ፤ አፍቅርኒ እንበለ ንትጋ ለብእሴ ደም ወሥጋ፤ ዘየዐቢ እምዝ ኢየኀሥሥ ጸጋ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዚቅ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት ሕፅርት፤ ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት፤ ንጉሥኪ ጽዮን፤ ኢይትመዋዕ ለፀር ወኢየኃድጋ ለሀገር።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወረብ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት ሕፅርት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት/፪/
ንጉሥኪ ጽዮን ኢይትመዋዕ ለፀር ወኢየኃድጋ ለሀገር/፪/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

መልክአ ማርያም
ሰላም ለከርሥኪ ዘአፈድፈደ ተበጽዖ፤ እምታቦተ ሙሴ ነቢይ ለጽሌ ትእዛዝ ዘየኀብኦ፤ ማርያም ድንግል ጊዜ ጸዋዕኩኪ በአስተብቊዖ፤ ለፀርየ ብእሴ ዐመፃ ሃይለ ዚአኪ ይጽብኦ፤ እስከነ ያስቆቁ ጥቀ ድኅሪተ ገቢኦ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ በጾም ወበጸሎት ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ፤ ጽላተ አሥሮነ ቃላተ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ጽላት ዘሙሴ ዕፀ ጳጦስ ዘሲና፤ ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን ካህን።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት/፪/
ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ ጽላተ አሥሮነ ቃላተ/፪/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወረብ
ጽላት ዘሙሴ ዕፀ ጳጦስ ዘሲና ጽላት ዘሙሴ/፪/
ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን ካህን ካህን ለአሮን ካህን/፪/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

መልክአ ማርያም
ሰላም ለመከየድኪ እለ ረከቦን መከራ፤ እምፍርሃተ ቀተልት ሐራ እንበለ አሣእን አመ ሖራ፤ ማርያም ጽዮን ታቦተ ቃለ ጽድቅ መንፈቀ ዕሥራ፤ ዕጎላት እምጎሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ፤ አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እምይእዜ ለግሙራ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወረብ
ማርያም ጽዮን ታቦተ ታቦተ ፍሲለደስ ወኢያሱ ታቦተ ቃለ ጽድቅ/፪/
ዕጎላት እምጎሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ አፍቀራ እምጎሊሆን/፪/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዚቅ
ሃሌ ሉያ፤ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ፤ ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ፤ አእመርክዋ አፍቀርክዋ፤ ከመ እኅትየ ኀለይኩ፤ እምድኅረ ጒንዱይ መዋዕል፤ ወእምዝ እምድኅረ ኅዳጥ ዓመታት፤ ካዕበ ርኢክዋ፤ ወትትሐፀብ በፈለገ ጢሮስ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ታቦት ታቦት እንተ ውስቴታ ኦሪት፤ ውቱረ ይከድንዋ በወርቅ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወረብ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ/፪/
ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ አእመርክዋ አፍቀርክዋ ለቤተ ክርስቲያን/፪/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

መልክአ ማርያም
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ ለዘይስእለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ ብጽሒ ፍጡነ ትሠጠዊዮ ዘይቤ፤ ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤ ዘጸገየ ማኅፀንኪ አፈወ ነባቤ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ዚቅ
አብርሒ አብርሒ ጽዮን፤ ዕንቊ ዘጳዝዮን፤ ዘኃረየኪ ሰሎሞን።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወረብ
አብርሒ አብርሒ ጽዮን አብርሒ/፪/
ዕንቊ ዘጳዝዮን ዘኃረየኪ ሰሎሞን/፪/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ማኅሌተ ጽጌ
ዘካርያስ ርእየ ለወርኃ ሳባጥ በሠርቁ፤ ተአምርኪ ለዘይት ማዕከለ ፪ኤ አዕፁቁ፤ ማርያም ጽዮን ለብርሃን ተቅዋመ ወርቁ፤ ዕዝራኒ በገዳም አመ ወዓለ ውዱቁ፤ ለኅብረ ገጽኪ ጽጌ አተወ መብረቁ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈
ዚቅ
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ ፯ቱ መኃትዊሃ ወ፯ቱ መሣውር ዘዲቤሃ፤ ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ዘኲለንታሃ ወርቅ ወያከንት፤ ዕዝራኒ ርእያ በርዕየተ ብእሲት፤ ወሶበ ርእያ ኢኮነት ብእሲተ አላ ሀገር ቅድስት።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወረብ
ለቅድስት "ቤተ ክርስቲያን"/፪/ መኃትዊሃ ፯ቱ መኃትዊሃ/፪/
ዕዝራኒ ርእያ በርዕየት ብእሲት/፪/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

አንገርጋሪ
ዓይ ይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ፤ ከመ ማኅቶት ብርህት ከመ ፀሐይ፤ ሙሴኒ ርእያ፤ ሀገር ቅድስት፤ ዕዝራኒ ተናገራ ዳዊት ዘመራ።
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

አመላለስ
ዕዝራኒ ተናገራ/፪/
ተናገራ ዳዊት ዘመራ/፬/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

ወረብ
"ሙሴኒ ርእያ"/፪/ ሀገር ቅድስት/፪/
ዕዝራኒ ተናገራ ተናገራ ዘመራ ዳዊት/፪/
👉 hottg.com/mezgebehaymanot👈

እስመ ለዓለም
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ዘኲለንታሃ ወርቅ፤ በየማና ወበጸጋማ አዕፁቀ ዘይት፤ ደብተራ ፍጽምት ሀገር ቅድስት፤ ነቢያት ይትፌሥሑ በውስቴታ፤ ሐዋርያት ይትኃሠዩ በውስቴታ፤ ወዳዊት ይዜምር በውስተ ማኅፈዲሃ፤ ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ በቃለ ዳዊት ይሴብሑ፤ ወይብሉ ኲሎሙ ሃሌ ሉያ።

አዘጋጅ በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ) አዲስ አበባ ጣፎ 2008 የተጻፈ ደጋሚ ተለጠፈ

❖ ጸሎታችን ልመናችንን ማኅሌታችን ቁመታችን ተቀብሎ ለሀገራችን ሰላምና ለሕዝቦቿም ፍቅር ና አንድነትን የድንግል ማርያም ልጅ ይስጠን እመቤታችን የአስራት ሀገሯን በበረከቷ ትጎብኝልን🙏🙏🙏

╔​✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል_ይሁንልን
╚✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏

በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot

በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

hottg.com/mezgebehaymanot ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✥ በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ያለውን ምስጢራዊ ትርጉም ምንድን ነው? ከስር ያንብቡ👇👇👇

✥በቅዱሳት መጻሕፍት ጽዮን የሚለው ቃል ተደጋግሞ በነቢያቱ ተነግሯል፡፡ ሆኖም የጽዮን ትርጉም እንደተነገረበት ዐውደ ትንቢት እንደተሰበከበት መዋዕለ ትምህርት ምስጢሩ ይለያያል፡፡

✥በዚህ ጽሑፍ በጥቂቱ የምንመለከተው ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ እንዴት እንደመጣች፣ ኅዳር 21 ቀን ስለምናከብረው ዓመታዊ በዓል፣ በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በእመቤታችን በቅድስትድንግል ማርያም ያለውን ምስጢራዊ ትርጉም ነው፡፡

✥ታቦተ ጽዮን በፈቃደ እግዚአብሔር በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት ለሰው ልጆች ተሰጥታ እስራኤላውያን ሲባረኩባት፣ መሥዋዕታቸውን ሲያቀርቡባት ከእግዚአብሔር ሲታረቁባት ኖረዋል፡፡

✥በደብተራ ኦሪት ታቦተ ጽዮንን እንዲያገለግሉ የተሾሙት ሁለቱ ወጣት ካህናት 《አፍኒን እና ፊንሐስ》ፈቃደ እግዚአብሔርን ተላልፈው ሦስት ታላላቅ በደሎችን ፈጸሙ፡፡ የመጀመሪያው በደል፤ በሙሴ ሥርዓት በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት በርታ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት የምትጠፋ መብራት እንድትቀመጥ የተሠራ ሥርዓት ነበር፡፡ ሆኖም አገልግሎት ከሌለ ሲበራ ማደሩ ለምን ? ብለው መቅረዙን አነሡ፤ መብራቱንም አጠፉ፡፡

✥ሁለተኛ፣ ለራሳቸው ሥጋዊ ጥቅም ቅድሚያ ሰጥተው ለመሥዋዕት እንዲሆን ከመጣው እንስሳ ታርዶ ስቡ ሳይጤስ፣ደሙ ሳይፈስ ሥጋውን እየመረጡ ተመገቡ፡፡

✥ሦስተኛ ጸሎት እናደርሳለን ሥርዓተ አምልኮ፣ እንፈጽማለን ብለው ወደ መገናኛው ድንኳን ይመጡ ከነበሩት እስራኤላውያን ቆነጃጅት ጋራ በዝሙት ወደቁ፡፡

✥አባታቸው ካህኑ ዔሊም የልጆቹን በደል እያየ እንዳላየ እየሰማ እንዳልሰማ ቸል በማለቱ እግዚአብሔርአዘነ፡፡ በዚህም ምክንያት ፍልስጥኤማውያንን አስነሥቶ በጦርነት ቀጣቸው፡፡

✥ዕብራውያን በጦርነት ውሎ ያለልማዳቸው በአሕዛብ ተሸነፉ፡፡ ሕዝበ እስራኤልም ግራ ቢገባቸው «ድል የተነሣነው ታቦተ ጽዮንን ይዘን ባለመዝመታችን ነው» ብለው አፍኒን እና ፊንሐስ ጽላቱን እንዲሸከሙ አድርገው ወደ ፍልስጥኤማውያን የጦር ምሽግ ገሠገሡ፡፡

✥ሆኖም ያሰቡት ሳይሳካ ታቦተ ጽዮን ተማረከች፣ አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ፤ ዕብራውያንም በጦርነቱ ድል ተደረጉ፡፡ፍልስጥኤማውያንም ታቦተ ጽዮንን ማርከው ዳጎን ከተባለው ጣዖታቸው ላይ አስቀመጧት፡

✥በማግስቱ ሲመለሱ ዳጎን ተገልብጦ ታቦተ ጽዮን በላይ ተቀምጣ አገኟት፡፡ በማግስቱም ተመሳሳይ ድርጊት ተፈጽሞ ዳጎን ወድቆና ተሰባብሮ አገኙት፡፡ ለእስራኤላውያን ታቦተ ጽዮንን መለሷት

✟✟✟ በታቦተ ጽዮን እና በዘመነ ሐዲስ በተገለጠችው በእመቤታችን በቅድስትድንግል ማርያም ያለውን ምስጢራዊ ትርጉም ነው✟✟✟

1.እግዚአብሔር ለሙሴ ታቦትን እንዲሠራ ያዘዘው ‹ሸምሸር ሸጢን› ከሚባል ዕንጨት ነበር፡፡ ሸጢን ማለት የግራር ዓይነት ሲሆን የማይነቅዝ ዕንጨት  ነው - እንዲሁም እሾሃማ፡፡ ይህ ምሳሌ ነው ፤

1. የግራር ዕንጨት የማይነቅዝና የማይለወጥ መሆኑ ድንግል ማርያም እንዲሁም ጥንተ አብሶ የሌለባት መሆኗን ያመለክታል፡፡ ዕፅዋት ሁሉ የሚጠወልጉና የሚነቅዙ ሲሆኑ ዕፀ ሰጢን (የግራር ዕንጨት) ግን የማይለወጥና የማይነቅዝ ሆኖ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የሰው ልጆች ሁሉ በኃጢአት ሲያድፉ በንጽሕና ጸንታ ፣ በሃሳቧ እንኳን ሳትበድል የተገኘችው እመቤታችን ናት፡፡

2.ታቦቱ ከግራር ዕንጨት መሠራቱ እመቤታችን በኃጢአት አትለወጥም ከሚለው ነጥብ በተጨማሪ በምድር ላይ በኖረችባቸው ስድሳ አራት ዓመታት ውስጥ ብልየት (እርጅና) ሳያገኛት እንደኖረችም ያስታውሰናል፡፡ ‹‹ወበእንተዝ ዐቀበኪ እንበለ ሙስና›› /ስለዚህም ባለመለወጥ አጸናሽ/ እንዲል፡፡

3. የግራር ዕንጨት ዙሪያውን በእሾህ የታጠረ ነው ፤ እመቤታችንም እንደ ግራርና እንደ አበባ በእሾህ የታጠረች ናት ፡፡ እሾህ የተባሉት አይሁድ ፣ አጋንንት ናቸው፡፡ በሕይወት ዘመኗ ያሳደዷትና ፣ በተደጋጋሚ በመርዝ ሊገድሏት ፣ ጠንቋይ ቀጥረው በምትሐት ሊያጠፏት በሞከሩት በክፉዎች አይሁድ ተከብባ የኖረች እመቤታችን በግራር ዕንጨት በተሠራችው ታቦት ትመሰላለች፡፡ አባታችን ቅዱስ ያሬድ ‹‹በማእከለ አስዋክ ዘጸገየት ጽጌ ሃይማኖት ዘበአማን›› (በእሾሆች መካከል ያበበች የሃይማኖት አበባ) ሲላት አባ ጽጌ ድንግልም ‹‹በእሾህ አይሁድ መካከል ያበብሽ አበባ›› ብሏታል ፤ ‹‹ዘጸገይኪ ጽጌ በማእከለ አይሁድ አስዋክ›› እንዲል፡፡ (ቅዱስ ያሬድ ድጓ ዘዮሐንስ ፤ አባ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌ) ዛሬም ድረስ እመአምላክ እመቤታችንን በክህደታቸው እሾህ የከበበቧት ብዙዎች ናቸው፡፡
ታቦት ሥጋ ወደሙ ይፈተትበታል ማደሪያነቱ ለፅላትና መና ለያዘው መሶበ ወርቅ ነው፡፡

4.ታቦተ ጽዮንን ዳጎ ሰባብራ እንደተመለሰች እመቤታችንም  《1ሳሙ 5÷4》 ይኽን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጽጌ ድንግል ሰቆቃወ ድንግል በተባለው ድርሰቱ፤

❖«ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤
❖ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፤
❖አመ ነገደት ቁስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤
❖ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፡፡
❖ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ. . .፤
❖ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡

5.ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» በማለት በንጽጽር አስቀምጦታል፡፡ 《ኢሳ 19÷1》
❖ ኃይል እና ድል ማድረጉን በዳጎን የጀመረችው ታቦተ ጽዮን የፍልስጥኤማውያንን መንደር በአባርና በቸነፈር በእባጭም መታች፡፡ ሕዝበ ፍልስጥኤምም ታቦተ ጽዮን ወደ እስራኤል ምድር እንድትመለስ አደረጉ፡፡

❖በእንደዚህ ዓይነት ታላቅ ክብር በሀገረ እስራኤል ትኖር የነበረችው ታቦተ ጽዮን ወደ ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷ እመቤታችን በስደት ወቅ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷን ያሳያል ታላቅ የሆነ መንፈሳዊ ሐሴት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡
✥የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት✥

❖ከአርባ ሁለት ጊዜ በላይ ስሟ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ሀገር ቅድስት ኢትዮጵያ በእግዚአብሔርየተወደደች ለመሆኗ ነቢያቱ መስክረዋል፡፡
❖ከነቢያት አንዱ አሞፅም፤ «የእስራኤል ልጆች ሆይ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን ?» ብሎ እግዚአብሔር መናገሩን ጽፏል /9÷7/፡፡ ከሁሉም ከፍ ባለመልኩ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት፤ «ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች» ብሎ ሕዝበ ኢትዮጵያ እደ ሕሊናውን እና እደ ልቡናውን ዘወትር በአምልኮተ እግዚአብሔር፣ በጾምና በጸሎት፣ በምጽዋትና በትሩፋት፣ ዘርግቶ በሃይማኖት ጸንቶ፣ በምግባር ቀንቶ የሚኖር በመሆኑ፤ ሕዝቡ ሕዝበ እግዚአብሔር ምድሪቱ ሀገረ እግዚአብሔር ተብለዋል፤ 《መዝ.68÷31》፡፡
❖ለታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ዋናው ምክንያት በእስራኤል እና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው የሠመረ ግንኙነት ነው፡፡ ይኽም በመሆኑ የንግሥት ሳባ እና የንጉሥ ሰሎሞን ግንኙነት ሰፊውን ታሪክ ይዞ ይገኛል፡፡
❖የንግሥተ ሳባ ዕቃ ግምጃ ቤት የነበረው ታምሪን ወደ ኢየሩሳሌም ሔዶ ንጉሥ ሰሎሞን ያሠራውን ቤተ መቅደስ ዓይቶ፣ የሰሎሞንን ጥበባዊ ዝና ሰምቶ በፍጹም መደነቅ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡ ያየውንና የሰማውን ለንግሥቲቱ አጫወታት፡፡ እሷም የሰማችውን ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ የሰሎሞንን መንፈሳዊና ሥጋዊ ጥበብ ተመልክታ እግዚብሔርን አመስግና ተመለሰች፡፡
❖ከንጉሥ ሰሎሞን ምኒልክን ፀንሳ ከኢየሩሳሌም ተነሥታ ባሕረ ኤርትራን ተሻግራ፣ ሐማሴን አውራጃ ስትደርስ አሥመራ ከተማ በሚገኘው ማይበላ ከተባለው ቦታ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ የሕፃኑንም ስም የንጉሥ ልጅ ስትል «እብነ መለክ» አለችው፡፡ ይኽ ስም በዘመን ሒደት ምኒልክ ተብሎ ተለወጠ፡፡
❖ምኒልክ ተወልዶ በአእምሮ እያደገ ሲሔድ አባቴ ማን ነው ? አድራሻውስ ወዴት ነው ? እያለ ጥያቄ ቢያበዛባት በሃያ ሁለት ዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ላከችው፡፡ ምኒልክም አባቱ ንጉሥ ሰሎሞንን አግኝቶ ሕገ ኦሪትንና የዕብራይስጥ ቋንቋ ሲያጠና ከቆየ በኋላ፤ ዐሥራ ሁለት ሺሕ እስራኤላውያንን አስከትሎ ከምድረ እስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ጉዞውን አቀና፡፡
❖ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር ለጉዞ የተነሡ ዕብራውያን ከቤተሰቦቻቸው መለየታቸው ሳያሳዝናቸው ከታቦተ ጽዮን መለየታቸው እጅግ ከበዳቸው፡፡ ወዲያው በፈቃደ እግዚአብሔር ታቦተ ጽዮንን ከመንበሯ አንሥተው በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ፡፡
❖ቀዳማዊ ምኒልክ እና እስራኤላውያን ታቦተ ጽዮንን ይዘው አክሱም የደረሱት ኅዳር 21 ቀን ነበር፡፡ ንግሥተ ሳባም የታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በጣም ስላስደሰታት በክብር ተቀበለቻቸው፡፡ «ወአንበርዋ ውስተ ሕፅነ ደብረ ሀገረ ማክዳ» እንዲል በአክሱም ከተማ መካከል ደብረ ማክዳ /ዛሬ ቤተ ጊዮርጊስ ከሚባለው/ ላይ ደብተራ ኦሪት ሠርተው አስቀመጧት፡፡
❖አሁን ያለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ ዐቅድ የታነፀው የአክሱም ጽዮን ገዳም ቅዳሴ ቤቱ ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ፣ ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ /የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት/ እና ልዑል ፊልፕ ከክብር ባለሟሎቻቸው ጋር በተገኙበት ነው ።

🌼 መልካም በዓል 🌼

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስ፤ቀሉ ክብር አሜን

╔​✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╗
#መልካም_የበረከት_በዓል_ይሁንልን
╚✞═┉✽🌹✥✥✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ  አንብቡት🙏🙏🙏

በዪቲዩብ ቻናላች ስብስክራይብ ያድርጉ
#ሰብስክራይብ #Subscribe በማደግ ይቀላቀላሉ https://youtube.com/channel/UC0-pqPv3c7alERhdDpW1wrQ

በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" hottg.com/mezgebehaymanot
 
በ Facebook በፔጃችን "መዝገበ ሃይማኖት" ወይም ከዚህ እታች ያለውን በመጫን ፔጁን ይቀላቀላሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇...  ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

hottg.com/mezgebehaymanot ለሌሎች ያስተላልፉ መልካሙን ያካፍሉ🤳🤳🤳

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
HTML Embed Code:
2024/04/19 02:02:19
Back to Top