TG Telegram Group & Channel
Nahi moods | United States America (US)
Create: Update:

#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 ቢዝነስ እቅዱ ለደንበኞቹ ለማቅረብ ባቀዳቸው አዳዲስ እና የተሻሻሉ ምርት እና አገልግሎቶች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

ተቋሙ በቀጣይ አመት 70 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ያቀደ ሲሆን ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ24 በመቶ ጭማሪ አለው።

ከነገ ጀምሮ በአጠቃላይ ጥቅል አገልግሎት ላይ የ20 በመቶ ቅናሽ ማድረጉንም ያስታወቀ ሲሆን ጥቅል ሳይገዙ የድምጽ አገልግሎት ለሚጠቀሙ ደንበኞችም ከ20 እስከ 30 በመቶ የታሪፍ ቅናሽም ማድረጉን ገልጿል።

ማሻሻያው ከሶስት እስከ አስር ደቂቃ የድምጽ አገልግሎት ለሚጠቀሙ ደንበኞች ከመደበኛው ታሪፍ የ20 በመቶ ቅናሽ የተደረገበት ሲሆን ከአስር ደቂቃ በላይ ለሚጠቀሙ ደንበኞች ደግሞ የ30 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ መደረጉን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ጠቁመዋል።

ኩባንያው በ2014 በጀት ዓመት 178 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱንም አስታውቋል።

አጠቃላይ የደምበኞችን ቁጥር 56 ነጥብ 2 ሚሊዮን ወደ 64 ሚሊዮን ፤የሞባይል ዳታ እና ኢንተርኔት ደንበኞች ከ24 ነጥብ 5 ሚሊዮን ወደ 28 ነጥብ 5 ሚሊዮን ለማሳደግ ታቅዷል።

በተጨማሪም የመደበኛ ስልክ ደንበኞችን ከ912 ሺህ ወደ አንድ ሚሊዮን የመደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ደንበኞችን ከ374 ሺህ ወደ 554 ሺህ ፤ የቴሌ ብር ደንበኞች ከ6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ወደ 21 ነጥብ 2 ሚሊዮን ለማሳደግ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

(Capital, ETIradioshow, Ethiopia insider)

@tikvahethiopia

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA

>>Click here to continue<<

Nahi moods

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)