TG Telegram Group Link
Channel: ኢንፎክን የመጻሕፍት እና የመረጃ ማዕከል
Back to Bottom
በአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ የኢንፎክን የመጻሕፍትና የመረጃ ማዕከል 14ተኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበር ምስሎች በጥቂቱ!

#INFOKEN_BOOKS_AND_INFORMATION_CENTER

Join us @infokenamu
ጥቆማ
ሰኚሆክ ቅዳሜ ግንቦት 20 በ7:00 ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር ይታያል። መግቢያ 50 ብር ነው።

#ኢንፎክን_የመጽሐፍት_እና_የመረጃ_ማዕከል
የህይወትን ጣዕም የምንለካው በመነካታችን ልክ ነው። በዚህ ምድር ላይ ስትኖር ማድረግ ያለብህ ወይም የሌለብህ የሚባል የተሰላ ቀመር የለም። ምናልባት የምታደርግበትን መንገድ ልትመርጥ ይገባህ ይሆናል። ልብህን በክፋት እንዳታነሳሳው፣ የተቀደሰ የተባለ ተግባርን እንኳን ሳይቀር በክፋት ባትፈፅም መልካም መሆኑ የታመነ ነው። ከዚህ በዘለለ ግን ላንተ ትርጉም የሰጠህ ነገር ሁሉ ዓለምህ ነው። ባቲና አንቺሆዬን ትተህ በሩቅ ምስራቅ ዋሽንት ነፍስህን ታሳርፍ ይሆናል። ከሳሽ የለብህም። መኖርህን የምትለካውም የምትመሰክረውም አንተው ነህ። በዙሪያህ ካሉ ነገሮችና ከምትወዳቸው ነገሮች ጋር ሁሉ ምን ያህል ከልብህ Connect አድርገሃል ይሆናል የመኖርህ ትርጉሙ።

እናትና አባትህ በህይወት ካሉ በደንብ አስጨንቀህ ልጅ ሁንላቸው። ብልጭታህ ቀለሟ ይደምቅ ዘንድ ፍቅርን ስትሰጥ አትሰስት። በሚወዱህ ሰዎች ልብ ውስጥ ያለ ቀመር ያለ ስሌት ደምቀህ ታይ። በቃ! በዚህ መንገድ ሁሉንም መከፋፈያዎች አልፈህ የራስህ ዓለም ንጉስ ትሆናለህ። ይሄ ሁሉም ነገር የሚሆነው ግን በፍቅርና ያለስስት ያለስሌት በሚኖር ዛሬ ነው። ከዛሬ ጋር በደንብ Connect ሁን። ዛሬ ካሉህ ወዳጆች፣ ጓደኞች፣ ቤተሰቦች፣ እንዲሁም ሃብት፣ አቅምና ጊዜ ጋር ስምምነት ፍጠር። ስለምታገኘው 1 ሚሊዮን ብር እያሰብክ በእጅህ ላይ ላለው 1ሺህ ብር ባዕድ አትሁን።

ስለ Connection ስናወራ ነገሮችን ሁሉ Sentimental ለማድረግ ሳይሆን ሁሉም ሰው የየራሱን Reality ቀለም፣ ውብና ደማቅ ማድረግ የሚችልበት መንገድ መሆኑን ለመጠቆም ነው። የየቀን አጀንዳዎቻችን የምር እኛን ይመለከታሉ ወይ የሚለው ጥያቄም ወሳኝ ነው። ለዚህም ነው ትርጉም የሚሰጠን ነገር ላይ ማተኮር ያለብን። ዓለም የምናያትን ያህል ሰፊ አይደለችም። ዓለም የምትጠፋው በኒዩክለር ቦንብ ወይም በዳግም ንፍር ውሃ የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ዓለም የምትጠፋው በሰዎች ልብ ውስጥ ነው። አንድ ልጅ ያላት እናት ልጇ የሞተ ቀን ዓለሟ ትጠፋለች። አንዲት ውሻ ያለችው የጎዳና አዳሪ ውሻውን መኪና የገጫት ቀን ዓለሙ ትጠፋለች። Value የምንሰጣቸውን ነገሮች እንዲበዙ መጣርና ከነዚህም ነገሮች ጋር በፍቅር መቆራኘት ህይወትን ውብና አጓጊ ከማድረግ አልፈው የነገዋን ፀሃይ እንድንናፍቅ ያደርጉናል።

በዓለሙ ካለው ሁሉ አንተ የምትወደውና Value የምትሰጠው ነገር የመኖርህ ምክንያት ይሆናል። Purpose ይሰጥሃል። የሰው ልጅን ከሌሎች ፍጡራን የሚለያቸው ነገር አንዱ ኪነጥበብ ነው። የኪነትንና የሰው ልጅን ቁርኝት ስናስብ ሁሉም ነገር በጥቅምና በውለታ የሚቀየር እንዳልሆነ ይገባናል። ግጥም የሚወድን ሰው ለምን ግጥም ወደድክ ብትለው ምክንያታዊ መልስ አይመልስልህም። ትያትር ለማየት 200 ብር የሚከፍልን ሰው ለምን በርገር አትበላበትም ብትለው የሚያቀርብልህ ምክንያት አጥጋቢ ላይሆን ይችላል። ግን በቃ 'በርገር ይበልጣል' ወይም 'ትያትር ይበልጣል' የሚለን የተሰላ ቀመር የለም። ሰው Value የሰጠው ነገር ይበልጣል። ከላይ ያነሳሁላችሁን ነጥቦች በሙሉ በጥበብ ሊነግረን የሚችልና እኔም Value ሰጥቼ ከልቤ የወደድኩትን አንድ ነገር ልጠቁማችሁ። THIS IS US

በቤተሰባዊ ዘውግ የምንጊዜም ምርጡና እጅግ ተወዳጁ THIS IS US ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ባለፈው ሳምንት አየር ላይ በዋለው የመጨረሻውና 108ኛው ክፍል ላይ "If something makes you sad when it ends, it must have been pretty wonderful when it was happening" በማለት ተመልካቾቹን ተሰናብቷል።

በርግጥ እንደኔ ላሉ ተመልካቾቹ ይሄ ቃል ትልቅ መፅናኛ ነበር። አንድም ላለፉት 8 ዓመታት በየሳምንቱ ረቡዕን ጠብቄ ያየሁት ድራማ 'ጨርሻለሁ' ማለቱ የሚፈጥረው ጥሩ ያልሆነ ስሜት በመኖሩ፣ እንዲሁም እንደማንኛውም ሰው በህይወት ውጣውረድ ውስጥ የመጨረሻ የተባሉ ቀናትን ደጋግሜ አሳልፌም ስለማውቅ። This Is Us ሰዎች እንዲያዩት የተሰራ ፊልም አይደለም፣ ራሳቸውን አስገብተው እንዲተውኑት እንጂ። ወደትወናው ለማስገባት triggering button አድርጎ የሚጠቀመው Perfect Melody አለው። ማንም እሱን Escape ማድረግ አይችልም። ለመሳቅ የቀልዱን መጨረሻ መስማትን አይጠይቅም። ለማልቀስም የተዋንያኑን የፊት ገፅታ መመልከት አያስፈልግም።

This Is Us የቤተሰብ ዘውግ የሚመቻቸውን ተመልካቾች ለማርካት የተሰራ ድራማ አይደለም። ይልቁንም ለሰው ልጆች ሁሉ የቀረበ Therapy ነው። ልክ እንደ ርዕሱ ስለ እኛ ነው የሚያወራው። እኛ ማለት ደግሞ ልጅነት፣ ወጣትነት፣ ጉልምስና፣ እርጅና፣ እናትነት፣ አባትነት፣ ሚስትነት፣ ባልነት፣ ፍቅረኛነት፣ አያትነት፣ አማችነት፣ አማትነት ከመሳሰሉት ነገሮች አናልፍም። ተወልደናል ወይም ወልደናል፣ ወደናል ወይም ተወደናል። በዚህ በዚህ ውስጥ ሁሉ እኛ የተነካንባቸውን ወይም ወደፊት የምንነካባቸውን ነገሮች የቴሌቪዥን መስኮት ያመጣልናል። ርዕሱን ሰጥቶን ይሄዳል። ትወናው ከኛ ነው፣ ምክንያቱም This is Us.

This is Us'ን ከልጆቻችሁ ጋር እዩት፣ ከወላጆቻችሁ ወይም አሳዳጊዎቻችሁ ጋር እዩት፣ ከባለቤታችሁ ጋር እዩት፣ ከፍቅረኛችሁ ጋር እዩት፣ ለብቻችሁም እዩት ለውጥ የለውም። ሁሉም ቦታ ላይ እናንተ የምትነኩበትን ርዕስ ያመጣላችኋል። አታመልጡም፣ ሊያስቆዝማችሁ ሳይሆን ራሳችሁን እንድትፈትሹበትና እንድትመለከቱት ጊዜ ለመስጠት ነው። የሚያብሰለስላችሁ ጉዳይ እናንተ ጋር ብቻ ያለ ነገር አለመሆኑን ያሳያችኋል። ከዚያ ደግሞ ማምለጫ መንገድ መኖሩንም ያሳያችኋል። በመደለል ሂደት ሳይሆን በተጨባጭ አመክንዮ ይሞግታችኋል። በቃ its a complete therapy. በስድስት ምዕራፍ የተደራጁ 108 ክፍሎች የናንተን አይኖች ይጠብቃሉ። የፒርሰን ቤተሰቦች ስለብዙ የሰውነት አጀንዳዎች ሃሳብ አላቸው። ፊልም እንደዚህ መሰራት ይችላል እንዴ እስክትሉ ድረስ ያስደምሟችኋል።

"Take the sourest lemon that life has to offer and turn it into something resembling lemonade"

This Is Real, This Is Love, This Is Us! #MoviesToWatch

©ገረመው ፀጋው (@gere_perspective)

#INFOKEN_BOOKS_AND_INFORMATION_CENTER

Join us @infokenamu
የተጠላው እንዳልተጠላ፣ የያዘው መንገድ
ገንፎን አጥላልቶ፣ ለሙቅ ማጎብደድ!!!
-©ገረመው ፀጋው(@gere_perspective)-

አለማየሁ ገላጋይ (የእኔን ምስክርነት የማይሻ) ጎበዝ ደራሲ ነው። ለስነፅሁፍ ራሱን አሳልፎ ሰጥቷል። ተፈትኗል፣ ዋጋ ከፍሏል፣ በዚያውም ልክ ብዙዎቹ ያልታደሉትን መከበርና ተቀባይነትንም አግኝቷል። አሌክስ ሲናገር ጆሮዎች ሁሉ ይከፈታሉ። ንግግሩ በራሱ በዜማ የታጀበ ነውና የአድማጭን ቀልብ ይገዛል። በየጊዜው አዳዳስ ሃሳቦችንና የአፃፃፍ ዘዴዎችን የሚያስተዋውቀን ለትውልዱ የተሰጠ የስነፅሁፍ ገፀበረከት ነው። ይህም በመሆኑ ይሄ ፅሁፍ ከአለማየሁ ገላጋይ የስነፅሁፍ ችሎታ ጋር በተነሳ ለውዳሴም ለወቀሳም የተወደረ አይደለም።

በምድር የሚኖር የሰው ልጅ ሁሉ ፖለቲካዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ውስጥ መሆኑን ሁላችንም እናስተውላለን። ይሄ ቀውስ በመጠን ይለያይ እንደሆነ እንጂ የሌለበት የዓለም ንፍቀ ክበብ የለም። በርግጥ ችግሮች አፍሪካ ውስጥ ውስብስብና የጎሉ ናቸው። ከበርካታ አፍሪካ ሃገራት አንፃር ሲታይ ግን የኢትዮጵያ ችግር ቀለል ሊል ይችል ይሆናል እንጂ የበለጠ አይደለም። ይሄ ማለት ግን የኛ የኢትዮጵያውያን ችግር የሚናቅና ለይደር የሚተው ነው ማለትም አይደለም። በርካታ ውስብስብ ችግሮች አሉብን። ዘርፈ ብዙ ቀውስና ችግር መሃል ነው ጥርሳችንን የነቀልነው። የምንተነፍሰው፣ የምናስበው ሁሉ ችግር ችግር ይሸታል።

የአለንበትን የችግር መጠን ለመግለፅ የዓለማችን ጉምቱ ፀሃፊዎች ሁሉ ተሰብስበው ቃል ቢያዋጡ እንኳን ከውስብስብነቱ አንፃር በትክክል ሊገልፁት ሁሉ የሚችሉ አይመስለኝም። 'መልሱን ተይው ጥያቄው ከገባሽ ይበቃል' እንዲል እያዩ ፈንገስ፣ እንደሃገር የጋራ ችግራችንን በትክክል ለይቶ የሚነግረን ሰው ቢገኝ ትልቅ ባለውለታችን ለመሆን ይበቃል።

ከዚህ ጋር በተገናኘ አለማየሁ ገላጋይ ሃገሩና የሚኖርበት ማህበረሰብ የሚገኝበት ቀውስ አስደንግጦታል። ሁላችንም አይተን እንዳላየንና ምን አገባኝ ብለን የተውናቸው የጋራ አዘቅቶቻችንን እንደዋዛ ሊተዋቸው አልፈለገም። መደንገጥና መታዘብ የአንድ ጎበዝ ደራሲ Motive ነው። ቀጣዩ ጉዳይ የሚሆነው ተደራሲን በሚገባው ቋንቋ ማስደንገጥ ይሆናል። ይሄኔ ነው አሌክስ ሙሉ አቅሙንና ችሎታውን ተጠቅሞ ሊያስደነግጠን ያልቻለው።

ችግር ውስጥ መሆናችንን የተናገረበት ቋንቋ የሚጋባ አይደለም። አሌክስ ካለው የስነ ፅሁፍ አቅም አንፃር በተጠላው እንዳልተጠላ ላይ ሲሶውንም የተጠቀመ አይመስልም። በቂ መደንገጥን መፍጠር አልቻለም። አንድን አንባቢ መፍትሔ አብሮህ እንዲፈልግ ካሰብክ የጋራ ችግር አንስተህ፣ ተንትነህና አባብለህ ልታስደነግጠው ይገባል። የደነገጠ ሰው ደግሞ የችግሩን መፍትሔ አብሮህ ባይፈልግ እንኳን የምታቀርብለትን ምርጫ ተጣድፎ ይመርጣል፤ የምትወስንለትን ውሳኔ ሳያቅማማ ይቀበላል።

አሌክስ በማህበረሰቡ ልብ ውስጥ ያለውን እግዜር ሊመረምር ተነስቷል። የዋዛ ድፍረት አይደለምና 'የነብሩን ጅራት ጨብጧል' ልንለው እንችላለን። ከዚህ በኋላ ማፈግፈግ የለም፣ ጅራቱን አጥብቆ ይዞ በጠንካራ አመክንዮ መሞገት ይኖርበት ነበር። አሌክስ ግን ያነሳውን ርዕሰ ጉዳይ የማይመጥን ግልብ Premises ደርድሮ ለውሳኔ ይጣደፋል። የሚከተለውን አንቀፅ እንመልከት....

[“አንድ ጊዜ ለአንዲት መንደር የጉድጓድ ውሃ ልናወጣ ማስቆፈር ጀመርን። ግማሽ ስንደርስ ጉድጓዱ በድንጋይ ይደፈናል። አሁንም አውጥተን ስንጨርስ ድጋሚ በድንጋይ ይሞላል። ለምን? ብለን መንደሩን ስናጠያይቅ እንዲህ የሚያደርጉት ወጣቶቹ ናቸው። ምክንያታቸውም የከንፈር ወዳጆቻቸውን የሚያገኙት ውሃ ሊቀዱ ራቅ ብለው ሲሄዱ ስለሆነ መንደር ውስጥ ውሃ ከወጣ አያገኙዋቸውም፡፡ ትንሽ ራቅ ብለን ጉድጓዱን አስቆፈርን።” ገፅ 6] ይህ አንቀፅ ወደ አንባቢ ልብ ውስጥ የመጋባት አቅሙ አንድ ለዛ ቢስ ኮሜዲያን ሳይዘጋጅ መድረክ ላይ ከሚቀልደው ቀልድ ያነሰ ነው።

ሌላ ቦታ ላይ ጥያቄ ማጋነን መልስ እንደሚያቀጭጭ አሌክስ የተረዳ አልመሰለኝም። [“አንዲት ልጅ ወዛ ብላለች፣ ጋይቴ ደስታ እሚባል ነበርና እሱ እየረዳት ተነስታ ፍሎሃ ወረደች ፤ ብዙ ሰው የተቀመጠው እዚያ ነው፣ ይኸ ስደተኛው ሁሉ ተቀበለና እዚያ አረደና በላት፡፡ ልጆቻቸውን ጥቃቅኖቹን እያረዱ የበሉ ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡" ገፅ 93]

እውነቱን ለመናገር ስለመጨካከን ካነሳን እኛ ጨካኞች ነን። ጭካኔያችን ግን የራሱ የእኛነት ለዛ እና አይነት አለው። በእንተማርያም ብሎ ለምኖ የሚበላ ሰው የተሰጠውን ነገር ሁሉ አለመብላቱን አሌክስ ዋጋ አልሰጠውም።  መከልከል ስንፈልግ "እምቢ" ከማለት ይልቅ "ውይ አሁን ጨረስኩ፣ አለቀብኝ" ብለን መዋሸታችን የእኛ የብቻችን ክፋት መሆኑንና አብረን ለመቀጠል የሚያስችል ዋጋ እንዳለው አልተረዳም።(ማስተዋል አልፈለገም)

ጣት ጠቋሚ ሃሳቦች፣ አንኳሳሽና የሚፈርጁ (ሰዳቢ) ቃላት እንዴትም ሆነው በሚያምር ቋንቋ ቢፃፉ በሰዎች ልብ ውስጥ ቦታ አግኝተው ለለውጥ የማነሳሳት አቅማቸው ደካማ ነው።

["ጥቁር ሽሮ፣ ነገሩ የጥንት ነው። ንጉሳውያን ቤተሰቦች፣ መሣፍንቶች፣ መኳንንቶች፣ ጳጳሳትና፣ ሊቆች ሁሉ በፆም ወቅት በምስጢር የሚገባበዙት ነው።"
"እንዴት ያለ?"
"ለፆም መያዣ የታረደ ሥጋ ሲተርፍ ቋንጣ ተደርጎ ይወቀጣል። ቡን ብሎ ሲደቅ ከሽሮ ጋር ተቀላቅሎ ትክን ተደርጎ ይሰራና በምስጢር 'ጥቁር ሽሮ ይብሉ' እየተባባሉ ይገባበዛሉ።" ገፅ 85]

አዲስ ሃሳብ ወደሰዎች ማጋባት የፈለገ የለውጥ ሰው አሮጌውን በመስደብ ላይ ከተጠመደ ሊሳካለት አይችልም። መጀመሪያ ለመደማመጫ የሚሆን የጋራ መሬትን መፍጠር ያስፈልጋል። አለማየሁ አሮጌውን መስደቡና ማንቋሸሹ ከደከመው በኋላ አጠገቡ አዲስ ቤት ሊሰራ ሞክሯል። አሮጌውን አስንቆ 'ኑ ወደ እኔ' እያለ የሚያስጎመጀን አዲሱን ቤት እንይለት ብለን ስንመረምር የሚከተለውን እናገኛለን።

#የሚቀጥል
#የቀጠለ

[እነሆ እግዚአብሔርና ስሙ ከተሰለቹበት ከተማ ደረስሁ። የሰማይ አሞሮችና የባህር ነፍሳት ግን ጠግበዋል። የማያመሰግኑበትን በረከት አግኝተዋል። ከማይፀለይበት ገበታ ዙሪያ ተሰይመዋል። ምስጋና ስላልከፈሉ ገበታቸው ከመሙላት አትጎድልም፣ እነሆ የእግዚአብሔርና የህግጋቱ አውዶች ፈርሰዋል። ወንድ ከወንድ ይጋባል፣ በወደደ ጊዜ ሰው ከእንስሳት ቢገባ ከልካይ የለበትም። የማያመሰኳና ሸኾናው ክፍት የሆነ ሁሉ ይበላል። እግራቸው ወደ ክፉ ሁሉ ትሮጣለች፣ ግን አልተሰናከለችም። ገፅ 10]

["ሀገር ይዘው ህዝብ ይፈልጋሉ።  እንደ እስራኤሎች ህዝብ ይዘው ሀገር በፈለጉ እንዴት ደግ ነበር፤ እንደ አሜሪካኖች መስፈሪያ ያጣች የሰፋሪዎች ጀልባ ብንሆን እንዴት መልካም ነበር።" ገፅ 123]

ኢትዮጵያኖች የቱንም ያህል ችግር ቢያቆራምዳቸውና አሌክስ በገለፀው ልክ ሰው ለመብላት የበቁ ሰዎች ቢሆኑ እንኳን ሰውነትን ተውና እንስሳ ሁኑ ማለት የተሻለ አማራጭ መንገድ እንደመጠቆም የሚቆጠር አይመስለኝም። በርካታ ቀውስ አለብን፣ ረሃብተኞች ነን፤ ነገር ግን የመዳረሻ ሞዴሎቻችን አሜሪካና እስራኤል ሊሆኑ አይገባም። ለምን እግዜራችንን ነካህ ወይም ደግሞ ስራን አምልኩ አልከን የሚል ጥያቄ ማንሳቴ አይደለም። ጥያቄው የትኛውን ችግራችንን ለመቅረፍ ነው በመስቀል ቆፍረን ዶማን የምንሳለመው የሚለው ነው።

ችግራችን ስንፍና ብቻ ነው ወይ? መጥገብ አለመቻላችን ብቻ ነው ወዬ? የሰማይ ዝናብ መጠበቃችን፣ ለሶስት ሺህ ምናምን ዓመት በበበሬ ማረሳችን፣ ቅዳሴና ሰዓታት መቆማችን ነው ወይ ይሄን ሁሉ ቀውስ ያመጣብን? ማነው በድፍረት ችግራችን ይሄ ብቻ ነው ብሎ ሊነግረን የሚችለው? አሌክስ በትክክል የገባው ነገር ቢኖር ችግርና ቀውስ ውስጥ ስለመሆናችን ብቻ ነው። ከዚያ በዘለለ የችግራችንን መንሰኤ ስንፍናና አምልኮ፣ ከችግራችን የመውጫ መንገዱ ደግሞ ለስራ ባሪያ መሆንን ብቻ እንደመፍትሄ መቁጠር የትም ሊያደርሰን አይችልም። ነጩ መንገድ አላዋጣንም ብሎ ሙሉ በሙሉ ጥቁሩን መከተል ዞሮ ዞሮ ሚዛኑን መሳቱ አይቀርም።

በአንድ የኪነጥበብ መድረክ ላይ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ በኢህአዴግና በደርግ መካከል የመንገድ እንጂ የመዳረሻ ለውጥ እንደሌለ ለማሳየት የጠቀሰውን ማብራሪያ ላካፍላችሁ። "ደርግ ብሔሮችን ሁሉ ችላ ብሎ ኢትዮጵያን በማጉላት ላይ ያተኮረ ሃገረ መንግስት ገነባ። ውጤቱ የሚያምር አለመሆኑን ተተኪው ኢህአዴግ ተገነዘበ። ኢህአዴግም ከደርግ ትምህርት ወሰድኩኝ ብሎ ኢትዮጵያን ተወና ብሔሮችን ብቻ በማጉላት ላይ ያተኮረ መንግስትን ገነባ። ያመጣው ውጤት ግን ከደርግ የባሰ መሆኑን ሁሉም የገፈቱ ቀማሽ ሁሉ ይረዳዋል።"

እዚህ ጋር የጎደለው ነጭም ጥቁርም ያልሆነው ግራጫው መንገድ ነው። ነገሮችን ከምንም በላይ ማቻቻል (Balance ማድረግ) ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ችግር የዶማና የመስቀል ዋጋን በመለዋወጥ ብቻ የሚፈታ እንዴት ሊሆን ይችላል? በልባችን አብሮ ያደገውን እግዜርን ስንተወው ሽልማታችን ምንድነው? እንደ አሜሪካውያን መሆን? ይሄ የሚያጓጓ መዳረሻ አይደለም በጭራሽ። ያጓጓል ብንል እንኳን የልባችንን እግዜር ከመተው ጋር ሊመጣጠን ፈፅሞ አይችልም።

ሌላኛው ትልቁ ጥያቄ መዳረሻችን ምንድነው የሚለው ይሆናል። የሰው ልጅ መለወጥ አለበት ካልን ምንድነው መምሰል ያለበት። አንበሳ? ዝሆን? ንስር? ጉንዳን? ንብ? ወዘተ? ...የሰው ልጅ ሄዶ ሄዶ ተለውጦ ሰው ብቻ ነው መምሰል ያለበት። ሰው ደግሞ ሆዱን ስለሞላ ብቻ ምሉዕ አይሆንም። ጎተራው ስላልጎደለ ብቻ ደስታውን በእጁ ሊጨብጥ አይችልም። ምክንያቱም ሰው አንበሳም፣ ጅብም ጉንዳንም አይደለም። ሰው፣ ሰው ብቻ ነው። የመንፈስ ረሃብ አለበት፣ ልቦናው መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት እንደሚያስፈልገው ያምናል። እንደዛ ባይሆን ኖሮ በየጊዜው አማዞን ጫካ ውስጥ እንደ አዲስ Discover የሚደረጉ  የጎሳ አባላት ድንጋይ ወይም ዛፍ ሲያመልኩ ባልተገኙ ነበር። በቃ ህገ ልቦናቸው ወይም የማሰብ አድማሳቸው አንዳች Devine Intervention እንዳለ ሹክ ብሏቸዋል። በገባቸው ልክም Connection ለመፍጠር ይተጋሉ።

ይሄ ይሄ ሁሉ ቢዘነጋ እና 'የእግዜር ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም' የሚለው ላይ ብንደርስ እንኳን አለማየሁ አውቆ ችላ ያለው ነገር እንዳለ ይሰማኛል። እንደ ጃፓን በጠንካራ የሞራል እሴት ያልበለፀገና እንደ ቻይና ጠንካራ የህግ አንቀፆችን ያልተለማመደ ማህበረሰብ ይዘህ አንዲት የቀረች ማስፈራሪያን (ፈሪሀ እግዚአብሔርን) ተው ለማለት መነሳሳት በራሱ ፍፁም ኃላፊነት የጎደለው አካሄድም ይመስለኛል።

ስንቱ ነው ለፅድቅ ይሆነኛል እያለ የተቸገረን (በመስቀል መቆፈር የማይችልን) ሰው ሆድ የሚሞላው። ስንቱስ ነው በሰማይ ይመጣብኛል ብሎ የሚያምነውን ቅጣት እያሰበ ብቻ በሰዎች ላይ ክፋትን ከመስራት የሚያቅማማው? ቆይ ለመሆኑ በዚህ የኑሮ ውድነት ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ተረጋግተው በሰላም መገበያየት የቻሉት ለምንድነው? አንዱ እያድፋፋ ሌላው እየላሰ ግን አብረን መኖር የቻልነው በምን ምክንያት ነው? በፈሪሀ እግዚአብሔር አይደለም ወይ? ታዲያ ምንም አማራጭ ሳናለማምደው ያለውን (አለው ተብሎ የሚታሰበውን) ብቸኛ የጋራ መስመር ልንበጥስበት የምንታገለው?

በነገራችን ላይ እንኳን የእስራኤልና የአሜሪካውያን ስብእና ይቅርና የጃፓናውያን አኗኗርም በራሱ ኢትዮጲያኖች ሊቀኑበት የሚገባ ለመሆኑ በቂ ጥናት ያስፈልጋል። ምክንያቱ ደግሞ ከልክ ያለፈ የስራ ፍቅራቸው፣ ግላዊነታቸውና አንዱ በአንዱ ህይወት ውስጥ ቦታ አለመኖሩ በርካታ ወጣቶችን በጭንቀት ራሳቸውን እንዲያጠፉ ምክንያት ሆኗል። ህይወት Balancing ትፈልጋለች የሚባለውም ለዚህ ነው። በአጠቃላይ አለማየሁ ገላጋይ ያነሳቸው አብዛኞቹ በአመክንዮ ያልተደገፉ Dictated ገለፃዎቹ አንባቢ ላይ የመጋባት አቅም የላቸውም።

በሽማግሌ መዳኘትን፣ የታመመ መጠየቅን፣ የዝምድና ተዋረዳችንን ሁሉ በገፀባህሪ በኩል ሆኖ የሚኮንንበት መንገድ Aggressive ነው። ያለንን ሁሉ ነጥቆ ሊሰጠን የሚሞክረው ነገር ደግሞ ሊቀማን ከሚታገለው አንፃር አጓጊ አይደለም። አለን ብለን የምናምነው ወርቅ፣ እንጨት እንደሆነ ይነግረናል። በምትኩ 'አልማዝ ነው እንካችሁ' የሚለን ግን ጭራሹኑ አመድ ነው። ገንፎን አጥላልቶ ለሙቅ የማጎብደድ አይነት።

ሳጠቃልለው፣ መጀመሪያ ላይ እንዳነሳሁት የሰው ልጅ በሙሉ ዘርፈ ብዙ ቀውስ ውስጥ ነው። እንደ እከሌ መሆን አለብን ብለን በኩራት የምንጠቅሰው ቡድን ወይም ሃገር የለም። ሃምሳ ጎበዝ ካለ ሃምሳ ሰነፍ አይጠፋም። የሆነ ቦታ ሰዎች ተሰባስበው ክፋ ነገርን ሲያደርጉ ብናይ ሰው ሁሉ ክፉ ነው ማለት ተገቢ አይደለም። ሌላ ቦታ ላይም ሰዎች ተሰብስበው መልካምና ቀና የሆነን ነገር ሲያደርጉ ብናይ ሰው ሁሉ መልካም ነው አንልም። በቃ ሰው መልካምም ክፉም ነው። ኢትዮጵያም መልካም ሰዎችን ብቻ ለአለም እንድታስተዋውቅ የተቀበለችው ቀብድ የለም። በዓለም ካሉት ጨካኝ ሰዎች መካከል ኢትዮጵያ ድርሻ አላት። ዓለም ካሏት መልካም ሰዎች ውስጥም ኢትዮጵውያን አሉበት።

#የሚቀጥል
#የቀጠለ

ድንቄም ኢትዮጵያዊነት፣ ድንቄም ደግ ሃበሻ፣ ድንቄም አማኝ ህዝብ፣ ድንቄም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለበት ህዝብ፣ ድሮስ አማራ፣ ድሮስ ኦሮሞ፣ ድሮስ ትግሬ እያሉ የሚያንኳስሷችሁን አትስሟቸው። ስለክፋታችሁ ብቻ ሲነግሯችሁ ደግ መሆናችሁንም ለመግለፅ አትቦዝኑ። ስለ መልካምነታችሁ ብቻ በነገሯችሁ ጊዜም ክፋትም የናንተ እንደሆነች አስባችሁ ከመታበይ ራሳችሁን ጠብቁ። 'እናነተ ኢትዮጵያኖች' ብሎ የሚጀምርን ሰው ንግግር በጥንቃቄ ስሙት። ክፉ ናችሁ ከተባላችሁ 'ሰው ስለሆንን ነው' በሉት። ደግ ናችሁም ከተባላችሁ 'ሃበሻነታችን ነው' ብላችሁ ከመታበይ ይልቅ 'ሰው ስለሆንን ነው' በሉ። ሁሉም ውስጥ አለንበት። ሃበሻነት ሊያኮራም ሊያሸማቅቅም አይገባም።

በመጨረሻም በየተጠላው እንዳልተጠላ ላይ ሁሉም ሰው በጥሞና ሊያስተውላት የምትገባ (በእኔ ምልከታ) አንዲት ደረቅ ሃቅ አለች። ["የእኛን መሬት ያህል ጠፍ መሬት እያለ እስትንፋሳቸውን አዝለው ማርስ ላይ ይኖሩ ይመስላችኋል? አትሳሳቱ እነዚህ አድላቢዎች የሚጠብቁት ነብያቸውን ዳግማዊ ጆርጅ ዋሽንግተንን ነው። እኛም ከእንቅልፍ መበርከት የምናልቅ ቀይ ህንዶች ነን።" ገፅ 132]

መውጪያ፦ "አንተን ከገባህ ምኑን ተቀኘሁት" ያሉትን የጎንደር ባለቅኔ እያሰባችሁ የእግዜር ጠበቃዎች ሆይ፣ በልባችሁ ያለው እግዜር ከአንድ ደራሲ የምናብ ጥያቄ በላይ ካልሆነ ምኑን እግዜር ሆነላችሁ? የአሌክስ ጠበቃዎችም፣ ጎበዝ ደራሲ ከአንባቢዎቹ ትችትና ወቀሳ በላይ ካልሆነ ምኑን ጎበዝ ደራሲ ሆነ? መልሱን ለየራሳችን፣ አበቃሁ! ከታላቅ አክብሮት ጋር።

©ገረመው ፀጋው (@gere_perspective)

#INFOKEN_BOOKS_AND_INFORMATION_CENTER
Join us @infokenamu
🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎክን የመጻሕፍትና የመረጃ ማዕከል የ2014 ዓ.ም ምሩቅ ቤተሰቦች
🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆🎆

#INFOKEN_BOOKS_AND_INFORMATION_CENTER
Join Us @infokenamu
ኢንፎክን የመጻሕፍትና የመረጃ ማዕከል ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ / ወመዘክር በስጦታ ያገኛቸውን 1000 የሚሆኑ ሁለገብ መጻሕፍት፣ አርባምንጭ ዩንቨርስቲ ለሚገኘው ማዕከል አስረክቧል። ለተደረገለት ቀና ትብብርም ወመዘክር'ን በትልቁ ያመሰግናል።

በንባብ የበለፀገ የነቃ ትውልድ እንፍጠር! ወደ ንባብ እንመለስ!

Join us @infokenamu
#የኢትዮጵያ_በረከቶች
በሒሶፕ ኢንተርቴይመንት ተከሽኖ የኛን መምጣት እና ማክሰኞ መጋቢት 12ን የሚጠብቀው ድንቅ የስነጽሁፍ ዝግጅት... የተለያዩ ገጣምያን፣ ድምፃውያንን እና በድንቅ ወጉ የምናውቀውን አዱኛው አዲስን ጨምሮ የኢትዮጵያ የባህል ቡድን ጊዜያችንን ለማሳመር ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል። በመድረክ አጋፋሪው አዲሱ ገረመው ውብ ለዛ የሚመራውን ድንቅ ፕሮግራም ልጋብዛችሁ...ሄደን ዘና ፈታ ብለን ተረፍረፍ አድርገን እንመለስ!!
0939015249 ላይ እየደወልን አለን ቦታ ያዙልን እንበላቸው😁😁

@infokenamu
እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን አደረሳችሁ
በሁለተኛው ሚሊኒየም መባቻ ላይ በሰባት የአርባ ምንጭ ተማሪዎች ምስረታውን ያደረገው የሁላችን ቤት የባች ልዩነትን በቁጥር እንጂ ለክለቡ ባለን ፍቅር ያላሳየን ዛሬ አስራ አምስት ዓመት በኋላም እንደያኔው በፍቅር ግን በብዛት በዝተን የምስረታ በዓሉን ልናከብር ዕለተ እሁድን ግንቦት 27 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የሚገኘው ቤታችን እንገናኝ ተብላችኃል ያው እዛ ካሉት ቤተሰቦቻችን ውጭ ኢንፎክንን በቅርቡ የማየት ዕድል በማግኘት ይህንን መልዕክት እንዳስተላልፍ ተነግሮኝ ነው ስለዚህ ከሩቅም ከቅርብም ያላችሁ የኢንፎክን ቤተሰቦች በዕለቱ እንድንገናኝ ይሁን።
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎክን (INFOKEN) የመጻሕፍትና መረጃ ማዕከል ከበጎ አድራጎት ማዕከል (Charity Center) ጋር በመተባበር የማጣቀሻ መጻሕፍትና አልባሳት ድጋፍ አበረከተ!

ለተጨማሪ ንባብ:- https://www.amu.edu.et/2741-infoken-charity-
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ ኢንፎክናዊያን። የኢንፎክን ጀግና የሆነው ወንድማችን ካሌብ የፊታችን ማክሰኞ ድንቅ የጥበብ ድግስ አዘጋጅቷል።ሁላችንም በቦታው በመገኘት የድግሱ ተካፋይ እንድንሆን በአክብሮት ተጋብዘናል።
HTML Embed Code:
2024/03/29 05:32:25
Back to Top