Channel: hawassa City sport club
የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ ያጋጠመውን የውጤት ማጣትን አስመልክቶ የክለቡ የበላይ ጠባቂ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በተገኙበት ዛሬ ውይይት አድርጓል
በዚህም የሀዋሳ ከተማ የፊት አመራርና የስፖርት ክለቡ ጠባቂ በጋራ በመሆን ለክለቡ ውጤታማነት መክረዋል።
የስፖርት ክለቡ በቀጣይ ያለውን ውጤት አስጠብቆ መቀጠል በሚያሰረችለው ጉዳይ ላይ በመምከርም ነው ውይይት የተደረገው። ውሳኔዎችን በቀጣይ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

Forwarded from 4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ™ (Teddy)
"ያላረጀውን አንበሳ ከመጫወቻነት እንታደገው" የሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ለ4-3-3 እንደገለፁት !
ከታቦር ተራራ እስከ አላሙራ፥ ከግብርና ግቢው air lines እስከ አሞራ ገደል፥ ከቃጫ ፋብሪካ እስከ ሎቄ፥ ከአሁን ጊዜዋ ዳቶ እስከ ዘመነኛዋ አሊቶ እኚህ ሁሉ ተሰባጥረው መሀል ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎችን አሰባጥረው ለአንድ ታላቅ ስም ቅኔ ሲዘርፉና በነቂስ ወጥተው ሲደግፉ ኖረዋል።
ሀዋሳ ከሀይቁና ከተራሮችዋ በላይ የምትሳሳለት የስለት ልጅ አላት ስሙም "ሐዋሳ ከነማ" ይሰኛል። በ1968 ከፍተኛ 1 እና ከፍተኛ 2 የሚባሉ ቀደምት ቡድኖች ተመስርተው በ1976 የስለት ልጁዋን ሀዋሳ ከነማን ወለዱላት። በህዝብ ምጥና ዕድሜ ባልገደባቸው አዋላጆች የተወለደው ሀዋሳ ከነማ በእግርኳስ ፍቅር ልክፍት ውስጥ ከገቡ ህዝቦች አብራክ የተገኘ የስለትም የስስትም ልጅ ሆኖ ኖሯል.....ሙሉ ዝርዝሩን ለማንበብ https://www.facebook.com/share/p/19gAe2XcpL/
https://hottg.com/Bisrat_Sport_433et https://hottg.com/Bisrat_Sport_433et

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ለቀጣዩ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ማሻሻያ ተደርጎበታል
ቀጣዩን የሁለተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለማስተናገድ ሽር ጉድ ላይ የምትገኘው ሀዋሳ ከተማ ውድድር የሚደረግበትን የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ቀድሞው የነበረውን የመጫወቻ ሳሩን ሙሉ በሙሉ በመለወጥ በአዲስ አፈር እና በአዲስ ሳር ሙሉ በሙሉ ለውጥ ተደርጎበታል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከጅምሩ 1990 አንስቶ በመወዳደር ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ታሪክን የተጋራው አንጋፋው ክለባችን የሁለተኛውን ዙር ጨዋታ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት እንዲያደርግ የከተማ አስተዳደሩም ሆነ የክለባችን የደጋፊ ማህበር ከፍተኛ ስራን ሲሰራ የቆየ ሲሆን እየተሰሩ ካሉ ስራዎች መካከል አንዱ ደግሞ ዋነኛ የውድድር ቦታ የሆነውን የዩኒቨርስቲውን ሜዳ የመጫወቻ ሳር ሙሉ በሙሉ በመቀየር ማሻሻያ ማድረግ አንዱ ስራ በመሆኑ በስኬት ይህንን ተግባር አጠናቆ ለሊጉ ውድድር አዘጋጅቷል። ከሳሩ በተጨማሪ በስታዲየሙ ዙሪያ በመልበሻ ክፍል ያሉ ተጨማሪ ተግባራት እየተከወኑ ሲሆን የልምምድ ሜዳዎችን በበቂ ሁኔታ ምቹ የማድረግ ስራም መሰራት ተጀምሯል።
ካለፈው የ17ኛ ሳምንት የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ጀምሮ ክለባችንን ወደ ውጤት ጎዳና እንዲመጣ ከደጋፊ ማህበሩ አንስቶ እስከ ከተማው ባለሀብት እና ነጋዴው ድረስ ከፍተኛ ንቅናቄዎች በመፍጠር የክለቡ ታሪክ እንዳይበላሽ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን በቀጣዩ ሐሙስ ከመቻል ጋር አንጋፋው ክለባችን ለሚያከናውነው ጨዋታም ደጋፊው ወደ አዳማ ለመጓዝ እንዲዘጋጅ ተገልጿል። ከአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ ጋር የተለያየው እና በጊዜያዊ አሰልጣኝ እየተመራ ያለው ቡድናቸው ከቀድሞው ተሰናባች አሰልጣኝ ጋር የነበረውን ውል በስምምነት ለማፍረስ በጥረት ላይ ሲሆን በቀናት ውስጥም አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር እየሰራ መሆኑንም ተመላክቷል።

HTML Embed Code: