TG Telegram Group Link
Channel: የፊልም ቋንቋ አካዳሚ / Film Language Academy👌
Back to Bottom
#Editing Festival ለኤዲተሮች የተዘጋጀ
የኤዲት ፌስቲቫል!

የኤዲት ፌስት ከsep 07–oct 08 የተዘጋጀ ሲሆን በምስሉ ላይ በምትመለከቷቸው ዳይሬክተሮች እና ሙዚቀኞች የተዘጋጀላችሁን ፍቴጅ እና ሙዚቃ ከዌብሳይቱ በማውረድ እና በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ኤዲት በማድረግ በምርጥ ኤዲት፣ ቪኤፍኤክስ፣ ምርጥ ከለር አስከ 50 ሺ ዶላር የምትሸለሙበት ነው ተወዳደሩ እድላችሁን ሞክሩ መልካም እድል!
F.L.003- Producing/ፕሮዲውሲንግ#Topic 02*  
                        ክፍል 3/Part 3
የፊልም ፕሮዳክሽን 7 የስራ ሂደት ደረጃዎች/The 7
Stages Of Film Production/

4. ማምረት/Production

ከፊልም የማምረት ደረጃዎች ሁሉ በጣም አስደሳች የሆነው ይህ ጊዜ ነው ሁሉም ምትሀት ወይም አስማት የሚከሰትበት ጊዜ ማለት ነው ፡፡ ይህ የምርት ደረጃ የፊልም ሥራው ሲጀመር ማለት ነው - ይህ ማለት የቀረፃ ቀናት ሲጀመር እንደ ማለት ነው ፡፡ ሁሉም የቀደሙት የቅድመ ምርት/Pre production ተግባራቶች በትክክል ከተከናወኑ ይህ የስራ ጊዜ አጓጊ እና እጅግ አስደሳች ይሆናል! በበቂ ሁኔታ ዝግጁ ካልሆነ ግን፣ ወደ ሌሊት ቅዠት አይነት ሊለወጥባችሁ ይችላል ስለዚህ ቀድሞውኑ የቅድመ ምርት /Pre–Production/ ስራዎቻችሁን ቀድማችሁ በሚገባ መስራት አለባችሁ በዝርዝር እና አንድ በአንድ ነጥላችሁ ዝግጁ መሆን አለባችሁ ያንጊዜ እንደተባባልነው አስደሳችና አይረሴ የስራ ጊዜ ይሆንላችኃል ማለት ነው፡፡

ሌላው በጣም አስፈላጊው ነገር ከበጀት እቅዳችሁ ውጪ ንቅንቅ አለማለት ነው፤ እናም ይህ ሊከናወን የሚችለው ደግሞ የፊልም ፕሮዳክሽን መርሃ ግብራችሁን አክብራችሁ በመከተል ብቻ ነው ፡፡ ድንገት ሊፈጠሩ በሚችሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ውሳኔዎችን ለመወሰን እንድትችሉ በትኩረት መከታተል እና ለፈጠራ መፍትሄዎች ዝግጁ ሆኖ መቆየት ይጠበቅባችኋል ፡፡
በፊልም የማምረት/ፕሮዳክሽን/ የስራ ሂደት መሰረት ይህ የስራ ክፍለጊዜ ተዋንያን ቀድመው ሲዘጋጁበት ከነበረው የቀናት ልምምዶች በኋላ ትዕይንታቸውን የሚቀረፁበት ጊዜ ነው ፡፡ የፊልም ሙያተኞቹ ደግሞ እያንዳንዱ ትዕይንት በሰዓቱ ተሰርቶ መጠናቀቁን ለማረጋገጥ ጠንክረው የሚሰሩ ሲሆን በተለይ ሲኒማቶግራፈሩ/ዲፒው/ እና የፊልም ዳይሬክተሩ የምርቱ ሂደት በጥሩ ሁኔታ ተከናውኖ የሚቀርፁትን ፊልም በተቻለ መጠን ምርጥ ለማድረግ ትኩረት አድርገው የሚሰሩበት ጊዜ ነው ፡፡ፕሮዲውሰሮች/አምራቾች እንደ ሥራቸው ጫና ወይም እንደየአምራችነት ተግባራቸው ዓይነት በመመርኮዝ ቀድመው የተለያዩ ዝግጅቶችን ሊያደርጉ ይችላሉ።

አብዛኛውን ጊዜ ፕሮዲውሰሮች/አምራቾች በተቀናጀ ሁኔታ የፕሮዳክሽን ስራቸውን መሥራት እንዲችሉ የሚሰሩበት የፊልም ካምፓኒ ጽ/ቤቶች የተቀናጁ ቢሮዎች እና ስቱድዬዎች ያላቸው ካምፓኒዎች ይሆናሉ ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ አምራቾች/ፕሮዲውሰሮቹ በየራሳቸው ቢሮ ውስጥ ሆነው ይቆያሉ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እንዲሁ ወጣ እያሉ ይሳተፋሉ ፡፡ በአንዳንድ የፕሮዳክሽን ስራ ሂደቶች ውስጥ ደግሞ ፣ እንደ ስራው ስምምነት ዳይሬክተሩ ወይ ፕሮዲውሰሩ ፍቃደኛ ከሆኑ የፊልሙ ፀሀፊዎች በፕሮዳክሽን/ሴት ላይ በመገኘት ፕሮዲውሰሩን ወይም ፕሮዳክሽን ካምፓኒውን በመወከል የተለያዩ ውሳኔዎችን በመወሰን ማንኛውንም ዝርዝር ጉዳዬችን በመከታተል የተቆጣጣሪነትን/ሱፐርቫይዘርነትን ሚና የመጫወት ስራ ሊሰሩ ይችላሉ።
በመጀመሪያ ወደቀረፃ ከመሄዳችሁ በፊት እነዚህን የፕሮዳክሽን/ቀረፃ እቅድ መመሪያዎችን ተከትላችሁ ለመስራት ሞክሩ ውጤቱ ያማረና ቀላል ያለ ይሆንላችኃል። በተለይ ለጀማሪ ፊልም ሰሪዎች ደግሞ እነዚህ ቀላል አሥር የቀረፃ ምክሮች ተግባራዊ ለማድረግ ሞክሩ!

ቀለል ያሉ ታሪኮችን መቅረፅ

የአንድን የታሪክ ስፍራ ወይም ክስተት እየቀረፃችሁ ከሆነ ምናልባት ስቶሪቦርድ/የታሪክ ሰሌዳ ወይም ስክሪፕቱን ይዛችሁ መከተል ላያስፈልጋችሁ ይችላል። ነገር ግን ምንም እንኳን ቀለል ያለ ታሪክ ቢሆንም የምትቀርፁት ታሪክ ምን እንደሆነ እንዴት እንደሚጓዝ በቅድሚያ በአይምሯችሁ መያዝ አስፈላጊ ነው ግዴታም ነው።

የተለያዩ የቀረፃ ልኬቶችን/size አቀናብራችሁ ያዙ

ለምሳሌ አጠቃላይ ስፍራውን ለማሳየት እጅግ በጣም ሰፋ ያሉ እይታዎች(የመመስረቺያ ሾቶች/Stablishing shots or ረዘም ያሉ እይታዎች/long shot ፣ እና ሰዎችን በሚገባ ለማንሳት እንዲረዳችሁ መካከለኛ እይታዎች/Middim shoots ፣ እና ደግሞ በርከት ያሉ የሰዎች የቅርብ እይታዎች/Close up shots የመሳሰሉትን በተለያዩ አቅጣጫዎች አቅዳችሁ መገኘት አለባችሁ።
እያንዳንዱን የቀረፃ አቋቋማችሁን/Setups/ በጥንቃቄ
ማዘጋጀት!

በቀረፃ ወቅት የምትፈልጉትን አይነት ምስል ለማንሳት አካባቢያችሁን በምትፈልጉት መንገድ ለመጠቀምና ካሜራችሁን ዙሪያችሁን ወደምትፈልጉት አቅጣጫ ማንቀሳቀስ ሊኖርባችሁ ይችላል ስለዚህ ቀድማችሁ የካሜራ አጋዥ ቁሶችን ፣ መብራቱን እና ሌላውን አጋዥ መሳሪያዎችን እንደምትፈልጉት ለማድረግ እንድትችሉ አድርጋችሁ ማሰናዳት/መሰቃቀል፣ ማቆም እና መደበቅ አለባችሁ(ብዙን ጊዜ ከላይ ተንጠልጣይ የሆኑ ቴክኒኮችን ብትጠቀሙ ይመከራል)።

ክፈፉችሁን/Freaming/ ፈትሹ!

ማንኛውንም አስፈላጊ ነገር ላለመቁረጥዎ እርግጠኛ ሁኑ በክፈፉ በስክሪናችሁ ፍሬሚንግ ውስጥ መካተቱን ሁልጊዜ ሳትሰላቹ አረጋህጡ፣ እና ደሞ የማያስፈልግ ወይም ግራ የሚያጋባ ማንኛውንም ነገር በክፈፉ/fram/ ውስጥ አለመግባቱን አረጋግጡ።

መብራቱን/lighting/ ፈትሹ!

በካሜራው ማያ መስኮት ወይ በማሳያ ስክሪን ላይ ያለውን ምስል በሚገባ ተመልከቱ። እንዴት ነው ትክክል ይመስላል? ትክክለኛ ብርሃን ይታያችኃል? በጣም ብሩህ ወይም በጣም ጨለማ የሚመስል ከሆነ የብርሃን ተጋላጭነቱን/Exposure/መለወጥ ይኖርባችኃል ማለት ነው (እራስችሁ ያዘጋጃችሁት ልዩ የብርሃን ሴታፕ ካለ ጥሩ ወይም የካሜራውን የተጋላጭነት/exposure/ ማንዋልን ተጠቅማችሁ ማስተካከል ይኖርባችኃል።)
የካሜራችሁን ትኩረትን/focus/ ፈትሹ!

እንዴት ነው ምስሉ ጥርት ያለ ነው? ወይም ሻርፕ ነው ምስላችሁ የጥራት ጥልቀቱ መለስተኛ ወይም shallow focus እንዲሆን ፈልጋችሁ ከሆነ የሌለው ጥርት ያለው ፎከስ እንዲመጣ የምትፈልጉት የትኛው የትዕይንቱ ትክክለኛ ክፍል ላይ ነው? ወይም ከደብዛዛ ምስል ወደ ጥራት ያለው ምስል የምትለውጡት መቼ ነው ነጥቡን ማወቅ ትችላላችሁ ይሄ ከዲ ፎከስ ወደ ዲፕ ፎከስ የምንለውጥበት ወይም ራክ ፎከስ የምንለውን የምስል ቅንብር/Composition/ በምንሰራበት ጊዜ ሊሆን ይችላል። (በሞሽን ፒክቸር ቀረፃ ላይ ይሄን ስራ ብቻውን የሚሰሩ ፎከስ ፑለር የሚባሉ ሙያተኞች መኖራቸውን ማስታወስ ይገባል)

ድምፁን/Sound/ ፈትሹ።

በቅድሚያ ሁሉም ሰው ዝም እንዲል አድርጉ ፣ ከዚያ ለግማሽ ደቂቃ በፀጥታ አዳምጡ። በፊልሙ ቀረፃ ላይ ተደርቦ የሚመጣ ማንኛውንም ነገር መስማት ቻላችሁ? የፊልሙን ድምፅ ቀረፃ የሚያበላች ሆኖ ካገኛችሁት እሱን ለማስተካከል የምትችሉት ነገር አለ? ከቻላችሁ በድጋሜ የጆሮ ማዳመጫዎችን በመጠቀም የሚረብሽ ድምፅ እንዳለ አረጋግጡ ለሱም መፍትሄ ፈልጉለት እና በቀጣይነት ደግሞ የሚፈለገው የተዋንያኑም ሆነ ሌሎች ድምፆች ቀረፃውን ሳያስተጓጉሉ በተገቢው ቅርበትና ርቀት ሆነው የሚፈለገውን ድምፅ መቅረፅ እንደሚያስችሉ በሚገባ አረጋግጡ።

በመጨረሺያም ሁሉም ሰው ዝግጁ እንደሆኑ አረጋግጡ። ከዛ ከፍ ባለ ድመፅ ‘ልንጀምር ነው’ ወይ ‘ተዘጋጁ’(standby) በማለት ይናገሩ ወይንም በአካባቢው ላሉ ሰዎች ፊልሙ ሊቀረፅ እንደሆነ በመናገር ቀጥሎ በቀጥታ ‘Action’ በማለት የተለመደውን የቀረፃ ማስጀመሪያ ትዕዛዝ በመናገር ፊልሙ መቅረጽ እንዲጀመር ተናገሩ።
የሚፈልጉትን ሁሉ ምስል መገኘቱን ማረጋገጥ

የተሟላ የቀረፃ ሽፋን/Coverage/ ማለት እርስዎ ለትዕይንትዎ የሚያስፈልጉዎትን ሁሉንም የተቀረፁ ፉቴጆች ማግኘታችሁን ማረጋገጥ ነው ፣ ስለሆነም በኃላ ላይ ሳይቀረፅ ተዘሎ ወይ ተረስቶ የነበረ ትዕይንት እንዳይኖር በዛው ስፍራ መፈተሽ እና ያልተቀረፀ ክፍል ካለ መቅረፅና ሙሉ ማድረግ፣ በመጨረሺያም ለኤዲተሩ ማስረከብ አስፈላጊው የቀረፃው የመጨረሺያ ተግባር ይሆናል ማለት ነው።

ጠቅለል ባለ መልኩ ደግሞ በተለይ ለጀማሪ ፊልም ሰሪዎች ይህን የቀረፃ ሂደት ተከትላችሁ ለመስራት ሞክሩ!
፠ መሰረታዊ የቀረፃ ሂደቶች!

★በመጀመሪያ ለውስን የሆኑ እይታዎች ፣ የተለመደውን የዳይሬክቲንግ ፍሬሚንግ ልኬት አውራጣትን እና ሌባ ጣትን በማገጣጠም ክፈፋችሁን/ፍሬማችሁን በመወሰን እንዲቀረፅ ማድረጋችሁን እንዳትረሱ!

★አንድ ሰው አንድ ነገር ሲያደርግ ለማሳየት አስባችሁ ከሆነ ደግሞ፣ በመጀመሪያ መቼቱን በሚገባ ለማስተዋወቅ (exposition shot) ሁለት ረዥም እይታዎች/long shot/ ወይም በጣም የረዘመ እይታ/extrem long shot/ ቅረጹ!

★ከዚያ ደግሞ የግለሰቡን የቅርብ እይታ/Close shot/ ወይንም መሀከለኛ እይታ/Middim shot/ ማግታችሁን አረጋግጡ።

★እና ደግሞ ሰውየው ከሚያደርገው ነገር ጋር መቅረፃችሁንም እንዳትረሱ በተጨማሪ ሰውየውን ለብቻው የሚደረገውን ነገር እንዲሁም የሚደረግበትን ቁስ፣ ነገር ወይም አንዳች አስፈላጊ ሁኔታ ሊሆን ይችላል ለብቻ ቅረፁት።

★በስተመጨረሺያ ደግሞ ሁልጊዜ እርሶ ሊቀርፁ ተዘጋጅተውበት ከመጡት ሁለት ተጨማሪ እይታዎችን/shots/ ቅረፁ።
★ሌላው ደግሞ ትዕይንቱ በቂ ሽፋን(Coverege) ማግኘቱን ለማረጋገጥ አንደኛው መንገድ ሙሉውን ትዕይንት ዋና እይታ/Master shot/ መቅረጽ ነው - ይህ ማለት ከሞላጎደል ሁሉምነገር በሚታይበት አቅጣጫ የሁሉም እንቅስቃሴዎች በሚያሳይ መልኩ በረጅም እይታ/long shot ወይም በጣም በረዘመ እይታ/etrem long shot/ መቅረፅ ማለት ነው።

★እንዲሁም ደግሞ የመቁረጫ ነጥቦችን(Cutaways) መቅረፅ አለባችሁ - ይህ ማለት የትዕይንቶችን አነስተኛ ነገሮች፣ ቁሶች ወዘተ ቅረፁና በኃላ ኤዲት/አርትዖት ስታረጉ ከአስፈላጊነታችው በተጨማሪ ፉቴጃችሁን/shots/ ለመቆራረጪያና ለመገጣጠሚያ ትጠቀሙበታላችሁ።

★አንድ ካሜራ ብቻ ካሎት እና የድራማ ትዕይንት እየቀረፁ ከሆነ ፣ አጠቃላይ ድርጊቱን በሚያሳይ ስፍራ ላይ ለዋና እይታ ቀረፃ/Masster Shot/ ካሜራዎን ያዘጋጁ ፣ ከዚያ የቅርብ እይታ/closeshot/ እና የመካከለኛውን እይታ/middim shot/ ከመቅረጽዎ በፊት ተዋንያንኑ ሙሉ ትዕይንት እንዲለማመዱና በአንዲ ጊዜ እንዲሰሩት በማድረግ ሙሉውን ትዕይንት ቅረፁት። ከዛ የምትፈልጉትን ክፍል እየነጠላችሁ በምትፈልጉት የሾት አይነት ቅረፁት!
★የምትቀርፁት የቀጥታ ክስተት ወይም ክንውን ከሆነ (ማለትም የማይደገም አይነት ወይም እንደ ስፓርታዊ ክንውን ሊሆን ይችላል)፣ ለዚህ አይነት ቀረፃ ​​ደግሞ ሁለተኛ ካሜራ ምናልባትም ከዛ በላይ ካሜራ ሊያስፈልጎት ይችላል። መላውን ድርጊት የሚሸፍንሎት ማለት ነው ፣ ይህም ማለት ክንውኑ ሩጫ ቢሆን ሲጀምር የሚቀርፅ፣ በመሀከል እና መጨረሺያውን የሚቀርፅሎት እንደማለት ነው የአንድ ስፍራ ክንውን ቢሆን እንደቦክስ ፍልሚያ ከሆነ ደግሞ በተለያዩ አቅጣጫዎች ካሜራችሁን በመጣድ መቅረፅ ማለት ነው።

★አስታውሱ
የ DSLR ካሜራዎች በጣም ረጅም የሆኑ እይታዎችን በበቂ ብቃት መቅዳት አይችሉም ፣ ስለዚህ ክስተቱ ከከፍተኛው የእይታ ርዝመት በላይ የሚቆይ ከሆነ በምትኩ እንደ ካሜራኮርድ ያሉ ካሜራዎች መጠቀም ያስፈልግዎታል።

★ትዕይንቱ እርስ በእርስ በሚነጋገሩ ሁለት ተዋናዮች መካከል የቅርብ እይታቸውን(closeups) እየተመላለሰ የሚታይ ከሆነ ፣ በመጀመሪያ ትዕይንቱን በሙሉ ካሜራዎን በተዋናይ 1 ላይ በማድረግ ሙሉውን ይቅረጹ ፣ ከዚያ ካሜራውን ወደ ተዋናይ 2 ፊት ይለውጡና ቅደምተከተሉን(Continuity) በማስጠበቅ አጠቃላይ ትዕይንቱን እንደገና ይቅረጹት ።
★ከዚያ ኤዲት(አርትዖት) በሚያደርጉበት ጊዜ የቀረፁትን ዋና እይታ/masster shot/ እና መቁረጫ እይታዎችን (cutaways) በማዋሀድ በቀላሉ መገጣጠም ትችላላችሁ ማለት ነው። (እነዚህን እይታዎች/ሾትስ ለመገጣጠም ግን ወሳኝ የተባሉትን የኮንቲኒቲ (ቅደምተከተል) ህጎች ማለትም የትወና፣ የንግግር፣ የድርጊት፣ የአልባሳት/ጌጣጌጥ፣ የሜካፕ/ፀጉር ስራ፣ የቁስ/ቁስ አጠቃቀም፣ የካሜራ አቅጣጫና ልኬት እና የመቼት እና የብርሃን አጠቃቀም ቅደምተከተሎችን ተመሳሳይ አርጋችሁ መቅረፅ ስትችሉ ነው)
★ለቃለ መጠይቆችም በትክክልና በተመሳሳይ ሁኔታ ይህኑ ዘዴ መጠቀም ይችላሉ።

★ሌላው ልምምድ ነው!
ከተመልካቾች ወይም ከተወናዬች ጋር ከቀረፃ በፊት መለማመድ ፣ ቀረፃውን ከመጀመሮት በፊት ትዕይንቱን ሁለት ጊዜ መለማመድ ያስፈልግዎታል። ከአጠቃላይ የቀረፃ ሙያተኞች ጋር የትወና፣ የካሜራ፣ ብርሃን እና ድምፅ ልምምድ ማድረግ ደግሞ Blocking ተብሎ ይጠራል (ይህ አሰራር በሀገራችን ፊልም ስራ ውስጥ ብዙም የተለመደ አይደለም ነገር ግን አስፈላጊው የቀረፃ ሂደት ነው) አንድ ሁለት ጊዜ ሙያተኞቹን በየስፍራዎቻቸው እንዲለማመዱ በማድረግ ማንኛውንም አስፈላጊ ለውጥ ካለ ለውጡ፣ አዳብሩት እና ወደ ዋናው ቀረፃ እለፉ።
፠ ምን ያህል መቅረፅ አለብዎት? የቀረፃው ሰዓት
መግባቢያዎችስ ምን ይመስላሉ?

ለማይንቀሳቀሱ ነገሮች ፣ ወይም ለአጠቃላይ እይታ (exposition shot) ወይም ለብዙ ሰዎች እይታ፣ ለእያንዳንዱ ሾት ቢያንስ አስር ሰከንዶች ያንሱ።

ሰዎች የሚያወሩበት ወይም ድርጊት ያለበት ትዕይንት ፣ ሲሆን ደግሞ ለቀረፃዎቻችሁ “መግቢያ እና መውጪያ” መቅረፅ ያስፈልግዎታል፤ ይህውም ትወናው ወይም ድርጊቱ ከመጀመሩ ከጥቂት ሰከንዶች በፊት ካሜራውን አስጀምሩት ፣ እና ትወናው/ድርጊቱ ካበቃ በኋላ ለጥቂት ሰከንዶች ያህል ዝምብሎ እንዲቀርፅ ተውት።

ቀረፃውን ራስዎ እየሰሩ ከሆነ(ወይም እራሶ ካሜራማን ሆነው እየቀረፁ ከሆነም ሊሆን ይችላል)፣ ማድረግ ያለብዎት በጣም ጥሩው ነገር ካሜራውን መጀመር እና መቅረፁን ማረጋገጥ ፣ ቀስ በቀስ እስከ አምስት መቁጠር እና ከዚያ ተዋናዮቹን የእጅ ምልክት በመስጠት ወይም ‘Action’‹ጀምር› ብሎ በመጮህ እንዲጀምሩ ማድረግ ነው። ከዚያ ሲጠናቀቅ፣ ቀረፃውን ከማቆምዎ በፊት ሌላ አምስት ሰከንዶች ይቆጥሩ።
እንደ ቡድን እየሰሩ ከሆነ ደሞ ፣ የዚህን መልመጃ የተወሰነ ሂደት መከተል ይችላሉ; -

★መጀመሪያ ካሜራዎን ያዘጋጁ እና ተዋንያኖቻችሁን
በየስፍራቸው እንዲዘጋጁ አድርጉ!
★ከዛ እነሱ ዝግጁ እንደሆኑ የካሜራ ኦፕሬተሩ
‹ካሜራ ዝግጁ› /comera set ይላል።
★ከዚያ ዳይሬክተሩ ‹ፀጥታ› ይላል።ሁሉም ሰው ዝም ካለ በኋላ ‹ተዘጋጁ› standby ይላል እና ከዚያ ‹turn over/ record› (ቀረፃ ጀምር) ይላል።
★የካሜራ ኦፕሬተሩ መቅረፅ ይጀምራል እና መቅረፅ መጀመሩን አረጋግጦ ከዚያ ‹በቀረፃ ላይ› Rooling/ Recording ይላል።
★ከዛ ዳይሬክተሩ አምስት ይቆጥራል ከዚያም ‹አክሽን›
‘Action’ ይላል (ወይም ለተዋንያንኑ በእጅ ምልክት
መቁጠር ይችላሉ)።
★ተዋናዮቹ ወይም አቅራቢዎቹ ስራቸውን ይጀምራሉ፣
★ከዚያ ዳይሬክተሩ የሚፈልገው እንደተቀረፀለት እንደገና አምስት ይቆጥራል እና ‹ቁረጥ› ‘Cut’ይላል።
★የካሜራ ኦፕሬተር መቅረፁን ያቆማል እና የምርት ረዳቱ/production assistunt/ የተቀረፀውን ቀረፃ/shot/ ማስታወሻ ይጽፋል እና በቀረፃ ዝርዝሩ/shot list ላይ ይወስዳዋል።
በተጨማሪ
★በድምፅ በኩልም የቀረፃ ትዕዛዛትን በአካባቢው ላሉ ሰዎች በማስተላለፍ የአካባቢውን ድምጽ ለብቻው ይቅዱ፤ ሁል ጊዜ ያለ ንግግር ቢያንስ ከግማሽ ደቂቃ የጀርባ ድምጽ ከአከባቢው መቅዳት አለብዎት። ይሄ ድምፅ በተለምዶ ሀሽ የምንለው ሊሆን ይችላል፣ የጫካ ድምፅ ወይም የመሀል ከተማ ድምፅም ሊሆን ይችላል በኤዲቲንግ ወቅት በጣም ጠቃሚ ይሆናል።
★ታሪክዎን ለመናገር ሊያግዙ የሚችሉ አስደሳች ወይም ልዩ ድምፆች ባሉበት ቦታ ላይ እየቀረጹ ከሆነ ደግሞ፣ የነዚህን አካባቢዎችድምፆች በተለየ ሁኔታ ለደቂቃዎች ለብቻው ይቅረፁ።
★የቀረፃ ስፍራውን ለቀው ከመሄዶ በፊት የሠሩትን ወይም የቀረፁትን ይፈትሹ ፣ ከቻሉ። ያለበለዚያ ቢያንስ በታሪክ ሰሌዳዎ/story bord/ ወይም የቀረፃ ዝርዝርዎ/shot list ላይ ሁሉንም ነገር እንደቀረጹ አረጋግጡ።
★በመጨረሺያም የቀረፃ ቁሶቾን ሸክፈው አካባቢውን ለቀው መሄድ የመጨረሺያ ስራዎ ይሆናል ማለት ነው።

ይቀጥላል…

Up next Step!

5. ድህረ ምርት/Post production
The World Health Organization Health for All Film Festival invites independent filmmakers, public institutions, NGOs, communities and students from around the 🌎 to submit their original short films on health issues.

Deadline; 30 January 2022

More info 👉 bit.ly/3G9mMy5
HTML Embed Code:
2024/03/28 23:25:20
Back to Top