TG Telegram Group Link
Channel: ጦቢያ ግጥምን በጃዝ
Back to Bottom
Well come /channel ጦቢያ ግጥምን በጃዝ
የውበት ጀርባው

ላንተ የሚታይህ፤ የሚያምር ፈገግታ
ያበባ  ጉትቻ
ላንተ እሚታይህ ውብ ገፅታ ብቻ
ጥርሷን ጉራማይሌ፤ የተነቀሰች ቀን
ያየቺው መከራ፤ ያየቺው ሰቀቀን
የጆሮዋን ጫፉን ፤ በሾህ  ስትበሳ
የበላችው ፍዳ ፤ ያየቺው አበሳ
የዋጠችው ህመም፤  ከሬት የመረረ
የቀመሰው ማነው፤ከሷ በስተቀረ?  
ከያንዳንዱ ታላቅ ፤ ውበት በስተጀርባ
ሲንዠቀዠቅ ኑሯል ፤ ብዙ ደምና እንባ
ይሄም ታላቅ ዜማ
ይሄም ታላቅ ስእል
ይሄም ታላቅ ተረት
ይሄም ታላቅ ድርሰት
ከፊትህ አልቆመም፤ እንደመና ወርዶ 
ስቃይ ያቃልላል፤ ከስቃይ ተወልዶ ፤ 👍


|በዕውቀቱ ስዪም| @Ethio_Art
@Daves_Art
Best art 😍😍
@Ethio_Art
🇪🇹ጦብያው🇪🇹
ጦብያው ለይቅርታ ቅደም
ቀድመህ እንዳትተው ድገም
ደግሞ ቢያስቀይምህ ሰልስ
ያባትክን አደራ መልስ....❤️
@Ethio_Art
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251707601574
ወይም @DaveidArt ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!


ተጨማሪ ስዕሎችን ለመመልከት ከታች ባለው Link ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@Daves_Art 🤏
don't judge fast😂😂
😋
@Ethio_Art
ሱሰኛው መነኩሴ Part 1

የኔ ልጅ እባክህ ላስቸግርህ እርዳኝ(መለኩሴው ጫት ከምሸጥበት መደብ ፊት ቆመው
አይ አባ እኛም እኮ ቸግሮናል ኑሮ ውድ ነው(ወደ ኪሴ እየገባሁ
አይደለም ልጄ እኔኮ ብር ፈልጌ አይደለም(ሰው እንዳይሰማ በሹክሹክታ እያወሩ
እሺ ምን ፈልገው ነው አባቴ መንገድ ልጠቁሞት?
አረ በፍፁም፤ዘእኔማ ከዝች ከጫቷ ቆንጠር አድርገህ እንድትሰጠኝ ብዬ ነበር በመሸማቀቅ አይናቸወን ስብር አድርገው
የተቀመጥኩበት ወንበር የሰመጠ ያህል ተሰማኝ ጥያቄያቸውን ተከትሎ አፌን ከፍቼ አይኔን አትጉረጥርጩ ቅንድቤን ሰቅዬ አየኋቸው፡፡ምናልባት ይህን ቃል የሠማሁት አጠገቤ ካለ የጫት ደንበኛዬ እንዲሆን በማሰብ አከባቢዬን ቃኘሁት ግን ሁሉም ተርዚናውን አጭቆ አፉን የሚያላውስ የለም የተናገሩት እኚ መለኩሴ ናቸው ጆሮዬ ነው ግራ በመጋባት ደርቄ ስቀር..
የኔ ልጅ አልሰማከኝም እባክህ ሱስ ሆኖብኝ ነው ሰው ሳያይ ቀስ ብለህ ስጠኝ
ተነስቼ መሮጥ ፈለኩኝ፣አልያም በአስማት ከዛ ቦታ የሚሰልበኝን ተአምር ባገኝ ብዬ ተመኘሁ ግን እፒ በነጭ ቆብና በጥቁር ካባ ያሸበረቁ ለሠማይና ለምድር የከበዱ መልዐክ የሚመስሉ መለኩሴ
አሁንም ከፊቴ ፊትለፊቴ ቆመው በልምምጥ እያዩኝ ነው
አባ ይቅርታ እኔ ለእርሶ አልሸጥም እንዴ ለምን እኔ ሰው አይደለሁ
አይ እርሶ የእግዜር ሰው ኖት ሌላ ቦታ ይሂዱ
ብታቅማ አንተም የእግዜር ልጅ ነህ ግን ደሞ ሱስ ነው የምልከው ልጅ የምልከው ልጅ አጥቼ ብቸገር እንጂ ..
እኚ መለኩሴ ለምን አይሄዱም ደግሞስ እውነት ብሰጣቸው እዚ አደባባይ ላይ ይቀበሉኛል?የሚሆነውን ለማየት እጄ እየተንቀጠቀጠ
አንድ እስር ጫት በፔስታል አድርጌ እየፈራሁ ወደ መለኩሴው እጄን ስዘረጋ....ይቀጥላል

jᵒⁱⁿ⇝ @Ethio_Art
የሚወዱትን ያስሉ ዘመን ተሻጋሪ ስጦታ ያበርክቱ 🎁 (Art)
በተመጣጣኝ ዋጋ
📞 0942041374

@DaveidArt
ሱሰኛው መነኩሴ Part 2

እጄን ስዘረጋ ጎሽ የኔ ልጅ በል እንካ ሂሳብክን(በደስታ እየተፍለቀለቁ
እኔ የእርሶን ብር አልፈልግም ሂዱልኝ ከዚ ቦታ ሁለተኛ እኔ ጋር እንዳይመጡ!
እኚ መለኩሴ ዛሬ ምነው ሚስማር ካልዘነበ መብረቅ ካልወረደ አሉሳ
ንዴቴ አናቴ ላይ ወጥቶ አንባረቅኩባቸው የማየው የምሰማው ነገር ድብልቅልቅ አለብኝ እወነት ግን ለምን ተናደድኩ? እኚ ሰው ቆብ ያድርጉ እንጂ እንደኔ ሰው አደሉ ደሞስ እኔ ማን ሆኜ ነው ምወቅሳቸው? ምናልባትም አንዱ የቸገረው ዱርዬ ጫት መቃም ፈልጎ የፈጠረው ድራማ ቢሆንስ? ጭንቅላቴን በጥያቄ ወጥሬ ያልተሸጠ ጫቴን እያስተካከልኩ መልሶ የሚጥል ድንጋጤ ወረረኝ...እኛ ጫት ካልሰጠከኝ እያሉ ሲነታረኩኝ የነበሩት መለኩሴ ለጫት ሲንገበገቡ መስቀላቸውን የጫት መሸጫዬ ላይ ጥለውት
ሄደዋል!!
ድንጋጤ ቅፅበታዊ ሲሆን ፍርሀት ትከሻ ሲወዘወዝ የገጠመኝ በዚህ ቀን ነበር ፍርሀት የማያውቀኝ ሰውዬ እየተርበተበትኩ መስቀሉን አንስቼ እኛ መዘዘኛ መለኩሴ ወደሄዱበት አቅጣጫ ከነፍኩ..ደርሼባቸው በእጄ የያዝኩትን መስቀል እስክሰጣቸው ልቤ ቆሟል ከኋላ አውሬ የሚያባርረኝ ያህል እየተሰባበርኩ ስሮጥ ከሩቁ አባ መቋሚያቸውን እያስቀደሙ ሲራመዱ አየኋቸው ግን እንደ እብድ ብጮኽ አባ ብል አይሰሙም የምርቃና ሰአታቸው ደርሷል... አባ አባቴ ይቁሙ አጠገባቸው ደርሼ ትንፋሼ እየተቆራረጠ ጠራኋቸው አባ የቤ/ክኑ በር ላይ ደርሰው እየተሳለሙ ጥሪዬን ሰምተው በድንጋጤ ዞር አሉ አቤት ምን አጣህ ምን ፈለክ?በቁጣ ግንባራቸውን ቋጥረው እያዩኝ
አረ እኔ መስቀሎትን ጥለው...በፍርሀት እያየኋቸው
በል ና እዚህ ጥሩ አይደለም ውስጥ እቀበልሀለው አሉኝ
እኚ ሰው ዛሬ ለምን አይተወኝም ገብቼ ደሞ እንቃም ሊሉ ነው፣ደሞስ ጫቱን ወደ ቤ/ክ ይዘው ሲገቡ አያፍሩም በዛ ሁሉ ድካም ውስጥ
ይሄ ሀሳብ አእምሮዬ ላይ ሲያቃጭል ዘገነነኝ።ግን አማራጭ ስለሌለኝ
ተከትያቸው ቤ/ክኑን አልፈን እስከ ቤታቸው አደረስኳቸው ና እስቲ አረፍ በል ቆንጆ ምሳ አለ
አረ አባ መስቀሉን ይቀበሉኝ እኔ ለዚ ቦታ አልገባም ልሂድ ስላቸው ....ይቀጥላል

jᵒⁱⁿ⇝ @Ethio_Art
የታዋቂ ሰዓሊያንን ስዕል ለማየት እና ስዕል ለመግዛት ቻናላችንን ይቀላቀሉ ለሚወዱትም ያጋሩ ❇️link (ማስፈንጠሪያውን) ይጫኑ 👉 @Ethio_Art
0707601574
ሱሰኛው መነኩሴ የመጨረሻ ክፍል

አረ አባ መስቀሉን ይቀበሉኝ እኔ ለዚ ቦታ አልገባም ልሂድ ስላቸው ...ግድ የለም አትፍራ ...አባ ፈጠን ብለው በሰሀን እንጀራ በምስር ወጥ ይዘው መጡ
እኚ ሰውዬ ግራ እያጋቡኝ ነው ውስጤ ብዙ ጥያቄ አለ ይሄን የመሠለ የመመረጥ ህይወት ትተው አለማዊ ነገር መመኘታቸው እያስገረመኝ...
ቆይ አባ ጫት መቃም ሀጥያት አይደለም እንዴ? ፤ በጥርጣሬ ጠየኳቸው...አረ በፍፁም ሀጥያት አይደለም፤ይኸው አንተ ትቅም የለም እንዴ?
እኔማ ሀጥያተኛ ነኝ ሁሌም ስራዬ ይህ ነው እርሶ ግን...ጎሽ የኔ ልጅ ተባረክ አየህ አሁን ትልቅ ቁም ነገር አወራክ ሰው ከፈጣሪ እንዳይታረቅ የሚያደርገው ዋናው ነገር ሀጥያት ሰልጥኖበት ሳለ ሀጥያተኛ ነኝ ብሎ አለማመኑ ነው ሰው ሁሉ ሀጥያተኛ ነው ግን ደሞ መርሳት የሌለብህ እግዚአብሔርም መሀሪ መሆኑን ነው። (አባ እያወሩኝ ከሰል ማንደጃቸው ላይ የገዙትን ጫት እያስቀመጡ ታድያ ሀጥያት ከሆነ ለምን እኔ ጋር መጥተው ገዙ ደሞስ ለምን ያቃጥሉታል፣[ጋዝ አርከፍክፈው የሚያቃጥሉትን ጫት ሲንቦገቦግ በድንጋጤ እያየሁ...አየህ ወጣትነት ማለት እንደዚህ እሳት ነው የያዘውን የቀረበውን ሁሉ ይፈጃል።ይህ እሳት ንፋሱ ወዳለበት አቅጣጫ እንደሚነድ ሁሉ ወጣትነትም አለም ባነፈሰችው ባራገበችው የሀጥያት አየር እንድንገፋ ያደርገናል።ይህ እሳት እንዲነድ ጋዝና ወረቀት ጨምሬበታለሁ ያለዚያ እንዲህ አይነድም ነበር ወጣትነትም ከልክ በላይ ሰውን እንዲያነድ
እና እንዲያጠፋ በጋዙ ቦታ ጫት ሱስ ዝሙት የመሣሠሉትን ሰይጣን ይጨምርልናል ያኔ እንደዚ እሳት በአለም ላይ እንነዳለን፡፡ ቅድም ጫት ስጠኝ ስልክ ድንጋጤክን አስተውያለሁ...አንተ እኔ እንዳልገዛ እንዳልቅም እየከለከልከኝ እንዴት ለራስህ መሆን ያቅትሀል? እኔም አንተም በእግዜር አምሳል የተሠራን ክቡር ፍጥረታት ነን ለኔ ያልተገባ ሀጥያት እንዴት ላንተ ይገባል ጫት ማለት ለጊዜያዊ መነቃቃት እና ደስታ ለስጋችን የምንጠቀመው እፅ ነው ይሄን ተከትሎ ደሞ መጠጥ ስካር ዝሙት የሚባል ሀጥያት ይመጣል። አንተ ይህን ጫት ቤ/ክ ይዤ ስገባ የጨነቀክ የእግዚአብሔር ቤት ስለሆነ አደል በምድር ላይ ግን ሰውን የሚያክል የእ/ር ቤተመቅደስ የለም! እና የእግዜር ቤተመቅደስን በጫት በሱስ ታረክሳለህ ሱስ ማለት እግዜር የሠጠኝ ደስታ ሰላም አቅም አንሶብኛልና ሌላ ተጨማሪ ነገር ያስፈልገኛል ብሎ መልፋት ከፈጣሪ መጣላት በስራው መጠራጠር ነው፤ስለዚህ የመዳን ቀን ዛሬ ነውና ከፈጣሪህ ታረቅ አምላካችን ሀጥያትን እንጂ ሀጥያተኛን አይጠላም ከሴሰኞች ጋር አትተባበሩ እንዳለ መፅሐፍ ለሀጥያት ለሱስ አትተባበር፡፡ ቅድም እንደዛ ሲነድ የነበረው እሳት አሁን አመድ ሆኗል፤ሰው እንዲ ነው..ወጣትነት ማያልፍ ይመስላል ግን እንደዚ አመድ መክሰማችን አይቀርም። ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወዳለች ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች  ስለዚህ የሞት ሞት እንዳትሞት የስጋ ምኞትህን ለፈጣሪ አስገዛ። እኔም ሱሰኛ ነኝ ግን የፆም የፀሎት የስግደት ነው፡፡ቅድም መስቀሌን ጥዬው ሳይሆን አንተ ተከትለከኝ እንድትመጣ ስለፈለኩ ነው ጥዬው
የመጣሁት።አንዳንዴ ሰወች ወደ ቤ/ክ መምጣት ሲደክሙ ቤ/ክ ወደ ህዝቡ መሄድ አለባት እኔ የቤ/ክ አንድ አካል ስለሆንኩ አንተን ፈልጌ መጣሁ ታድያ ተሳክቶልኛል? በትክክል አባ፤ሁለተኛ እዚ ሀጥያት ውስጥ አልገባም እንደኔ ያሉትንም ለማምጣት ቃል እገባለሁ ይቅር በሉኝ አባቴ(እንባ ተናንቆኝ እግራቸው ስር እየወደቅኩ
እግዚአብሔር ይቅር ይበልክ በል ተነስ አባ በፈገግታ ተሞልተው አነሱኝ እኔም የማትጠገብ ምስር እና የማይጠፋ ምክር ተመክሬ ቡራኬ ተቀብዬ ልቤን ለፍቅሩ አስገዝቼ ወደቤቴ ተመለስኩ፡፡


jᵒⁱⁿ⇝ @Ethio_Art
♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
jᵒⁱⁿ⇝ @Ethio_Art
🎤 🎤 🎤 😂 😂 😂 😂
( ትምሮ አስበላኝ )
🤯🤯🤯🤯

Thahahahahaha
የምር በቃ join በሉ
የማይለመጥበት ነገር የለም

👇👇👇👇👇👇👇👇? @ethio_Art
ማሰብህ ካልቀረ.....🤔


♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
jᵒⁱⁿ⇝ @Daves_Art
          @pamfalon
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251707601574 🤗
ወይም @DaveidArt🧡 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!


ተጨማሪ ስዕሎችን ለመመልከት ከታች ባለው Link ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@Daves_Art🤍
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በናፍቆት ተይዤ ሲደክም ጉልበቴ 🙄
ደሞ ይባስ ብሎ ታሰረ አንደበቴ😒
ስብር ያለ ለታ ስሜም እንደቅስሜ😔
እፅናናለው ሳይሽ እንኳንስ ተስሜ😘
ብክንክን ስል አደብ ሲያሳጣኝ🥺
ትዝታሽ ደርሶ ከጭንቅ አወጣኝ🤩
አወይ መታደል አወይ መገፋት 💘
ከሞት ያስጥላል እንኳን ከዕንቅፋት 🖤
ሀኪሜ ነሽ መዳኒቴ 💝

♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
jᵒⁱⁿ⇝ @Daves_Art🧡
          @pamfalon🧡
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኔ ፍቅር 🥰
🔤🔤🅰️ 🔤🔤 ✈️
@Daves_Art💠
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😊❤️......
@Ethio_Art
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
HTML Embed Code:
2024/04/23 17:18:45
Back to Top