TG Telegram Group Link
Channel: ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
Back to Bottom
ማሳሰቢያ!

እንዲህ አይነት ማስታወቂያዎችን እዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይም ሆነ ሌሎች ቻናሎች ላይ ተመልክታችሁ ይሆናል። ማስታወቂያዎቹን እኔ ያቀረብኳቸው እንዳልሆኑ እና ቴሌግራም በራሱ አዲስ አሰራር ቻናሎች ላይ ማስታወቂያ መለጠፍ በመጀመሩ እንደሆነ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

መልካም ምሽት።

@EliasMeseret
ከሳምንታት በፊት በአዲስ አበባ ከፀጥታ አካላት ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው የተገደሉ ሁለት ወጣቶች ቤተሰቦች አስከሬናቸውን ሳያገኙ ፍትሀትና ባህላዊ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ጎንደር ውስጥ መፈፀሙ ተሰምቷል

እኔን ግን የሚገርመኝ... እነዚህ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፣ ከዚህ ምድር ተሰናብተዋል።

ታድያ መንግስት አስከሬን አግቶ ይዞ ለቤተሰብ አልሰጥም ማለት ለምን ይሆን? ምን ሊያረጉት ይሆን?

ይህ ድርጊት በየትኛውም አለም፣ በየትኛውም ሀይማኖት እና ባህል ሲፈፀም አይታይም። ኦሳማ ቢንላደን እንኳን ከተገደለ በኋላ ቀብሩ ባህር ላይ ሲፈፀም ስርዐቱን ተከትሎ ነበር።

ጭካኔን ለማሳየት እና ለሌሎች ማስፈራርያ ለማድረግ ታስቦ ሊሆን ይችላል፣ የራሱን የአድራጊውን የድንጋጤ መጠን ግን ወለል አርጎ የሚያሳይም ይመስለኛል።

የትኛዋም የሀገራችን እናት ግን ይሄ አይገባትም።

Via BBC

@EliasMeseret
የትግራይ ህዝብ ሲጨፈጨፍ ቃል ስትተነፍስ... ጁንታ ነህ!

የአማራ ህዝብ ተጎዳ፣ ተሰቃየ ስትል... ፋኖ ነህ!

ኦሮሚያ ውስጥ ህዝብ በሁለት ተፋላሚ ሀይል መሀል ሆኖ ተሰቃየ ስትል... ሸኔ ነህ!

የካድሬው ውዥንብር እንዳለ ሆኖ ከእውነት እና ከህዝብ ጋር የቆመ ግን በመጨረሻ አያፍርም።

@EliasMeseret
#ጥቆማ ለአዲስ አበባ ፖሊስ!

ለሚ ኩራ ወረዳ 9 ቀጠና 6 እና 7 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፖሊሶች በር እያንኳኩ ለአካባቢ ጥበቃ አንድ፣ አንድ ሺህ ብር ክፈሉ በማለት ነዋሪዎችን እያስገደዱ እንደሆነ የሚደርሱኝ ጥቆማዎች ያሳያሉ።

ይህ ጥቆማ በለሚ ኩራ ዙርያ ይሁን እንጂ በበርካታ የአዲስ አበባ ከተማ እና አዋሳኝ ስፍራዎች ተመሳሳይ በፀጥታ አካላት የገንዘብ አምጡ ማስገደጃዎች እየታዩ ነው። ገንዘብ የለኝም ያለ ደግሞ የመንግስት ተቃዋሚ ተደርጎ ሊታይ እንደሚችል ፍርሀት አለባቸው።

መልካም ፖሊስ በብዛት እንዳለ ሁሉ እንዲህ አይነት ፀያፍ ድርጊት የሚፈፅሙም አንዳንዶች ስላሉ ክትትል በማድረግ እርምጃ እንድትወስዱ ጥቆማዬ ይድረሳችሁ።

@EliasMeseret
ተወዳጁ ተዋናይ አማኑኤል ሐብታሙ ከ42 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ዳይሬክተሩን ዳግማዊ ፈይሳ ጨምሮ ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ፍርድ ቤት ቀርቧል

"በቡድን በመደራጀት ወጣቶችን መልምሎ በማሰማራት፣ ገንዘብ ለሽብር ቡድኑ ሎጂስቲክስ መግዣ ለማዋል... ሕገ-መንግስቱን እና ሕገ-መንግታዊ ስርዓቱን በኃይል በትጥቅ ትግል ለመቀየር ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው ተጠርጥረው".... የሚሉ መዘርዝሮችን የያዘ የጊዜ ቀጥሮ ማመልከቻ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል (የተያያዘው ምስል ላይ ዝርዝሩን ያገኙታል)።

ተዋናይ አማኑኤል እስራኤል አገር "እብደት በሕብረት" የተሰኘ ቴአትሩን ለማሳየት አውሮፕላን ሊሳፈር ሲል ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዶ መታሰሩ ይታወሳል።

አማኑኤል ከታሰረ ከ42 ቀናት በኋላ በዛሬው ዕለት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ፖሊስ ፍርድ ቤት አቅርቦት የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለሰኔ 11 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ተዋናይ አማኑኤል በተጨማሪም በቅርቡ በፖሊስ ተይዞ ለእስር የበቃው የ"እብደት በሕብረት" ቴአትር አዘጋጅ አንጋፋው ከያኒ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን በአንድ መዝገብ ለፌደራል መደበኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

ጠበቆች ተወክለው በመቅረብ የዋስትና መብታቸው ከዚህ ሁሉ የእስር ቀናት በኃላ እንኩዋን ሊፈቀድላቸው የሚገባ መሆኑን እና እስሩም አግባብነት የሌለው መሆኑ አንስተው ተከራክረዋል።

ሕገ መንግስታዊ እና ስነ ስርአታዊ የሕግ ድንጋጌዎች ተጠቅሶ ሰፊ ክርክር ከተደረገ በኋላ ችሎቱ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች ለሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ ችያለሁ።

Via Yared Shumete
“በትግራይ ክልል የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደተፈጸመ የሚያሳዩ ጠንካራ ማስረጃዎች አሉ”--- ሪፖርት

ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ያደረገ ኒው ላይንስ ኢንስቲትዩት የተባለ ተቋም “የኢትዮጵያ ኃይሎች በትግራይ ጦርነት ወቅት በክልሉ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸማቸውን” የሚያመላክት ጠንካራ ማስረጃዎች ማግኘቱን አዲስ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።

ተቋሙ ማክሰኞ ዕለት ባወጣው ባለ 120 ገጸ ሪፖርት እንዳመላከተው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርትራ መከላከያ ኃይል እና የአማራ ክልል ሚሊሻዎች በትግራይ ተወላጆች ላይ "የጅምላ ግድያ መፈጸማቸውን” የሚያሳይ ማስረጃዎች መኖራቸውን ገልጿል።

ተጨማሪ ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፦ https://wp.me/pfjhHd-1aP

Story via Addis Standard
ከስድስት ቀን በፊት ይህንን ሽልማት ልማደኛው African Leadership Magazine ለጉምሩክ ኮሚሽን አበረከተ፣ አሁን ግን እንደድሮው "እንኳን ደስ አላችሁ፣ ምርጥ ተብለን ተመረጥን"... ወዘተ የለም!

ለምን? እድሜ ለሶሻል ሚድያ የሸላሚው ድርጅት አጭቤነት ስለተጋለጠ።

በነገራችን ላይ ሽልማቱን ተፈላጊ፣ መንግስታዊ እና ወሳኝ ለማስመሰል ስነ-ስርዐቱ ሊደረግ የታሰበው በእንግሊዙ House of Lords አዳራሽ ነው። አዳራሹን ግን ማንም የፈለገ በገንዘብ ሊከራየው ይችላል፣ ሊንክ: https://www.parliament.uk/visiting/venue-hire/lords/venues/

@EliasMeseret
ምልዓተ ጉባኤውን ያካሄደው ቅዱስ ሲኖዶስ ከወራት በፊት ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ጠ/ሚሩን በተመለከተ ያደረጉትን ንግግር "ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና አስተምህሮት ውጭ የሆነ፣ ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው" ብሎ ውሳኔ አሳልፏል

ይህ በጣም ትክክለኛ የሆነ እርምጃ እንደሆነ ይሰማኛል፣ ንግግሩን ከሰማሁት ጀምሮ ከአንድ የሀይማኖት አባት የማይጠበቅ እንደሆነ በግሌ ሳስብ ነበር።

ሲኖዶሱ ንግግሩ ቤተክርስቲያኒቱን የማይወክል፣ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆነ፣ ቅዱስ ሲኖዶስን የማይወክል፣ ለዘመናት ጸንቶ የቆየውን የአባቶች ክብር ዝቅ የሚያደርግ፣ የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ዝቅ የሚያደርግ፣ ከህገ ኦሪትም ሆነ ከቃለ ወንጌል ያፈነገጠ ንግግር እንደሆነ ቅዱስ ገልጿል።

ከዛሬ ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ አህጉረ ስክበት ስህተት እንዳይፈጸም ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉ ያን ሳያደረጉ ቀርተው የተሳሳቱ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ትምህርቶች አውደምህረት ላይ ቢተላለፉ በኃላፊነት እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ መመሪያ እንዲተላለፍ ተወስኗል።

Quote via Tikvah

@EliasMeseret
የ “ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” አስተባባሪ አቶ ዘለሌ ጸጋስላሴ መታሰራቸው ተሰምቷል

በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው እና የ “ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” አስተባባሪ አቶ ዘለሌ ጸጋስላሴ መታሰራቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

ታድያ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው "ኢትዮጵያ እየመከረች ነው" ተብሎ በምክክር ሰላም ለማፅናት ስራ በተጀመረበት ወቅት ነው።

@EliasMeseret
አቶ ታዬ ደንደአ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገር፣ የመንግሥትና የሕዝብን ደኅንነት ማስጠበቅና ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው የሽብር ቡድኖችና የፀረ-ሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ ፕሮፓጋንዳ መልዕክቶችን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሲያስተላልፉ ነበር የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ይታወቃል።

ግለሰቡ የታሰሩት ግን ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ የሀገሪቱን መሪ በፌስቡክ ገፃቸው ሀይለቃል ከተናገሩ አንድ ቀን ቆይቶ ነበር።

ታድያ ስልጣን ላይ እያሉ የሽብር ቡድኖችና የፀረ-ሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ ፕሮፓጋንዳ መልዕክቶችን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሲያስተላልፉ ከነበረ መንግስት ምን ይጠብቅ ነበር?

ጉዳዩን ይፋ ለማረግ ለምን ሀይለቃል ተናግረው እስኪታሰሩ ተጠበቀ?

ይህ በራሱ የክሱን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ አያስገባውም ወይ?

Food for thought...! 

@EliasMeseret
በሰሜን ጎንደር የትግራይ ኃይሎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን አድርቃይ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት 15 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን እና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች እና የአካባቢው አስተዳደር ተናገሩ።

በወረዳው አሊጣራ ቀበሌ አንካቶ በተባለ ጎጥ ማክሰኞ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት “የቡድን መሳሪያ” ታጥቀዋል የተባሉ ከየትግራይ ክልል በኩል የመጡ ናቸው ያሏቸው ኃይሎች ከባድ ጥቃት መፈጸማቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ለትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆነው አካባቢው “በዋልድባ ገዳም” በኩል አድርገው ገብተዋል የተባሉ በመቶዎች የተገመቱ “የትግራይ ኃይሎች” ቤቶችን ማቃጠላቸውን እና ከብቶችን መዝረፋቸውንም የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ከትግራይ በኩል ጥቃት ተፈጽሞበታል ወደ ተባለው “አካባቢ የተደረገ እንቅስቃሴ የለም” ሲል ጥቃቱን አስተባብሏል።

የአካባቢው ነዋሪ በተኛበት የተኩስ እሩምታ እንደተከፈተ በስፍራው ነዋሪ የሆኑት አቶ ታለ ጥላሁን ለቢቢሲ ገልጸው፤ ጥቃቱ ከንጋቱ 11፡00 ጀምሮ እስከ ጠዋት 2፡30 ገደማ መዝለቁን ተናግረዋል።

ጥቃቱ ሲፈጸም “ከተኛንበት በውስጥ ሱሪያችን ነው የወጣነው” ያሉት አቶ ባቡል ፀጋዬ፤ በጥቃቱ አራት ቤተሰቦቻቸው እንደተገደሉባቸው ተናግረዋል።

“በአንድ ቤት አምስት ነበርን፣ ከአምስታችን እኔ ነኝ በአጋጣሚ የተረፍኩት፤ ሌሎቹ ሞቱ። አሰልፈው ነው የተኮሱብን።. . . እኔንም ሞቷል ብለው ነው ትተውኝ የሄዱት። በፈጣሪ ፈቃድ ነው የተረፍኩት” ሲሉ ጥቃቱን የገለጹት ነዋሪው፤ በጥይት ጀርባቸውን ተመተው ሆስፒታል መተኘኛታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በጥቃቱ 15 ሠዎች መገደላቸውን በዐይናቸው እንተመለከቱ የተናገሩት ሌላ እማኝ፤ ሁለት የ16 እና የ19 ዓመት የእህት ልጆቻቸው እንደተገደሉባቸውም ተናግረዋል።

ይህኑ ቁጥር ያረጋገጡት ሌላ ነዋሪ በእሳት እና በጥይት ሦስት ታዳጊዎችን ጨምሮ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸዋል።

“. . .ህጻናትን ጨምሮ 15 ሠዎች መገደላቸውን አይቻለሁ” ያሉት ነዋሪው፤ በጥቃቱ እግራቸውን ሁለት ቦታ ላይ ተመተው መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

የአድርቃይ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ታደሰ በበኩላቸው በጥቃቱ ተገድለው ቀብራቸው መፈጸሙን ማረጋገጥ የቻሉት ስምንት ሰዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከስምንቱ ሟቾች መካከል ስድስቱ ንጹሃን ነዋሪዎች ናቸው ያሉት አስተዳዳሪው፤ ሁለቱ ደግሞ የአካባቢው ሚሊሻ አባላት የነበሩ ናቸው ብለዋል።

Via BBC Amharic

@EliasMeseret
Advertisement!

ኦሪጂናል ስልኮችን በጥሩ ዋጋ ለመግዛት ከፈለጉ ልጠቁምዎት!

G Tech Mobile & Computer Accessories.

🔥SALE🔥

💥የቴሌግራም ቻናሉን በመቀላቀል በጥሩ ዋጋ የቀረቡ ስልኮችን፣ ታብሌቶችን እና ላፕቶፖችን ይመልከቱ፣ ይግዙ።

💥በተጨማሪ ስልኮት ላይ ብር በመጨመር(Exchange )የተሻሉ የቅርብ ምርቶችን መውሰድ ይችላሉ ።
👇👇👇👇
https://hottg.com/GTechMobile
#FactCheck በትናንትናው እለት ወደ አክሱም የበረረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አርማ (livery) ለምን አልነበረውም?

ጉዳዩ በርካታ የተሳሳቱ ግምቶችን፣ ሴራ ትንተናዎችን እና ጥያቄዎችን አስነስቷል፣ እውነታው ግን ይህ ነው:

አየር መንገዱ የቶጎ፣ ማላዊ እና ዛምቢያ አየር መንገዶች ላይ ሼር አለው። እነዚህ አየር መንገዶች አውሮፕላኖቻቸውን ለጥገና ወደ ኢትዮጵያ ሲያመጡ በረራ እንዳይስተጓጎልባቸው እነዚህ ነጭ የተቀቡ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን አርማ ያልያዙ አውሮፕላኖች በምትክነት ይላካሉ፣ ምክንያቱም ራሳቸውን የቻሉ አየር መንገዶች ስለሆኑና የኢትዮጵያ አየር መንገድን አርማ መጠቀም ስለማይችሉ። አየር መንገዱ በዚህ መልኩ በሚያቀርበው አውሮፕላን ጥቅም/ገቢ ያገኛል።

የአየር መንገድ ምንጭ ይህን ለኢትዮጵያ ቼክ ሲያብራሩ "ይህ አውሮፕላን ትናንት በአጋጣሚ በበረራ ስምሪት ክፍል የተመረጠ ነው፣ ለምሳሌ ዛሬ ባለው በረራ እሱ አውሮፕላን ሳይሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አርማ ያለው ወደ አክሱም ይበራል" ብለዋል።

ከአየር መንገዱ እና በረራውን ካስተባበሩ አካላት የተኘው የተረጋገጠ መረጃ እንደሚያሳየው የአየር መንገዱ ይህ ትናንት ወደ አክሱም የበረረ አውሮፕላን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ጥቂት ቦይንግ 737 እና Q-400 (Bombardier) አውሮፕላኖች ነጭ ቀለም ተቀብተው ይገኛሉ።

እውነታው ይኼው ነው።

Story via www.ethiopiacheck.org

@EliasMeseret
ባሳለፍነው ሳምንት ቻይና ዢንጂያንግ ግዛቷ ውስጥ 3.5 ጊጋ ዋት ሀይል ከፀሀይ የሚያመነጭ የአለማችን ግዙፉን የሶላር ፋርም ስታስመርቅ እኛ ደግሞ እየተካሄዱ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶች ውስጥ የሚሳተፉ ወጣቶችን ከብር ሸለቆ በዚሁ ሳምንት አስመርቀናል።

የማዝነው እነዚህ ወጣት ዜጎቻችን የሚፋለሙት ድንበር ለማስከበር እና የውጭ ወራሪ ሀይል ለመመከት ሳይሆን ወንድም ከወንድሙ በሚያደርገው ውጊያ ለመሳተፍ ነው።

#Facts

@EliasMeseret
HTML Embed Code:
2024/06/10 21:34:19
Back to Top