TG Telegram Group Link
Channel: Commercial Bank of Ethiopia - Official
Back to Bottom
#EthioDirect
በኢትዮ-ዳይሬክት ከውጭ ሀገራት የተላከ ገንዘብ አሁኑኑ ይደርሳል!
************
በኢትዮ-ዳይሬክት መተግበሪያ
ሀገር ቤት ላሉ ወዳጅ ዘመዶችዎ
ገንዘብ በነፃ ይላኩ፤
በብርሀን ፍጥነት ለጉዳይ ሳይዘገይ ይደርሳል!

EthioDirect
#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
#CBE #ethiodirect #visa #mastercard #money #transfer #ethiopia

*********
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም App Store በማውረድ አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ500 አባዋራዎች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ፡፡
***************************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ በጅግጅጋ፣ ሐረር እና ሀሮማያ ከተሞች ለሚገኙና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 500 አባዋራዎች ከሰሞኑ የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር አከናውኗል፡፡

ባንኩ በሀሮማያ ከተማ ለ200፣ በሐረር ከተማ ለ150 እንዲሁም በጅግጅጋ ከተማ ለ150 ሰዎች በአጠቃላይ ለ500 አባዋራዎች ነው ማዕድ ያጋራው፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸውን ወገኖች በመለየት የሶስቱም ከተማ አስተዳደሮች በተሳተፉበት በዚህ የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር ለእያንዳንዱ አባዋራ የዱቄትና ዘይት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተከታታይ ዓመታት በተለያዩ አከባቢዎች ዓመት በዓላትንና ልዩ ልዩ ሁነቶችን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብሮችን ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል ይመኛል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጠረ ችግር ምክንያት ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ብር 801.4 ሚሊዮን ገንዘብ ውስጥ 99.13% ወይም ብር 794.43 ሚሊዮን የሚሆነውን ማስመለስ ችሏል፡፡

ቀሪው 0.87% ወይም ብር 6.99 ሚሊዮን ገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚመለስ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በባንኩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ምስላቸው እና ስማቸው ይፋ ተደርጎ የነበሩ ብዛት ያላቸው ግለሰቦች የሚጠበቅባቸውን ገንዘብ ስለከፈሉ እና ቀሪውን ገንዘብ በሌሎች አማራጮች ለማስከፈል ባንኩ እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ መረጃዎቹን ከገፆቹ ላይ አንስቷል።
CBE has recovered 99.13%, or Birr 794.43 million, of the total illegally withdrawn money of Birr 801.4 million in relation to the IT system upgrade incident on March 16, 2024. The remaining 0.87% of the money, or Birr 6.99 million, is expected to be recovered shortly.

All previously posted identities and photographs have been removed from the bank's social media accounts since the majority of the people whose names and images were placed there have paid for the money that was taken inappropriately.
እየቆጠቡ ንያዎትን ያሳኩ፤
ትርፍ ይጋሩ!
ለበይክ ሙዷራባህ የቁጠባ ሂሳብ
======
ሐጅ / ኡምራ የማድረግ ንያዎትን በለበይክ የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት
በመቆጠብ እውን ያድርጉ!

ባንካችን ከለበይክ ወዲዓህ የቁጠባ ሂሳብ በተጨማሪ
ከትርፍ ላይ 70 በመቶ የሚያጋራውን ሙዷራባህ ለበይክ
የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#CBE #cbenoor #interestfree #saving #mudarabah #wadiah #lebbeyk
ለክቡራን ደንበኞቻችን፡
************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በማሻሻል የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት እንዲያግዘው የክቡራን ደንበኞቹን አስተያየት በቀጣይነት በመሰብሰብ ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በቅርንጫፎች አገልግሎት ሲያገኙ እንዲሁም የኤቲኤም (ATM)፣ የፖስ (POS) እና የሲቢኢ ብር (CBE Birr) አገልግሎቶችን ከተጠቀሙ በኋላ ከላይ በምስሉ ላይ እንደተመለከተው ከፅሁፍ ማረጋገጫ መልእክት (SMS) ጋር አገልግሎቶቹን በተመለከተ የደንበኞችን ግብረ መልስ ለመሰብሰብ ወደ ተዘጋጀው መጠይቅ የሚወስድ ማስፈንጠሪያ (link) እንልካለን ፡፡

እርስዎም አገልግሎት ካገኙ በኋላ የሚደርስዎትን ማስፈንጠሪያ /link/ በመጫን እና መጠይቁን በመሙላት አስተያየትዎን እንዲሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ማሳሰቢያ፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስልክ በሚላክ መጠይቅ ምንም አይነት የባንክ መረጃዎንና የሚስጢር ቁጥርዎን አይጠይቅም፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የደስታ እና የጤና ይሁንላችሁ!

ዒድ ሙባረክ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዒድ አል አድሃ (አረፋ) ልዩ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በሚንበር ቴሌቪዥን
**

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያዘጋጀውን የዒድ አል አድሃ (አረፋ) ልዩ የቴሌቪዥን ፕሮግራም እሁድ የበዓሉ ቀን ከቀኑ 11:00 እስከ 12:30 በሚንበር ቴሌቪዥን (MINBER TV) ይከታተሉ።
**
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
HTML Embed Code:
2024/06/15 20:28:02
Back to Top