TG Telegram Group Link
Channel: ብርቅ APPS
Back to Bottom
ሙዚቃ ለምትሞክሩ ሰዎች እሚገርም Application ነዉ ይዘንላቹ የመጣነዉ
Tully ይባላል የሙዚቃ መስሪያ Application ነዉ ይሄ App የተሰራዉ ብዙዎቻቹ ታዉቁታላቹ በJoyner Lucas ነዉ ይሄም App ምንድን ነዉ እሚሰራዉ ብላቹ ከጠየቃቹ ብዙ ነገር ነዉ እሚሰራዉ beat መስራት ትችላላቹ ግጥም መፃፍ ትችላላቹ
ዘፈን መስራት ከምትፈልጉት ሰዉ ጋር አንድ ላይ ባትሆኑ ዜማና ግጥም እየተላላካቹ በዚህ App አሪፍ ሙዚቃ መስራት ትችላላቹ
Joyner ft Logic "Isis" የተሰኘ ሙዚቃቸዉ ለምሳሌ በዚህ Application አማካኝነት ነዉ ምን ያህል ተፅኖ ፈጣሪ እንደሆነ በዚህ ማዉቅ ትችላላቹ
ዘፈን ከሰራቹ በኃላ እዚሁ App ላይ Upload አርጋቹ ከትልልቅ አርቲስቶቹ ጋር ልትተዋወቁ ትችላላቹ ዘፈን ለምስራትም ሆነ ለመፃፍ ፍላጎቱ ያላቹ ሰዎች አሁኑኑ ይሄን App ጭናቹ እራሳችሁን ከአለም ጋር አስተዋዉቁ
ማን ያዉቃል ትልቅ አርቲስት ሆናቹ ይሄን Group የምታመሰግኑት ጊዜ ሊመጣ ይችላል

@berkapps @berkappsbot
🔻Laptop እየጋለ ላስቸገራቹ አሪፍ 🔻
የPc Application ይዘንላቹ መጥተናል
"Smc fan Control" ይባላል በቀላሉ ከGoogle ማግኘት ትችላላቹ Apple (mac) ላላለቹ Window ላላቹ ይሆናል ስራዉ ምንድን ነዉ ብላቹ ለጠየቃቹ የብዙ ላፕቶፖች ችግር መጋል ነዉ ያ ማለት ደሞ ረጅም ሰአት እግራችን ላይ አስቀምጥን ስራ መስራት አንችልም ስለዚህ ይሄ App እሚያረገዉ በDefault ይሰራ የነበረዉን የFan System እኛ Control እንድናረግ ያስችለናል ያም ማለት የPc ፋናችን Maximum Limit እንዲጠቀም አዘን በቀላሉ ላፕቶፓቸንን ማቀዝቀዝ እንቸላለን እንደሚጠቅማቹ ተስፋ አረጋለዉ

@berkapps @berkappsbot
"Trevor Noah" ይለያል አባዬ!🙏

የታዋቂው "Daily Show" አቅራቢ የሆነው "Trevor Noah" በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ፕሮግራሙን ከስቱድዮ ማስተላለፍ ካቆመ ቆይቷል። ለግዜው "The Daily Social Distancing Show" በሚል መርሃ ግብር ከቤቱ ሆኖ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል። "Camera man"ቹ፣ "Floor manager"ቹ፣ "Coordinator'ቹ እና ለፕሮግራሙ መሳካት ከጀርባ ሆነው አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ወደ 25 የሚጠጉ የስራ ባልደረቦቹ ካለክፍያ እረፍት (Unpaid leave) እንዲወጡ ተደርጓል። ነገር ግን "Trevor Noah" እነዚህ ረዳቶቹን ከራሱ ኪስ ለእያንዳንዳቸው ደሞዝ እየከፈለ ነው! ወደ ስቱድዮ ተመልሰው ስራ እስኪጀምሩም ደሞዛቸውን ከራሱ ኪስ መክፈል እንደማያቆም ተናግሯል!

"Born a Crime" በሚል ሰቃይ መፅሃፉ የምናውቀው "Trevor Noah" ከሶስት ወር በፊት አፍሪካ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን ለደሃዎች ለማስገንባት በማሰብ ሁለቱን የዓለም ምርጥ የሜዳ ቴኒስ ፈርጦች "Roger Federer" እና "Rafael Nadal"ን እንዲሁም የዓለማችን ቁጥር 2 ባለ ሃብት የሆነው "Bill gates"ን በማሳመን በደቡብ አፍሪካዊቷ "Cape town" ከተማ የሜዳ ቴኒስ እንዲጫወቱ በማድረግ ከተመልካች 3 ሚልዮን ዶላር ሰብስቦ መስጠቱ ይታወሳል!

"...Life’s most persistent and urgent question is, What are you doing for others?” ይላል "Martin Luther King, Jr."

አሰሪዎቻችሁን እና የቤት አከራዮቻችሁን ቀስ ብላችሁ "share" አድርጉ!😜

@berkapps @berkappsbot
ብርቅ APPS
Photo
"Google"ልን እራሱ "Google" ለምን አታደርግም አባዬ?

እሺ እሱን ተወው እና ለመጀመርያ ግዜ ኢንተርኔት አግኝተህ "Google" ላይ "Search" ያደረከው ነገር ምንድነው?
.
.
.

ለማንኛውም ስለ "Google" እና "Google" ኩባንያ የገረሙኝን እና ብታውቃቸው ይጠቅሙሃል ብዬ ያሰብኳቸውን ነገሮች እንደሚከተለው ቀድጄልሃለሁ!😃

የአሜሪካዋ የቴክኖሎጂ መናገሻ በምትባለው "San Francisco" "Silicon Valley" ውስጥ የሚገኘው "Google" ኩባንያን ለየት የሚያደርገው የቢሮው ሁኔታ እና የሰራተኞቹ የአሰራር መንገድ ነው።

ተቀጣሪዎች "....በዚህ ሰዓት ውጣ፣ በዚህ ሰዓት ግባ ፣ ከዚህ እስከ እዚህ ሰዓት ስራ፣ ፊርማ ፈርም፣ እዚህ ተቀመጥ ፣ ይሄንን አትጠይቅ፣ ይሄንን አትንካ፣ ይሄንን ብቻ ስራ!...." ምናምን መባል የለባቸውም! እንደዚህ አይነት ኃላ ቀር አሰራሮች ለብዙ አመታት ውጤት አላመጡም!፣ ፈጠራን አላበረታቱም!፣ ሰራተኛውንም አሰሪውንም አልጠቀሙም!" ብሎ የሚያምነው የ "Google" ኩባንያ የራሴ አሰራር፣ የራሴ የስራ ፍልስፍና አለኝ ይላል! በዚህም ፍልስፍና እጅግ ውጤታማ ሆኗል!

የመጀመርያው ድርጅቱን ከስራ ቦታ ይልቅ ሁሉም ነገር የተሟላለት መኖርያ ቤት የሚመስልበትን መንገድ ፈጠሩ። የተለመደውን የቢሮ ቅርፅ አስወገዱ! ድርጅቱ ውስጥ የአለቃ እና የሰራተኛ ወንበር የሚባል ነገር የለም። ሁሉም ቢሮ ክፍት ነው። ሁሉም የፈለገበት ቦታ ላይ ተቀምጦ መስራት ይችላል! የግል ንብረት፣ የግል ኮምፒውተር፣ የግል ወንበር ምናምን የለም! ማንም የምንም ነገር ባለቤት አይደለም! ሁሉም ነገር የሁሉም ንብረት ነው።

የሰራተኞቹን የፈጠራ ብቃት ለመጨመር እና አዕምሯቸው የተፍታታ እንዲሆን በማሰብ የሚዝናኑባቸው እንደ ፑል፣ ቴኒስ፣ ጆተኒ፣ ጎልፍ፣ ዲጅታል ጌም መጫወቻዎች፣ መዋኛ ገንዳዎች እና የሙዚቃ መሳርያዎች በየቦታው አሉ። አንድ ሰራተኛ በፈለገበት ሰዓት መጫወት እና መዝናናት ይችላል።

ስራህን ስትሰራ የተሻለ ስሜት እንዲሰማህ ውሻህ ወይም ድመትህን ጭምር ይዘህ መሄድ ትችላለህ። ድርጅቱ ገደብ (Limitation) የሰዎችን የመፍጠር "tendency" ይቀንሳል! ብሎ ያምናል።

ውስጡ 25 ትልልቅ ካፍቴርያዎች እና ሬስቶራንቶች ያሉት "Google" ሰራተኞቹ በፈለጉት አጋጣሚ ያሻቸው ምግብ እንዲቀርብላቸው ያደርጋል። አንድ ሰራተኛ ከ 200 ጫማ (60 ሜትር) በላይ ከምግብ መራቅ የለበትም በሚል ፍልስፍናም ድርጅቱ ያምናል! "የራበው አይሰራም! ሁሉም ነገር የቀረበለት ሰራተኛ ደግሞ ትኩረቱን ወደ ስራ እና ስራ ብቻ ማድረግ ይችላል!" በሚል አመለካከት ያምናሉ።

ሰራተኞቹ አዓምሯቸው ከተወጣጠረ እራሳቸውን ለማፍታታት በቢሮ ውስጥ ማሳጅ የሚደረጉባቸው ክፍሎች እና የሰለጠኑ እና ፍቃድ ያላቸው የማሳጅ ቴራፒስቶች ዝግጁ ሆነው ይጠብቋቸዋል!

ለአካባቢያዊ አየር ጥበቃ ካላቸው ትኩረት የተነሳ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞቹ ከስራ ቦታ ወደ ቤት/ከቤት ወደ ስራ ቦታ የሚመላለሱት የልቀቅ መጠናቸው እጅግ በጣም ዝቅተኛ በሆኑ ባሶች ነው። እያንዳንዱ ሰራተኛ የራሱን መኪና እየነዳ ቢመላለስ በአመት ሊለቀቅ የሚችለውን ከ 20 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ልቀት መቀነስ ተችሏል። ግቢ ውስጥ ሰራተኞች የሚንቀሳቀሱት በሳይክል ነው! ይህም ልቀትን ከመቀነስ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል!

በቅጥር ግቢው የሚበቅለውን ሳር/አረም ለማስወገድ "Google" ማሽኖችን" ሳይሆን "ፍየሎችን" ነው የሚጠቀመው! በየግዜው ፍየሎችን እየተከራየ በግቢው ውስጥ የሚበቅለውን ሳር/አረም እንዲግጡለት ያደርጋል! አንድ ሰራተኛ እየሰራ በአጠገቡ ፍየል ሲያልፍ አይደንቀውም!😃 ሰራተኞቹ እንደውም እነዚህን ፍየሎች ማየታችን የፈጠራ አቅማችንን ጨምሮልናል ይላሉ።

"Google" ዋናው ኩባንያ አጠገብ ለምትገኘው "Mountain View" ለምትባል አነስተኛ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ በነፃ ዋይ ፋይ እንዲያገኙ እና ኢንተርኔትን ያለምንም ገደብ እንዲጠቀሙ አድርጓል።

በድርጅቱ የተቀጠረ ሰራተኛ ህይወቱ ቢያልፍ ሚስት ወይም ባል የሟች 50% ደሞዝን ለ 10 ዓመታት እንዲከፈላት/እንዲከፈለው ይደረጋል።

በአጠቃላይ በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኞች ላፕቶፓቸውን ይዘው ሸርተቴ እና ዥዋዥዌ ሲጫወቱ ማየት ብርቅ አይደለም አባዬ!😃

"Larry page" እና "Sergey Brin" በተባሉ በ "Stanford University" የ "PHD" ተማሪዎች የተመሰረተው "Google" ኩባንያ አሁን ላይ ከ 500 ቢልዮን ዶላር በላይ "worth" የሚያደርግ ሲሆን የዓለማችን "Most Visited website" ነው። የዛሬ 22 ዓመት ሲመሰረት የመጀመርያ ቢሮው የክራይ ጋራዥ ውስጥ ነበር። በወቅቱ በተከራዩት ገራዥ ውስጥ 16 ሰራተኞች ብቻ ነበራቸው! አሁን ላይ በዓለም የተለያዩ 50 ሃገራት 70 ግዙፍ ቢሮዎች እና በ ብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞች አሉት።

የመጨረሻ!

"Google" በመጀመርያ ስፔሊንጉ "Googol" የነበረ ሲሆን መስራቾቹ የድርጅቱን "Domain" ለማስመዝገብ ሲሄዱ በተፈጠረ የስፔሊንግ ስህተት ነው "Google" ተብሎ የቀረው። በነገራችን ላይ በአማካይ በቀን "1 ቢልዮን" ነገሮች "Google" ላይ "Search" ይደረጋሉ።

ደህና እደሩ!

አባዬ! ደግሞ ቢሮ ሄደህ "ለምን ግን የኛ ቢሮ እንደ "Google" አይሆንም?!" ብለህ ጠይቅ አሉህ!😃

I take no responsibility!😜

@berkapps @berkappsbot
ብርቅ APPS
Photo
"......የ 12 ዓመት ልጅ እያለው ቤት ውስጥ የተቀመጠ ሽጉጥ አግንቼ ስጎረጉር ደረቴ ላይ ሳላውቅ ቃታውን ሳብኩት። የጥይቱ ቀለሓ ውስጤ ዘልቆ ገብቶ መሬት ላይ ጣለኝ። በደም ተጥለቀለኩ! በወቅቱ ለፖሊስ ከየት እንደተደወለ ባላውቅም ፖሊሶች መጡ። ከዛም የቤታችንን በር ሰብረው ገቡ። በዛ ለጋ እድሜዬ መሬት ላይ በደም ተጥለቅልቄ ሳለው ፖሊሶቹ በሰውነቴ ላይ እየዘለሉ ቤት ውስጥ ጥይት፣ አደንዛዥ እፅ ወይንም ሌላ ህገ ወጥ ነገር ካለ መፈለግ ጀመሩ። ተመልከቱ! ያንን ሁሉ የሚያደርጉት እራሴ ላይ በስህተት የተኮስኩት ጥይት ሊገድለኝ ጫፍ ላይ ደርሶ ደረቴን በእጄ ይዤ የሲቃ ድምፅ እያሰማው ባለሁበት ሰዓት ነው። በመካከል አንዱ ፖሊስ "ምን እያደረጋችሁ ነው?" ሲል የስራ አጋር ፖሊሶቹን ጠየቃቸው! "....ቤት ውስጥ ህገ ወጥ ነገር ካለ እየፈለግን ነው!...." ብለው መለሱለት!...በጣም ተናዶ እየተሳደበ "...እዚህ ጋር የዚህ ህፃን ልጅ ነብስ ልትወጣ ትንሽ ቀርቷት እናንተ ሌላ ስራ ትሰራላችሁ!? ቶሎ አምቡላንስ ጥሩልኝ!" ብሎ ከመሬት ላይ አፋፍሶኝ በሚፈሰው ደሜ እየተጨመላለቀ ይዞኝ ወጣ! አምቡላንሱ ስለዘገየ ወደ ራሱ መኪና ይዞኝ እሮጠ። ሆስፒታል በር ላይ አይደለም ጥሎኝ የሄደው! ውስጥ አስገብቶኝ ለሰዓታት ዶክተሮቹ ቀዶ ጥገና አድርገው እስኪጨርሱ ጠብቆ መትረፌን አረጋግጧል! እሱን ብቻ አይደለም ያደረገው! ያንን ሁሉ ሰዓት ጠብቆ የተኛሁበት ክፍል መጥቶ ደስ በሚል ፈገግታ "አይዞህ አትጨነቅ ቦብ እባላለሁ! ከፈለክ አጎቴ ቦብ ልትለኝ ትችላለህ!" አለኝ! ይህ ህይወቴን ያተረፈው እና ይህንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለልኝ ሰውዬ ነጭ ፖሊስ ነው። እንደውም ከበረዶ ይነጣል! እራሴ ላይ ጥይት ተኩሼ በሬሳዬ ላይ እየዘለሉ ሌላ ነገር ቤት ውስጥ በወቅቱ ሲፈልጉ የነበሩት ፖሊሶች ደግሞ ጥቁሮች ናቸው። ከኔ በላይ እንደውም ሳይጠቁሩ አይቀሩም! ህይወቴን የታደገው እና ለዚህ ሁሉ ዝና እና ክብር እንድበቃ ያደረገኝ አመንክም አላመንክም ነጭ ፖሊስ ነው! ለኔ ዘረኝነት ምን እንደሆነ አላውቅም! አንድ ነገር ግን አውቃለው! አጎቴ ቦብን!....አሁን ላይ እኔ ሃብታም ነኝ! ሁሉም ነገር አለኝ! በተለያየ ግዜ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ላደርግለት ቃል ገብቼለታሁ። እንደ ቤተሰብ ነን! እሱ ግን ከኔ ምንም አይነት እርዳታ አይፈልግም! ብዙ ግዜ ብር ልስጥህ ስለው "አይሆንም ስራ አለኝ!" ብሎ ይቆጣኛል! አሁን ላይ እድሜው ገፍቶ ጡረታ ወጥቷል!...."እሺ አሁን እንኳን በዚህ ሰዓት ልርዳህ! ምንድነው የምትፈልገው? ቤት፣ መኪና፣ ገንዘብ???" ስለው "ምንም አልፈልግም! ባይሆን ቀለል ያለ ስራ ፈልግልኝ!" ነው የሚለኝ!...."

ታዋቂው ጥቁር አሜሪካዊ ራፐር፣ ሙዚቀኛ፣ ፕሮዲውሰር እና ስራ ፈጣሪ "Dwayne Michael Carter Jr./Lil Wayne" ካደረገው አንድ ቃለ መጠይቅ እና "BET" የተሰኘ የሽልማት መድረክ ላይ በ 2018 ከተናገረው የተወሰደ!

ምን ልልህ መሰለህ አባዬ!

የሰዎች የቆዳ ቀለም ነጭ፣ ጥቁር ወይም ቢጫ ስለሆነ ወይም ስለተመሳሰለ አንድ ሊገልፃቸው የሚችል የጋራ ባህሪ ወይም ልጥፍ ስም ሊኖራቸው አይገባም! ሁሉም ነጭ "ሰው" ነው! ሁሉም ነጭ ግን ዘረኛ አይደለም! ሁሉም ነጭ ለጥቁር መጥፎ አመለካከት ሊኖረው አይችልም! ሁሉም ነጭ ፖሊስ የጥቁር አንገት ላይ 9 ደቂቃ ቆሞ ይገላል ማለት አይደለም! ሁሉም ነጭ የበላይ ነኝ ብሎ ያስባል ማለት አይደለም! አንድ ነጭ ሰው ከሌላው ነጭ ሰው ጋር የቆዳ ቀለም ሊጋራ ይችላል። ነገር ግን እምነት፣ አመለካከት፣ እሳቤ፣ የስነ ልቦና ውቅር ወይም የህይወት ፍልስፍናን ሙሉ ለሙሉ ይጋራል ማለት ግን አይደለም! ጥቁር ለጥቁርም እንደዛው!

መልካም ምሽት!😀
@berkapps @berkappsbot
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ፓስፖርት ለማሰደስ እና አዲስ አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ:-


❶. አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት
- ❖ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
- ❖ የልደት ካርድ
- ❖ ስልክ ቁጥር

❷. ለማሳደስ
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ ፓስፖርት ኮፒ
-❖ ስልክ ቁጥር

❸. የጠፋ / የተሰረቀ ለማውጣት
-❖ የቀበሌ መታወቂያ
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ የፖሊስ ማስረጃ ደብዳቤ
-❖ ስልክ ቁጥር

❹. ከ18 ዓመት በታች
-❖ የወላጅ መታወቂያ
-❖ የልጅ የልደት ካርድ
-❖ ስልክ ቁጥር

❺. እድሜ ለማስተካከል
-❖ የልደት ካርድ
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ ፓስፖርት ኮፒ
-❖ ስልክ ቁጥር

❻. ስም ለመቀየር ውይም ለማስተካከል
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ ፓስፖርት ኮፒ
-❖ የፍርድ ቤት ወረቀት
-❖ ስልክ ቁጥር

ለበለጠ መረጃ:-
▫️+251919723884 ይደውሉ።

@berkappsbot
Notcoin ከቴሌግራም የተበረከተ Digital Coin ነው! በቅርቡም ቴሌግራም ለማስታወቂያ የሚከፍለው በTON እና Notcoin ይሆናል። አሁን በነጻ ማግኘት ይቻላል። ይሄን ቦት መክፈት እና Tap Tap ማድረግ ብቻ!! 👇👇👇👇👇 10 Million notcoin እስከ April 1 ድረስ መድረስ አለባችሁ ይፍጠኑ


https://hottg.com/notcoin_bot?start=r_573809_30705612
🎁 +2.5k Notcoin as a first-time gift
🎁🎁🎁 +50k Notcoin if you have Telegram Premium
ሰበር ኖትኮይን 🌟💎
አዲስ TAPswap የተሰኘ አዲስ ኮይን የመጣ ሲሆን በዚ ሊንክ ታገኙታላቹ

https://hottg.com/tapswap_bot?start=r_281543678
🎁 +2.5k Shares as a first-time gift

ገና ከመጀመሩ በአንድ ደቂቃ ውስጥ 22,000 ሰው ነው የተቀላቀለው 😱
HTML Embed Code:
2024/04/18 09:26:24
Back to Top