TG Telegram Group Link
Channel: የሕይወት መንገድ
Back to Bottom
ማታ ስንተኛ ህልም እያየን ተቸገርን በሰላም መተኛት አቃተን ላላቹ መፍትሄው ይኸው
፦ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ፀሎት በእንተ ማዕሰሩ ለጋኔን ወማዕሰሮሙ ለአገጋንንት አዊን ጋዴን አዮስ ሜሎስ ኢራኤል ግራኤል በተናዊ ቀተናዊ አዮን ኢራን ራፎን ራኮን አውካኤል ብርሱባሔል በስመ እግዚአብሔር ማዕሰሩ ለጋኔል አስማተ እግዚአብሔር በዕሉ ቃላቲከ አድህነኒ ለገብርከ (ለአመትከ) እገሌ................
_____ [አቡነ ዘበሰማያት]_____
አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ፣
ትምጻእ መንግሥትከ ፣ወይኩን ፈቃድከ ፣
በከመ በሰማይ ፣ከማሁ በምድር፣
ሲሳየነ፣ዘለለ ዕለትነ፣ሃበነ ዮም።
ኅድግ ለነ፣አበሳነ ወጌጋየነ፣
ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ።
ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት፣
ኣላ አድኅነነ ወባልሐነ፣እምኩሉ እኩይ፣
እስመ ዚኣከ፣ይእቲ መንግሥት፣ኃይል ወስብሐት፣
ለዓለመ ዓለም፣አሜን።

በሰላመ፣ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ፣
ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፣
ድንግል ብኅሊናኪ ፣ወድንግል በሥጋኪ።
እመ እግዚአብሔር ጸባዖት ሰላም ለኪ።
ቡርክት አንቲ እምአንስት፣ ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ።
ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ እግዚአብሔር
ምስሌኪ።
ሰአሊ ወጸልዪ ምሕረት በእንቲኣነ፣
ኀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ፣
ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።

_______[ ጸሎተ ኪዳን] _____

ይበል ካህን :- ቅዱስ
ይበሉ ህዝብ :- እግዚአብሔር ቅዱስ ኃይል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት
ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ::

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል::
ተሣለነ እግዚኦ::

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን እመ ሣልስት ዕለተ ዐረገ በስበሐት ውስተ ሰማይ ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስበሐት ይኲነነ ሕያዋን ወሙታነ ተሣለነ እግዚኦ: :

ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ። ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለአለም አለም አሜን ወአሜን ለይኩን ለይኩን ።

ቅዱስ ሥሉስ እግዚአብሔር
ሕያው ተሣለነ ::

_______[ ስብሐት ] _______

ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት
ለመንፈስ ቅዱስ (ሰለስተ ግዜ በል።)
ስብሐት ለእግዘትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ
አምላክ፡
ስብሐት ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ክርስቶስ በምሕረቱ ይዘከረነ።
አመ ዳግም ምጽአቱ ኢያስተኅፍረነ።
ለሰብሖተ ስሙ ያንቅሀነ
ወበአምልኮቱ ያጽንአነ
እግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
አዕርጊ ጸሎተነ፣
ወአስተሥርዪ ኩሎ ኃጢአተነ
ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ
ለዘአብልዐነ ዘንተ ኅብስተ
ወለዘአስተየነዘንተ ጽዋዓ
ወለዘሠርዐ ለነ ሲሳየነ ወአራዘነ
ወለዘተዐገሠ ለነ ኵሎ ኃጢአተነ
ወለዘወሀበነሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ
ወለዘአብጽሐነእስከ ዛቲ ሰዓት።
ነሀብ ሎቱ ስብሐተ ወአኰቴተ ለእግዚአብሔር
ልዑል
ወለወላዲቱ ድንግል። ወለመስቀሉ ክቡር
ይትአኰት ወይሰባሕ ስሙ ለእግዚአብሔር ወትረ
ብኵሉ ጊዜ ወበኵሉ ሰዓት።
+ የአያቶች ቀን +

እናትነት ጸጋ ነው:: አባትነትም ደስታ ነው:: ከሁለቱ በላይ ደግሞ አያት መሆን ይበልጣል:: ልጅን ከማየት የበለጠ የልጅ ልጅን የማየት ደስታ እጅግ ትልቅ ነው:: እናት ለልጅዋ ከምታሳየው ፍቅር የአያት ፍቅር የሚበልጠው በአያት እጅ ያደጉ ልጆች ስስትና እንክብካቤ የሚበዛባቸው ለዚህ ነው:: ወላጆች የሚቆጡት ልጅ አያት ሥር የሚደበቀው ለዚህ ነው::

የአባቶችና የእናቶች ቀን እንደሚታሰበው ሁሉ አብልጦ ሊታሰብ የሚገባው የአያቶች ቀን ነው:: ዕድሜ ቢጫናቸው እንኳን ለልጅ ልጆቻቸው ፈገግታቸው የማይደበዝዝ በዕድሜያቸው ፀሐይ መጥለቂያ ሳይደክማቸው ፍቅር የሚሠጡ የፍቅር ጥግ ማሳያዎች አያቶች ናቸው::

ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የአያቶች ቀን በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው:: በምድር ካሉ አያቶች ሁሉ የሚበልጡት አያቶች ቅድስት ሃና እና ቅዱስ ኢያቄም የሚታሰቡበትክብረ በዓል ነው:: ድንግል ማርያም ከእናቶች ሁሉ እንደምትበልጥ ወላጆችዋም ከአያቶች ሁሉ ይበልጣሉ:: እርስዋን የአምላክ እናት ብለን እንደምናከብር እነርሱንም የአምላክ አያቶች ብለን እናከብራቸዋለን::
በመለኮቱ አባት እንጂ አያት ለሌለው ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ አያቶቹ የሆኑ ሃና እና ኢያቄም እጅ ክቡራን ናቸው::

ሃና ሰማይን ወለደች ልጅዋ ፀሐይን ወለደች:: ሃና ምንጭን ወለደች ልጅዋ የሕይወትን ውኃ ወለደች:: በጌታ የዘር ሐረግ ውስጥ የተቆጠሩ ሁሉ ክቡራን ናቸው የመጨረሻዎቹ አያቶቹ ደግሞ የመጨረሻው ክብር ይገባቸዋል::

ሃና እና ኢያቄም የልጅ ልጄ የሚሉት ፈጣሪያቸውን ነው:: እርግጥ ነው በሕይወት ቆይተው ቀድሞ በሕልም አይተው ያልተረዱትን የልጃቸውን ልጅ ክርስቶስን አቅፈው ለመሳም አልታደሉም:: ሆኖም ድል አድራጊው የልጅ ልጃቸው የሲኦልን መዝጊያ ሰብሮ ነፍሳትን ሲያወጣ አያቶቹንም አውጥቶአቸዋልና ልጃቸው የወለደችውን ፀሐይ በሲኦል ሲያበራ አይተው ሕልማቸው ተፈትቶአል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 11 2013 ዓ.ም.
ድሬዳዋ ኢትዮጵያ
ተማሪዎች ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ምን ብለው ይጸልዩ?

የግብፅ ቤተክርስቲያን በቅርቡ ማዕረገ ቅድስና የሠጠቻቸው ቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡

ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡

+++ ጸሎት +++

‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ

‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!

አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡

ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡

ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"

ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን!

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
#አስሩ_ቆንጃጅት

ማቴ 25 :1-13
ከአስሩ፡ደናግል #አምስቱ_ልባሞች አምስቱ ሰነፎች፡ነበሩ።
ልባምቹ ዘይት ሞልተው መብራታቸውን አብርተው የሙሽራውን መምጣት ይጠባበቁ፡ነበር ።

'---#አምስቱ ሰነፎች ግን፡ማሰሮ፡አላቸው መብራትም አብርተዋል በማሰቶቸው ላይ ዘይት አልበራቸውም መብርት ሊበራ የሚችለው ዘይት፡ሲጨመርበት ነው። ያለ ዘይት መብራትአይችልም፡በዚህ፡ሁኔታላይ፡ሆነው ሙሽራው፡መጣ ትቀበሉ ዘንድ ውጡ የሚል የሁካታ፡ድምጽ ሆነ ።
በዚህን ሰአት አስሩም ተነሱ አምስቱ መብራታቸውን አብርተው ዘይታቸውንበማሰሮቸው ሞልተው ሙሽራውን ለመቀበል ተሰለፉ፡#አምስቱ ሰንፎች ግን ማሰሮቸው ባዶ፡ነበር ።ዘይት አልነበረውም መብራታቸውን አላበሩም፡ለመቀበል፡ብቁ አልሆኑም ዘይት ስለሌላቸው ማለት ነው።
#ስለዚህ መብራታቸው ጠፋባቸው ወደ፡አምስቱ፡ልባሞች ሄደው እባካችሁ ከዘይታችሁ ስጡን ሲሎቸው የኛ ዘይት ለእናንተ ስለማይሆን፡ወደ፡ሚሸጡበት ሄዱ፡አላቸው እነሱም ሊገዙ ሄዱ ።
አምስቱ ደናግል ሙሽራውን ይዘው፡ወደ ስርጉ ቤት ገቡ የሰርጉ ቤትም፡ተዘጋ እነዛ ሊገዙ፡የሄዱት ሰነፎች የሚሸጥላቸው አጥተው፡ሲመልሱ በሩ ተዘግቶ ሙሽራው ገብቶ ጠበቃቸው።
የማቴ ምዕ. 25 ፣11በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና። ጌታ ሆይ ጌታ ሆይክፈትልን አሉ።

12፤ እርሱ ግን መልሶ። እውነት እላችኋለሁ አላውቃችሁም አለ።
ይህ ትምህርት፡ክርስቶስ፡ስለመምጣቱ በምሳሌ ያስተማረው ትምህርት ነው፡።
#ሙሽራው የተባለው ክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ነው፥
አሁን የምንጠብቀው *ሙሽራውን፡ኢየሱስ፡ክርስቶስን፡ነው* ስለዚህ መልካም ስራችንን ሁሉ የምንጀምርበት፡ነው።እነዚህ አምስቱ ደናግል በማሰሮቸው ዘይት የያዙት *ማሰሮ የተባለው ህይወት፡ነው*
*ዘይት የተባለው ፍቅር፡ነው*
*መብራት የተባለው ሀይማኖት፡ነው።*

እነዚህ፡ሰዎች እምነታቸውን፡በስራ ገልጠው ሙሽራውን፡ክርስቶስን በመቀበላቸው ከሙሽራው፡ከክርስቶስ ጋር በመንግስተ ሰማያት ገብተዋል። እኛም ሙሽራችን ክርስቶስ ወደ ገባበት ወደ መንግስተ ሰማያት፡መግባት የምንችለው በማሰሮችን ዘይት ሞልተን መብራታችንን አብርተን እውነተኛውን ሙሽራ ክርስቶስን ስናምን፡እና ክርስቶስ ስሩ ያለንን ስንሰራ፡እና ትዛዛቱን ስንጠብቅ ነው።
#ሰነፎቹ ዘይት፡ስላልነበራቸው መብራታቸው ጠፍቶባቸው ከሰርግ፡ቤቱ፡ውጭ ሆነዋል ቀርተዋል እምነታቸውን በስራ ስላልገለጹ፡ሙሻራውን መቀበል ስላልቻሉ፡ከውጭ ቀርተዋል ስለዚህ እኛም፡ሙሽራውን ለመቀበል በማሰሮችን፡ዘይት ያስፈልገናል ማለት ነው ይህም፡እምነት ምግባር፡ፍቅር ሀይማኖት ጠብቀንና፡ተዘጋጅተን፡ስንጠብቅ፡፡ከሙሽራው ጋር መንግስተ ሰማያት እንገባለን ።አምላካችን እግዚአብሔር ይህንን፡እንድናደርግ ፈቃዱ ይሁንልን

ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 25:13)
[ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።"
(የማቴዎስ ወንጌል 24:44)
[0" በጽድቅ ንቁ ኃጢአትንም አትሥሩ
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:34)
=========== #ሰውነትሽን #ለባልሽ #ብቻ ==========

👉👉#ምክር_ለወጣት_ሴቶች👈👈

ሁለት ወጣት ሴቶች የሰውነታቸውን ክፍል አጋልጦ የሚያሳይ ልብስ ለብሰው ወደ አንድ ስብሰባ ደረሱ፡፡
የስብሰባው መሪ በደንብ ካያቸው በኋላ እንዲቀመጡ አደረገ፡፡ ከዛ በኋላ የተናገራቸው ንግግር ምናልባት በህይወት ዘመናቸው ሙሉ የማይረሱትን ንግግር ነው፡፡
አይን አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው
"እናንተ ሴቶች እግዚአብሄር በምድር ላይ የፈጠራቸው ውድ ነገሮች በሙሉ በደንብ የተሸፈኑና ለማየትም ሆነ ለማግኘት የሚከብዱና ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው፡፡

👉አልማዝ የት ነው ምታገኙት? በመሬት ጥልቅ ውስጥ! ተሸፍኖና ተጠብቆ

👉ዕንቁ የት ነው ምታገኙት በውቅያኖስ የታችኛው ጥልቅ ክፍል ውስጥ!

👉ወርቅንስ ከየት ነው ምታገኙት? ወደታች ብዙ ቆፍራችሁ፣ በአለቶች ተሸፍኖ ነው! እሱን ለማግኘት ብዙ መልፋት አለባችሁ"

ኮስተር ብሎ አያቸውና ንግግሩን ቀጠለ
"ሰውነታችሁ ውድና እና ልዩ ነው፡፡
ከወርቅ ከአልማዝና ከዕንቁ ሁሉ ይልቅ እጅግ ውድ ነው፡፡ ስለዚህ እናንተም መሸፈን አለባችሁ፡፡

የከበረውን ማዕድናችሁን እንደ ወርቅና አልማዝ በደንብ ከደበቃችሁት የማዕድን አውጪ ድርጅቶች ከአስፈላጊ ማሽኖች ጋር #በጨረታ ተወዳድረው የአመታት ፍለጋ ለመድረግ ይሰለፋሉ፡፡

በመጀመሪያ መንግስታችሁን (#ቤተሰባችሁን) ይጠይቃሉ፡፡ ከዛም ሙያዊ ኮንትራት ይፈርማሉ(#ሰርግ) በመቀጠል በሙያቸው መሠረት ማዕድን የማውጣቱን ስራ ይቀጥላሉ(ህጋዊ #ትዳር)

ነገርግን ውዱን ማዕድናችሁን ካልሸፈናችሁትና በግልጥ ካስቀመጣችሁት ማንም ህገወጥ ማዕድን አውጪ መጥቶ በማይረባ መሳሪያ ነካክቶ እንደ ጠጠር በቀላሉ ይወስድበችኋል፡፡

#ሰውነታችሁ_እንቁ_ነውና_ደብቁት

ወንድሞች እህቶቻችሁን ፣ ባሎች ሚስቶቻችሁን ፣ እናም ወላጆችም ሴት ልጆቻችሁን መልካም አለባበስ እንዲለብሱ እበረታቷቸው
ስለ ጥፍር ቀለም፣ቅንድብ መቀንደብ.... ልጠይቃችሁት ጥያቄ👇👇👇👇👇
መጽሐፈ ሄኖክ 2:18 ኣዛዝዔልም ለሰዎች ሾተልና ሰይፍ መሥ ራትን ጋሻ መሰጐድንም ጥሩር መሥራትንም አስተማራቸው።
፲፱
19 ከነሱ በታች የሚሆኑ ሥራቸውንም ሌላ ጌጸና አምባሮችን ቅንድብ መሸለልንና ዓይን መኳልን ከተመረጠና ከከበረ ዕንቁ ሁሉ የሚበልጥ ዕንቁንም እንሶስላ መሞቅን ሁሉ የዓለምንም ለውጥ ኣሳይዋቸው

20 ጽኑ በደል ብዙ ሰሰንም ተደረገ ፣ ሳቱ ሰሰኑ ሥራቸውም ሁሉ ጠፋ።
፳፩
21 አሚዛራክ ጋኔን መሳብን ምታት ማሳየ ትን ሥር መማስን ቅጠል መበጠስንም ሁሉ አስተማረ አርማሮስም ጋኔን መሳብን አስተማረ።
፳፪
22 በረቅእልም ኮከብ መቁጠርን አስተማረ።
፳፫
23 ኮከብኤልም ምልክት ማሳየትን ኣስተማረ።
፳፬
24 ጥሞኤልም ኮከብ መቁጠርን አስተማረ።
፳፭
25 ኣስሪድኤልም የጨረቃን አካሄድ ኣስተ ማረ።
፳፮
26 በሰዎችም ጥፋት ሰዎች ጮሁ ቃላቸውም ወደ ሰማይ ደረሰ።
Forwarded from Deleted Account
🔵ትልቁ ኃይል- አእምሮ


በእድሜ የገፉ ገበሬ አባት በእስር ቤት ለሚገኝ ልጃቸው ደብዳቤን ይፅፋሉ። "ልጄ፥ ያው በዚህ ዓመት ድንችና ቲማቲም መትከል አልችልም ምክንያቱም ማሳውን የማረስ አቅም ስለሌለኝ፤ አንተ ግን እዚህ ሆነህ ቢሆን ኖሮ ልትረዳኝ እንደምትችል አውቃለሁ"።

ልጅም ለአባቱ መለሰ፦ "አባቴ ሆይ፥ ማሳውን ለማረስ ፈጽሞውኑ እንዳታስብ ምክንያቱም የሰረቅሁትን ገንዘብ በዛ ስፍራ ቀብሬዋለሁና!"።

ታዲያ የእስር ቤቱ አለቃና ፓሊሶች ልጅና አባት የሚመላለሱትን ደብዳቤ ቀድመው አንብበውት ኖሮ በጧት ተነስተው ወደ ስፍራው በማቅናት ገንዘቡን ለማግኘት ከዳር እስከ ዳር ማሳውን ቆፈሩ፤ ነገር ግን ምንም አይነት ነገር ሊያገኙ አልቻሉም።

በቀጣዩ ቀንም ልጅ ለአባቱ በድጋሚ ደብዳቤን ጻፈ፦ "አባቴ፣ አሁን ድንችና ቲማቲሙን መትከል ትችላለህ፤ ከዚህ ሆኜ ላደርግልህ የምችለው ትልቁ ነገር ይህንን ነው"።

አባትም መለሱ፦ "ሃ.ሃ.ሃ ልጄ ሆይ፥ በርግጥም ብርቱ መሆንህን አውቃለሁ፣ ይኸው በእስር ቤት ሆነህ እንኳን እኔን እንዲያገለግሉኝ ፓሊሶችን ታዛለህ፤ የእስር ቤቱ አለቃና ጀሌዎቹ አካፋና ዶማ ይዘው ማሳውን ሲቆፍሩ በማየቴ ተገርሜአለሁ። የመኸር ጊዜ ምርቱን ለመሰብሰብ ስፈልግ ደግሞ እፅፍልሃለሁ"።

ልብ በል፤

• ሰዎችና ሁኔታዎች አካልህን ያስሩ ይሆናል፤ አእምሮህን ግን ፈጽሞ ሊያስሩ አይችሉም።

• አእምሮህ ታስሮ ከሆነ ግን እንዲለቅህ ራስህን ጠይቀው፤ ያለፈቃድህ አእምሮህን ማሰር የሚችል ኃይል የለምና።

• ጥንካሬ ከሚታየውና ከሚታሰረው አካልህ አይመጣም፤ ከማይታየውና ከማይበገረው አእምሮህ እንጂ።

ትልቁን ኃይል፣ አእምሮህን ያለመሰሰት ሁልጊዜም ተጠቀምበት!
enquane aderesachew
HTML Embed Code:
2024/04/20 05:09:04
Back to Top