TG Telegram Group Link
Channel: Azig Habesha™
Back to Bottom
https://100seconds.et/join/2df7be0e-d7e0-4c01-9b72-e30ea9ab8b2f
Hey Friend! Help me get my free credits by joining me in the 100 Seconds competition. Click the link and subscribe. You will also enjoy answering 10 questions and win!
Forwarded from Mela Muziqa 1000 Giveaway
መላ ሙዚቃ አዳዲስ አማረኛ የሙዚቃ ክሊፖች በየሳምንቱ ወደ ዉድ የኢትዮጵያ ህዝቦች ማድረስ ጀምሯል።

https://youtube.com/@melamuziqavevo5875

ቶሎ ሰብስክራይብ በማድረግ ቀዳሚ ተምልካች ሁኑ።

በቴሌግራም ቻናላችን አሪፍ ሽልማቶችም መስጠት ጀምረናል።#Kidusafrica
@melamuziqarecords

Join us!!
Forwarded from የ1990ዎቹ ሙዚቃ አድናቂዎች (K i d u s . A f r i k a)
የድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ ይወጣል !

በዘመን አይሽሬ ድምጿ እና ከመድረክ አያያዟ በተጨማሪ በራሷ ተወዳጅ ግጥምና ዜማዎቿ የምትታወቀው ተወዳጇ ድምጻዊት አስቴር አወቀ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበም የጥምቀት ዋዜማ እንደሚወጣ ሰዋሰው መልቲሚድያ አስታውቋል፡፡

በያዝነው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ለሕዝብ የተዋወቀው እና ከመቶ በላይ አንጋፋና ወጣት ተወዳጅ ድምጻዊያንን በጋራ ለመስራት ያስፈረመው ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ፤ አስር የሙዚቃ ስራዎችን ያካተተው የድምጻዊቷ “ሶባ” የተሰኘ አዲስ አልበምን የጥምቀት ዋዜማ በሰዋሰው መተግበሪያ በኩል ለአድማጮች ያደርሳል ተብሏል፡፡

ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ/ም ድምጻዊ አስቴር አወቀ ከሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጋር ስትፈራረም የሰዋሰው የማኔጅመንት አባላት ድምጻዊ አስቴር አወቀ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ድምጻዊት አስቴር አወቀ ከዚህ በፊት ሃያ አራት የሚደርሱ ዘመን አይሽሬ ተወዳጅ የሙዚቃ አልበሞችን እና ሁለት ነጠላ ዘፈኖችን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ያደረሰች ሲሆን “ሶባ” ሃያ አምስተኛ አልበሟ ነው፡፡

ድምጻዊቷ ከሃገር ውስጥም በተጨማሪ በታላላቅ ዓለማቀፍ መድረኮች ስራዎቿን በማቅረብ ከፍተኛ አድናቆትን በማግኘት ኢትዮጵያዊቷ የሶል ሙዚቃ ንግስት በመባልም ትታወቃለች፡፡
ሰዋሰው መልቲ ሚድያ ጥበበኞች የሚገባቸውን የፈጠራ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ የሃገራችን ጥበብ ባህር ማዶ ተሸጋሪ እንዲሆን ለማስቻል በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የተቋቋመ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡@oldsongs90th
@Oldsongsgroup
Og is back show some love
Follow
Hh
HTML Embed Code:
2024/04/19 14:37:09
Back to Top