TG Telegram Group Link
Channel: P H O E N I X B A T C H 2 k 1 2
Back to Bottom
"...የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዴት በምርጫው ይሳተፉ በሚለው መንገድ ላይ የተወሰነ ነገር የለም" - የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለ @tikvahuniversity

ከቅድመ ምረቃ ጀምሮ በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች እንዴት በምርጫው የሚሳተፉበት መንገድ ላይ በሚለው ጉዳይ ላይ የተወሰነ ነገር አለመኖሩን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለ @tikvahuniversity ገልጿል።

በጉዳዩ ላይ ውሳኔውን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ/መግለጫም እንደሚሰጥ ነው የገለፀልን።

በሌላ በኩል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅሬታ ማቅረቢያ ግዜ ዛሬ ማብቃቱን አሳውቋል።

ቅሬታዎችን ዛሬም ሲቀበል መዋሉን የገለፀው ሚኒስቴሩ ፤ ከዛሬ በኋላ ምንም አይነት ቅሬታ እንደማይቀበል ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያላቸውን ቅሬታ በድረ ገጽ፣ በኢ-ሜይል እና በስልክ ላለፋት አምስት ቀናት ለሚኒስቴሩ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#MoSHE

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት የምርምር፤ አፕላይድ ሳይንስ፣ ኮምፕሬሄንሲቭ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ቴክኒካል በሚል ከለያቸው ውስጥ የትኞቹ የቅድመ ምዘና ፈተና ይሰጣሉ ?

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በመባል ከተለዩት ፦
- ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
- ከኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ውጪ ምንም አይነት የቅድመ ምዘና ፈተና እንደማይሰጥ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለ @tikvahuniversity ገልጿል።

ሚኒስቴሩ አሁን ላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ እንደሚገቡ ነው የገለፀው፤ ሆኖም የመጀመሪያ ዓመት (freshman) ትምህርታቸውን አጠናቀው የትምህርት ክፍል ምርጫ ሲያደርጉ የምዘና ፈተና ሊወስዱ እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

በተጨማሪ መረጃ ፦ የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መኩሪያ ንጋቱ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና እንደሚሰጥ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጠዋል።

"የምንሰጠው ስልጠና 50 በመቶው የተግባር ስልጠና በመሆኑ ብዙ ተማሪዎችን መቀበል አንችልም" ያሉት ኃላፊው፤ ስልጠናው ብዙ ሰርቶ ማሳያ ማዕከላና ከፍተኛ ሃብት እንደሚጠይቅ ነው የገለፁት።

#CARD #TikvahUniversity

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#BREAKING

6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ቀን እንደማይካሄድ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ይህ ያሳወቀው ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየመከረ ባለበት መድረክ ላይ ነው።

ምርጫው ግንቦት 28 ይካሄዳል ተብሎ ነበር።

የምርጫ ካርድ ምዝገባውና ሌሎች ስራዎች በተያዘላቸው ቀናት ባለመጠናቀቃቸው ምርጫው በተያዘለት ቀን አይካሄድም ተብሏል።

ምርጫ ቦርድ ድምጽ መስጫው ቀን በ3 ሳምንት እንዲራዘም ፓርቲዎችን መጠየቁን አል ዓይን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
"በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም በትምህርት ገበታቸው ይቆያሉ"፦ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም ባሉበት እንደሚቆዩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለ @tikvahuniversity አሳውቋል።

የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አመለወርቅ ህዝቄል እስከዛ ባለው ጊዜ ምርጫው የሚደረግበትን ቀን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል ብለዋል።

ምርጫው በማይካሄድባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ጉዳይ ላይም በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጥ ኃላፊዋ ገልፀዋል።

ትምህርት የሚጀምርበትን ወቅት ለመወሰን ወጥ የሆነ የጊዜ መርሀ ግብር ያስፈልጋል ያሉት ኃላፊዋ ፤ ሚኒስቴሩ እስከ መጪው አርብ የተደረሱ ውሳኔዎችን እንደሚያሳውቅ ለቲክቫህ ገልፀዋል።

https://hottg.com/+RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር በበይነ መረብ ባደረገው ውይይት ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ?

ውይይቱ የነባር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምርጫ ወቅት ቆይታና የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ቅበላን የተመለከቱ ጉዳዮች ተነስተውበታል፡፡

የመጪው ምርጫ ቀን ሊራዘም እንደሚችል ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለፁን ተከትሎ የተማሪዎችን ቆይታ በተመለከተ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ወጥ የሆነ መመሪያ መከተል ያስፈልጋል ተብሏል።

በመሆኑም በቅርቡ በበይነመረብ አማካይነት ስብሰባ በማካሄድ ግልጽ መመሪያዎች ይፋ እንደሚደረጉ ተነስቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም ድረስ የመማር ማስተማር ሥራቸውን እንዲቀጥሉም አቅጣጫ ተቀምጧል።

ተማሪዎች በምርጫ ወቅት የት መሆን እንዳለባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በማኔጅመንት ካውንስል በመወያየት የውሳኔ ሀሳቦቻቸውን በአጭር ጊዜ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲልኩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

በምርጫው ዩኒቨርሲቲዎች ከፖለቲካ ጉዳዮች ገለልተኛ በመሆን ሰላም የሚያሰፍኑ ጉዳዮችን በማንሳትና የዕውቀት ክፍተቶችን በመሙላት በሳይንሳዊ እይታ ሁኔታዎችን መተቸት እንደሚገባቸውም ተነስቷል፡፡

የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ ቋንቋዎች በተለይ በአረብኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በሱማሊኛ ውይይት በማድረግ ምሁራን አስተዋጽዖ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገልጿል።

በውይይት መድረኩ የዩኒቨርሲቲዎች የኮቪድ-19 መከላከል ሥራም ተዳሷል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#MoSHE

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተው የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ወደተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ እንደሚደረግ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።

የዘንድሮውን የመመዘኛ ፈተና ካለፉት ከ147 ሺ በላይ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 206 ተማሪዎች በሚፈልጉት የትምህርት መስክ እና የትምህርት ተቋም እንዲመደቡ መደረጉን ተገልጿል።

ከምደባ ጋር ተያይዞ ቅሬታ ካቀረቡ 23 ሺህ በላይ ተማሪዎች መካከልም ከ1 ሺህ 800 በላይ የሚሆኑት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ የምደባ ማስተካከያ ተደርጎላቸዋል።

የትምህርት መስክ ምርጫን አስመልክቶ በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማረም 386 ተማሪዎች በመረጡት ዘርፍ እንዲመደቡ ተደርጓል ተብሏል።

ከፍተኛ የጤና እክል ያለባቸው፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች ፣ ነፍሰ ጡር እና ከሁለት አመት በታች ልጅ ያላቸው እናቶች ፣ አካል ጉዳተኞች እና ከአርብቶ እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ቅሬታን በማየት በቂ ማስረጃ ላቀረቡት አዎንታዊ ምላሽ ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል ፦ የትምህርት ተቋማትን ምርጫ በሚመለከት ርቀትን፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መሰረት አድርገው የቀረቡ ጥያቄዎችን ውድቅ ማድረጉን ሚኒስቴሩ ማሳወቁን ኢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvagethiopiaBOT
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር በተያያዘ 23 ሺህ 100 ቅሬታዎች ቀርበውለት ምላሽ ሰጧል።

በዚህም
• የጤና ችግር ያለባቸውና ማስረጃ ያቀረቡ፣
• አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች፣
• ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናት ተማሪዎች፣
• በፆታ ስህተት የተመደቡ ተማሪዎች፣
• መንትዮች፣
• በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ የሚገኙ ተማሪዎች ያቀረቧቸው በጠቅላላው 1 ሺህ 891 ቅሬታዎች ምላሽ አጊኝተዋል።

ከትምህርት ምርጫ ቅያሬ ጋር በተያያዘ (የተፈጥሮ ሳይንስ ተምረው ማህበራዊ ሳይንስ የተመደቡ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተምረው የተፈጥሮ ሳይንስ የተመደቡ) 386 ተማሪዎች ምላሽ አጊኝተዋል።

ከተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መራቅና ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ጋር በተያያዘ የቀረቡ ቅሬታዎች ሚኒስቴሩ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ በተመደቡበት እንዲቀጥሉ ወስኗል።

ቅሬታ ያቀረቡ ተማሪዎች ከሰኞ ግንቦት 16/2013 ዓ.ም ጀምሮ የቅሬታውን ምላሽ በበይነ መረብ መመልከት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ምንጭ:- MoSHE

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
#ማስታወሻ

በ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወስደዉ ቅሬታ ያቀረቡ ተማሪዎች ዳግም ምደባ ከዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በበየነ መረብ መመልከት ይችላሉ።

@tikvahethiopia
#update

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር ለቀረቡ ቅሬታዎች የተሰጠ ምላሽ እና የተማሪዎች ዳግም ምደባን ከዛሬ ግንቦት 16/2013 ዓ.ም #ከ10 ሰዓት ጀምሮ በበየነ መረብ መመልከት ይቻላል ብሏል።

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
"አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከሰኔ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ" - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመጪው ምርጫ በኋላ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ የየሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

ከምርጫው በኋላ ሰኔ 21 ሁሉም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ነባር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመጪው ምርጫ ወደደቤተሰቦቻቸው በመሄድ በምርጫው ይሳተፋሉ ብለዋል።

"የተማሪዎቹ መሄድ ግዴታ አይደለም" ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ፤ መምረጥ ለሚፈልጉ ነባር ተማሪዎች እንዲመች ከምርጫው በፊትና በኋላ ያሉ ቀናት የዕረፍት ጊዜ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

"ምርጫ ማድረግ መብት እንደመሆኑ፤ መምረጥ የማይፈልጉ ነባር ተማሪዎች በያሉበት ዩኒቨርሲቲ መቆየት ይችላሉ" ብለዋል።

ነባር ተማሪዎቹ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ባዘጋጀው የበይነ መረብ የመራጭነት መመዝገቢያ አማካኝነት በምርጫው ለመሳተፍ የመራጭነት ምዝገባ አድርገዋል።

ተማሪዎቹ ወደየመጡበት አካባቢ በመሄድ በምርጫው እንዲሳተፉ ምርጫ ቦርዱ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ : https://hottg.com/+RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity
የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 ጀምሮ እንደሚሰጥ የአ/አ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ።

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 23-25/2013 ድረስ እንደሚሰጥ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
The average adult will spend 34 years of their life staring at screens.

#Humans

Join and share @SHOCKINGFACT
አምቦ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ በጊዚያዊነት ሰኔ 24 እና 25/2013 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

ከሰኔ 06 እስከ ሰኔ 20/2013 ዓ.ም ልዩ የምርጫ እረፍት ጊዜ መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ይሁን እንጂ ወደየመጡበት አካባቢ መሄድ የማይፈልጉ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው መቆየት እንደሚችሉ እና የተማሪዎች አገልገሎትም እንደማይቋረጥ የዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መንግስቱ ቱሉ ባላቻ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

ከምርጫው በኋላ የነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ሰኔ 21 እና 22/2013 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

@tikvahuniversity @TikvahUniversityybot
Forwarded from Ethio University News®
#UPDATED NEWS

♻️እስከአሁን ለፍሬሾች ጥሪ ያደረጉ ገቢዎች👇👇👇👇


1⃣ 🌐#Hawassa_University

♻️በ2013 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች #ምዝገባ_በበየነመረብ ”Online” ከሰኔ 15-20/2013 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን ሲሆን የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ #የመግቢያ_ጊዜ ሰኔ 21-22/2013 ዓ.ም መሆኑን ይገልጻል፡፡

Online_ምዝገባ_ከሰኔ15-20/2013
👇👇👇👇👇
https://portal.hu.edu.et/Home/Freshman

2⃣ 🌐#WollegaUniversity

♻️ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች #ምዝገባ ከሰኔ 28-30/2013 ዓ.ም ድረስ የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን፡፡

3⃣ 🌐#DebarkUniversity

♻️በ#2013 ደባርቅ ዩንቨርሲቲ የተመደባቹህ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ግቢ መግቢያ ቀን ከሰኔ 26-30/2013 ድረስ ብቻ በመሆኑ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ዩንቨርሲቲው ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ አሳውቋል።

4⃣ 🌐#MekelleUniversity

♻️ዩኒቨርሲቲው የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ከሰኔ 21 እስከ 26/ 2013 ዓ.ም ጥሪ ለማድረግ ጊዚያዊ እቅድ ይዟል።

5⃣ 🌐#Selale_University

📌በ2013 ሰላሌ ዩንቨርሲቲ የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ነባር ተማሪዎች ከምርጫ በኋላ ግቢ ከተጠሩ በኋላ ማለትም ከሰኔ 21/2013 በኋላ በሳምንቱ ጥሪ እንደሚደረግላቸው የሰላሌ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት መረጃ አድርሰዋል።

6⃣ 🌐#Bahirdar_University

♻️በ2013 የትምህርት ዘመን በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ሰኔ 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም በመሆኑ በዕለቱ ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታከናውኑ እየገለጽን በምዝገባ ወቅት የ10ኛና የ12ኛ ክፍል የብሄራዊና ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣ 3x4 ስድስት ጉርድ ፎቶግራፎች፣ የመኝታ አልባሳትና የስፖርት ትጥቅ አሟልታችሁ እንድትገኙ እናስታውቃለን፡፡


7⃣ 🌐 #ወላይታ_ሶዶ_ዩኒቨርሲቲ የአዲስ

🔖 ገቢ ተማሪዎች ጥሪና ምዝገባ ከሰኔ 26 እስከ 30/2013 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አሳውቋል።

8⃣ 🌐#ደብረ_ብርሀን_ዩኒቨርሲቲ

🔖 ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ከሰኔ 25/2013 ዓ.ም በኋላ ጥሪ አደርጋለሁ ብሏል።

9⃣ 💠#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

🔖 በ2013 የትምህርት ዘመን የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም መደበኛ መርሃግብር ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ሰኔ 23 እና 24 /2013 ነው።

🔟 💠 #አሶሳ_ዩኒቨርሲቲ

🔖 የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 26 እስከ 30/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

1⃣1⃣ 💠 #ደብረ_ታቦር_ዩኒቨርሲቲ አዲስ
🔖 ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 26 እስከ 30/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

1⃣2⃣ 💠 #አዲስ_አበባ_ዩኒቨርስቲ

ለ2013 #አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሰኔ 01 እና 02 2013 ዓ.ም በ http://portal.aau.edu.et በመጠቀም የኦንላየን ምዝገባ እንድታከናውኑ አሳስቧል።

1⃣3⃣ 🌐#Semera_University
#ሰመራ_ዮኒቨርስቲ

♻️በ2013 የትምህርት ዘመን በሰመራ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ሰኔ 26 እና 27 ቀን 2013 ዓ.ም በመሆኑ በዕለቱ ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታከናውኑ እንገልፃለን ።

1⃣4⃣ 🌐#የወሎ _ዩኒቨርሲቲ

♻️አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 28 እና 29/2013 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ለአስተያየት ፣አልያም ለጥያቄ👇👇👇
@Entrance_Exambot
@yerasulwadjnegn

🔥ትምህርት ነክ መረጃ ለማግኘት👇👇
@Ethio_Entrance_preparation_Exam
@Ethio_Entrance_preparation_Exam
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
HTML Embed Code:
2024/04/24 00:41:03
Back to Top