TG Telegram Group & Channel
P H O E N I X B A T C H 2 k 1 2 | United States America (US)
Create: Update:

#MoSHE

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተው የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እስከ ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ወደተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ እንደሚደረግ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።

የዘንድሮውን የመመዘኛ ፈተና ካለፉት ከ147 ሺ በላይ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 206 ተማሪዎች በሚፈልጉት የትምህርት መስክ እና የትምህርት ተቋም እንዲመደቡ መደረጉን ተገልጿል።

ከምደባ ጋር ተያይዞ ቅሬታ ካቀረቡ 23 ሺህ በላይ ተማሪዎች መካከልም ከ1 ሺህ 800 በላይ የሚሆኑት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ የምደባ ማስተካከያ ተደርጎላቸዋል።

የትምህርት መስክ ምርጫን አስመልክቶ በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተፈጠሩ ስህተቶችን በማረም 386 ተማሪዎች በመረጡት ዘርፍ እንዲመደቡ ተደርጓል ተብሏል።

ከፍተኛ የጤና እክል ያለባቸው፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች ፣ ነፍሰ ጡር እና ከሁለት አመት በታች ልጅ ያላቸው እናቶች ፣ አካል ጉዳተኞች እና ከአርብቶ እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ቅሬታን በማየት በቂ ማስረጃ ላቀረቡት አዎንታዊ ምላሽ ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል ፦ የትምህርት ተቋማትን ምርጫ በሚመለከት ርቀትን፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መሰረት አድርገው የቀረቡ ጥያቄዎችን ውድቅ ማድረጉን ሚኒስቴሩ ማሳወቁን ኢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvagethiopiaBOT

>>Click here to continue<<

P H O E N I X B A T C H 2 k 1 2

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)