TG Telegram Group Link
Channel: Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Back to Bottom
• በመሃል ሸዋ አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ባሚገኘው የጉራጌ ምድር ላይ ኦሮሙማው አቢይ አህመድ እና ሽመልስ አብዲሳ ከጫካ አምጥተው ያሰፈሩት የኦነግ ጦር የተቆጣጠረው የጉራጌ ክፍል የቱ ነው?

"…ሰሞኑን አቢይ ጉራጌ ወልቂጤ ይቅርታ ጠይቁኝ ብሎ በሄደ ጊዜ ለአቢይ ክብር ሲባል የደም ግብር መስዋእት ተደርገው የታረዱት የትኞቹ ጉራጌዎች ናቸው።

"…ቀልድ አይደለም የያዝኩት። በጣም የሚገርመው ጉራጌን ያህል ታላቅ ሕዝብ በዝምታ እንዲያል መደረጉ ነው። ኦነግ ተቆጣጥሮታል እያሉክት የሚያላግጥ እንደማየት የሚገርም ምን አለ?

• የግዳችሁን መወያየት፣ መነጋገር ጀምሩ። እስላም ጉራጌዎች በሃይማኖት አንድ ነን በማለት ከኦሮሙማው ጋር በአንድ ቡታንቲ መጠቀም ከጀመሩ ቆይተዋል። ስልጤ በፊት ለወያኔ፣ አሁን ለኦነግ መገረዱን እያየህ ነው። እናም የግድህን ተናገር።

"…ብዙ ጉራጌዎች በኦነግ እየታገቱ ገነዝብ እየቀፈቀፉ ነው። ጥቂቶች ከኦነግ ጋር ባላቸው መሣሪያ እየተጋደሉ ነው። ጠንከር ያሉት ጉራጌዎች እናንተማ ዐማራ ናችሁ ተብለው እየታደኑ እየታሰሩ፣ እየተገደሉም ነው። ይሄን ታውቃላችሁ…? የጉራጌን ከብት የኦነግ ሠራዊት በልቶ እየጨረሰው ነው።

• እደግመዋለሁ በአሁን ሰዓት በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ስር ያለው ጉራጌ የቱ ክፍል ነው? አበሸጌ? ቸሀ? እኖር? ጌታ? እንደጋኝ? ጉመር? ቀቤና? ምሑር አክሊል? እዣ? ኮኪር ገደባኖ? ዶቢ? መስቃን? ማረቆ ወይስ ሶዶ? የትኛው ነው በኦነግ ሥር የገባው? የትኛው ነው ከኦነግ ጋር እየተዋደቀ ያለው?

• ለምን ትፈራላችሁ? ተናገሩ እንጂ…?
ጅማሮው ጥሩ ነው።

"…የጉራጌን ጉዳይ ጀምሬዋለሁ። ጉራጌ በካርታ ላይ የት እንዳለ እንኳ የማያውቁ ሰዎች ሁላ ነው የገጠሙኝ። ጉራጌን መርካቶ፣ ታይዋን እና አትክልት ተራ እና በየ ቡቲኩ፣ በሸምሱ ሱቅ እና በየሆቴል የንግድ ሥራ ዘርፍ ላይ ብቻ ያለ የሚመስለው ሁሉ እንዳለ ነው እየታዘብኩ የመጣሁት።

"…ጉራጌዎች ሳንቲም ለቀማ ላይ ብቻ የሚያተኩሩ እንጂ በእርሻ ሥራ፣ በከብት እርባታ ወዘተ የሚሳተፉ፣ መሬትም ያላቸው የማይመስላቸውም የትየለሌ መሆናቸውን ነው እየታዘብኩ ያለሁት። ስለ ዐማራ፣ ትግሬ እና ኦሮሞ ብቻ እያጮሁ በሚያወሩበት ሀገር ስለ ጉራጌ ቀስ ብሎ እንኳ ለማውራት እንኳን ሌላው ጉራጌው ራሱ ሲሽኮረመም ስታይ ትደመማለህ።

"…ጉራጌ ገና ከመጀመሪያው በዘመነ ህወሓት የራሳቸው ቋንቋና ማንነት የነበራቸውን መልጋ፣ ውልባረግ እና አዘርነት በርበሬን ጨፍልቀው ወደ ስልጤ አስገቧቸው። ቀጥሎ በ7ቤት ስም ደግሞ ጌቶ፣ ሙኸር፣ እንደገኝ፣ ቸሀ፣ ኢነሞርና አዣ መወሰዳቸውን ሰምቻለሁ። ወሊሶ፣ ዓለምገና የጉራጌ፣ በሰበታ በኩልም እነ ሱተን፣ ተሬ፣ ሌመን፣ አዋሽ የሚባሉ አካባቢዎች የጉራጌ ምድር እንደነበሩም ካርታዎች ይመሰክራሉ።

"…ለማንኛውም ጉራጌን እየኮረኮርኩም ቢሆን ማናገር ጀምሬአለሁ። በገጼም ላይ መወራት ተጀምሯል። በቲክቶክም፣ በመረጃ ተለቭዥንም ማውራት ማወያየት እጀምራለሁ። በእውቀት የሚመሩ ልጁቹ ሰከመጡ ደግሞ ይጠነክራል፣ ያድጋል፣ ይጎለምሳል። ይኸው ነው። ለእኔ ጅማሮው ጥሩ ነው።

• እህሳ ጉራጌ ምን ትላለህ…? የመወያያ መድረኩን ላዘጋጅልህና ልክ እንደ ዐማራው ተሰብስበህ ትመክራለህ ወይስ ይቅርብህ…?
ሃሉ… በቲክቶክ ልመጣ ነኝ

"…እለቱ ማክሰኞም አይደል…?… አዎ ያው እንደተለመደው ነጭ ነጯን ለመነጋገር በቲክቶክ መንደራችን ልመጣ ነኝ። ዛሬ የጉራጌ እንግዳ ይዤ ነው የምመጣው። ሂዱ እናንተም እዚያው ሞቅ ሞቅ እያደረጋችሁ ጠብቁኝ።

• እኔ ዘመዴ፣ አክሊለ ገብርኤል፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቅ ኢትዮጵያው ሰው፣ የሐረርጌው መራታ ባለ ማዕተቡ እያለሁ የፋኖ ትግል አይቆምም፣ መረጃ ቲቪም ጫፉን አትነኩትም። አሳይሃለሁ። ወላዲተ አምላክ የለችማ። ጠብቁኝ እመጣለሁ።

• አላችሁ አይደል…?
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሜን ነው…?

"…የዓድዋ ድል ሙዚየም… ሲበለጽግ ይሄን ይመስላል። አመራሩ በሙሉ ኢትዮጵያን ተረክቧል። ትግሬና ዐማራ ይቧቀሳል ይደቅቃል። ትግሬና ዐማራ ሲጠፋ በመጨረሻ የኦሮሞ እስላም እና ጴንጤ ለጠቅላይ ይፋለጣል። ከዚያ አቅም ያለው ብቻ ሳይሆን ጨካኙ ቆርጥሞት ያሸንፋል። ዕቅዱ እንደዙያ ነው።

"…ጴንጤ ወይ እስላም ያልሆነ አሁን ቦታ የለውም በኢትዮጵያ። እናም አንተ ቄሱና ዲያቆኑ፣ መነኩሴውም ታገቱ፣ ተገደሉ፣ ጳጳሱ ተሰደቡ፣ ተዋረዱ፣ ምእመናን መሪጌቶች ታረዱ ብለህ ስትለፋደድብኝ አለማፈርህ።

"…እና ደግሞ እናንት ኦርቶዶክሳውያን እና የዐማራ እስላሞች ይሄን ዓይታችሁ እኛም በአዳራሹ እንዘምርበት፣ እንስገድበትም አሉ አሏችሁ። እናንተ እኮ አታፍሩም። እንኳን እነርሱ ባነፁት አዳራሽ ይቅርና ገና ከመስጊድህና ከቤተ ክርስቲያንህ፣ ከሰፈር ከመንደርህ ትባረራታለህ።

"…ይልቅ ዘመኑ "የጌታቸው ልጆች" ዘመን ነው። አሜን ነው…? ሃሌሉያ…
"…እነሆ ቀኑ፥ እነሆ፥ መጥቶአል፤ ተራህ ወጥቶአል፤ ብትር አብቦአል፥ ትዕቢትም አጅብጅፎአል። ግፍ ወደ ክፋት ብትር ተነስቶአል ከእነርሱና ከብዛታቸው ከሀብታቸውም ምንም አይቀርም፥ የሚያለቅስላቸውም የለም። ጊዜው መጥቶአል፥ ቀኑ ቀርቦአል፤ መዓት በብዙዎች ሁሉ ላይ ነውና የሚገዛ ደስ አይበለው የሚሸጥም አያልቅስ። የሚሸጥ ወደሸጠው ነገር አይመለስም፥ ሰውም በነፍሱ ኃጢአት አይጸናም።

…ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ ወርቃቸውም እንደ ጕድፍ ይሆናል፤ በእግዚአብሔር መዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ያድናቸው ዘንድ አይችልም። እርሱ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና ሰውነታቸውን አያጠግቡም ሆዳቸውንም አይሞሉም።” ሕዝ 7፥ 10-19

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
የምሥራች አለኝ…!

"…የጎንደር ፋኖን በተመለከተ ታላቅ የምሥራች አለኝ። ለጎንደር ብቻ አይደለም ለመላው ዐማራ የሚሆን የምሥራች ነው ያለኝ። ወገን እንዴት ባለ ሁናቴ ነው የምትቀበሉኝ። ኣ…?
የምሥራች ለዐማራውያን…!

"…በራሳቸው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ነቢያት በሆኑት ጎንደሬዎች፣ በአፄ ቴዎድሮስ ልጆች፣ በጀግኖቹና በአርበኞቹ ጋባዥነት ለአንድ ዓላማ ቆመው ሳለ በሓሳብ ልዩነት ከሁለት ጎራ ተከፍለው ቁርሾ ገብቷቸው የነበሩት ጀግኖች ባቀረቡልኝ "የአሸማግለን" ጥሪ መሠረት እኔ ዘመዴ አባ ደፋር አንድ ለእናቱ፣ ሺ ለጠላቱ፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር፣ የምሥራቁ ሰው፣ ባለማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ፣ የሐረርጌውን መራታ ጥሪያቸውን ተቀብዬ እንደ መጽሐፍም ቃል “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።” ማቴ 5፥9 ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት የማሸማገል ሥራውን ጀመርኩ።

"…ጎንደሬዎቹን ጆኒ፣ ዘመንና አዱኛን ከጀርባ አሰልፌ፣ የሸዋውን ካህን ከኦሀዮ በጸሎት አስጀምሬ፣ በመጨረሻም ከወሎ የደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ አስተዳዳሪ የነበሩትን አባ ጽጌሥላሴን ጨምሬ፣ ገዳማውያን በጸሎት እንዲያግዙን ፈቃደ እግዚአብሔርንም ጠይቀን ስናበቃ ወደ ውይይቱ ገባን። ውይይቱ ሲጀመር ከባድ ነበር። ውሎ ሲያድር እየቀለለ መጥቶ ዛሬ ሚያዚያ 16/2016 ዓም እግዚአብሔር ከብሮ ሰይጣን ዲያብሎስም አፍሮ፣ በእለተ ኪዳነምህረት በደስታ፣ በእንባ፣ በፍቅር የሽምግልናውን ሂደት በይቅርታ ተፈጸመ።

"…አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የጎንደር ዕዝ የበላይ ጠባቂ፣ አርበኛ ባዬ ቀናው የዐማራ ፋኖ በጎንደር ሰብሳቢ፣ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የዐማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ መሪ፣ ኮ/ል ታደሰ የዐማራ ፋኖ በጎንደር የጦር አዛዥ በተለይ አርበኛ ፋኖ ደረጀ ሁላችንንም አስለቅሶን ሁላቸውም ታርቀው፣ ይቅር ተባብለው፣ የደስታ ጥይት ተተኩሶ፣ የተራራቁት ተቀራርበው በአጭር ጊዜ ውስጥ የጋራ የተዋሐደ አመራር መርጠው በአንድ የጎንደር ፋኖ ሊገለጡ ወስነው ይሄንኑ ለመላው ዐማራ ንገር ብለው አዘውኝ ነገሩ ተቋጭቷል።

• እግዚአብሔር ይመስገን 🙏
ሲንቄ ባንክ በጅማ ዞን…!😂😂

"…የኢትዮጵያ ባንኮች የገንዘብ እጥረት እንደገጠማቸው፣ ብድር መስጠት እስከማቆም የደረሱም እንዳሉ ይነገራል። ከዚህም በላይ ዋናው አሳሳቢው ነገር በገላን ከተማ የኦሮሚያ መንግሥት በማተሚያ ማሽን ብር ማተም መጀመሩ ነው። የመሃይም ስብስቡ ብልጽግና ጦርነት አቁሞ ኢኮኖሚው ላይ እንደመሥራት ቦንብና ጥይት በዶላር እየገዛ እንደ ሎተሪ የወረቀት ገንዘብ ያትማል።

"…ይሄ በምሥሉ ላይ የምታዩት የገንዘብ ክምር ሃርጌሳ ሳይሆን በኢትዮጵያዋ በአቢይ አሕመድ የትውልድ አከባቢ በጅማ ዞን ነው። በምሥሉ ላይ በቀይ ያከበብኩት ሰውዬ የጅማ ዞን አስተዳዳሪው አቶ ቲጃኒ ይባላል። ከአብይ ጋር የሥጋ ዝምድና ቢጤም ስላለው ከመከላከያ አምጥቶ የሾመው ራሱ አቢይ አህመድ ነው የሚሉም አሉ። ልክ እንደ አዲስ አበባ በጅማም ቀደምት ሰፈሮችንና መንደሮችን በተለይም የዐማራ ይዞታዎችን ልክ እንደ አዳነች አበቤ በጭካኔ ያለ ርህራሄ ይደመስስ ዘንድ ለጥፋት ያመጣው ሰው ነውም ይላሉ።

"…የምታዩት ብርም የአካባቢው ገበሬዎች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘባቸውን አውጥተው በምታዩት መልኩ በመሃላ😂 ወደ ስንቄ ባንክ ያስገቡ ዘንድ በግዳጅ ያመጡት ነውም ተብሏል። በኦሮሚያ ኢትዮጵያ የሚል ስም አዳክመው የራሳቸውን የቤት ሥራ በሚገባ እየሠሩ እንዳለም ማሳያ ነው። እንደ አየር መንገድ ወዘተ የመሳሰሉት በሙሉ የሠራተኛ ደሞዝ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አውጥተው ወደ ኦሮሞ ባንኮች እንዲያስገቡ መደረጉም ይታወቃል።

"…በቅርቡ 1የአሜሪካ ዶላር ከ90-120 ብር ይዘረዘራል። ባለ 1ሺ ኖት ይታተማል። 1ዳቦ ለመግዛት አንድ ፌስታል ሙሉ ብር ተሸክመን እንዞራለን። በዚንባቡዌ ላይ ያሾፍን፣ ያላገጥን ሁሉ የዚንባቡዌ አምላክ ይቅር ካላለን በቀር እንጃልን የሚሉ መተርጉማንም አሉ።

• አዲስ አበባስ ብር እንዴት ነው? 😁
የባህር ኃይል ማሪን ኮማንዶ ነገር…!

"…መለስ ዜናዊ የሸጠውን የኢትዮጵያ የባህር በር ዐማራ ክልል ገብቼ የዐማራን ፋኖ በመደምሰስ ዐማራን የኦሮሞና የትግሬ ዘላለማዊ ባርያ፣ ገረድ፣ አሽከር አድርጌ አሳያችኋለሁ ብሎ የማይነካ የነካው ሀ ገደሉ አቢይ አህመድ ከገባበት ቅርቃር ለመውጣት ሲል እንደ አጀንዳ ማስቀየሻነት "የባህር በር የምትል ካርታ መዘዘ" መጀመሪያ ምጽዋ ላይ፣ ቀጥሎ አሰብ ላይ ደነፋ። ዐማራውም ትግሬውም ጮጋ አሉት። ሶማሊላንድ ሄደ፣ ወፍ የለም። አሁን የት እንደደረሰ አላውቅም። ኡጁንቡራ ደርሶ ይሆን?

"…አጭቤክሱ አቢይ አሕመድ ለባህሩ ባሕር ኃይል አቋቁሞ ሥልጠና ያሰጥ ነበር። አስመርቋልም። ኋላ ላይ የባህር በሩ ሲጠፋ፣ የባህር ኃይል ምሩቃኖቹን ወደ ዐማራ ክልል ልኮ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት በሰሜን ሸዋ ውስጥ ባሉ ወረዳዎችና አካባቢዎች ዘመቻ እያካሄደ እንደሚገኝ የባህር ኃይሉ ዋና አዛዥ ተወካይ በሬር አዲሚራል ናስር አባድጋ በኩል ገለጸ።

"…እናንላችሁ…  ይሄ እሳት የላሰ የአቢይ አሕመድ ውኃ በሌለበት የባሕር ኃይል ነኝ የሚለው ቡድን በደረቅ መሬት ላይ ከሰሜን ሸዋ አናብስቱ ከእምዬ ምኒልክ የመንፈስ ልጆች ጋር ከአርበኛ አሰግድ እና ከሻለቃ መከታው ጋር ገጥመው አይሆኑ ሆነው ተበለሻሽተዋል። ድንቄም ባህር ኃይል። 😂 ኡኡቴ…  አልቀረብሽም አለ ገለቴ። አቢይ አሕመድ እና ኮተት አገዛዙ አልቆለታል። ዐማራ አሸንፏል። ምስኪን ወታደሮቹን ግን ነፍስ ይማር።

• ነፍስ ይማር…!
እንደ ፎከሩት እየተበቀሏት ነው።

"…የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን በተለምዶ የመሐሙድ ሙዚቃ ቤት ተብሎ የሚታወቀውን ህንፃ በወታደር "መንገድ ዘግተው" አቧራ የዓድዋ ሚዝየሙን እንዳያቆሽሸው የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪና አምጥተው ቅርሱን እያፈረሱት እንደሆነ ተነግሯል። ኤትአባታችን።

"…በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረር ከተማ ከተማም የሚገኘው ጥንታዊው እንቁላል ቤት ወይም የቀድሞ እስታስቲክስ ቢሮ የነበረበት እስከ 2016 ዓም ድረስ የግብር አበል ለቤተ ክርስቲያኒቱ ግብር እየከፈለበት የነበረውንና በሕግ አግባብ በፍርድ ቤት እግድ ያለበትን የቤተ ክርስቲያኒቱን የግል ቅርስ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ቤት እንዲሁ "የምን አባቱ ፍርድ ቤት ነው" በማለት ግሬደር አምጥተው በጉልበት ማፍረሳቸው ተነግሯል።

ቤተ ክህነቱ፦ በፍርድ ቤት የተያዘ ሕጋዊ ንብረታችንን አኮ ነው።

ኦሮሙማው ወሐረሪማ፦ የምን አባታችሁ ፍርድ ቤት ነው ምድረ ነፍጠኛ ሁላ።

ቤተ ክህነቱ፦ ለምንድነው የምታፈርሱት…?

ኦሮሙማ ወሐረሪማ፦ ለብልፅግና ጽሕፈት ቤት ህንጻ ልንሠራበት።

"…የኦሮሞ እስላሞቹና ጴንጤዎቹ ወንዶች ናቸው። ታግለው ሥልጣን ይዘው ይሄን ቡካቲያም ኦርቶዶክሳዊ ወገኔን ሽንቱን ያስጨርሱታል። የምንአባክ ሕግ አለ ሐረሪማም… ? አይ አደሬ… አሸናፊ ሁሌም ጌታ ኖ፣ አለቃ ኖ…

• እኛ ግን አናሳዝንም ወይ…?
HTML Embed Code:
2024/04/25 00:07:30
Back to Top