TG Telegram Group Link
Channel: Tsegaye R Ararssa
Back to Bottom
በኦሮሚያ ብቻ ባለፉት አምስት አመታት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች በተለያዩ ማጎሪያ (ማሰቃያ) ካምፖች እና ጊዜያዊ እስር ቤቶች ታስረዋል። ከኦነግ እና ኦፌኮ አመራር ጋር እነዚህ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። ይኼ ለእነሱ አይገባም ነበር። በነፃ መፈታት አለባቸው።

የሕግ ማሻሻያዎቹ የፖለቲካ ምህዳሩን ከመክፈት ሂደት አካል መሆን አለበት፣ ከእነዚህም መካከል የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ። ማንኛውም ነጻ የሆነ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታዛቢ በኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጎች ስለ ሽብርተኝነት ወይም ሁከት ፈፅሞ እንደዳልነበረ ይገነዘባል። ሕጉ ሁሌም የተደራጁ ተቃዋሚዎችን እና የተቃውሞ ድምፆችን ዝም ለማሰኘት የሚያገለግል የአፈና መሳሪያ ነው። የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማጥበብ በቀጥታ የተዘጋጀ ነው። ግንቦት 2021 ብልፅግና የእርስ በርስ ጦርነቱ በድርድር እንዲቆም አለማቀፋዊ ጫና እንዳይፈጠር በማሰብ ህወሓትን እና ኦነግ-ኦነሰን በሽብርተኝነት ለመፈረጅ በፍጥነት ወደ ፓርላማ አቅርቧል። አዋጁ የታወጀዉ እውነተኛ ውይይትን ለማጨለም ነበር።

2. በመላ ሐገሪቱ እውነተኛ ፖለቲካዊ መግባባት ላይ መድረስ

ዋናው የግዛቲቱ የፖለቲካ ፉክክር መድረክ የጦር አውድማ በሆነበት ወቅት በሐገሪቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዉስጥ ምን አይነት ውይይት ነዉ የሚደረገው? ወጣትና በእድሜ የገፉ ለሰላማዊ ትግል ፍላጎት የነበራቸው ፍትህን እንዳያገኙና ውይይትም እንዳይደረግ አውቆ በማሳጣቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽን ትተው ወደ ጫካ ትግል እየተመሙ ባለበት ግዜ ምን አይነት የፖለቲካ ውይይት ነው ኢትዮጵያ የምታካሂደው? አሰቃቂና ጭካኔን የተካኑ ወንጀሎችን በመፈልፈል የምታወቁትን የእርስ በርስ ጦርነቶችን እያባባሱ የሽግግር ፍትህ ሂደቱ የሚዘጋው የትኛውን የጭካኔ እና የወንጀል ምዕራፍን ነው? የነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልስ የጠ/ሚ አብይን ኢትዮጵያ ወለፈንዲ መራር ቀልዶች እያስጋተ ቀጥሏል።

በቅርብ ጊዜ ዉስጥ በትግራይ ክልል አንፃራዊ እፎይታ የታየ ቢሆንም ሀገሪቱ በዉስብስብ እና ስር የሰደደ ግጭቶችን እያስተናገደችም፣ የአየር ላይ ጥቃቶች በምዕራብ (ወለጋ አከባቢዎች)፣ በደቡብ (ጉጂ አካባቢ)፣ በማዕከላዊ (ሰሜን እና ምዕራብ ሸዋ) እና በሰሜን (የአማራ ክልል አራት ዞኖች) እየማቀቀች ትገኛለች። በኦሮሚያ ላይ በኦሮሞ ህዝብ ልብ እና አእምሮ ላይ የከፈተዉን ጦርነት ማሸነፍ ባለመቻሉ አገዛዙ እቅዴን ያሳኩልኛል ብሎ ያሰበውን የተለያዩ ስልቶችን እንደ ሚድያ ላይ ፕሮፓጋንዳ፣ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ሕዝብ ላይ ቦምብ በማዝነብ እና የሰው ማዕበል እየተጠቀመ ይገኛል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወታደሮቹን እና የአካባቢውን ካድሬዎች በማስተባበር የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የቤተሰብ አባላት፣ አባቶች እና እናቶች፣ እና የተቃውሞ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ናቸው ብሎ የጠረጠራቸዉን ወገኖች የጤና ጥበቃ ተቋማትን፣ ሆስፒታሎችን፣ ት/ቤቶችን ፣ ፍርድ ቤቶችን፣ እና ማናቸዉም የማህበረሰባዊ አገልግሎቶችን የመቃብር ቦታዎችን ጨምሮ ለሞቱ የቤተሰብ አባላት እንዳይጠቀሙ እየከለከለ ይገኛል። መሬት ላይ ያለው እውነታ የፌደራል መንግስት እና የክልል ልዩ ሃይል አዳዲስ ወታደሮችን እየመለመለ እና እያሰለጠነ ይገኛል። ይህ መቀየር አለበት።

በመላ አገሪቱ ትርጉም ያለው ፖለቲካዊ መግባባት ላይ መድረስ ለማንኛውም ውይይት ወይም ፍትህ (የሽግግር ፍትህ) አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ነው። እዉነተኛ ፖለቲካዊ መግባባቶች በመላው ሐገሪቱ መስፈን አለባቸው። እውነተኛ የፖለቲካ ድርድር ማለት ትጥቅ ማስፈታት፣ ወደ ህብረተሰቡ መመለስና መልሶ ማቋቋም (DDR) አይደለም። በተለይ ትጥቅ ማስፈታት፣ ወደ ህብረተሰቡ መመለስና መልሶ ማቋቋም ላይ ብቻ በማተኮር ነገር ግን ስለ መሰረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች ሳያነሳ መቆየቱ አገዛዙ ከግጭት በኋላ ህይወትና ሰላማዊ ኑሮ የሚያብብበት ማህበረሰብ ለመፍጠር ፍፁም ፍላጎት እንደሌለው ማሳያ ነው። ይልቁንም አቋሙ ሐገሪቱን ከራሷ ጋር በማጋጨት የሐገሪቱን የተበታተነ ሃብት በማሰባሰብ ስልጣኑን ማጠናከር ነው። የፖለቲካ መግባባቱም አገሪቷን በሙሉ ያቀፉ መሆን አለባቸው። በእኛ እምነት ትግራይም የፖለቲካ መግባባት ያስፈልገዋል። በጥይት መግደልን ማስቆም የተቻለውን ያህል፣ CoHA የጦርነት ማቋረጥ ስምምነት ብቻ እንጂ አጠቃላይ የሰላም ስምምነት አልነበረም። ሆኖም በአሁኑ ወቅት፣ ሁሉም መረጃዎች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያ መንግሥት እውነተኛ የፖለቲካ መግባባት ፍላጎት እንዳለው ያሳያል። ይህም ማለት የተቃውሞው ትግል፣ ትውልድ አምባገነንነትን መታገል እና የሀገሪቱን እና የአከባቢውን የወደፊት እጣ ፈንታ የመቅረጽ ከባድ ሃላፊነት አለበት።

3. ሁሉን አቀፍ ሂደት ገለልተኛ ኮሚሽን (ኮሚሽኖች) መመስረት- ተቀባይነቱ በሁሉም ዋና ባለድርሻ እካላት መሆን

ውይይት ሰብሳቢዎችና አስተባባሪዎች በሂደት ወደ ፊት መምጣት አለባቸው፣ ይህም ዋና ባለድርሻ አካላትን በማያገል ሂደት መሆን አለበት።

ከላይ የተጠቀሱት በሌሉበት፣ የጠ/ሚኒስትር አብይ ሐገራዊ ውይይት እና የሽግግር ፍትሃዊነት ወገንተኛ አላማዎችን ብቻ ያሳካል።

በአገር ውስጥ ውይይቱ ለአማራ እና ኢትዮጵያዊነት ካምፕ ሕገ-መንግሥት ለማሻሻል ነዉ በሚል መልኩ ይንጸባረቃል። በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የተከሰተው የውስጥ ልዩነቶች እና ቅራኔዎች ወደ ደጋፊዎቻቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ መጥቷል። በርካታ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደጋፊዎች የነበሩ ወደ መረረ ጠላትነት ተቀይረዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ለዚህ ካምፕ የብሔራዊ ውይይቱ ሲጠናቀቅ ከዓላማቸው ጋር እንደሚጣጣሙ ቃል በመግባት ፓርቲያቸውን እና የድጋፍ መሰረታቸዉን ለጊዜውም ቢሆን አንድ ለማድረግ ይፈልጋሉ። ያለፉት ስድስት ዓመታት ትምህርት ከሆነ፣ መንግሥት ለሌሎቹ የፖለቲካ ካምፖች ደግሞ ፍጹም ተቃራኒ የሆነውን ቃል እንደሚገባ እንጠብቃለን።

ሐገራዊው ውይይቱ አገዛዙ በየፖለቲካ ካምፑ ውስጥ ያሉ ለዘብተኛና ወላዋይ ሃይሎች ብሎ የፈረጃቸውን ለመቆጣጠር የሚሞክርበትን እድል መፍጠር ነው። አገዛዙ በኦሮሞ፣ በአማራ እና በትግራይ መካከል አለመግባባት ለመፍጠር ሲጥር ቆይቷል። አገዛዙ ለዘብተኛና ወላዋይ የሚላቸውን የፖለቲካ ቡድኖችን በማበረታታት እና ብሄራዊ ውይይቱን በተሳትፎ በማስጌጥ በየፖለቲካ ካምፑ ውስጥ አዲስ አለመግባባት ለመፍጠር ተስፋ አድርጓል።

አብይ በግጭትና በኢኮኖሚ ችግር ለሚማቅቀው ህዝብ የተሳሳተ የተስፋ እና የዕድገት ስሜት ለመፍጠርም ተስፋ ያደርጋል። በመጨረሻም ከዚህ ሂደት ውስጥ አንዳች ነገር ቢመጣ ያዉ አብይ ስልጣኑን ለማጠናከር መንገድ የሚከፍትለት ህገ-መንግስታዊ ተንኮል ብቻ ነው። በሂደትም በድህረ 1991 የስርዓት ለውጥ ላይ የተደረሰውን ስስ የፖለቲካ እልባት ሊያናጋ ይችላል።
በብሔራዊ ውይይት ኮሚሽን ውስጥ የተቀመጡት ኮሚሽነሮች፣ አንዳንዶቹን ከፍ አድርገን የያዝናቸው፣ እነዚህን እውነታዎች ማጤን አለባቸው። በጠ/ሚንስትር አብይ እንደተቋቋሙት ኮሚሽኖች በጥቂት ወራት ውስጥ ካልተበተነ ኮሚሽናቸው፦ ሀ) አገዛዙ ሊጋፈጣቸው የማይፈልጋቸው ጥያቄዎች ሁሉ የማያልቁ እና ቆራጥ ውሳኔ የማይሰጡበት የወሬ መደብር (talking shop) አይነት የውይይት መድረክ መሆን ወይም፣ (ለ) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ማጠናከሪያ (power consolidation) መሳሪያ ይሆናል። በዚህ ሂደት ውስጥ ምንም አይነት ውጤት ቢመጣ፣ የናንተ ትሩፋት ግን በስልጣን ላይ ያለው አካል ስልጣኑን ለማጠናከር እንዲረዳው እና በሂደቱም ወደ ሰላምና ዲሞክራሲ ለሚደረገው ሽግግር ዉድቀት ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረግ ብቻ ይሆናል። ኮሚሽነሮቹ ለትጥቅ ትግል ተሳታፊዎች በቅርቡ ባደረጉት ጥሪ ደህንነት ዋስትና ሲሰጡም በመገረም ተመልክተናል። ከአክብሮት ጋር፣ የገለልተኛነት ምልክት ካሳዩ ኮሚሽነሮቹ የሌላዉን ይቅርና የራሳቸውን ደህንነት ማረጋገጥ አይችሉም። ለዚህ ደግሞ በቅርቡ ሃሳባቸውን ለመግለፅ የሞከሩት የአገዛዙ ባለስልጣናት እጣ ፈንታ የመጨረሻው የማንቂያ ደወል መሆን ነበረበት።

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የብልፅግና ዋና ስልታዊ ጥቅም ከBretton Woods እና ሰፊው ምዕራብ ሐገራት ጦርነቱን ለማስቀጠል እርዳታ ማግኘት ነዉ። ብዙ ጊዜ ውድ የሆኑ የግብይት ስምምነቶችን ከተባበሩት አረብ ኤሚሬት፣ ቻይና፣ ቱርክ እና ኢራን ጋር የሚያደርገው አገዛዙ ፈጣን የጦር መሳሪያ ግዢ ለማድረግ እና ጊዜያዊ ችግሩን ለመቅረፍ ስለሚረዳው ይሆናል። አገዛዙ ግን በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የተንሰራፋውን መዋቅራዊ ችግር ያለ ምዕራባውያን የዋስትና ገንዘብ መቅረፍ እንደማይቻል ተገንዝቧል። ውጤታማ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ከዋለ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትርጉም ያለው ተፅእኖ አለው። ለአጭር ጊዜ ስልታዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል አስፈላጊ የፖለቲካ መግባባት እና ተገቢ ተጠያቂነትን መተው የለበትም። ይህ ከሆነ፣ ከምዕራባውያን የተገኘው ገንዘብ የእርስ በርስ ጦርነቶችን ለመደገፍ የሚያስችል ኢኮኖሚ ለመደገፍ ይጠቅማል። የምዕራባውያኑ ዋስትና መድህን ገንዘብ በአብይ ከንቱ ፓርክ ፕሮጀክቶች የህዝብን (ከተማ ነዋሪዎችን) ትኩረት ለመቀየር የሚረዱትን ምግባሮች ለመግዛት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ነገር ግን በወሳኝ ሁኔታ ፖለቲካውን መድረሻ ወደሌለው ገደል የሚያስገቡና ለዘር ማጥፋት ጀብዱዎች የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ። ምዕራባውያን አቅማቸውን በብቃት ካልተጠቀሙበት እና በዋናነት በዩክሬን እና በጋዛ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰሳቸው ከቀጠለ፣ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ በሚገኙት የአፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባህር ኮሪደር ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ ህዝብ ያላት ሀገር ቀስ በቀስ ትፈርሳለች።

የኦነግ-ኦነሰ ከፍተኛ እዝ

ግንቦት 7፣ 2024
ሰንበትበት ብለን ብንመለስ: የነአወሉ አብዲና የነአዳነ ብልጥግና (እና የብርሃኑ ጁላ ጦር): ከተማ ተቀምጠው: በሚዲያ ላይ "ይህን ወረዳ ነፃ አወጣን: ያንን ክልል በእንደዚህ ፐርሰንት ከታጣቂዎች አስለቀቅን" ሲሉ መሰንበታቸውን አየን::

አይ ጊዜ!!! መንግሥት ነኝ የሚለው ፓርቲና በዓለም ላይ አቻ የለኝም የሚለው የብልጥግና ጦር: የቀበሌዎችና የወረዳዎች ነፃ አውጪ ሆኖ አረፈው! ?!

ለመሆኑ: ጦሩም ሥራው በሚዲያ ላይ ፕሮፓጋንዳ ማሟሟቅ ብቻ ከሆነ: በመከላከያ ሠራዊቱና (5ኛ ትውልድ ጦርነትን ይከውናል በተባለው) በሚዲያ ሠራዊቱ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ሊሆን ነው? በፖለቲከኞቹ (እነ አዲሱ አረጋ/አወሉ አብዲ: ወዘተ) እና በወታደሮቹ (ብርሃኑ ጅሉ/ስዩም በላይ: ወዘተ) መካከል ያለው ልዩነት እንኳን ከጠፋ አምስት ዓመት አልፎታልና እነዚህስ አንድና ያው መሆናቸው ግልጽ ነው::

መሬት ላይ መዋጋት ሲያቅታቸው: የሚዲያ ላይ ነፃ አውጪ የመሆናቸውን ነገር ግን ተቀቃዋሚዎቹ እንደ ትልቅ ድል ሊወስዱት ይገባል::

#Kunis_Tokko!
#Genocidaires_are_doomed!
ለእነ ኔታንያሁ የተጠየቀው የዓለምአቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ (arrest warrant) ለኛዎቹ ዘር-አጥፊዎችና የጦር ወንጀለኞችም የሚጠየቅበት ወቅት እየተቃረበ ይመስላል:: #Genocidaires_are_doomed!
#Abiy_Ahmed_is_a_genocidaire!
#Birhanu_jula_must_be_arrested_now!
ትናንት፣ ብልጥግና በትግራይ የሚያካሂደው የዘር ማጥፋት ጦርነት "ይቁም" ስንል ከኛ ጋር የነበረ ሰው፣ ዛሬ "ብልጥግና በኦሮሚያ ላይ የሚያካሂደውን ተመሳሳይ ጦርነት ያቁም" ማለት አቅቶት፣ WBO ሰላም ማምጣትና ከአብይ ጋር መሥራት አለበት እያለ ሚያላዝን ከሆነ፣ ጀርባው ሲጠና (ኧረ ሳይጠናም)፣ ይህ ስው ከመጀመሪያውም የፍትሓዊ ትግልና የሰላም ሰው ሳይሆን፣ undercover ብልጥግና ነበር ማለት ነው።
#የታሪክና_የትግል_እባጭ_ሁላ! #ለማያውቃችሁ
የአገራዊ መግባባት ውይይት??? ጽድቁ ቀርቶ፣ በቅጡ በኮነነን!
====================
ከ70% በላይ የአገሪቱ ሕዝብ በጦርነት እሳት እየተቃጠለ፤

አንድ ክልል በጦርነት ሥጋት እየተናጠ፤

ቁልፍ የሆኑ ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉ ከሕጋዊው የፖለቲካ መድረክ ተገፍተው በወጡበት ሁኔታ፤

በየሥፍራው ማሕበረሰባዊ ጦረኝነት እየተስፋፋ፤

ፖለቲካው፣ የመፋጠጥ (የconfrontation)፣ የመካረር (የpolarization)፣ እና እርስ በርስ የመጠራጠር (mutual distrust) ሆኖ በተንሠራፋበት ሁኔታ፤

ሥርዓቱ፣ 'ሕይወቱና' እንቅስቃሴው በፊንፊኔና ፊንፊኔ ዙሪያ ባሉት መንደሮች ተወስኖ ባለበት ሁኔታ፤

... የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ ጦርነቶች አስቻይ ከሆኑት ሕገ-ወጥ ተቋማት አንዱ የሆነው "አገራዊ መግባባት ኮሚሽን"፣ አገራዊ ውይይት ጀመርኩ... እያለ ነው።

ይሄ ደሞ የብልጥግና ሰሞነኛ ቀልድ መሆኑ ነው።

ሕገ-ወጦች ሕጋዊነትና ፍትሕን፣ ጦረኞች ሰላምንና መግባባትን ሊተገብሩና ሊያስፈጽሙ አይችሉም። ዘር-አጥፊዎችና ፋሽስቶችም እርቅና የሕዝቦች መረጋጋትን አይሹም።

እየተቀጣጠለ ያለውን ጦርነት ለማስቆም፣ ጠንከር ያለ መግለጫ እንኳን አውጥቶ የማያውቅ ድርጅት፣ እስካሁኑአም ሰዓት ጦርነት ባልቆመበት ሁኔታ: 'ውይይት እያካሄድኩ ነው' ማለቱ፣ ፋይዳው፣ ተጠያቂነትን በመሸፋፈን፣ ለወንጀለኞች ሕጋዊነትን ማላበስ ብቻ ነው።

#No_National_Dialog_amidst_a_raging_war!
When these genociders are the ones to do the so called national ‘dialog’ (and they do so in the absence of any opposition party), then you know it is neither a dialog nor national.
#no_national_dialog_amidst_a_raging_war!
#Abiys_Dialog_Commission_is_a_talking_club_of_genociders!
Forwarded from Biyya Tesfaye (Biyya Tesfaye)
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ስምሪት በማወጅ ጠንካራ ውጊያዎችን በኦሮሚያ ውስጥ ሲያካሄድ በዋለው መሰረት፣ በደቡብ ቦረና ዞንም ጠላትን በሙት እና በቁስል ቀጥቷል

ግንቦት 30፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) 

ግንቦት 28፣ 2024 የሽኒጋ ቃለ-መሃላ ዘመቻን ለማሳካት ጀግኖቹ የነፃነት ጮራ አብሳሪዎች የኦነሰ ባወጣው አዋጅ መሰረት በደቡብ ኦሮሚያ ዕዝ በቦረና ዞን፣ በሚዮ ወረዳ ውስጥ ባደረጉት የማጥቃት እርምጃ በጠላት ኃይል ላይ አኩሪ ድልን አስመዝግበዋል።

ይህ በደቡብ ዞን የሚገኘው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሚዮ ወረዳ በተለያዩ ቦታዎች ከባባድ ጦርነት ያካሄደ ሲሆን፣ ዱከሌ፤ ሜጢ፤ እና ጎምቢሳ በሚባሉ ቦታዎች ድል ማስመዝገቡን የዞኑ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አዛዥ ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግሯል።

በዚህ ጦርነትም 12 የጠላት ወታደሮችን ሲገድል በርካታ ቁጥር ያላቸውን ደግሞ በማያገግም ቁስለ ቀጥተዋል።

ቁስለኞቻቸውንም በሶስት መኪናዎች ሞልተው ለህክምና ወደ ሆስፒታል መውሰዳቸውን አቢኦ ከምንጮቹ ተነግሮታል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ስምሪት በማወጅ ጠንካራ ውጊያዎችን በኦሮሚያ ውስጥ ሲያካሄድ በዋለው መሰረት፣ በደቡብ ቦረና ዞንም ጠላትን በሙት እና በቁስል ቀጥቷል

ግንቦት 30፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) 

ግንቦት 28፣ 2024 የሽኒጋ ቃለ-መሃላ ዘመቻን ለማሳካት ጀግኖቹ የነፃነት ጮራ አብሳሪዎች የኦነሰ ባወጣው አዋጅ መሰረት በደቡብ ኦሮሚያ ዕዝ በቦረና ዞን፣ በሚዮ ወረዳ ውስጥ ባደረጉት የማጥቃት እርምጃ በጠላት ኃይል ላይ አኩሪ ድልን አስመዝግበዋል።

ይህ በደቡብ ዞን የሚገኘው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሚዮ ወረዳ በተለያዩ ቦታዎች ከባባድ ጦርነት ያካሄደ ሲሆን፣ ዱከሌ፤ ሜጢ፤ እና ጎምቢሳ በሚባሉ ቦታዎች ድል ማስመዝገቡን የዞኑ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አዛዥ ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግሯል።

በዚህ ጦርነትም 12 የጠላት ወታደሮችን ሲገድል በርካታ ቁጥር ያላቸውን ደግሞ በማያገግም ቁስለ ቀጥተዋል።

ቁስለኞቻቸውንም በሶስት መኪናዎች ሞልተው ለህክምና ወደ ሆስፒታል መውሰዳቸውን አቢኦ ከምንጮቹ ተነግሮታል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!

~via BT
የፊንፊኔ ጉዳይ በማይመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ናቸው በተባሉ የአጀንዳ ልየታ መከናወኑ እንዲሁም ነባሩን፡ባለቤቱንና ተወላጁን ባገለለ መልኩ የሚደረግ የትኛውም ሀገራዊ ምክክር አካታች ያልሆነና ውጤት አልባ ያደርገዋል። የፊንፊኔና ዙርያው ኦሮሞ ከ150 አመት በላይ በደረሰበት በደል፣የተነፈገውን ፍትህና መብቱን ለማስከበር ዛሬም እንደ ሁልግዜው ጥረት ላይ ነው።

ከየትኛውም የኦሮሚያ አከባቢዎች በተለየ መልኩ ቋንቋውን፣ባህሉን፣ማንነቱን ዘሩ እንዲጠፋ ጭምር የተፈረደበት የፊንፊኔና ዙርያው ኦሮሞን እና ኦሮሚያን ያላካተተ የትኛውም ከተማዋን የተመለከተ አጀንዳ ልየታና ምክክርን ፋይዳ ቢስ ይሆናል። እውነታን ከማውጣት ይልቅ የሚመቻቸውን ብቻ እንደ አመቺነቱ የሚወስዱ ግለሰቦች በሞሉበት የአጀንዳ ልየታው አካታች ነው ብለንም አናምንም።

Haaromsa Finfinnee
Dhimmi Finfinnee, ajandaa qooda fudhattoota dhimmichi hin ilaallee kan raawwatamaa jiru yoo ta'u, marii biyyoolessaa kamiyyuu haala kanaan abbaa biyyaa/Saba Oromoo Tuulammaa fi dhalataan ala ta'een raawwatamuun isaa bu'aa kan hin qabne akka ta'u taasisa.

Oromoon Finfinenee fi Naannoo isaa afaan isaa,aadaa fi eenyummaanisaa akka badu itti murtaa’e, ammas mirga waggoota 150 oliif sarbameef, abbaa magaalichaa fi haqa isaatiif ciminaan gaafachaa fi hojjachaa jira.

Rakkoo fi dhugaasaa baasanii,fala itti barbaachuun ala, ajandaa naannoo Oromiyaa kamiiyyuu irraa adda ta’een dhimma magaala Finfinnee ilaaluun ajandaa Oromoo Finfinenee fi Oromiyaa haaluu dha, kunis bu’aa hin qabu.

Ajandaan kun namoota dhuunfaa dhugaa haalanii fedhii fi yaada dhuunfaa isaaniif mijatu qofaan waan guutameef, hunda hirmaachisaadha jennee hin amannu.

Haaromsa Finfinnee
Oromo Scholars and Professionals’ Statement regarding the so called “National Dialog”.

https://ogfonline.org/oromos-should-reject-the-ethiopian-national-dialogue-commission/
HTML Embed Code:
2024/06/06 06:08:58
Back to Top