TG Telegram Group Link
Channel: Sport 360
Back to Bottom
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች በተመሳሳይ ወቀት አንድ ላይ ሊከፈቱ እንደማይችሉና ደረጃ በደረጃ የመክፈት ሂደት እንደሚኖር ለኢዜአ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ የትምህርት አጀማመሩ ከክልል ክልል እና ከዞን ዞን ሊለያይ እንደሚችልም አመልክተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ትምህርት ሚኒስቴር አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ጭማሪ እየጠየቁ መሆኑ የገለፀ ሲሆን ይህን በሚያደርጉ ተቋማት ላይ ትምህርት ቤቶችን እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል!

ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግና ኮሮናን በመከላከል ትምህርት መጀመር የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች እያጠና ይገኛል።

በተደረጉ የዳሰሳ ጥናቶች ተማሪዎች የትምህርት መጀመርን በጉጉት እየጠበቁ መሆናቸውን ለመረዳት እንደተቻለ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በሌላ በኩል ወላጆች የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት ልጆቻቸው ትምህርት ቤት ሲሄዱ ለኮሮና ቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ የሚለው ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

እነዚህን ተቃራኒ ሃሳቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት ትምህርት ሚኒስቴር እንደ አካባቢዎቹ ወቅታዊ የኮሮና ስርጭት ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በደረጃ መክፈት የሚያስችሉ መንገዶችን እየገመገመ ይገኛል።

ትምህርት ሚኒስቴር እያካሄደ ባለው ጥናት ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት በአንድ ክፍል ከ20 እስከ 25 ተማሪዎችን ማስተማር ፣ የንፅህና መጠበቂያ ለትምህርት ቤቶች ማቅረብ፣ ተጨማሪ ትምህርት ቤቶችን መገንባት የሚሉ አማራጮች ቀርበዋል።

ሚኒስቴሩ ጥናቱ ሲጠናቀቅ በሚቀርበው ተጨማሪ ምክረ ሃሳብ መሰረት አስፈላጊው ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ትምህርት ለመጀመር ጥረት ይደረጋል ብሏል።
ማስታወቂያ!

ለመላው የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማህበረሰብ!

በኮቪድ 19 ወረርሸኝ ምክንያት የገጽ ለገጽ ትምህርት መቋረጡና ለበለጠ ጥንቃቄ ሲባል ተማሪዎች በልዩ ዝግጅት ወደቤተሰቦቻቸው መሸኛታቸው ይታወሳል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችሉ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ቀደም ብለን መግለጻችን ይታወቃል።

ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርስቲዎች የሚከፈቱበት ቀን እንደተቆረጠ ሆኖ በተለያዩ አካላት የሚወጣው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነና የተቋረጠው ትምህርት ሊቀጥል የሚችለው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ትምህርት ማስቀጠል የሚያስችል መረጃ ሲገኝ ብቻ እንደሆነ እና መረጃውም የሚሰጠው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።

እስከዛው ድረስ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከለካል የሚያስችል አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረጋችሁ ከክፍያ ነጻ በሆነው የዲጂታል ላይበራሪያችን http://ndl.ethernet.edu.et በመግባት አጋዥ መጻህፍትን እያነበባችሁ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
ጳጉሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም
የግል ትምህርት ቤቶች በ2013 አመት የትምህርት ዘመን ምዝገባ ምንም አይነት ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ፋታህ፦

"እንደሚታወቀው ከነሃሴ 20/2012 ጀምሮ የግል ትምህርት ቤቶች ምዝገባ እየተካሄደ እንዳለ ይታወቃል። ትምህርት የሚጀምርበት ጊዜ በፌደራል እና በሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ መሰረት ነው።

አሁን መግለፅ የምፈልገው ግን በግል ትምህርት ቤቶች የምዝገባ ወቅት ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርት ቤቶች በተዘጉበት ወቅት የመምህራን ደሞዝ ለመሸፈን ወላጆችን ክፍያ እንዲፈፅሙ መጠየቁ የሚታወስ ነው።

ዛሬ ላይ ድግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የወቅቱን ሁኔታ በማየት ክፍያ የመጨመር አዝማሚያ የሚታይ በመሆኑ ጉዳዩ ከህግና ስርዓት ውጭ መሆኑን ሊረዱ ይገባል።

በዚህም ከአንዳንድ ወላጆች የደረሱን መረጃዎች በመኖራቸው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ይህን ጉዳይ የሚከታተል ይሆናል።"
Share
የዩኒቨርሲቲ ምደባ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

የ2013 ትምህርት ዘመን የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከዛሬ ሚያዝያ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይፋ ሆኗል።

በመሆኑም ተማሪዎች ከታች በተገለጸዉ የበየነ መረብ ጠቋሚ በመግባት የተመደቡበትን ተቋም ማወቅ ይችላሉ።

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉ ተብሏል።

• ዉጤት ለማየት መግቢያ ዌብሳይት፡- http://result.neaea.gov.et/Home/Placement

• ቅሬታ ለማቅረብ መግቢያ ዌብሳይት (በአካል መምጣት አያስፈልግም)፡- https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 122 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

ጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው በጤናው ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን እያፈራ ይገኛል፡፡

ይህም የዩኒቨርሲቲውን ተሞክሮ ያሳያል ማለታቸውን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘገባ ያመላክታል።

ዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ አገልግሎት በመስጠት እንደሚታወቅ ያነሱት ሚኒስትር ዲኤታው፥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ያደረገው ጥረት አንዱ ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል።

ተመራቂዎች በሥራ ዓለም የተለያዩ ፈተናዎች እንደሚያጋጥማቸው አውቀው ከወዲሁ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡
https://hottg.com/timhirt_minister
አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከሰኔ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ:- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመጪው ምርጫ በኋላ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም ወደተመደቡበት ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ የየሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

ከምርጫው በኋላ ሰኔ 21 ሁሉም የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ነባር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመጪው ምርጫ ወደደቤተሰቦቻቸው በመሄድ በምርጫው ይሳተፋሉ ብለዋል።

"የተማሪዎቹ መሄድ ግዴታ አይደለም" ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው ፤ መምረጥ ለሚፈልጉ ነባር ተማሪዎች እንዲመች ከምርጫው በፊትና በኋላ ያሉ ቀናት የዕረፍት ጊዜ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

"ምርጫ ማድረግ መብት እንደመሆኑ፤ መምረጥ የማይፈልጉ ነባር ተማሪዎች በያሉበት ዩኒቨርሲቲ መቆየት ይችላሉ" ብለዋል።

ነባር ተማሪዎቹ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ባዘጋጀው የበይነ መረብ የመራጭነት መመዝገቢያ አማካኝነት በምርጫው ለመሳተፍ የመራጭነት ምዝገባ አድርገዋል።

ተማሪዎቹ ወደየመጡበት አካባቢ በመሄድ በምርጫው እንዲሳተፉ ምርጫ ቦርዱ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።
https://hottg.com/timhirt_minister
የ 2014 ዓ.ም የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ተገለፀ!

ትምህርት ሚኒስቴር በ2014ዓ.ም በሚኖረው የመደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ሂደት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደሚካሄድ አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር በ2013ዓ.ም የትምህርት ዘመን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባስቀመጠው የኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መሰረት ትምህርት በቀንና ፈረቃ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት አሰጣጡ እንዴት መሆን እንዳለበት ትምህርት ሚኒስቴር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል አዘጋጅቷል።

ስለሆነም በቀጣይየሚኖረው የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበት ወደ ፊት ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ የሚወጣለትና ለህዝብ የሚገለፅ ይሆናል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ2013 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል።

በመጀምሪያ ዙር ፈተና 565ሺ 255 ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ይህም ፈተናውን ይወስዳሉ ተብለው ከተጠበቁት 96 ከመቶ ነው።

የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በሀገራችን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ፈተናው በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተናግረዋል።

በ2ሺ 36 የፈተና ጣቢያዎች በተሰጠው በዚህ ፈተና፣ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ከታሰበው 617ሺ 991 ተማሪዎች ውስጥ 565ሺ 255ቱ ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ የህልውና ትግል ወቅት ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ የፀጥታ አካላት፣ የትምህርት ዘርፉ ሰራተኞችና ወላጆች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"በማህበራዊ ሚዲያ አንዳንድ ፈተናዎች ተሰርቀው ወጥተዋል የሚባለው ጉዳይ እውነት ነወይ" ተበለው በጋዜጠኞች የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የተለያዩ ምርምርራዎችና ትንተናዎች ተደርገው አስፈላጊው ማስተካከያ ስለሚደረግ ምንም የሚያስጋ ነገር የለም ብለዋል።

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ፈተና ያልተሰጠባቸው አካባቢዎች ለተማሪዎቹ የስነ ልቦና ግንባታ ስራ ተሰርቶ በሁለተኛ ዙር በመፈተን ከመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ ተብሏል።
Hello, if you like football, could you check out 1 channel called NEX Comps?
I uploaded new, fresh video recently, I hope you like it!
You found?
Channel photo updated
Channel name was changed to «Sport 360»
NEX Comps የተባለውን የዩቲዩብ ቻናል ማየት እንዳትረሱ
👋👋👋
U saw NEX Comps?
የኔን የዩቲዩብ ቻናል NEX Comps ብትጎበኙ እያንዳንዳችሁን በጣም አመሰግናለሁ
HTML Embed Code:
2024/04/24 06:05:57
Back to Top