Channel: Sheger Press️️
Sheger Press️️
Photo
#በበረሀው ውስጥ አርባ ሰባት አመት ኖረች
ትውልዷ ከእስክንድርያ፣ ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው። በአስራ ሁለት ዓመቷ የሰው ሁሉ ጠላት ሰይጣን ሸንግሎ አሳታት፡፡ በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ፡፡ ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ስጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና። በየእለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር። ሰውን የሚወድ የእግዚአብሄርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት። ከእነርሱና ከሌሎች ሰዎችም ጋራ በመርከብ ተሳፈረች። ባለ መርከቦችም የጉዞ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ስለ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው፡፡ የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወደ አለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት። እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም።
ይህን ጊዜ የረከሰ ስራዋን አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ እግዚአብሔር አይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስእል አየች። በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጂያቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ስራዬን የፈፀምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት። ወደ ቤተ ክርስቲያን በገባችም ጊዜ የበዓሉን ስራ ፈፀመች። ከዚህም በኃላ ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም ስእል ተመልሳ፣ እያለቀሰች ነፍሰዋን ለማዳን እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ ፀለየች፡፡
አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእልም ዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ አንቺ እረፍትንና ድኀነትን ታገኛለሽ የሚል ቃል ወጣ። ወጥታ ስትሄድም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ዲናር ሰጣትና ሕብስት ገዛችበትና የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራ በበረሀው ፅኑእ ተጋድሎ እየተጋደለች በበረሀው ውስጥ አርባ ሰባት ዓመት ኖረች፡፡ ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር። እርሷ ግን በተጋድሎ ፀናች የገዛችውን ሕብስትም ብዙ ቀን ተመገበች። ሁለትና ሶስት ቀናት እየጾመች ጥቂት ሕብስት ትቀምስ ነበር፡፡ በአለቀም ጊዜ የዱር ሳር ተመገበች። ከአርባ ሰባት ዓመት በኋላ ቅዱስ አባ ዞሲማ እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ፆምን ሊፈፅም ወደዚያች በረሀ መጣ። ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚጽናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው።
በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን ምትሀት መሰለችው በጸለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት። ነገር ግን ከእርሱ ሸሸች ከኃላዋ በመሮጥም ተከተላት። እርሷም በስሙ ጠርታ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ አለችው። በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ እርሱ ካህን ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት በላዩዋም ጸለየላት። በብዙ ልመናም ገድሏን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው። በቀጣዩ ዓመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው አምጥቶም ጸልዮ አቀበላት። በሁለተኛው ዓመት ወደ ዮርዳኖስ በረሀ ሲመጣ ግብጻዊቷ ቅድስት ማርያም ሙታ አገኛት፣ አንበሳ ጉድጓዷን ቆፍሮለትም በላይዋ ፀሎት አድርጎ ቀበራት።
በዚህ የጾም ወቅት በገዳማዊ ኑሮ ያሉትን እየረዳንና በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

በድሬዳዋ የ23 ዓመት ነፍሰ ጡር በአነር ተነክሳ ህይወቷ አለፈ
በድሬዳዋ አስተዳደር አዋሌ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም፣ የ23 ዓመት ነፍሰ ጡር በአነር ተነክሳ ህይወቷ ማለፉ ተነግሯል፡፡
ህይወቷ ያለፈው ወጣት ኡስኒያ ሙስጠፋ የተባለች ግለሰብ ስትሆን፤ ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰአት ገደማ በመኖሪያ አካባቢዋ ላይ በመንቀሳቀስ ላይ ሳለች በአነር ተነክሳ ህይወቷ ማለፉን ድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሚዲያና ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ዳግም ተፈራ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
ፖሊስ የሚመለከተው አካል በአካባቢው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበትና ማህበረሰቡ ከመሰል አደጋዎች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል፡፡
@Sheger_Press

"ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሆኖው መሾማቸውን እደግፋለሁ::
ሹመታቸውን ከኢትዮጵያ መንግስት የተስማማሁበት፣ የምደግፈውና የምቀበለው ነው። ስልጣኑ ባከተመው [በአቶ ጌታቸው ረዳ ሲመራ የነበረው ጊዚያዊ አስተዳደር\ የጠፋው ጊዜን ለማካካስ በቁርጠኝነት እሰራለሁ። ግን የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚፃረሩ የተናጠል አዋጆች ፣ ደንቦችና መመሪያዎች ከማውጣት ይቆጠብ። ብሄራዊ የክህደት ቡድኑ (የጌታቸውን አስተዳደር) ከስልጣኑ እንዲወገድ የህዝባችን አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነበር።
በደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ሕወሓት ዛሬ ካወጣው መግለጫ

የአዲስ አበባ ፖሊስ "ከኢትዮጵያውያን ባህል፣ ኃይማኖትና ወግ ተቃራኒ የሆነ በርካታ ድርጊቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሰራጨ ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውዬ ምርመራ እያጣራሁ ነው" አለ።
በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን ሲያነጋገር የነበረው ግለሰቡ፣ ሚሊዮን ድሪባ የሚባል እንደሆነ የገለጸው ፖሊስ፣ "በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስል በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታቸውን ያነሱበት ጉዳይ ሆኗል" ሲል ጠቅሷል።
"ከህዝብ ቅሬታ ባሻገር በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ፀያፍ ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈፀም ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል።" ሲል ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ "ግለሰቡ በጎዳናዎች ላይ የተለያዩ አፀያፊ በተለይም የሴቶችን ክብር የሚነካ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች በመፈፀም የቀረፃቸውን ምስሎች በመልቀቅ በፈፀመው ህገ ወጥ ተግባርና በለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል በቁጥጥር ስር አውዬው ምርመራ እያጣራሁበት ነው" ሲል መግለጫ ሰጥቷል።

#የሕማማት ማክሰኞ የጥያቄና የትምህርት ቀን
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠው ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡ አንድም በዚህ ዕለት ጌታችን በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ ዕለቱ “የትምህርት ቀን” ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር፣ ሲጠይቅ መሰንበት እንደሚገባው ይህ መጽሐፋዊ ሥርዓት ይነግረናል፡፡ የማቴዎስ ወንጌል 21÷28፣ 25÷46፣ የማርቆስ ወንጌል 12÷12፣ 13÷37፤ የሉቃስ ወንጌል 20÷9፣ 21÷38፣ የሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ማክሰኞ ዕለት የሚነገሩ ትምህርቶችን ይዘዋል፡፡ በዚህ ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡
የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች በዕለተ ሰኞ የሰራውን አንጽሆተ ቤተ መቅደስ፣ ወይም የነጋዴዎችን ንብረት መገልበጥና ማባረሩን መነሻ በማድረግ “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” ሲሉ ጠይቀውታል፡፡ ጌታችን ሰኞ በመርገመ በለስ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማከናወኑን ተከትሎ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩ ተአምራትና ድንቅ ድንቅ ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀኗቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡ ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ ጌታችን ‹‹በራሴ ሥልጣን›› ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡
ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡለት ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ ዓላማ መሳካት አመቺ ኹኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሶላቸዋል፡፡ አንድም ጌታችን ግን የፈሪሳውያንን ጠማማ ሀሳብ ስለሚያውቅ “የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው? ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር?” ሲል ጠይቋቸዋል፡፡ እነርሱም ሁለት አስቸጋሪ ሀሳች ወጥረው ያዟቸው “ከሰማይ ነው” ቢሉት “ለምን አላመናችሁበትም?” እንዳይላቸው ሰጉ፤ “ከሰው ነው” ቢሉት ደግሞ ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ መምህር ይፈሩት፣ እንደ አባት ያከብሩት ነበርና ሕዝቡ እንዳይጣሏቸው ፈሩ እናም “ከወዴት እንደ ኾነ አናውቅም” የሚል የተንኮል ምላሽ ሰጡት፡፡ እርሱም “እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው፡፡
ይህን ጥያቄ መጠየቃቸውም እርሱ የሚያደርጋቸውን ተግባራት ዅሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፤ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥሬ ስለተሞላ ነበር እንጂ፡፡ ዳግመኛም ይህ ዕለት ጌታችን ስለዳግም ምጽአቱ ሰፊ ትምህርት የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ፣ ከዋዛ ፈዛዛ ተጠብቆ የጌታችንን ውለታ፣ ሕማሙን፣ ግረፋትና ስቅለቱን፣ ሞቱንና መከራውን እያሰበ በስግደት ይህን ሳምንት ሊያሳልፈው ይገባል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን፣ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ንቀው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው፣ ዳዋ ለብሰው በምናኔ የኖሩ ቅዱሳንን ገድል ማንበብ ይገባል፡፡

የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ..‼
በኬንያ ከዛሬ ጀምሮ ለ1 ወር የሚቆይ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ ተደርጓል‼️
የኬንያ ኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ቁጥጥር ባለስልጣን (EPRA) ትናንት እንዳስታወቀው
📌የቤንዚን ዋጋ በሊትር የ1.95 የኬንያ ሽልንግ፣
📌የናፍጣ ዋጋ በሊትር የ2.20 የኬንያ ሽልንግ እና
📌የኬሮሲን ዋጋ በሊትር የ2.40 የኬንያ ሽልንግ የዋጋ ቅናሽ ተደርጎባቸዋል ብሏል።
ባለስልጣኑ ነዳጅ ከውጪ የሚገባበት ዋጋ በየካቲት እና መጋቢት ወር መቀነሱን የገለፀ ሲሆን:
📌ቤንዚን የ4.89%፣
📌ናፍጣ የ6.45% እና
📌ኬሮሲን የ6.53% የዋጋ ቅናሽ ማድረጋቸውን ገልጿል።
📌ቤንዚን በሊትር 174.63 ሽልንግ (178.97 ብር)፣
📌ናፍጣ በሊትር 164.86 ሽልንግ (168.96 ብር) እንደዚሁም
📌ኬሮሲን በሊትር 148.99 ሽልንግ (152.70 ብር) በሆነ ዋጋ በናይሮቢ እንደሚሸጡም ተገልጿል።
ኬንያ በነዳጅ ምርት ላይ የ16% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምትጥል ሲሆን ከላይ የተገለጸው ዋጋም ይህንን አካቶ እንደሆነ ተገልጿል።

ዶ/ር ደብረጺዮን ስለ ፕሪቶሪያው ስምምነት ምን አሉ⁉️
የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፣ የአፍሪካ ኅብረት የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ተከታታይ ከፍተኛ ቡድን በፍጥነት በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አፈጻጸም ላይ እንዲወያይ መጠየቃቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ደብረጺዮን ይህን የጠየቁት፣ የአፍሪካ ኅብረት የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ተከታታይ፣ አረጋጋጭና ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ከፍተኛ ሃላፊ ኾነው አዲስ ከተሾሙት ሜጀር ጀኔራል ሳማድ አላዴ አሶዴ ጋር ዛሬ መቀሌ ውስጥ በተወያዩበት ወቅት ነው።
ሕወሓት እና መንግሥት በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት እስካሁን የፖለቲካ ውይይት እንዳልጀመሩና የፓርቲው ሕጋዊ እውቅና እንዳልተመለሰለት ደብረጺዮን መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
አፍሪካ ኅብረት ጀኔራል ሳማድን የሾመው፣ የሥራ ጊዜያቸውን ባጠናቀቁት ጀኔራል እስጢፋኖስ ራዲናን ምትክ ነው። ሕወሓት ከኮሚቴው ጋር በትብብር እንደሚሠራ ያረጋገጡት ደብረጺዮን፣ ኮሚቴው መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ኹኔታ በግልጽ በመለየት ሪፖርት እንዲያቀርብ ጠይቀዋል ተብሏል።

#MoE
" ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)
በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ሳይገቡ በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ጠቁመዋል።
ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፤ " በሚቀጥለው ዓመት ላይደርስልን ይችላል ግን ህጋዊ ስርዓቱን በሙሉ ጨርሰን በ2019 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች ከ2019 ጀምሮ 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይድረጋል " ብለዋል።
" ከዚህ በፊት የነበረ ነው አዲስ አይደለም በጃንሆይ ጊዜ (በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ማለታቸው ነው) የነበረ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ሁለት ጥቅም አለው ብለን ነው ይሄን የምናደርገው አንደኛ ልጆቹ ዝም ብሎ የቀለም ትምህርት ብቻ ተምረው ሳይሆን ተግባራዊ የሆነ ትምህርትም ለአንድ ዓመት ሄደው የሚሰሩበት ከማህበረሰቡ ጋር የሚተዋወቁበት ነው። ሁለተኛ የአስተማሪዎች እጥረትም ስላለ ልጆችን ወደ አስተማሪነት ለአንድ አመት ቢሆንም ለማስገባት ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

ባለፉት 9 ወራት ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ከትራፊክ ቅጣት መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣናት ተናገረ።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ባለፉት 9 ወራት ከትራፊክ እና ከመሰል ቅጣቶች በአጠቃላይ ከ700ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ተናግሯል።
በከተማዋ ከሚስተዋለው የትራፊክ ደንብ ጥሰት ውስጥ 40 በመቶው የፍጥነት ወሰን ህግን አለማክበር ነው ተብሏል።
የትራፊክ ቁጥጥሩን ለማዘመን፣ የሙስና ተጋላጭነትን እና የደንብ ጥሰትን ለመቀነስ፣ የተገልጋዮችን እንግልት ለማስቀረት እንዲሁም መሰል የአሰራር ስርአትን ለማሻሻል ዲጂታል አሰራርን እየተገበርኩ ነው ሲል ባለስልጣን መ/ቤቱ ተናግሯል።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚዴቅሳ በትራፊክ ደንብ እና በመሰል ጥሰቶች ቅጣት የምንጥለው ገቢ ለመሰብሰብ ሳይሆን ህግን ለማስከበር ነው ብለዋል።(ሸገር )

7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ኾነዋል‼️
ትምህርት ሚኒስቴር በ6ተኛው የህዝብ ተወካዮች 4ተኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ተኛ መደበኛ ስብሰባ የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርቧል፡፡
በሪፖርቱም በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች 7.2 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
በተለያዩ ክስተቶች ከ5 ሺህ 300 በላይ ትምህርት ቤቶቸ መውደማቸውን ተከትሎ ነው ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታቸው እንደራቁ የተገለጸው፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር በ9ወራት እቅድ አፈጻጸሙ ከተነሱ ጉዳዮች መካከልም የትምህረትን ጥራት ለማረጋገጥ የመምህራን ብሎም የትምህርት አስተዳደሩ አቅምን ማሳደግ ላይ እየተሰራ መሆኑ ተጠቁማሉ፡፡
በ2017 ክረምት መርሃግብርም 84 ሺህ ለሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና አስተዳደሮችን ስልጠና ለመስጠት ታቅዷል ተብሏል፡፡
(ሰላም ይልማ - NBC)

Video
#ሰባት ጊዜ ሙቶ ሰባት ጊዜ ተነስቷል
የቅዱሳኑ ተጋድሎ በዋነኝነት ከ2 አካላት ጋር ነው፡፡ በመጀመሪያ በስጋ ፍላጎትና በኃጢአት ከሚፈትኑ አጋንንት ጋር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ሃይማኖቸታችሁን ካዱ፣ ለጣዖትም ስገዱ" ከሚሉ ከሃድያን መሪዎችና ነገስታት ጋር የሚደረግ ነው፡፡ በተለይ 2ኛው እስከ ሞት የሚያደርስ ውሳኔ ይጠይቃል፡፡ ታላቁ አባ ባውላ ገዳማዊ ጻድቅ ሲሆን ትግሉ የነበረው ከአጋንንት ጋር ነው፡፡ ቅዱሳኑ ሁሌም አንድ ነገርን እያሰቡ ይኖራሉ፡፡ ይኸውም ሰማያዊው አምላክ ከዙፋኑ ወርዶ በተዋሐደው ሥጋ በቃል ሊገለጽ የማይችል መከራን ስለ እኛ መቀበሉ ነው፡፡ ክርስትና ማለት ቀራንዮን በልብ ውስጥ መሳል ነው፡፡ ፍቅረ መስቀሉን፣ የጌታንም ውለታ የሚያስብ ማንኛውም ሰው የትኛውም ዓይነት መከራ ቢመጣበት አይታወክም፡፡ ቅዱሳኑም የፍቅራቸውና የትእግስታቸው ምሥጢር ይኼው ነው፡፡
ጌታ በማቴዎስ 16÷24 "የሚወደኝ ቢኖር የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" እንዳለው ቅዱሳኑ ይህንን ቃል በተግባር ፈጽመውታል፡፡ ታላቁ አባ ባውላ በላይኛው ግብጽ አካባቢ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተወለደ፡፡ ከክርስቲያን ወላጆቹ መንፈሳዊ ነገሮችን ተምሮ በወጣትነቱ መንኗል፡፡ ያ ዘመን እልፍ አእላፍ ቅዱሳን የነበሩበት ነውና ወደ ጠመው አካባቢ ሔዶ ምናኔን ተምሯል፡፡ ሥርዓተ ገዳምን፣ አገልግሎትን፣ ፍቅርን፣ ተጋድሎንና የመሳሰሉትን ከተማረ በሁዋላም ደቀ መዝሙሩን አባ ሕዝቅኤልን አስከትሎ ለዋናው የተጋድሎ ሕይወት ወደ በርሃ ወጣ፡፡ አባ ባውላ ዘወትር በፍቅረ ክርስቶስ ይመሰጥ ነበርና "ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ለኃጥአን ኃፍረተ መስቀልን ታግሠህ ከሞትክልን እኛ ደግሞ ስለ ንጹሑ አምላክነትህ ስንል እልፍ ሞትን መታገስ አለብን::" ብሎም ዘወትር ያስብ ነበር፡፡ ተጋድሎውም በዚህ የተቃኘ ነበር፡፡
በዚህ እጅግ የጸና ተጋድሎው ምክንያትም 7 ጊዜ ሙቶ 7 ጊዜ ተነስቷል፡፡ እግሩን ከረዥም ዛፍ ላይ አስሮ፣ ወደ ታች ተዘቅዝቆ እህል ሳይቀምስ እንቅልፍና ዕረፍት ሳይሻ ሲጸልይ፤ ደሙ በአፍ በአፍንጫው ፈሶ አለቀ፡፡ በ40ኛው ቀንም ሲሞት መልአከ እግዚአብሔር ከሞት አስነሳው፡፡ ጥልቅ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ ለ40 ቀናት ሲጸልይም በ40ኛው ቀን ለ2ኛ ጊዜ ሞቶ ቅዱስ መልአክ ከሞት አስነሳው፡፡ በሚኖርበት ጠመው አካባቢ ወደሚገኝ ረዥም ተራራ ጫፍ ወጥቶ፤ የተጠራረቡ ድንጋዮች ተመለከተ በቅጽበት የጌታ ኅማማት ከፊቱ ቢደቀንበት ከላይ ወደ ታች ተወርውረ፣ ጥርብ ድንጋዮቹም እየተቀባበሉት አካሉ እየተነከፈና እየተቆራረጠ በየመንገዱ ቀርቶ ሲሞት አሁንም ፈጣሪው ከሞት አስነሳው፡፡
ከዚህ በኋላም ሁለት ጊዜ ሞቶ ተነስቷል፡፡ በመጨረሻም የጌታን ሕማማት እያሰበ ወደ ጽኑ ቆላ ወረደ፡፡ አሸዋ በሞላው ስፍራ ቆሞ ሲጸልይም አሸዋው ውጦ ደፈነውና ለ7ኛ ጊዜ ሞተ፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ሊያስነሳው የመጣው እንደ ወትሮው ቅዱስ መልአክ ሳይሆን ራሱ የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ ነበር፡፡ ጌታችን አባ ባውላን ከሞተበት አስነስቶ "ወዳጄ ባውላ! ስለ እኔ ፍቅር እጅግ ተሰቃየህ አሁንም ይበቃሃል፡፡ መጥቼ እስክወስድህ ድረስ ከአባ ብሶይ ጋር ቆይ" ብሎት ባርኮት ዐረገ፡፡ አባ ባውላም እንደ ታዘዘው በአባ ብሶይ ገዳም ከቅዱስ ብሶይ ጋር ቆይቶ ሚያዝ 7 ቀን ለ8ኛ ጊዜ ዐርፏል፡፡ በረከተቱ ትደርብን፡፡

ከሩሲያ ጋር ጦርነቱን የጀመረው ዘለንስኪ ነዉ - ዶናልድ ትራምፕ
ትራምፕ ከሩሲያ ከፍተኛ ጥቃት በኋላ ጦርነት በመጀመሩ ዘሌንስኪን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
በዩክሬን በደረሰ እና ከባድ ነዉ በተባለ የሩሲያ ጥቃት 35 ሰዎች ሲሞቱ 1መቶ17 ሌሎች ቆስለዋል።
በሶስት ሰዎች ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል ያሉት ትራምፕ፤ ለዚህ ጦርነት ምክንያት ፑቲን የመጀመሪያዉን ሃላፊነት ይወስዳል፣ ሁለተኛዉ ምን እንደሚያደርግ እንኳን የማያዉቅ የነበረዉ ጆ ባይደን እና ሶስተኛዉ ደግሞ ዘለንስኪ ናቸዉ ብለዋል፡፡
የትራምፕ አስተያየት ሩሲያ እሁድ እለት በዩክሬኗ ሱሚ ከተማ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱን ተከትሎ የመጣ ሲሆን፤ ይህም በዚህ ዓመት ሩሲያ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያደረሰችዉ እጅግ የከፋ ጉዳት ነዉ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ38 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ መሰረተ ልማቶች መውደማቸውን የትግራይ ክልል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በዚህም መንገዶች፣ መብራት፣ የቴሌኮምና ውሀ መስመሮች ጭምር መቋረጣቸውን አስረድቷል፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ሀፍቱ ሚካኤል ሲናገሩ ‹‹በመሰረተ ልማቶች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት የሰላማዊ ሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል›› ያሉ ሲሆን ለዚህም በቅርቡ ለመቀሌ ውሀ ያቀርብ በነበረው ትራንስፎርመር ላይ የደረሰውን አደጋ እንደምሳሌ አንስተዋል፡፡
ይህ ወደአምስት መቶ ሺህ ለሚቆጠሩ የመቀሌ ነዋሪዎች በሚቀርበው ውሀ ላይ ተፅእኖ መፍጠሩን ገልፀውም ስርቆት የሚፈፅሙት ሰዎች በክልሉ ያለውን የፖለቲካ ውጥረት እንደመልካም አጋጣሚ መጠቀማቸውን አስረድተዋል፡፡
ኮሚሽኑ ትናንት ባዘጋጀው ፎረም ላይ ማብራሪያ የሰጡት ኮማንደር ወርቄ ገብረህይወት በበኩላቸው ‹‹እንዲህ አይነቱ ድርጊት ተራ የወንጀል ባህርይ የሌለው ነው፡፡
ውድመቱ የሚፈፀመው ሆነ ተብሎ ለሰዎች የእለት ተእለት ህይወት አስፈላጊ በሆኑ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ አድርጎ ነው፡፡ ስለዚህም ከስርቆት ወይንም ከሌብነት የበለጠ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያለው ነው›› ማለታቸውን ወጋህታ ፋክትስ ዘግቧል፡፡

መንገድ ላይ ሽንት የሸኑ ግለሰቦች 100,000 ብር ተቀጡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመርካቶ እና በመሳለሚያ አካባቢ በመንገድ ሽንት በመሽናት ደንብ ቁጥር 167/2016 የተላለፉ 50 ግለሰቦች እየዳዳቸው 2000 ብር በድምሩ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን ውብና ፅዱ ለማድረግ ቀንና ማታ እየሰራ ባለበት ወቅት አንዳንድ ሀላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች የተማውን ፅዳት ሲያበላሹ ህብረተሰቡ አካባቢውን ሊጠብቅ እንደሚገባ ተገልፃል።
ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 167/2016 ላይ ለህብረተሰቡ በተለያዩ አግባቦች ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱ የገለጸ ሲሆን ደንብ በሚተላለፉ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ተመዘገቡ‼️
ጽናጽል ከበሮና መቋሚያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ንብረት ሆኖ ተመዘገበ‼️
"ጸናጽል፣ ከበሮና መቋሚያ ከሌሎች ከ10 በላይ ቅዱሳት መጽሃፍት ጋር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዐዕምሮአዊ ንብረት መሆናቸው ተረጋግጦ ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዘግበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው እውቅና አግኝተዋል"
Via የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ህዝብ ግንኙነት

HTML Embed Code: