TG Telegram Group Link
Channel: ቆየት ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች
Back to Bottom
Forwarded from MAK BAG
MAK TOTE BAGS
Quality products
Free delivery some places in A.A
📞251 933 00 38 66
Forwarded from dc
በህይወታችን ችላ ያሉ እየመሰሉ በቁስላቸው ደስታችንን ላለማበላሸት ሲሉ ከአከባቢያችን የሚርቁ ሰዎችን ግን ፈጣሪ ያስባቸው 🙏🙏
Forwarded from Eyob Shiferaw
....ጥላቻና ፍቅር....


ጥላቻና ፍቅር እየተሽከረከረ
አዕምሮዬ ቢዞር ልቤ እየሰከረ
ረብ የለሽ ህይወት ህይወት አልባ ኑሮ
እንዲያው መጮህ ብቻ ልክ እንደከበሮ

ወዝ አለው ከበሮ ካልሆነ በባዶ
ልብን ያስደስታል በዜማ ታጅቦ
ጭብጨባ እልልታ በበዛበት ቦታ
ዝም ብሎ አይደለ ከበሮ ሲመታ
በወግ በአግባቡ በጥበብ ሲደለቅ
ከበሮ ድንቅ ነው ወደ ጆሮ ሲዘልቅ

አለሁ እንጂ እኔ ከከበሮ ያነስኩ
መቀደስ አቅቶኝ በሀጥያት የረከስኩ
ሰሚ እስከማጣ በደሌ የከፋ
ጽድቅን እየገፋሁ ለሀጥያት ምለፋ
መልካም ድምጽን ትቼ ክፋትን ምሰማ
ሀጥያት ሲደልቀኝ ክፋትን ማሰማ

አለሁ እኔ ከንቱ
ያነስኩኝ ከስንቱ
የጠፋኝ መንገዱ
የቃጣኝ ማበዱ

ፍቅርን ለመፈለግ
ጥላቻን የማድግ
ጥላቻን ሳብራራ
በፍቅር ሳቅራራ
ውል መንገዴን ስቼ
ከራሴው ጋር ተጣልቼ
እንዲያው መጮህ ብቻ
እኔው በእኔው ዛቻ።


ኢዮብ
ሰኔ 07/2015 ዓ.ም
04፡42 ማታ
Forwarded from Eyob Shiferaw
HTML Embed Code:
2024/04/30 02:00:21
Back to Top