TG Telegram Group Link
Channel: Natnael Mekonnen
Back to Bottom
ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛውን እጅግ ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ አገልግሎት በአዲስ አበባ አስጀምሯል።

ስራ የጀመረው ሁለተኛው ጣቢያ ከመገናኛ ቦሌ መንገድ አንበሳ ጋራጅ ፊት ነው የሚገኘው።

ይህ ጣቢያ የአውሮፓ ስሪት የሆኑ መኪኖችን የኤሌክትሪክ ኃይል መሙላት የሚያስችል እጅግ ፈጣን አቅም ያለው ተብሏል።

የኤሌክትሪክ መኪና መሙያዎቹ በ1 ሰከንድ 1 ኪሎሜትር ለመጓዝ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ኃይል በመሙላት በ15 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ (100%) የኤሌክትሪክ ኃይል የመሙላት አቅም እንዳላቸው ኩባንያው አሳውቋል።

በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ የባትሪ መስፈርቶች እና የደንበኛን ትዕዛዝ በመተንተን የባትሪውን ደህንነት እየፈተሸ የተሽከርካሪው ባትሪ በሚችለው ፍጥነት ቻርጅ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።

ኩባንያው ቀደም ሲል 16 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል ጣቢያ ወደስራ ያስገባ ሲሆን ከየካቲት 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ14,280 የኤሌክትሪክ መኪኖች፣ በ376,574.72 ኪሎዋት/ሰዓት ኃይል ቻርጅ ማድረግ እንደቻለ አመልክቷል።

አዲሱ የመሙያ ጣቢያ 4 እጅግ በጣም ፈጣን እና 12 በጣም ፈጣን መሙያዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ይህም ያሉንን የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያዎች የማስተናገድ አቅም ወደ 32 ለማድረስ አስችሏል፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ (Direct/ Whatsapp) ፦ በ 0987170752 / 0987335552 ይደውሉ
ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር እንዲሆን ተወሰነ

ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ባለው አከባቢ ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት፣ የምርምር፣ የእውቀትና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል የዩኒቨርሲቲ መንደር እንዲመሰረት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አፅድቋል።

ካቢኔው በ4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባው አራት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችንም አስተላልፏል።

የፕላንና ልማት ቢሮ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር አጥንተው ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር እንዲሆን በአካባቢዉ ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት፣ የምርምር፣ የእውቀትና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል አግባብ በመቅረቡ የመንደር ምስረታው ውሳኔው አፅድቋል፡፡
በደቡብ ኣፍሪካ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ አየደረሰ ያለው ደም መፍሰስ ፣ መታገት፣ መዘረፍ፣ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መደረሱ አሳሳቢ አየሆነ ነው።

በአሁኑ ሰዓት በደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ወንጀሎች መልካቸውንና የአካሄዳቸውን እንዲሁም አቅጣጫውን ቀይረው አንደ ISIS አይነት የአለም አቀፍ አሽባሪ ድርጅቶች ሰለባ መሆናቸው ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጏል ።

በዚህ አሽባሪ ድርጅት ውስጥ አባል በሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያውያን አየተቀነባበረ የኢትዮጵያውያን መጋዘን አንዲሁም መኪኖችን መዝረፍ ሱቆችን በማቃጠል በመደበኛነት ከፍተኛ ገንዘብ ለአሽባሪ ቡድኑ አንዲከፈል እያስገደዱ ይገኛሉ:: አንከፍልም ባሉ ወገኖች ላይ አስከ ግድያ የሚደርስ ቅጣት አየተፈጸመ ይገኛል ።

ለዚህም በቅርቡ ከሞት የተፈረፉ በተለይ አንደኛው በቅርበት የማውቀው ወዴጄ በምታዩት መልኩ አፈና ተደርጎበት በደቡብ አፍሪካ ልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት በሂልኮፕተር በታገዘ ስለላ ከአፈናውና ሞት ተርፏል::

ከላይ በገለጽኩላችሁ በቅርቡ በአንድ ኢትዮጵያዊ ነጋዴ ግለሰበ ላይ በተፈጸመ የማፈን ተግባር የደቡብ አፍሪካ የጸጥታ አካሎች በአደረጉት ርብርብ የታጋቹን ህይወት ለማትረፍ ቢቻልም ነግሩን ለየት አንዲል ያደረገውና ተግባሩን ያካሄደው (ወንጀሉ የተቀነባበረው) በኢትዮጵያውያን የሽበሩ ቡድን አባላት መሆኑ ነው:: እጅ ከፍንጅ ተይዘው በሕግ ጥላ ስር ሆነው መንግስትና የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እንዲሁም ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ከፍተኛ መርመራ እየተካሄደም ይገኛል::

በሂደቱም ብዙዎቹ ወንጀለኞችና በህግ ጥላ ሰር ያሉት ግለስቦች በአገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ግዜያት በሚደርስ ዝርፊያና አደጋዎች አጃቸው አንዳለና በወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ እንዲሁም በአሜሪካና በሌሎች አገራት የንብረት አገዳ አግድ ላይ ስም ዝራቸው ያለ መሆኑ ተገልጿል ።

ስለሆነም በደቡብ አፍሪካ የምትኖሩ ኢትዮያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የነገሩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በስራ ቦታ እና በመኖሪያ አካባቢያችን ሰላምን ለማስፈንና ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ስለሚደረገው ህጋዊ እንቅስቃሴ አጋር እንድትሆኑ በማክበር ልናሳስብ እንወዳለን ::
ልዩ መረጃ‼️

የኦብነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አብዲራማን ማሃዲን ከድርጅቱ ሊቀመንበርነት አነሣ

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ማዕከላዊ ኮሚቴ እያካሄደ በሚገኘው 2ኛ መደበኛ ስብሰባ አብዲራህማን ማሃዲን ከድርጅቱ ሊቀ መንበርነት አንሥቷል።

አብዲራህማን ማሃዲ ከድርጅቱ ሊቀመንበርነት ለመነሣታቸው የድርጅቱን አንድነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራትን ማከናወናቸው በምክንያትነት ተጠቅሷል።

ግንባሩ መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ወደ ሀገር ከገባ ጊዜ አንሥቶ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ ለሕዝብ የገባው ቃል ተግባራዊ እንዳይሆንም በግላቸው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ተጠቁሟል።

ኦብነግ በወርሃ ነሐሴ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ነበር መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ ወደ ሀገር የገባው።

ማዕከላዊ ኮሚቴው እያካሄደ በሚገኘው መደበኛ ስብሰባ በቀጣይ ለሚካሄደው ጉባኤ የጉባዔ አደራጅ ኮሚቴ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ሰበር መረጃ

የኦብነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አብዲከሪም ሼክ ሙሴ (ቀልቢ ደጋህ)ን የግንባሩ ተጠባባቂ ሊቀመንበር አድርጎ ሰየመ።

የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር እያካሄደ በሚገኘው 2ኛ መደበኛ ስብሰባው ከሀላፊነታቸው በተነሱት አብዲራህማን ማሃዲ ምትክ የግንባሩ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር የነበሩትን አብዲከሪም ሼክ ሙሴ የግንባሩ ተጠባባቂ ሊቀመንበር አድርጎ ሰይሟል።

አቶ አብዲከሪም ሼክ ሙሴ ኦብነግ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ በነበረበት ወቅት ለ20 አመታት የኦብነግ ወታደራዊ ክንፍ ከፍተኛ የጦር ኮማንድር ሆነ አገልግለዋል።

ድርጅቱ የግንባሩን ሊቀ መንበር በጠቅላላ ጉባኤ እስኪመረጥ ድረስ አብዲከሪም ሼክ ሙሴ (ቀልቢ ደጋህ) የግንባሩ ተጠባባቂ ሊቀመንበር ሆነው ይቀጥላሉ።

የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ማዕከላዊ ኮሚቴ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ከመጋቢት 30/ 2017 እስከ ሚያዚያ 2/2017 ዓ.ም ድረስ በጅግጅጋ እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ዜና ቡጢ 🥊

ትናት በዋሽንግተን ዲሲ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው መንጋጭላውን በቡጢ ተመትቶ መነጽሩ አይኑ ላይ የተሰበረውና መንጋጭላው የወለቀው ይልቃል ጌትነት የአቶ ገዱ ላይ ሊመሰርት የነበረውን ክስ በሸምጋዮች አማካኝነት በመተው በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሊሰጡ እንደሆነ ታውቋል:: ሚዲያም እየተመረጠ መሆኑን ሰምቻለሁ:: ይልቃል ጌትነት አቶ ገዱ ላይ ሊያቀርብ የነበረውን ክስ የተወው ሁለቱም ገና ለአሜሪካ መንግስት የስደት ጥያቂያቸውን ጠይቀው ጉዳያቸው እየታየ ለሆነ ሁለቱም ላይ ሌላ ተጽኖ ያመጣል በሚል እንደሆነ መረጃውን ሹክ ተብያለሁ:: አሁን በየትኛው ሚዲያ ላይ በመውጣት ማስተባብያ እንስጥ በማለት ሚዲያ እየተመረጠ ነው::
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ (Direct/ Whatsapp) ፦ በ 0987170752 / 0987335552 ይደውሉ
በትግራይ ክልል ባለፈው ሁለት አመት 1664 ሰዎች በተቀበሩ ፈንጂዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለፀ፡፡

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከተፈፀመ ወዲህ ይህንን ያህል ቁጥር ያላቸው ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው ከእነዚህ ውስጥ 259ኙ ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ የመልሶ ግንባታና ልማት ድርጅት(ራዶ) አስታውቋል፡፡

አለም አቀፍ የፈንጂ ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀንን ምክንያት በማድረግ በመቀሌ በተደረገ ስብሰባ ላይ የራዶ ሀላፊው አቶ ተስፋይ ገብረማሪያም እንደገለፁት የተቀበሩ ፈንጂዎችና ጥይቶች አሁንም በተለያዩ የትግራይ ክፍሎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡

የፈንጂ አምካኝ ግብረ ሀይል አስተባባሪ የሆኑት ኮሎኔል ተስፋይ አብርሀ በበኩላቸው በክልሉ ውስጥ በየቀኑ የፈንጂ አደጋዎች እየደረሱ መሆናቸውን ገልፀው የበጀት እጥረትና ለጉዳዩ በቂ ትኩረት አለመስጠት ስራቸውን እያደናቀፈባቸው መሆኑን አስረድተዋል ሲል የክልሉ ማስ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
🏠 በቅናሽ ዋጋ የቤት ባለቤት ይሁኑ

🏠 ሳይቶቻችን :-ካሳቺስ, ልደታ,ሲ ኤም ሲ ሚካኤል ,መሪ ቁጥር1, አያት ዞን 2,3,እና 8

🏠 ጊዜው አሁን በማይታመን አጋጣሚ የቤት ባለቤት ይሁኑ

💎ከባለ 1 እስከ 4 መኝታ አፓርታማዎች
💎ከአያት ቤት መግዛት አሁን ነው ።

1. በ8% -20% አነስተኛ ቅድመ ክፍያ
2. የሳይት አማራጭ
3. በ ኢትዮጵያ ብር
4, 60/40 የብድር አግልግሎት

በተጨማሪ በሲኤምሲ የሚገኘው ትልቁ ሞላችን አያት ግራንድ ሞል ከ21 ካሬ ጀምሮ የንግድ ሱቅ በታላቅ ቅናሽ በሽያጭ ላይ እንገኛለን።

ዉጭ ሀገር ለምትኖሩ ዳስፖራዎች በህጋዊ ተወካይ በኩል መግዛት ትችላላችሁ።

ግንባታቸው 85 % የደረሱ ቦታዎች
_ሲኤም ሲ
_አያት ባቡር ጣቢያ
_ጣፎ (ክብር ደመና )
#የካሬ አማራጮች
- 40-145 ድረስ

እንዲሁም የስምንት ትርፋማ ድርጀቶች የአክስዮን ሽያጭ ላይ እንገኛለን::

ይደውሉ
📞☎️ 0942585355
"የተደራጁ የኢኮኖሚ ወንጀሎችንና አሻጥሮችን ማምከን፤ ብሎም ፈጻሚዎቻቸውን ለሕግ ማቅረብ ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ነው፡፡ ከየትም አቅጣጫ የሚነሡ ሕገ ወጥ የሰዎች፣ የሸቀጦች እና የመሣሪያዎች ዝውውሮችን የሚከላከሉና የሚያስተካክሉ ሕጋዊና ተቋማዊ አሠራሮችን መዝርጋት ተገቢ ነው፡፡ የገንዘብ፣ የኢኮኖሚና የአስተዳደር ተቋማት ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን አስተዳደራዊና ሕጋዊ ርምጃዎች እንዲወስዱ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

"የኢትዮጵያን ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነት የሚያሳድጉ የዲፕሎማሲ ውጤቶች እየጨመሩ መጥተዋል፡፡ ይሄን ይበልጥ በማስፋፋትና በማጠናከር የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስከበር ተገቢ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት መብት ለማስከበር ዲፕሎማሲያዊ፣ ሕጋዊ እና ሰላማዊ መንገዶችን መሠረት አድርጎ የተጀመረው ሥራ በተጀመረው ግለት እንዲቀጥል የሚያስችል አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡"
- በ4 ኪሎ ቤተመንግስት ከተካሄደው የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት መግለጫ ላይ
HTML Embed Code:
2025/04/10 12:45:37
Back to Top