TG Telegram Group Link
Channel: የስብዕና ልህቀት
Back to Bottom
ከወሲብ ባሻገር

ኦሾ፣ አንተ ወሲብ የማይረባ ነገር መሆኑን ስትናገር ሰምተን እንደገና ሞክረነው ነገር ግን አልገባንም የማይረባ የሆነው ምኑ ላይ ነው?”


እየነገርኳችሁ የነበረው ስለ ሌላ ነገሮች ነው፡፡ እሺ እነሱን ሞከራችኋቸው፡፡ በየቀኑ ስለ መመሰጥ እነግራችኋለሁ ነገር ግን እያረዘማችሁ (ላለማድረግ እያዘገያችሁ) ወሲብን ግን ትሞክራላችሁ አያችሁ ይህ ነው እንግዲህ ቀሽምነታችሁን የሚያሳየው፡፡

ወሲብ የማይረባ አይደለም እናንተ ናችሁ የማትረቡት፡፡ ለዚህ ነው በእናንተ ምክንያት ተራ ወሲብ የማይረባ የማይሆነው፡፡ ማሳደግ ካልቻላችሁ፣ ንቁም ካልሆናችሁ ቀሽምነቱን ልትረዱት አትችሉም፡፡ በተመሳሳይ ደረጃ ሆናችሁ መገንዘብ አትችሉም፡፡

ወደ እብዶች ቤት ሂዱ አንድ እብድ ፈልጉና “እብድ ነህ" በሉት ነገር ግን ቅሉ ፍፁም ይናደድባችኋል፡፡ ማንም እብድ  መሆኑን አይቀበልም፡፡ "ምን እያወራችሁ ነው? ከእኔ በስተቀር አለም በሙሉ እብድ ነች" ይላችኋል፡፡ አንድ እብድ እብድነቱን አመነ ማለት በእርግጠኝነት ከእብድነት አለም እየወጣ መሆኑን ማወቅ ይኖርባችኋል፡፡


መመሰጥን ማግኘት ካልቻላችሁ የተሻለ መመልከት፣ ከተለየ አቅጣጫ መረዳት አትችሉምና የማይረባ መሆኑን ልትረዱት አትችሉም፡፡ አሁን እናንተ ምንም የምልከታ አቅጣጫ የላችሁም፡፡ ዝግ ናችሁ ዝግ፡፡
ወደ መስታውት ቅረቡ አፍንጫችሁ መስታወቱን እስኪነካ ድረስ፡፡ አስተውሉ በፍፁም ፊታችሁን ማየት አትችሉም፡፡ የመስታውቱ ችግር አይደለም፡፡ ከመስታወቱ ራቅ ስትሉና ቦታ ስትሰጡት አንፀባርቆ ፊታችሁን ያሳያችኋል ስለዚህ ከመስታውቱ ራቁ።

ወሲብ ትልቁ ተወዳጅ ነገር ይመስላል፡፡ ወንድ በሴት ይማረካል ሴትም በወንድ ትማረካለች፡፡ አንዱ የሚያስፈልገው ነገር ሁሉ የወሲብ አጋሩ ያለው ይመስለዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ሁለቱንም ለማኝ ያደርጋቸዋል፡፡ ፍላጐታቸውን ሁሉ ከወሲብ ጥላ ጀርባ የሚያገኙት ይመስላቸዋል፡፡

እንደዚህ አይነት ነገሮችን እንድትሰሩ የሚያደርጋችሁ ውስጣችው ያለው ሆርሞናችሁ ነው፡፡ ስነህይወታዊ ቀመር ነው፡፡ ምን እየሰራህ እንደሆነ፣ ለምን እየሰራኸው እንደሆነ ማየት ብትችል ለራስህ ይገርምሀል። ወሲብ በመፈፀምህ ያገኘኸው ነገር ምን ይሆን?፡፡ንቁ መንፈስ ውስጥ በምትገባበት ወቅት ምን እያወራሁ እንደሆነ ይገባሀል፡፡ ነገር ግን ንቁ መንፈስህ ጥልቅነት የሌለው በመሆኑ እያደገ ይገድልሀል እናም ወደ ነበርክበት የስህተት ጐዳና ትመለሳለህ።

እንደገና ሞክረው ነገር ግን ስትሞክረው እያስተዋልክ እና እየተመሰጥክ ይሁን፡፡ ያን ጊዜ ወሲብን ፈፅመህ ላለማድረግ ትወስናለህ ወይም ተፈጥሯዊ አስገዳጅ ሀይል መሆኑን ትረዳለህ፡፡

እኔን ልትሸውዱኝ አትችሉም፡፡ እኔ ወሲብ የማይረባ ነው ስላልኳችሁ የፈፀማችሁት ይመስላችኋል?፡፡ ወሲብ በጣም ምርጥ ነው፣ ወሲብ በጣም የማይረባ ነገር ነው ብላችሁ አልያም ስለወሲብ አለመናገርን ብመርጥ እናንተ ከመፈፀም ወደኋላ አትሉም፡፡
ወደ አእምሯችሁ ተመልከቱ፡፡ እንዴት እራሳችሁን እያታለላችሁ እንደሆነ ለመረዳት ሞክሩ፡፡ አለበለዚያ እኔ ምን እያወራሁ እንደሆነ የንቃት ደረጃችሁ ካላደገ ፈፅሞ ልትገነዘቡኝ አትችሉም፡፡ የበለጠ ነገር ለማየት ከፈለጋችሁ ከዚህ የበለጠ ማሻሻል (ማደግ) አለባችሁ፡፡

ለምሳሌ እኔ አንድ መንገድ ዳር ላይ ያለ ዛፍ ጫፉ ላይ ሆኜ እናንተ በመንገዱ ላይ እየሄዳችሁ ጋሪ እየመጣ ነው" ብላችሁ "ምንም ጋሪ አይታየኝም ጋሪ የለም ትሉኛላችሁ፡፡ ነገር ግን እኔ ጋሪውን ማየት የምትችሉት ወደ እናንተ በቀረበ ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ አልፏችሁ ሲሄድ እንደገና ከእይታችሁ ውጪ ይሆናል፡፡

አሁንም ወደ በለጠ ከፍታ በወጣችሁ ቁጥር የተሻለ ማየት ትችላላችሁ፡፡ የከፍታ ቁንጮ ላይ ስትሆኑ ሁሉንም ነገር ታያላችሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለፈም ይሁን መጪ ጊዜ የለም ያለው አሁን ብቻ ነው፡፡ እውነታው ሲገባችሁ ወሲብ በጣም የማይረባ አና ለረጅም ጊዜ በባርነት የሚይዝ መሆኑን ትረዱታላችሁ፡፡ እያጣጣልኩት (እየነቀፍኩት) አይደለም ነገር ግን እውነታው ይህ ነው እኔም የተናገርኩት ያንኑ ነው፡፡ አያችሁ በውስጡ ዘልቃችሁ በመግባታችሁ በባርነት አስሮ ምን እየሰራችሁ እንደሆነ እንኳን ማየት እንዳትችሉ ወደ ንቃት እንዳትመጡም አድርጓችኋል።

ወሲብ ከሚያሰክሩ (ስነህይወትህ) ውስጥ ነው፡፡ በደምስሮችህ ውስጥ የሚያሰራጨው ነገር በሱስ ተለክፈህ ምን እንደምትሰራ እንዳታውቅ እና ስሜቶችህን መቆጣጠር እንዲሳንህ ያደርጋል፡፡ በተደጋጋሚ እንድትፈፅመው የሚያስገድድህ ያልታወቀ ሀይል አለ እንደፈለጋችሁ ልትጠሩት ትችላላችሁ፡፡ በንቁ ጊዜያቶችህ ግን የማይረባ ነገር ስለምትረዳ "ምን እየሰራሁ ነበር? ለምን? ምን ነገርስ አገኘሁ?" በማለት ትጠይቃለህ፡፡ለዚህ ነው ብዙ ሴቶች ከወሲብ በኋላ የሚያለቅሱት እና የሚያዝኑት ምክንያቱም ሁሉም ነገር ትርጉም አልባ ሆኖ ያገኙታል፡፡ ለጊዜው ስሜትን የሚያነሳሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ቢደጋገምም የትም አያደርስም፡፡ ወንዱ ከወሲብ በኋላ ወዲያውኑ ይተኛል ምክንያቱ ደግሞ በተረጋጋ መንፈስ ስላደረገው ነገር ማሰብ አለመፈለጉነው ጧት ሲነሳ ሁሉንም ነገር ይረሳል፡፡

በርግጥ ይገበኛል ጥሩ ነው ብለህ አምነህ የምትኖርበትን ልምድ ሲያንቋሽሹብህ አትወድም። ማንም ጅል ሲባል ደስ አይለውም፡፡ የምትረበሸው ስለ ወሲብ ባለህ ጥያቄ ሳይሆን በህይወትህ በራሱ ነው፡፡ ጅል ከሆነ እና ከኖርክባት አንተም ጅል እየሆንክ ነው። በርግጥ ያስቆጣል ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ ከሱ የተሻሉ መልካም ነገሮች በህይወት ውስጥ መኖራቸው መናገር ይኖርብኛል፡፡ወሲብ ጅማሮ እንጂ ፍፃሜ አይደለም፡፡ እጥብቀህ እስካልያስከው ድረስ እንደ መጀመሪያ ያህል ከተጠቀምክበት ምንም ችግር የለውም፡፡

ፍቅር ከሰራህ በኋላ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል በዜን እሳቤ ተቀመጥ ያን ጊዜ የምለው ይገባሀል፡፡ ወሲብ ጅል ነው የምለው ለምን እንደሆነ ይገባሀል፡፡ ከወሲብ በኋላ ለአንድ ሰዓት ያህል ስለተፈጠረው ነገር አስብ፡፡ አውቀህ ነው ወይስ ስሜትህ አስገድዶህ? አውቀህ ከሆነ ጅል አይደለህም፡፡ ተገዢ ከነበርክ ግን ጅል መሆንህን ተረዳው ምክንያቱም እየደጋገምክ በመፈፀም ራስህን ለበለጠ ባርነት እየሰጠህ ነው፡፡
በተመስጦ ብቻ ነው ምን እያወራሁ እንደነበረ ሊገባህ የሚችለው፡፡ በክርክር የሚወሰን ጥያቄ አይደለም፡፡ በራስህ ንቃት፣ በራስህ ግንዛቤ እና በራስህ ተመሰጦ የሚወሰን መሆኑን ተገንዘብ፡፡

ኦሾ
የዜን መንገድ
@Zephilosophy
@Zephilosophy
ሰዓት ተሸካሚው

ምንጭ ፦ የፍልስፍና ማዕድ
በጥበበኛው ሰለሞን

“አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ ምን ያህል ትከፍላለህ?”

ሰዓት ተሸክሞ የሚዞር አንድ ሰው፣ በመንገድ ያገኘውን አንድ ህጻን ልጅ ጠየቀ ...

ህጻኑም ያለማመንታት “አምስት ሳንቲምም አልከፍልም" አለ፡፡

ዳግም ሰዓት ተሸክሞ የሚዞረው ሰው ተመልሶ መጣና ትናንት ህጻን የነበረውን የዛሬውን ወጣት ጠየቀው “አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ ምን ያህል ትከፍላለህ?”

“ቢበዛ አንድ ወይም ሁለት ብር” ወጣቱም መለሰ፣ ግድ በሌለው አኳሃን፡፡

ይህ ወጣት ሸምግሎ ለሞቱ አንድ ሐሙስ በሚጠባበቅበት ጊዜ ሰዓት ተሸካሚው ተመልሶ መጣ፡፡

“አንድ ቀን በሕይወትህ ላይ እንዲጨመርልህ  ‌ ምን ያህል ትከፍላለህ?”

"በባህር ውስጥ ያሉ እንቁዎችን፣ በሰማይ ላይ ያሉ ከዋክብትን ሁሉ እከፍላለሁ” ሽማግሌው መለሰ፡፡

ከፍልስፍና እሳቤዎች መኻል ላይ ልናነሳው የወደድነው ጊዜ ነው፡፡ የሰው ልጅ ስለ ሁለንተና ባወቀ እና ይበልጥ በተራቀቀበት መጠን፣ መልስ አልባ ጥያቄዎችን ያነሳል። ከየት መጣን? ጊዜ መጀመሪያ አለው? ጊዜስ በራሱ ምንድን ነው? በጊዜ መስመር ውስጥስ እንዳሻን ወደ ፊት እና ወደ ኋላ መመላለስ ይቻለናል?

እነዚህን መልስ አልባ እንቆቅልሾችን ፍልስፍናዊ መልስ እንስጣቸው ብንል፣ ጊዜ በራሱ እንቅፋት ይኾንብናልና ለአሁኑ በጊዜ ወደ ኋላ መመለስ ይቻላልን? ከተቻለስ ምን ይከሰታል እና ጊዜስ ምንድን ነው የሚሉትን ሃሳቦች ብቻ እናብላላለን፡፡

ጊዜ ሰዓታችን የሚለካው ነገር እንደሆነ እናስባለን፡፡ ምድር ላይ ያሉ ክስተቶችንም በቅደም ተከተል እናስቀምጥበታለን። እናም ጊዜ በእለት ተዕለት መንከላወሳችን ውስጥ ትልቅ ስፍራን ይይዛል፡፡ ጥድፊያችንንም ኾነ እርጋታችንን የሚወስነው ጊዜ ነው፡፡ ሆኖም እንደምናስበው ወይም ይህ ነው ብለን እንደጠራነው አይነት ጊዜን በቀላሉ ፍቺ ሰጥተን አውቀነዋል ማለት አንችልም። ለብዙ ዘመናት ሳይንሳዊያን እና ፍልስፍናውያን በጊዜ ጉዳይ ሲጨቃጨቁ ኖረዋል።

ፈላስፎችን ብዙው ክርክራቸው የሚያተኩረው፣ አሁን፣ አላፊው ጊዜ እና የወደፊቱ ላይ ነው፡፡ የጊዜን የፍልስፍና እሳቤዎች በሶስት አጠቃለን መመልከት እንችላለን፡-

የአሁናዊነት (Presentism) ፍልስፍና አራማጆች የእውኑ ዓለም አሁንን እና አሁንን ብቻ ይይዛል ይሉናል፤ ትናንት አልፏል እና የእውነት አይደለም፤ ነገም አልደረሰምና የእውነት አይደለም፤ የእውነት የሆነ ነገር ቢኖር አሁን ብቻ ነው፡፡ ያለፈው ትዝታችን፤ ያልደረሰው የወደፊቱም እንዲሁ ትንበያ ብቻ ነው። እውነት የአሁን ቅጽበት ላይ ብቻ ትገኛለች።

በአንጻሩ የአላፊነት (growing-past) ፍልስፍና አቀንቃኞች እውነት አላፊው እና የአሁን ጊዜ ላይ ብቻ ትገኛለች ፤ ያልተከወነው የወደፊቱ ጊዜ የእውኑ ዓለምን አይወክልልንም ይላሉ፡፡ ዳይኖሰሮች የእውነት ናቸው፤ የአድዋ ጦርነት እውነት ነው ሆኖም ወደ ፊት መከሰቱ የማይቀረው የእኔ እና ያንተ ሞት ግን እውነት አይደለም።

ሶስተኛው የጊዜ እሳቤ የዘላለማዊነት(eternalism) ይሰኛል። በአሁን፣ በአላፊ እና በወደፊት ጊዜ መካከል የእውነትነት ልዩነት የለም ይለናል። ለምሳሌ የአዶልፍ ሂትለር በጀርመን መነሳት የአላፊ ጊዜን አይጠቁምም፤ ላንተ ያለፈ ጊዜ ቢሆንም ለአርስቶትል ገና ያልተከሰተ የወደፊት ክስተት ነው።

ሆኖም ጊዜ በራሱ ምንድን ነው?

ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን፤ ህንዶች፣ ግብጾች እና ግሪካውያን ጊዜን በተለያዩ መንገዶች ይገልጹት ነበር። ጥንታውያኑ ሰዎች ስለጊዜ አላቂነት ወይም ዘላለማዊነት፣ ስለ ጊዜ እንዲሁ ፈሳሽነት አልያም ዙሮ ገጠምነት (ለምሳሌ ቀን ይደጋገማል፤ አመትም እንደ አዲስ ይጀምራል) የተለያዩ መላምቶች ነበሯቸው፡፡

ሬኒ ዴካርቴ 'ጊዜ ምን ማለት ነው?' ለሚለው ጥያቄ እንዲህ ይለናል:- “ቁስ አካሎች፣ ለምሳሌ አንተ ዘላለማዊ አይደለህም። እንዲያውም ከቅጽበታት ያለፈ እድሜ የለህም፡፡ በአንጻሩ እግዚአብሔር አንተን ጨምሮ ዓለምን በሙሉ በየቅጽበታቱ ይፈጥራል። ከአምስት ደቂቃ በፊት ያለው ዓለም እና አሁን ያለንበት ዓለም ይለያያል። ከቅጽበት በኋላም የሚኖረው ዓለም፣ አሁን ላይ ካለው ዓለም ይለያል። እናም የአሁኑን ቅጽበት ከቀጣዩ ቅጽበተ ዓለም የሚያቆራኘው ነገር ምን ይባላል?... ጊዜ። እግዜርም በእያንዳንዱ ቅጽበት አንተን እና ዓለምን ደጋግሞ ከጥቂት ልዩነቶች ጋር ይፈጥርሃል።”

ሁሉም እንስሳቶች ማለት ይቻላል አሁንን ነው የሚኖሩት፤ ሆኖም ሰው ትንኝ አይደለምና ትናንት ምን እንደነበር ያስታውሳል፤ ነገም እንደሚመጣ ያውቃል። ለጊዜም ያለን እይታም ከእንስሳት ለይቶናል፤ እናስባለን ... እናሰላስላለን እንወስናለን፡፡ ትናንት የረገጥነውን ፈንጂ ዛሬ ላይም መልሰን አንረግጠውም፡፡ ተፈጥሮ ጊዜን እንድናውቅ አድርጋናለች። ጊዜ የእውነት ያለ ነገር ነው? መስመሩስ እንዲሁ እንደ ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚፈስ ነውን? መጀመሪያ እና መጨረሻስ አለውን?

@Zephilosophy
@Zephilosophy
" ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች ”የለውጥ ኩርባ” አለችው።  አስተሳሰቡ ወይ ስሜቱ አሊያም ድርጊቱ የሚቀየርባት ። ወደ ዐዲስ  ምዕራፍ የሚታጠፍበት ወይም ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርበት ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት። ለውጥ ወደ ተሻለ ማደግ ብቻ አይደለምና ኩርባውን ሲታጠፍ ውድቀትም ሊሆን ይችላል። ያች የለውጥ ኩርባ አንድ የሆነች ኢምንት ክስተት ልትሆን ትችላለች ወይም ዐረፍተ ነገር ወይም አንዲት ቃል ምናልባት አንዲት መሳም ወይም የአንድት ደቂቃ መታቀፍ ወይም.... "

- ከ'ጠበኛ እውነቶች ' መጽሐፍ ገፅ  116

ደራሲ :- ሜሪ ፈለቀ
ያገዘፍከውና ያሳነስከው

የዛሬዋ ሕይወት በትናንትናውና በነገው መካከል እንደ ሳንዱዊች የተጣበቀች ሂደት ነች፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሕይወት ገጽታዎች በዛሬው የሕይወትህ ሂደት ላይ ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከእነዚህ ሁለት ገጽታዎች መካከል ያገዘፈው ህይወትህን የማንቀሳቀስ አቅም አለው፡፡

የትናንትናውን ስታገዝፈው፣ የነገው ይደበዝዛል፤ የነገውን ስታገዝፈው ደግሞ የትናንትናው ይደበዝዛል፡፡ በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች መካከል የመወሰን መብቱም አቅሙም አለህ፡፡

ብዙ የተሳካላቸው ሰዎች የትናንትናውን ልምምዳቸው “መልካምም” ሆነ “መጥፎ” ያንን ሳይክዱና ፈጽመው ሳይጥሉት ነገር ግን ከትናንትናው ይልቅ የነጋቸውን በማግዘፍ እንደሚያምኑ ይናገራሉ፡፡

የትናንትናውን በማግዘፍና የነገውን በማግዘፍ መካከል መምረጥ ማለት በመቃብር ውስጥ ባለውና በመሕጸን ውስጥ ባለው መካከል እንደመምረጥ ነው፡፡ የትናንትናህ መቃብር ውስጥ ነው - ሞቷል! በተቃራኒው፣ የነገህ ደግሞ በማህጸን ውስጥ ነው - ሊወለድ ተዘጋጅቷል! የትኛውን ትመርጣለህ? ለየጥኛው ትኖራለህ? የትናውን ስታሰላስል ታሳልፋለህ? ወደየትኛው አቅጣጫ መሄድ ትፈልጋለህ?

ያለፈው ታሪክ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ካለፈው ታሪክ ይልቅ የነገው ራእይህ ሲገዝፍ ሕይወት ወደፊት ትሄዳለች፡፡ ከመጣህበት ይልቅ የምትሄድበት ሲገዝፍ! ካለፈው ስቃይ ይልቅ ከዚያ በመማር የያዝከው የመለወጥ ሂደት ሲልቅ! ካለፈው ስኬት ይልቅ የነገው የላቀ ደረጃ ሲተልቅ! አስገራሚ ሕይወት!!! አስገራሚ የወደፊት!!!

ዶ/ር እዮብ ማሞ
"ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን"
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!!

    መልካም በአል!!
“ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ”

ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህ ታሪክ የሆነው በስፔን ሃገር ነው፡፡ አባትና ልጅ ችላ ቢሉት ቀለል ሊል የሚችልን አንድን የግጭት ሁኔታ በማካበዳቸው ምክንያት ተጣልተዋል፡፡ በጉዳዩ ተጎድቻለሁ ባይ አባት በልጁ ላይ ስለጨከነበትና ይቅር አልለው በማለቱ ምክንያት ልጅ ቤቱን ጥሎ በመሄድ ይጠፋል፡፡ በጊዜው ከነበረበት ንዴት የተነሳ አባት ምንም አልመሰለውም፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ግን ጉዳዩ እያሳሰበው ስለመጣ የልጁን ደህንነት ለማወቅ መፈለግ ጀመረ፡፡ በተለያዩ መንገዶች ሲያጣራ ከቆየ በኋላ ከብዙ ወራት ሙከራ በኋላ በዚያው ከተማ ውስጥ እንደሚኖር አወቀ፤ በትክክል የት እንዳለ ግን ማወቅ አልቻለም፡፡ ልጁ በሕይወት መኖሩንና እጅግም ያልራቀ መሆኑን ሲያውቅ የተከሰተውን ችግር ሁሉ በመርሳት ይቅርታን ሊሰጠው ፈለገ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ልጁን ማግኘት ስላልቻለ አንድን የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ ቆረጠ፡፡

በማድሪድ (ስፔን) ከተማ በሚታተመው ብዙ በመነበብ የታወቀ ጋዜጣ ላይ እንዲህ የሚልን መልእክት አወጣ፣ “ልጄ ፓኮ፣ ያለፈውን ስህተተህን ሁሉ ይቅር ስላልኩህ እባክህን ቅዳሜ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በዚህ ጋዜጣ ማተሚያ ዋና ቢሮ በር ላይ ላግኝህ፡፡ የሚወድህ አባትህ፡፡” በተባለው ቀን ይህ አባት ልጁን ለማግኘት በተቀጣጠሩበት ቦታ ሲሄድ አንድን አስገራሚ ነገር ተመለከተ፡፡ ስማቸው ፓኮ የሆነና ከአባታቸው ይቅርታን የሚፈልጉ 800 ወጣቶች መልእክቱ የተላከው ከእነሱ አባት ስለመሰላቸው በዚያ ቢሮ በር ላይ ተሰብስበዋል፡፡ በተከሰተው ነገር እጅግ የተገረመው አባት ከዚያ ሁሉ ወጣት መካከል ልጁን ፈልጎ አግኘቶ ከሳመው በኋላ፣ “ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ” አለውና ይዞት ወደቤቱ ወሰደው፡፡

ማሕበራዊ ኑሮ እስካለ ድረስ አለመግባባት የተሰኘው የሕይወት ሂደት የማይቀር ነው፡፡ ይህንን ምስጢር የዘነጉ ሰዎች ትኩረታቸውን ሁሉ በዚያ አለመግባባት ላይ ሲያደርጉ ይገኛሉ፡፡ ትኩታቸውን የሚጥሉበት ነገር የወደፊታቸው ላይ ታላቅ ተጽእኖ እንዳለው የገባቸው ሰዎች ያለፈውን በመተው ወደፊት በመዝለቃቸው ላይ ሲያተኩሩ፣ ሌሎች ግን በአለመግባባትና በጸብ “መንፈስ” ውስጥ የመቆየት ዝንባሌ አላቸው፡፡ ትኩረታቸውን በይቅርታና ከተከሰተው ችግር ባሻገር በመሄድ ላይ ማድረግን ትተው ነገርን በመጎተትና በማካበድ ላይ የሚያደርጉ ሰዎች ወደ ተሻለ ሕይወት ለመዝለቅ የሚያበቃ አመለካከት እንደጎደላቸው አመልካች ነው፡፡

ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ዝንብንና ንብን፡፡ ዝንብ ቆሻሻው፣ መጥፎ ሽታ ያለውና የሞተው ነገር ሲስባት፣ ንብ ደግሞ ንጹህ፣ መልካም ጠረን ያለውና ሕይወት ያለው ነገር ይስባታል፡፡ ዝንብ ቆሻሻን፣ በሽታንና ሞትን ስታዛምት፣ ንብ ስትሰራ ውላ ጣፋጭ ነገርን በማምረት የብዙዎችን ሕይወት ታጣፍጣለች፡፡

አሁንም ሁለት በአየር ላይ የሚበሩ ፍጥረታትን አስብ፤ ንስርንና ጥንብ አንሳን፡፡ ንስር ሕይወት ያለውን ነገር ተናጥቆ ሲመገብ፣ ጥንብ አንሳ የከረመን፣ የሞተንና የበሰበሰን ነገር ሲያነሳ ይኖራል፡፡ ምርጫው የእኔ ነው፡፡ ያለፈውንና የሞተውን ነገር መከታተልና ያንን “እየተመገቡ” መኖር፣ ወይስ ያንን ትቶ የወደፊቱን፣ ትኩሱንና በይቅርታ የታደሰውን?

መዘንጋት የሌለብህ እውነታዎች …

• ተበደልኩ በማለት ወደኋላ በመመለስ ወደምታስታውሰው የጊዜ ርቀት የመመለስና ኋላ ቀር የመሆን እድልህ የሰፋ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ የዛሬ 10 ዓመት የሆነብህን አሁንም የምትቆጥር ከሆነ በአመለካከትህም ሆነ በኑሮ እድገትህ 10 ዓመታት  ወደኋላ ተጎትተህ በመመለስ እንዳዘገምክ አትዘንጋ፡፡

• ይቅር ያላልከው ሰው በአንተ ላይ የበላይነት አለው፡፡ አንተ የሆነብህን ስታብሰለስል ምናልባት እርሱ የግሉን፣ የቤተሰቡንና የሕብረተሰቡን ሕይወት እንዴት እንደሚሳድግ እቅድ እያወጣ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡  

• አንተ ይቅር ያላልከው ሰው ምን እንዳደረገብህ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ ስታስተላልፍ፣ ምናልባት እርሱ አዳዲስ እውቀቶችንና ስልጣኔዎችን በማስተላለፍ አልፎህ ሄዶ ይሆናል፡፡

እኔ ዛሬ ይቅርታን ለመምረጥ ወስኛለሁ፣ አንተስ? አንቺስ?

ዶ/ር እዮብ ማሞ
ስለ ፍልስፍና
@Zephilosophy
@Zephilosophy
ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ

በአገራችን በፍልስፍና ምንነትና ፋይዳ ላይ እስከ ዛሬ ሲንፀባረቅ የቆየው አመለካከት አሉታዊነቱ የሚያመዝን
መሆኑ ከዚህ የእውቀት ዘርፍ ተገቢውን ጥቅም እንዳናገኝ አድርጎናል። እናም ብዙዎች ስለፍልስፍና ያላቸውን አሳቤ ስንመስከት-ከፈጣሪ ጋር መጋጨት፣ ከእውነት ከመራቅ እንዲሁም ከእብደት ጋር የተያያዘ ሆኖ አናገኘዋለን፡፡ ይህ የብዙዎች እምነት ይሁን እንጂ፣ ፍልስፍና ግን በተቃራኒው እውነትን ከመፈለግ- አልያም ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ ከመመርመር ባሻገር ስለፍትህ፣ ስለፖለቲካ፣ ስለ ስነ ውበት፣ ስለ መልካም ስነ-ምግባር አንዲሁም ስለመሰል የትምህርትና የአስተሳሰብ ዘርፎች እንደ የአቅጣጫው የሚያጠናና የሚመረምር አራሱን የቻለ ትልቅ የእውቀት ዘርፍ ነው።

ፍልስፍና ከራሱ አልፎ ለሌሎች ታላላቅ የእውቀት ዘርፎች መሰረት የሆነና የሰው ልጅ ዛሬ እዚህ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ጉልህ አስተዋፅዖ ያደረገ ነው። ለሁሉም ሩጫ ፍልስፍና የጀርባ አጥንቱ ነው፡፡ ምሰሶ ከሌለው ጎጆ እንደማይቆም ሁሉ፤ ፍልስፍና ከሌለ እውቀትና እውነት አንደጉም ይተናሉ። ምናልባትም ሀገራችን በሌሎች የትምህርት ዘርፎች ያሳየችውን ትጋት ለፍልስፍናም አቋድሳው ቢሆን ኖሮ ፣ ሌሎች ቤት የሚያበራው ሻማ ፣ ጨለማ ውስጥ ሆነን ባላደነቅን ነበር ፣ፍልስፍና ዳቦ አያበላም እያልንም በፈላስፋው የተጋገረውን ዳቦ ተሻምተን ለመቋደስ ባልተገደድንም ነበር።

በአጠቃላይ ፍልስፍና ከጨለማ_ወደ ብርሀን፣ ካለማወቅ ወደማወቅ፣
ከባርነት ወደ ነፃነት፣ ከስህተት ወደ እውነት የሚያሻግር ድልድይ ነው።

ድንቅ የፍልስፍና ቻናል ይቀላቀሉ
Join Now
👇👇👇👇
@Zephilosophy
@Zephilosophy
"ከፖለቲካ በሸሸህ ቁጥር በእውቀት እና በስነምግባር በምትበልጣቸው ሰዎች በመመራት ትቀጣለህ"
Audio
-ዛሬም የሚያስፈልጉን ነፃነቶች
-ቁልፍ እና ድልድይ
-ውይ ሴቶች!!
ተራኪ-አንዱአለም ተሰፋዬ
@zephilosophy
ዛፍ ቆራጩ
አስተማሪ ወግ በአንዱለም
በረከት ወይስ መርገምት
አስተማሪ ወግ
✍️ማክስ ሉካዶ እንደፃፈው

ተራኪ ፦ አንዱአለም

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence
በተሰማሩበት ሙያ ስኬትዎን የሚወስኑ 6 የሰብዕና መገለጫዎች

ጉጉ፣ ጠንቃቃ እና ተፎካካሪ ነዎት? ከሁኔታዎች ጋር ቶሎ የመላመድ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም እና ግራ መጋባትን አምኖ መቀበልን የመሰሉ ምስጢራዊ ችሎታ አለዎት?

- እንግዲያውስ እንኳን ደስ አለዎ! በሥነ-ልቦ ባለሙያዎች በተደረገ ጥናት መሰረት እነዚህ ስድስቱ መገለጫዎች በህይወትዎ እና በሚሰሩት ሥራ ስኬታማ እንዲሆኑ ያደርጋሉ።

እውነታው ግን አንዳንድ ልዩነቶች አሉት፡፡ እነዚህ ባህሪያት ሲበዙ ደግሞ ውጤታማነትዎን ሊቀንሱ ይችላሉ። ስለዚህ የስኬት ሚስጥሩ በሁለቱ ፅንፎች መካከል ሚዛንን ጠብቆ መቆየት መቻል እና ጠንካራ እና ደካማ ጎንን ለይቶ ማወቅ ነው።

ይህ አቀራረብ በሥራ ባህሪያችን ላይ ጫና የሚያሳድሩ የተወሳሰቡ የሥነ-ልቦና መገለጫዎችን ለመረዳት ይረዳል። ከዚህ በፊት የሥራ አካባቢ ባህሪያትን ለማወቅ የተደረገው ጥረት አከራካሪ ውጤቶች አስገኝቷል።

በሥነ-ልቦናው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች በሥራ አካባቢ ውጤታማ ያደርጋሉ የሚለውን ግኝት ከግምት ውስጥ በማስገባት የለንደን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎቹ ኢየን መክሪ እና ኤድሪየን ፈርሃም በተሰማሩበት ሙያ ስኬታማ የሚያደርጉ ስድስት የስብዕና መገለጫዎችን አስቀምጠዋል።

መክሪ እንደሚለው እያንዳንዱ መገለጫዎች የራሳቸው የሆነ ውስንነት እና ጠንካራ ጎን አላቸው።ስለዚህ የእያንዳንዱ መገለጫ ጥቅም የሚወሰነው ግለሰቦች በሚሰሩት ሥራ ላይ ስለሆነ መለኪያው ከእያንዳንዱ ሁኔታ ጋር ይቀያየራል።ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህ ስድስት የስብዕና መገለጫዎች እንዴት ወደ ስኬት እንደሚወስዱ እንመልከት

1. ጠንቃቃነት
ጠንቃቃ ሰዎች ሁሌም እቅዳቸውን በትክክል ይተገብራሉ።የእያንዳንዱ ውሳኔያቸው የወደፊት ውጤት ተጽዕኖን ያውቃሉ። ስሜታቸውንም መቆጣጠር ይችላሉ። ከአእምሮ ብቃት ምዘና ፈተና በኋላ ይህ የጠንቃቃነት ባህሪ በህይወትዎ ስኬታማ ለመሆን ወሳኝ ነው።በሥራ አካባቢ ለትንሽ ነገሮች ትኩረት መስጠት ስልታዊ በሆነ መልኩ እያንዳንዱን ሥራ ለማቀድ ይጠቅማል።

2. ከአዲስ ነገሮች ጋር ቶሎ መላመድ
ሁሉም ሰው የሚያስጨንቀው ነገር ያጋጥመዋል፤ ዋናው ጥያቄ ግን እንዴት ያልፈዋል የሚለው ነው። ይህ ማለት ሥራዎት እና ሌላ ህይወትዎ ላይ ጫና እንዳሳያሳድር ለመላመድ መሞከር ማለት ነው።ይህ ባህሪ የሌላቸው ሰዎች የሥራ አካባቢ አፈጻጸማቸው ደካማ ነው። ነገር ግን ተገቢውን የሥነ-ልቦና እርምጃ ከወሰዱ ውጤታማ መሆን ችላሉ።
ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ውጤታማ ለመሆን ሲባል አስጨናቂ ጉዳዮች ላይ በደንብ ትኩረትን መስጠት ከተቻለ፤ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለ ሰው ያሰበውን ነገር ማሳካት ይችላል።

3. ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል
የጥያቄዎን መልስ የሚያውቁበት አይነት ሥራ ነው የሚወዱት ወይስ ግራ የሚያጋባ እና አስጨናቂ የሥራ ቦታ?
የማያውቁትን ነገር የማይፈሩ እና ግራ መጋባትን አምነው የሚቀበሉ ሰዎች የተሻለ ውሳኔ ለመወሰን ይችላሉ። ብዙ  ነገሮችንም ከግምት ውስጥ ያስገባሉ።
ይህ ባህሪ ትንሽ አምባገነናዊ ወደ ሆነ አስተሳሰብ ይመራል ይላል መክሪ። እንደዚህ አይነት ሰዎች ትንሽ የምትባለው ነገር ትርጉም እስከምትሰጣቸው ድረስ ስለሚጨነቁ የራሳቸውን ውሳኔየመጨረሻ አድርገው ሊወስዱ ይችላሉ። ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል የሚችል ሰው ለማንኛውም አይነት ለውጥ ሁሌም ዝግጁ ነው፡፡ ግራ መጋባትን አምኖ አለመቀበል ግን ሁሌም መጥፎ ነው ማለት አይደለም።


4. ጉጉ መሆን
ከሌሎች ባህሪያት ጋር ሲነጻጸር በሥነ-ልቦና አጥኚዎች ዘንድ ጉጉት ብዙ ትኩረት አልተሰጠውም፡፡ነገር ግን በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የማናውቀውን ነገር ለማወቅ ያለን ጉጉት ሁሌም አዲስ ነገር ለመፍጠር ይረዳናል። ይህ ማለት ለአዳዲስ ነገሮች ክፍት የሆነ ጭንቅላት አለን ማለት ሲሆን፤ በምንሰራው ሥራ ደስተኞች እንድንሆን ይረዳናል።አንዳንዴ ግን የበዛ ጉጉት ወዳልተፈለገ የጊዜ ብክነት ሊወስደን ይችላል።


5. አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም
ደስ የማይል ነገር ሲያጋጥምዎት ለጊዜው ስለቀለልዎት ብቻ  ዝም ብለው ያልፋሉ ወይስ ምቾት ባይሰጦትም ጉዳዩን ተጋፍጠው ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ይሞክራሉ? ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች ጋር እራስን ማላመድ መቻል ወደፊት ወደ _ አመራር ቦታ እንድንመጣ እና ለብዙ ነገሮች ውሳኔ መስጠት እንድንችል ይረዳናል።


6. ተፎካካሪ መሆን
ለስኬት ሲባል የሚደረግ ትንቅንቅ እና ጤናማ ያልሆነ ፉክክር ወይም ቅናት ትልቅ ልዩነት አላቸው። ፉክክር ሁሌም ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሳ ሲሆን፤ ተጨማሪ ጥረት እንድናሳይና እቅዳችንን እንድናሳካ ሊረዳን ይችላል። ሲበዛ ግን የቡድን ሥራዎችን ያስተጓጉላል። እነዚህ ስድስቱ ባህሪያት በአንድነት በሥራ ገበታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። በተለይ ደግሞ ወደ አመራር ቦታ መምጣት ለሚፈልጉ ሰዎች።
( ምንም እንኳን ጥናቱ ገና ባያልቅም ከላይ የተዘረዘሩት የሰዎች ባህሪያት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የሥራችንን ፍሬ እና ውጤታማነታችንን ለመለካት ይረዱናል።)

Source - BBC

የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
አእምሮአችን ድንቅ ተአምራዊ ስጦታ ነወ።

የሠው ልጅ አእምሮ በአማካይ 10 ቢሊየን የአእምሮ ህዋሶችን (ኒውሮን ሴሎችን) በውስጡ ይይዛል፡፡ እነዚህ ሴሎች  ህዋሶች ደግሞ እርስ በእርስ በ100 ትሪሊየን ጥልፍልፍ መስመሮች ይገናኛሉ። አእምሮዋችን ይህ ነው የማይባል ምስጥራዊ ስሪት አለው፡፡ በዛኑ ልክ ስራውም እጅግ የተወሳሰበ ነው:: በመላ ሰውነታችን በተዘረጋው የመረጃ መረብ በመታገዝ ከአካባቢያችን ጋር በሰላም ያለምንም ችግር እንድንኖር አስችሎናል። በእነዚህ የግንኙነት መስመሮቸ ውስጥ ወደ አእምሮ እና ከአእምሮ የሚተላለፉ መልእክቶች እጅግ በጣም ፈጣን በሆነ መልኩ በሠአት 320 ኪሜ ይጓዛሉ፡፡ በአእምሮና በቀሪው ሰውነታችን መካከል ያሉት ነርቮች መልእክትን ለመለዋወጥ ልክ እንደዋና ጎዳና በመሆን ያገለግላሉ።

በአጭሩ ሰውነታችን በእያንዳንዷ ደቂቃና ቅፅበት እጅግ ከፍተኛ የትራፊክ እንቅስቃሴን ያስተናግዳል ማለት ነው።በአንዲት ነጠላ ሰከንድ ውስጥ ብቻ በሺ የሚቆጠሩ መልእክቶች በተናጠል በአእምሮና በቀሪው የአካል ክፍል መካከል ይመላለሳሉ።በአንዲት ደቂቃ ውስጥ ብቻ ከመቶ ሺህ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ኬሚካላዊ ለውጦች በአእምሮአችን ውስጥ ይካሄዳሉ። ሌላው ቀርቶ ይህንን ፅሁፍ በሚያነቡበት ወቅት እንኳን በእያንዳንዷ ሰኮንድ አንድ ሺኛ ጊዜ ውስጥ በሰውነታዎ ጡንቻዎችና በአእምሮዎ መካከል በመቶ የሚቆጠሩ የመልእክት ልውውጦች ተደርገዋል።


እነኚህ መልእክቶች ሲያነቡ መረጃ ከማቀበል ባለፈ ወንበርዎ ላይ ደገፍ ማለትዎን ያነበቡትን ነገር መረዳትዎን፡ የልብዎን ምት፣ እስትንፋስዎን፣ የአይንዎን መርገብገብ ፣የፀጉርዎን ማደግ፡ የአፍንጫዎን ማሽተትና የጆሮዎን መስማት የሚመለከቱ ሊሆኑ ይችላሉ። ከእነዚህ ድርጊቶች ውስጥ አንዱን እንኳን በቅጡ ለመረዳት ቢሞክሩ እጅግ ብዙ ገፅ የኬሚካል ቀመሮችን መፃፍ ይኖርብዎታል፡፡ በዚህ ቀመር ውስጥ ደግሞ አንዷ እንኳን ብትሣሣት የሰውነትን ሚዛን ልታሣጣ ትችላለች። ይህ የሚዛን መዛባት ፀጉርዎን ሲያበጥሩ በድንገት እጆዎችን እና አይንዎን በማበጠሪያው እንዲወጉ ሊያደርግዎ ወይም ሲራመዱ ተንገዳግደው እንዲወድቁ ሊያደርግዎ ይችላል::

የአእምሮችንን የህዋሳት ብዛትና የርስበርስ መያያዣ ስርዓተ በምሳሌ ብንመለከት።የኢትዮጵያ ሁለት እጥፍ የሚሆን ግዙፍ ቦታ እንዳለ እናስብ፡፡ይህ ቦታ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በዛፍ የተሞላ እንደሆነና እያንዳንዱ ዛፍ ደግሞ 10,000 ቅጠሎች እንዳሉት እንቁጠር፡፡ እንግዲህ የእነዚህ ቅጠሎች ድምር የአእምሮ ሴሎች ከሚገናኙባቸው መስመሮች ጋር እኩል ነው ማለት ነው፡፡

ታዲያ የዚህ ውስብስብ ዲዛይንና ምህንድስና ባለቤት ፈጣሪን ልናመሰግነው አይገባብ ትላላችሁ?
አምላክ የሠውን ልጅ እጅግ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ከመፍጠሩ የተነሣ እጅግ ውስብስብ ስራዎችን እንኳን ያለ እንከን መስራት እንዲችል አድርጎታል። ታዲያ ይህን ታላቅ ስጦታ  በአግባቡ አለመጠቀም ሀጥያት አይደለም ትላላችሁ?

✍️ባህሩን ያህያ

የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
Forwarded from Tesfaab Teshome
የኢትዮጵያ ታሪክ በአንድ አንቀፅ ቢገለፅ 'ንጉስ ተነሳ፥ ከውስጥም ከውጪም ተዋጋ፥ አሰረ ገደለ ዘረፈ። ሌላም ንጉስ መጣ፥ ከውጪም ከውስጥም ተዋጋ፥ አሰረ ገደለ ዘረፈ።... በዚህም የተነሳ ጉስቁልና ፣ ድንቁርና እና ኋላቀርነት በምድሪቱ ነገሰ' የሚል ነው።

ታሪክ እኛ አገር የፖለቲካ አሽከር ነው። ታሪክ ነጋሪዎቻችን ከፖለቲካ አሰላለፋቸው አንፃር ያለውን ትርፍ ስለሚያሳሉ እውነት ላይ ለመሸቀጥ አያመነቱም፡፡ ሲከፋም የፖለቲካ ሰዎች የታሪክ ነጋሪ ሆነው ይከሰታሉ። ፖለቲካ ከታሪክ መጋባቱ ሳያንስ የዘቀጠ ፖለቲካ ሲታከልበት ታሪክ መጠፋፊያ ይሆናል። እኛም ታሪካችን ጠልፎ የሚጥለን ገመድ እንጂ መማሪያችን አይደለም።

ቢሆንልን የታሪክ አላማ ከትላንት መማር፥ ጥንካሬን ማስቀጠል፥ ደካማ ጎንን ማረም ና እርስ በእርስ መተሳሰሪያ መሆን ነበረበት። ለዚህ ግን አልታደለንም!
ታሪክ አለን፥ ነገር ግን ታሪክን ይፅፉ ዘንድ ሞያው የሚፈቅድላቸው ዝም ብለዋል። ታሪክ ተራኪዎቻችን ደግሞ አንድም መሰረታዊ የታሪክ ነገራ አላባዊያንን ስተዋል። አሊያም ታሪክን የፖለቲካ ገረድ አድርገዋል። ስለዚህ እንደ ህዝብ ከታሪክ መማርና አገራዊ መተሳሰሪያ ገመድ ለመፍጠር አልታደልንም!


#ነገን_ፍለጋ መፅሐፍ የተወሰደ

@Tfanos
አንተ በሕይወትህ ላይ እርምጃ ካልወሰድክ ሕይወት በአንተ ላይ እርምጃ ትወስዳለች!!

በጣም ወሳኝ የሆኑ ግቦችን በግልጽ የማስቀመጥና እነርሱን በየእለቱ የመከለስ ያህል ለስኬት መሠረት የሚሆን ነገር የለም፡፡ ግብ በማስቀመጥና እነርሱን በቋሚነት ውሳኔ ለመስጠት የምታሳልፍበትን ጊዜ ሁሉ ከግምት ውስጥ ማስገባት ታላቅ ሕይወትን ለመምራት ወሳኝ ግብዕት ነው፡፡  ሰዎች እድሜ ዘመናቸውን ስኬታማ ለመሆን  ሲያልሙ እና ሲለፉ ይኖራሉ። ሆኖም ግን በወር ውስጥ ለአስር ደቂቃ እንኳን ግባቸውን በጽሁፍ ላይ አስፍረው፣ በማሰብና በማሰላሰል አያሳልፉም፡፡እውነት ነው፤ ብዙ ሰዎች የሕይወታቸውን አቅጣጫ ከመተለም ይልቅ የእረፍት ጊዜያቸውን እንዴትና የት እንደሚያሳልፉ በማሰብ ነው ጊዜያቸውን የሚያጠፉት።

እንዲሁ በዘፈቀደ መኖር ቀላል ነው፡፡ አንተ በሕይወት ላይ እርምጃ ካልወሰድክ ሕይወት በአንተ ላይ እርምጃ ትወስዳለች። ዘወትር ማለዳ ለአምስት ደቂቃ ግቦችህን በመወጠንና በመከለስ ብታሳልፍ ተጽእኖህን በሕይወት ላይ ታሳርፋለህ እንዲሁም ሕይወትህን የምትመራው ለሚደርስብህ ነገር የአጸፋ ምላሽ በመስጠት ሳይሆን አንተው አስቀድመህ በተለምከው መንገድ በመጓዝ ነው፡፡ ግቦችን በማስቀመጥ የተሻሉ አማራጮችን የሚያስገኝልህ ማዕቀፍ ይኖርሃል፡፡ እቅድ ስትነድፍ ከፊት ለፊትህ ስለሚጠብቅህ ነገር እውቀትና ግንዛቤ ይኖራል። የምትፈጽመው ስህተት ይቀንሳል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ነገር ትፈጽማለህ፡፡


«የሚለካ፣ የሚመዘን ነገር ይሻሻላል።» የሚል አባባል አለ። ግብ ማስቀመጥ የምትለካውን ነገር ይሰጥሃል። ግብህ የሰውነት ክብደትህን በ12% መቀነስ ቢሆን የምታስመዘግበውን መሻሻል የምትመዝንበት መለኪያ ይኖርሃል፡፡ ስትለካ ለመሻሻል መሠረት ይኖርሃል። ግቦችህን በግልጽ ስታውቅ የተሻሉ ምርጫዎች ይኖሩሃል። የተሻለ ምርጫ ሲኖርህ የተሻለ ውጤት ታገኛለህ፡፡


ግብን አስቀድመህ በማዘጋጀት በግቡ ውስጥ የሚካተቱትን ነገሮች በዝርዝር በወረቀት ላይ አሰፍራቸው።ግብህን ማቀድና በወረቀት ላይ ማስፈር፣ ህይወትህን በአስገራሚ ነገሮች ይሞላዋል።ይህንን ማርቀቅ በጀመርክበት ቅጽበት፣ የተፈጥሮ ሀይል በወረቀት ላይ የረቀቅውን ወደ እውነት ለመቀየር የራሱን ሚና ይጫወታል። እያንዳንዶቻችን በቀን በአማካይ 50,000 ሀሳቦችን እናስባለን፡፡ በእራፊ ወረቀት ላይ የራስህን ምኞቶችና ግብ በዝርዝር መክተቡ፣ ለጥልቁ አዕምሮህ እነዚህ ከቀሩት 49,999 የበለጠ አስፈላጊ እንደሆኑ የቀይ
ባንዲራ ምልክት ማሳየት እንደማለት ነው፡፡ ያንጊዜም አዕምሮህ ልክ አቅጣጫውን በራዳር እንደተዘጋጀለት ሚሳኤል ለመወንጨፍ፣አሰሳውን ይጀምራል፡፡ ይሄም በራሱ እጅግ አስደናቂ ሳይንሳዊ ሂደት ነው።

ግቦች በውሎህ ላይ የህይወት እስትንፋስን ይተነፍሳሉ፡፡ በአንድ ነጭ ወረቀት ላይ ግቦችህን ማስቀመጥ በራሱ ሕይወትህን ፍጹም ወደሚለውጥ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግርሃል። ግቦችህን ማስቀመጥ ተራ ለመሆን አለመፍቀድህን መግለጫ ነው። ግቦችህን ማስቀመጥ ጀግንነት ነው፤ ምክንያቱም በውስጥህ ያለውን እምቅ አቅም ለማውጣት ትችላለህና፡፡

✍️ሮቢን ሻርማ
#ሼር በማድረግ ሌሎችን እናስተምር

Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
ግብ እንዴት ልቅረጽ
_____
ለቢዝ
ነሳችንም ሆነ ለግል ሕይወታችን የት እና እንዴት መድረስ እንደምንፈልግ ግልጽ የሆነ ግብ መያዝ ከመባከን ያድነናል። ይሁን እንጂ ሰዎችም ሆኑ ቢዝነሶች ብዙ ጊዜ ግባቸውን ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስቀመጥ ይቸገራሉ፤ አንዳንዴ እንደውም ጭራሽ ምንም ግብ ሳይቀርጹ ይቀራሉ።

የትኛውም ዓይነት ግብ ሲቀረጽ፤ በሚከተለው መልኩ ቢሆን ለመቅረጽም፣ ለመከታተልም፣ እንዲሁም ለመተግበር ያመቻል። ይህ የግብ አቀራረጽ ዘዴ በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል "SMART" ተብሎ የሚጠራ ሲሆን 5 መስፈርቶች አሉት።

የትኛውም የምናስቀምጠው ግብ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ መሆን ይኖርበታል።

1⃣ የማያሻማ (Specific)

የማያሻማ ግብ ማለት ግልጽ እና "ምን ማለት ይሆን?" የማያሰኝ መሆን አለበት።

ለምሳሌ:-

"በዚህ ዓመት ስኬታማ መሆን" የሚለው ፈጽሞ ለአንድ ቢዝነስ ግብ ሊሆን አይችልም። ስኬታማ ሲል ምን ማለት እንደሆነ፣ በዝርዝር እና ቁልጭ ባለ መንገድ መገለጽ መቻል አለበት።

2⃣ የሚለካ (Measurable)

የሚለካ ግብ ማለት ተሳክቷል አልተሳካም የሚለው በቀላሉ መመዘን የሚችል ማለት ነው።

ለምሳሌ:-

"ትርፋማ መሆን" የሚለው ግብ የሚለካ አይደለም። "የአንድ ሺህ ብር ትርፍ ማግኘት" የሚል ብናደርገው፣ ምን ያህል ተሳክቷል የሚለው በቀላሉ መመዘን ስለሚችል የሚለካ ግብ ሆነ ማለት ይቻላል።

3⃣ ሊደረስበት የሚችል (Achievable)

ግባችን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ለመሳካት የማይቻል መሆን የለበትም። ሊደረስበት የሚችል የሚለው የሚያመለክተው ካለንበት ወቅታዊ ይዞታ አንጻር የመሳካት ዕድል ያለው መሆኑን ነው።

ለምሳሌ:-

በወር የ20 ሺህ ብር የገንዘብ ዝውውር ያለው ቢዝነስ፤ "በዓመቱ መጨረሻ የአንድ ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት" ቢል ካለበት ሁኔታ ጋር የማይጣጣም እና ሊደረስበት የማይችል ሆኖ ይገኛል። ይልቅ ነገሮችን አገናዝቦ የበለጠ ሥራን በሚያበረታታ መልኩ ከፍ ያለ ግን ከእውነታው በጣም ያልራቀ ግብ ማስቀመጥ ይኖርበታል።

4⃣ ከእውነት ያልራቀ (Realistic)

ይህ "ሊደረስበት የሚችል" ከሚለው ጋር ተቀራራቢ የሆን መለኪያ ነው። "ሊደረስበት የሚችል" የሚለው የራስን አቅም ማገናዘብን የሚመለከት ሲሆን፣ "ከእውነት ያልራቀ" የሚለው ደግሞ የምንኖርበትን አገር እና አካባቢያዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ማስገባትን የተመለከተ ነው።

ለምሳሌ:-

አሁን ባለው የአገራችን ሁኔታ፣ የቱንም ያህል የገንዘብ እና የሰው ኃይል አቅም ቢኖረን በኦንላይን የገንዘብ ዝውውር የመላው ዓለም ሰዎች የሚገበያዩበት የግብይት ቢዝነስ ኢትዮጵያ ውስጥ መጀመር አይቻልም። እንዲህ ያለ ግብ አንድ ሰው ቢቀርጽ፣ ከእውነት የራቀ ሆኖ ይገኛል።

5⃣ በጊዜ የተገደበ (Time-bound)

የጊዜ ወሰን ያልተበጀለት ግብ፣ ግብ ሳይሆን ሕልም ነው። "የእኔ ቢዝነስ ወደፊት አንድ ቀን አንድ ሚሊየን ብር ትርፍ ይኖረዋል" ማለት ጥሩ ሃሳብ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ግብ አይደለም። ይህ የሚሆነው መቼ ነው? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ መመለስ ይኖርበታል።

ለምሳሌ:-

"አንድ ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት" የሚለው #ሕልም "የሚቀጥለው ሰኔ መጨረሻ አንድ ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘት" የሚለው ቢጨመርበት በጊዜ የተገደበ ግብ ይሆናል።

ማሳሰብያ

አምስቱን የትክክለኛ ግብ መገለጫዎች ስናስብ መርሳት የሌለብን ነገር፣ አንድ ግብ እውነትም ግብ እንዲባል ከአምስቱ አንዱን ወይም ሁለቱን ቢያሳካ በትክክል ግብ ሊባል አለመቻሉን ነው። ግባችን እውነትም ግብ እንዲባል አምስቱንም የትክክለኛ ግብ መለያዎች ማሟላት ይኖርበታል።

የስብዕና ልህቀት
Join: @Human_intelligence
Join: @Human_intelligence
የስቴቨን ኮቬይ የጊዜ አጠቃቀም ማትሪክስ አራቱ ኳድራንቶች
እያንዳንዱ ኳድራንት የተለየ ባህሪ አለው እና ለእርስዎ ተግባራት እና ሃላፊነቶች ቅድሚያ እንዲሰጡ ለማገዝ የተነደፈ ነው።  እነዚህ አራት ማዕዘናት እንደሚከተለው ናቸው።

ኳድራንት 1 - አስቸኳይ እና አስፈላጊ
ኳድራንት 2 - አስቸኳይ ያልሆነ ነገር ግን አስፈላጊ የሆነ
ኳድራንት 3 - አስቸኳይ ግን አስፈላጊ ያልሆነ
ኳድራንት 4 - አስቸኳይ እና አስፈላጊ ያልሆነ

ኳድራንት 1 - አስቸኳይ እና አስፈላጊ
ከወሳኝ ውጤቶች ጋር የተያያዙ ኃላፊነቶችን ወይም ተግባሮችን ያካተተ ሲሆን አስቸኳይ ትኩረት ይጠይቃል።  በዚህ ባለ አራት ማእዘን ውስጥ ያሉት ጉዳዮች በአስቸኳይ እና አስፈላጊነታቸው ምክንያት አስጨናቂዎች ሊሆኑ ይችላሉ ፣ ስለዚህ እነዚህን ተግባራት ማወቅ እና በዚህ መሠረት መመደብ አስፈላጊውን ጊዜ እና ጥረት በእነሱ ላይ እንዲያተኩሩ ያስችልዎታል።  በ Q1 ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮች የሚከተሉት ባሕርያት አሏቸው:-

የሚመጡ የጊዜ ገደቦች
ከግዜ-ተኮር ግቦች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት
አስቸኳይ አደጋን በማቃለል ውስጥ የሚከወን

ኳድራንት 2 - አስቸኳይ አይደለም ነገር ግን አስፈላጊ ነው

Q2 የተግሣጽ እና የቁርጠኝነት ስሜትን ለማዳበር በእንቅስቃሴዎች ላይ ማተኮር ፣ እንዲሁም እርስዎ ሊቆጣጠሯቸው በሚችሏቸው ነገሮች ላይ መለየት እና መስራት ያካትታል።  አንዳንድ የ Q2 ንጥሎች የሚከተሉት ባሕርያት ሊኖራቸው ይችላል

ዕቅድ ወይም ተጨማሪ እርምጃዎችን ይጠይቁ
ከአጠቃላይ ግቦች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት

አራተኛ 3 - አስቸኳይ ግን አስፈላጊ አይደለም
በ Q3 ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች አስቸኳይ ናቸው እና በቅጽበት ውስጥ አንዳንድ አስፈላጊነትን ይይዛሉ።  እነዚህ ከሥራ ፍሰትዎ ሊቀንሱ ወይም ሊወገዱ የሚችሉ ባህርያት ወይም ነገሮች(items) ናቸው።  ከሚከተሉት ባሕርያት መካከል አንዳንዶቹን ሊኖራቸው ይችላል-

በ Q1 እና Q2 ውስጥ ያሉት ዝርዝሮች ላይ የሚኖር ደካማ ዕቅድ የሚከተሉትን ውጤቶች ያስከትላል:-
* ምርታማነትን ማቋረጥ
* መዘናጋት

አራተኛ 4 - አስቸኳይ እና አስፈላጊ አይደለም

በ Q4 ውስጥ ያሉ ተግባራት ሙሉ በሙሉ ሊወገዱ ወይም ሊቀነሱ ይችላሉ።  የትኞቹ ሥራዎች ወይም ጉዳዮች ዝቅተኛ ቅድሚያ(minimum priority) የሚሰጧቸው እንደሆኑ ማወቅ እና በዚህ አራት ማእዘን(ኳድራንት) ውስጥ የትኞቹ ዝርዝሮች እንደሆኑ መለየት አስፈላጊ ነው።  እነዚህ ዝርዝሮች በተለምዶ የሚከተሉት ባሕርያት አሏቸው:-

አነስተኛውን የጭንቀት መጠን ያስከትሉ
ከአጠቃላይ ወይም ጊዜ-ተኮር ግቦች ጋር በቀጥታ የተዛመደ አይደለም።

The four quadrants of the Covey Time Management Matrix
Each quadrant has a different property and is designed to help you prioritize your tasks and responsibilities. These quadrants are as follows:

Quadrant 1: Urgent and important
Quadrant 2: Not urgent but important
Quadrant 3: Urgent but not important
Quadrant 4: Not urgent and not important
Quadrant 1: Urgent and important
Q1 involves responsibilities or tasks related to critical results and require urgent attention. The items in this quadrant may also be stressors due to their urgency and importance, so being aware of these tasks and categorizing them accordingly can ensure you focus the necessary time and effort on them. Items that fall into Q1 have the following qualities:

Impending deadlines
Direct relation to time-sensitive goals
Involve alleviating immediate risk
This quadrant is located top left in the matrix.

Quadrant 2: Not urgent but important
Q2 involves focusing on activities to develop a sense of discipline and commitment, as well as identifying and working on things you can control. Some Q2 items may have the following qualities:

Require planning or additional steps
Direct relation to overall goals
This quadrant is located top right in the matrix.

Quadrant 3: Urgent but not important
Activities in Q3 are urgent and assume some form of importance in the moment. These are likely items that can be reduced or removed from your workflow. They likely have some of the following qualities:

Result of poor planning of items in Q1 and Q2
Interrupting productivity
Distraction
This quadrant is located bottom left in the matrix.

Quadrant 4: Not urgent and not important
Tasks in Q4 are more likely able to be removed completely or reduced. It is important to identify which items belong in this quadrant so you know which tasks to classify as lowest priority. These items typically have the following qualities:

Cause the least amount of stress
Not directly related to overall or time-sensitive goals

By Maximilian A. (Engineer)
❥••••በ ትንሽ ድንጋይ እስክትመታ አትጠብቅ!!

๏ የኮንስትራክሽን ተቆጣጣሪው ከ 6ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ የሚስራውን ሰራተኛ ይጠራዋል፣ ስራተኛው ሊስማው አልቻለም፡፡

ስራተኛው የአሰሪውን ጥሪ ሊስማው ስላልቻለ ተቆጣጣሪው መላ ዘየደ፡፡ እናም የሰራትኛውን ሃሳብ ልማግገኘት ሲል ተቆጣጣሪው ከላይ ብር ጣለለት ብሩም ከሰራተኛው እግር ስር አረፈ፣ ሰራተኛው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አሰገብቶ ስራውን ቀጠለ……

በድጋሜ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት ተቆጣጣሪው መጀመሪያ ከጣለው ብር በላይ ሌላ ብር ጨምሮ ጣለለት፣ የቀን ሰራተኛውም ልከ እንደ መጀመሪያው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አስገብቶ ስራውን ቀጠለ፡፡

በመጨረሻ ሌላ መላ ዘየደ ብር በመጣል የሰራተኛውን ሀሳብ ማግኘት ስላልቻለ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት አነስ ያለ ድንጋይ አነሳና ወደ ሰራተኛው ወረወረው፣ ድንጋዩም የሰራተኛውን ጭንቅላት አገኝው በዚህ ሰዓት ነበር ሰራተኛው ወደ ላይ የተመለከተው እና ከተቆጣጣሪው ጋር መነጋግር የጀመረው፡፡
---------------------------
:
:
ይሄ ታሪክ ከእኛ ህይወት ጋር ይመሳሰላል ፈጣሪ ከኛ ጋር መገናኘት ይፈልጋል ነገር ግን እኛ በጣም በ አለማዊ ስራ ራሳችንን ጠምደናል ከዛ ፈጣሪ ትንሽ ስጦታ ይሰጠናል እኛም ስራችንን እንቀጥላለን ከየት እንዳገኘነው ቀጥ ብለን ለማየት ጊዜ የለንም፡፡

በድጋሜ ፈጣሪ ከመጀመሪያው የተሸለ ስጦታን ይሰጠናል አሁንም ልክ እንደ መጀመሪያው ስጦታውን ወስደን ምስጋናም ለፈጣሪ ሳናቀርብ እድልኞች ነን ብቻ ብለን ስራችንን እንቀጥላልን ከየት እና ከማን እንዳገኘነው ቀና ብለን ለማየት አንሞክርም፡፡

እናም በትንሽ ድንጋይ ስንመታ፣ ማለት ትንሽ ችግር ቢጤ ስታገኘን ወደ ላይ ማየት እና መጮህ ከዚያም ከፈጣሪ ጋር መነጋገር እንጀምራለን፡፡ ስለዚህ ምንግዜም በህይወታችን ስጦታን ስናገኝ በፍጥነት ፈጣሪን ማመስገን አለብን በጭራሽ በትንሽ ድንጋይ እስክንመታ መጠበቅ የለብንም ሁሌም ቢሆን ከፈጣሪ ጋር እንገናኝ ...

#ሼር አድርጉ

Join: @Human_Intelligence
Join: @Human_Intelligence
“የጎራዴ ስልነቱ እና ጥንካሬው በፈሰሰበት እሳት እና በወደቀበት መዶሻ ልክ ነው!”

ተጠልፎ ወድቆ ወርቅ አፍሶ እንደሚነሳ ሰው እድለኛ ማነው? እሳት እና መዶሻስ ጎራዴን ስል ያደርጉት የለምን? ሰውስ ከመከራው ደንዳና በትር ምርኩዙን ያበጅ የለምን?... ከስቃዩ ጨካኝ ክንድስ የተፈተነና የነጠረ ጥበብን ይካን የለምን? ማን ነው እሳት ሳይበላው መዶሻ ሳያነኩተው ስል መኾን የሚቻለው?

ዮቶር-2
አለማየሁ ደመቀ
HTML Embed Code:
2024/06/01 15:11:14
Back to Top