TG Telegram Group Link
Channel: አቡሻኽር
Back to Bottom
ወይቤላ ተፈሥሒ ፍሥሕት
ቡርክት አንቲ እምአንስት ( 2)
#እመቤታችንን ቅድስት ድንግል #ማርያምን በጥዑም ምስጋና እንዲህ ዘወትር እናመስግናት🙏🙏
ይደውሉ ግእዝን በቀላሉ እናስጠናለን
💥ዮም ሠረቀ ለነ ወርኃ መስከረም ቡሩክ ወዘመነ ማርቆስ ሐዋርያ ያብጽሐነ እስከ ዘመነ ሉቃስ በዳኅና ወበሰላም
💥"ሰላም ለስዕርተ ርዕስከ እንተ ደለዎ እኳቴ፤ ወለርዕስከ ሰላም ዘተመትረ ከመ ናቡቴ ። ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ ። መብልዕ ዜና ፍቅርከ ወነገነ ቃልከ ስቴ። ያስተፌሥሕ መላእክተ ወሰብአ መዋቴ።
💥 እንደ ናቡቴ ለተቆረጠው ራስህ እና ምስጋና ለሚገባው የራስህ ፀጉርህ ሰላምታ ይገባል አበቅቴንና መጥቅዕን የምታስገኝ የዓውደ ዓመት ርእስ (አለቃ) ዮሐንስ የፍቅርህ ዜና ምግብና የቃልህ ነገር መጠጥ የሚሞት ሰውንና መላእክትን ያስደስታል" መልክዓ ዮሐንስ

💥እንቋዕ አብጽሐክሙ መትልዋነ ምኅላፍነ
የምኅፋችን( ቻናላችን )ተከታታዮች እንኳን አደረሳችሁ ።
...መንግሥቱ ዘለዓለም..
እስመ ኪያከ
አመክኗዊ ዕይታዎች ....:
የስላቅ እና በደልን የመሸፋፈኛ ቃላት

በኢትዮጵያ ቤ/ክ ታሪክ ውስጥ ብዙ የፈተና ጊዜያት አልፈዋል። የፈተና ምንጮቹ ከውጭም ከውስጥም ይነሳሉ።ምንም እንኳን በቤ/ክኗ ላይ በክፋት የተነሱ ሁሉም አልፈው ቤ/ክኗ እስካሁን ከነክብሯ ብትኖርም በዚህኛው ዘመንም መልኩን እየቀያየረ ብዙዎቹ ተግዳሮቶች እንደቀጠሉ ናቸው። በቤ/ክኗ ላይ የሚደርሰውን ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች በዚህ ጥሁፍ ዘርዝሮ መከተብ አይቻልም ግና በየጊዜው በቤ/ክኗ ላይ መዋቅራዊ የሆነ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ከየአቅጣቻው ለማጽናኛነት የሚወረወሩት ቃላት ከማጽናናት ይልቅ ስላቅ ሃዘን ከማስረሳት ይልቅ ይበልጥ በደል አስታዋሽ መሆናቸውን ለመገንዘብ መራቀቅ አይጠይቅም። የተወሰኑትን እንመልከት .......

1- “ኦርቶዶክስ ሀገር ናት”
ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከሃገር መሪ እስከ ካድሬ ይህችን ቃል ሲያሽሞነሙኗት ይውላሉ። ሀገርነቷን የሚነግሩን አማኞቿ በደል ከደረሰባቸው በኋል ነው።ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ኦርቶዶክስ ሃገር ናት እንደሚለው ቃል ማደንዘዣ የሆነ ቃል ያለ አይመስለኝም። ከአማኞቿ የኋህነት አንጻር የቤ/ክኔን ሀገርነት የሚያውቅ መሪ ተገኘ ብሎ ደስ ያላለው አልነበረም።ግን ሀገርነቷ በመሃል ከተማ ሲደሰኮር ከሶማሌ እስከ ባሌ አብያተክስትያናት ይቃጠሉ ነበር ካህናት በመንበሩ ፊት ይታረዱ ነበር። አዎ ሀገርነቷ ለማደንዘዣነት በሚደሰኮርበት ጊዜ በሻሸመኔ ክርስትያኖች መከራቸውን እንኳን ማስረዳት እስኪያቅታቸው ድረስ እየተፈተኑ ነበር። በሚገርም ሁኔታ ከሊቀጳጳጳስ እስከ ሰ/ትቤት አገልጋይ ከቤ/ክ ሚዲያዎች እስከ ግል የቤ/ክ ተቆርቋሪዎች ይህንን ቃል ስንሰማ ሁሉንም በደላችንን ዘንግተነው ልባችንን ነጋሪ በማያስፈልገው በመሪ ስለተነገረ ብቻ በሃገርነቷ ፍቅር ለውሰን ሌላ ቤ/ክ እስኪቃጠል ተጨማሪ ካህናት እስኪሰው ተጨማሪ ጥይት ለጥምቀት በዓል በሚዘምሩ መዘምራን ላይ እስኪተኮስ ታቦታት መመለሻ መንገድ አጥተው በሌላ አድባራት እስኪያድሩ ይህ ቃል ያደነዝዘናል። ወዳጄ ነጋሪ እና ምስክር የማያስፈልገውን ሃገርነቷን ከልባቸው አምነው ቢሆን ኖሮ የቤ/ክ ፈተና ባይጠፋ እንኳን በቀነሰ ነበር። እርስቷን እይቀሙ ሀገር ናር እንዴት ይባላል ? ማምለክያ ስፍራዎቿን ባቃጠሉት ላይ ህጋዊ እና ቆራጥ እርምጃ ሳይወስዱ ሃገር ናት እንዴት ይባላል? ዘወትር ስለኢትዮጵያ የምትጸልይን ቤ/ክ የሃገርሽን ባንዲራ መያዝ አትችይም ተብላ ወደ አገልጋዮቿ ጥይት እየተተኦሰ ሃገር ናት እንዴት ይባላል? ዝምታዋ እና ክርስቲያናዊ ትውፊቷ አርምሞ ውስጥ ከቷት እየተብደለች ስለበዳዮቿ የምትጸልይ ቤ/ክንን ከአንድ ነገድ ጋር በማቆራኘት እና የጥላቻ ማዕከል እያደረጉ ኦርቶዶክስ ሃገር ናት እንዴት ይባላል ? ሀገርን ለመምራት በተዘጋጀ የፖለቲካ ፓርቲ ሰነዶች ላይ ቤ/ክኗን የኋላቀርነት ምንጭ እና የእድገት እንቅፋት አድርጎ እያቀረቡ ኦርቶዶክስ ሃገር ናት እንዴት ይባላል ? የፖለቲካ ማስታገሻ ይሆን ዘንድ አስተዳደራዊ ነገሮች በሚከወኑበት የቤ/ክ አደረጃጀቶች ውስጥ ከሃይማኖታቸው ይልቅ ለጊዜያዊ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ግብዐት የሚሆን የሽፋን ስራ ለመስራት የተመደቡ በሁለት ሜዳ የሚጫወቱ ሰዎችን በቤ/ክኗ ከፍተኛ መዋቅር ላይ እያስገቡ ሀገርነቷን እንዴት መምስከር ይቻላል? በመሆኑም መስካሪ እና ተናጋሪ የማያስፈልገውን የሀገርነቷን ነገር ከምትነግግሩን ክብሯን ጠብቃችሁ አሳዩን ። እንደ ሕጻን ልጅ በመደለያ ቃላቶቻችሁ አትደልሉን። እየገደላችሁን ሃገርነታችንን አትነገሩን ። ታቦታት ከመንበራቸው እንዳይገቡ እየመለሳቹ ሀገርነታችንን አትንገሩን። የሰማይ መላእክት መስለው በሚዘምሩ ሰዎች ላይ እየተኮሳችሁ ኦርቶዶክስማ ሃገር ናት አትበሉን እንዲህ ባላችሁን ቁጥር ወትሮም ትንሾች ናችሁ ይበልጥ ትንሽነታችሁን ነው የምታሳዩን ።በእናንተ ልክ ዝቅ ማለት ይከብደናል።ጥይት ስታነሱ መስቀላንስታ እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ ማለቷ ብቻ ሃገርነቷን ያሳያል።ግራዋንም ቀኟንም ስትመቱ ልጆቿን ለአመጽ አለመጥራቷ ብቻ እናትነቷን ያሳያል። የቤ/ክኗን ሃገርነት ከእናንተ ዘንድ ምስክርነት አንፈልግም ።ሃገርነቷን ፊደል አበጅታ ድንቁርናን ስትፋለም አይታቿል ፣ ጥበብን ቀድታ ስታጎነጫችሁ ሃገርነቷን አይታችኋል ። ሀገር ናት ሃገር ናት እያላችሁ አታድክሙን ለሃገር ከሚሰጠው ክብር በጣም አነስተኛ የሆነውን ክብር አሳዩአት ።በእርግጥ ጌታዋ ክብሯ ለሆናት ቤተክርስቲያን ከእናንተ የሆነ ክብር ከዚህ ግባ የማይባል ቢሆንም ቅሉ እየገደላችሁ ግን ሃገር ናችሁ አትበሉን ።

2- “ የታሪክ መዝገብ የሆነች ቤ/ክ”

ለመደለል ድካም የሌለባቸው ፣ አማኞቿን ከማዘናጋት ወደኋላ የማይሉት የጊዜው ባለመድረኮች ሁሉ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን በደል በደረሰባት ቁጥር ከሚወረውሩት ማደንዘዣ ቃላት መካከል የታሪክ መዝገብነቷን ማስታወስና የጎብኚዎች መዳረሻነቷን እያነሱ ማሽሞንሞን ነው ። አሁን ማን ይሙት እንዲህ ያለውን የጨዋ ንግግር ሳያጤኑ ዝም ብለው ይቀበሉታል እና እንደ ዝም ማስባያ መንገድ እንጠቀምበት ብሎ ማሰብ እራስን ማሞኘት ካልሆነን በቀር ምን ይባላል። ወዳጄ ይህች ቤ/ክ ተቀዳሚ ስራዋ ክርስቶስን እና የእርሱን መንግስት መስበክ ነው። እርሷን እንደ ታሪክ ግምጃ ቤት እየቆጠርክ ሌላ ተቀዳሚ ዐላማ የሌላት በማስመሰል የታሪክ ማሰነጃ ግምጃ ቤት ወይም ሙዚየም ብቻ ያስመስሏታል።እኛም እውነት ነው ልክ ነው ብለን ተቀብለናል።ከቤ/ክኗ አስተምሕሮ ውጪ ያሉ በተለይ የሉተራዊያን መንገድ ተከታዮች ይህችን ቤ/ክ ያሞገሱ እየመሰሉ ያመሰገኑ እየመሰለኡ የሚናገሩትን ነገር ስትመለከቱ እጅጉን ያሳዝናል።በእነርሱ የጫዋነት ሚዛን የኛ ቤ/ክ የታሪክ ሙዚየም የቱሪስት መስህብ ጥንታዊ ድርሳናትን የምትሰበሥብ ተቋም ብቻ ያደርጉና የ እነርሱን ቤተ እምነት ደግሞ የክርስቶስን ወንጌል ሰባኪ አድርገው ይገልጻሉ በግልጽ አይናገሩት እንጂ ውስጠ ወይራው ዪሄው ነው።በተለይ እንዲህ ባለው ሕማማችን በሚበዛበት ጊዜ ብቅ እያሉ ያስተዛዘኝ የሚመስሉት አብዛኛዎቹ በቅንነት መንፈስ አይደለም።አባቶቻችን እንዲህ “ ደምና ብልሕ ነው ውሃን ከምድር አውጥቶ ምድርን ያጠጣልና” ይላሉ ። ምድር ከሰማይ ዝናብ ሲወርድላት ደመናን ታመሰኛለች ቅሉ ግን የውሃው ምንጭ ምድር ነበረች። አዎ እውነት ነው ቤ/ክ ብዙ ቅርሶች አሏት ።ከነዚያ ግባቶቿ የሚገኘውን በሙሉ ግን አሃገሯ ታበረክታለች እንደደመና የ እርሷ ያልሆነውን ወስዳ አይደለም የእራሷን ታሪክ ለቱሪዝም ሸጣ ሃገር ትመግባለች ለዚህ አበርክቶአ ደግሞ በደል ይከፈላታል።አዎ እውነት ነው መጽሐፍ ቅዱስን ተርጉማ ወደ ኢትዮጵያ ከማስገባት ጀምሮ የብሉይ እና የሐዲስ ኪዳንን ውበቶች አስተባብራ የያዘች ቤ/ክ እንዴት የታሪክ ማኅደር አትሆንም? አሁን እናንተ የእኛን ሃዘን ያስረሳቹ እየመሰላቹ ታሪካዊነቷን የምትናገሩላት ቤ/ክ የናንተን ምስክርነት የማትፈልግ ወንጌሉን መስበክ ተቀዳሚ ዓላማዋ ያደረገች የታሪክ ማኅደር ነች። ይህንን እኛን እንደመሸንገያ አትጠቀሙበት ።ቤ/ክኗን የታሪክ ጠባቂ የቅርስ ማጠራቀሚያ ሙዚየም ብቻ እያስመሰላቹ በቁስላችን ላይ እንጨት አትስደዱ። ተቀዳሚ ግብሯ ክርስቶስን ከነሙሉ ክብሩ ሰብካ አብልታ አጠጥታ በልጆቿ ልቦና ላይ ማንገስ ስራዋ የሆነን ቤ/ክ ተከታይ እና ተደራቢ በሆነ ስራዋ በመግለጽ ከእኛ እኩል የሃዘኗ ተካፋይ የሆናቹ አታስመስሉ። የቃላት ጋጋታቹ ሲመነዘር ከስላቅ ያለፈ ትርጉም የለውም ። እናት ቤ/ክ እያሉ መዋቅራዊ በደል ማስድረስ ፣ አማኞቿን ከገደሉ በኋል የታሪክ ማኅደር እያሉ የሃዘን
መግለጫ ማንጋጋት ከቀልድ ያለፈ ትርጉም አይኖረውም።

3- ጩኸቷን መቀማት

ሌላው በደል በአግባቡ እንኳን ጩኸቷን ማሰማት አለመቻሏ ነው። ተበደልኩ ብላ ስትጮህ በዳይዋም አብሮ ይጮሃል።እርስቷን ለመጠቅ ያሰፈሰፈ ሁሉ የአባቶቼን ንብረት አላስነካም ብትል የራሷ የሆነን መገልገያ አለማስደፈሯን እንደበደል ቆጥረው ይከሷታል። ልጆቼ ተገደሉብኝ ብላ ወደህግ አካላት ብትሄድ ገዳዮቹን ቀድማ እዛው ታገኛቸዋለች ። የጠነከረ መዋቅር ኖሯት ክርስቲያኑ ችግሮቹን ሙሉ ለማዋቅሩ አስረክቦ እንዳያርፍ የጠነከረ መዋቅር መገንባት ላም አለኝ በሰማይ አይነት ተረት የሚያስተርት ነገር ሆኗል። ስለዚህ እንደ ራሔል ወደላይ ዕንባዋብ ረጭታ በመቆዘም እስካሁን ሰንብታለች ካሁን በኋል በዚህ አይነት መንገድ መጓዝ ግን መዘዙ ብዙ ነው። ዛሬ የታቦት መንገድ ከልክሎ ያስመለሰ ፈርኦናዊ ጥጋብ ነገ ከመነበሩ ገብቼ ታቦታቱን አወጣለሁ ላለማለቱ ምን ዋስትና አለን? በደከመ የቤ/ክ የሚዲያ መዋቅር፣ ውሉ በማይታወቅ ችግር አፈታት ዘዴያችን ስሜታዊ በሆነው ሆይሆይታችን ከዛሬው ነጋችን የከፋ ነው። ርስታችንንም ጩኸታችንንም ተነጥቀን እንዴት ይሆናል ጎበዝ ?

ዲ. ፍጹም ( 2014)
Forwarded from yohannes
IPhone 11
128 GB storage
8 RAM
Price 38,000
HTML Embed Code:
2024/04/20 11:12:47
Back to Top