TG Telegram Group Link
Channel: ግጥም ብቻ 📘
Back to Bottom
ስማኝ ወዳጄ

ሲያንቋሽሹህ--- አርገው አሳሳች

ሲያስቀምጡህ---- ከሰው በታች

ፊት ሲነሱህ---- ስታያቸው

ሲያጣጥሉህ---- በቃላቸው

በዝምታ ንቀህ አልፈህ

በፈገግታህ ግረፋቸው::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
ስሚኝ እህቴ

ሲያንቋሽሹሽ---- አርገው አሳሳች

ሲያስቀምጡሽ-----ከሰው በታች

ፊት ሲነሱሽ----- ስታዪአቸው

ሲያጣጥሉሽ----- በቃላቸው

በዝምታ ንቀሽ አልፈሽ

በፈገግታሽ ግረፊያቸው::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
የማይጨንቀው ሲጨንቅ...
(በሳሙኤል አለሙ
.
በኩለ ቀንን አይባል
በኩለ ሌሊቱ አይባል
ሀብታም የውስኪ ፅዋውን ሲያጋጭ
ድሃ የቋጠረውን ዕንባውን ሲራጭ
"ተፈፀመ" ተብሎ ታይቶ ለሚጠፋው
ያፈጣል ከኩርሲው
ያፈጣል ከሶፋው
.
አንተስ ላይባሉት...
በኖረበት ሲያዝን
በኖረበት ሲደሰት መልሶ መላልሶ
ድራማው ህይወቱን አይቶ ጨርሶ
በድራማው ዓይኑ ቀልቶ ዓይኑን ያሻል
ይቀጥላልን ሲጠባበቅ ውሎ ያመሻል
።።።።።

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu

@getem
@getem
ይድረስልኝ ላንቺ ቀንሽ ለጨለመ፤
ልብሽ ለሚያነባ ዉስጥሽ ለታመመ፤

የመኖርሽ ዉሉ የህይወትሽ 'ጣሙ፤
መሪር ለሆነብሽ ሳይገባሽ ትርጉሙ፤

ይድረስልኝ ላንቺ ተስፋን ለቆረጥሽዉ፤
ከራስሽ ተጣልተሸ ሞት ለተመኘሽዉ፤

ይድረስልኝ ላንቺ.........

ምን ድቅድቅ ቢዉጥሽ ፤
ምን ፅልመት ቢከብሽ፤

ሌቱም ይገፍና ደግሞ ይነጋጋል፤
አሮጌዉ ያልፍና 'ባዲስ ቀን ይተካል።
.............................................

በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
.     👄አፍና ልብ❤️

🙅‍♂ አፌን አትመኝው አንዳንዴ ይዋሻል

🤥 በመግደርደር ብዛት እውነትን ያሸሻል

❤️ ልቤ ግን ሞኝ ነው ትንሽ ብትቀርቢው

            ሁሉም ይታይሻል

💓ከሌላ አብልጦ አንቺን እንደሚወድ

         በደንብ ይነግርሻል።❤️‍🔥

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
ወሰን አልባው ደግነሽ
ለካ ልክ ኖሯል ሞኝነሽ
የዛሬ መሳዩ አዋቂ
መነሻ ነጥቡን ናቂ
ገፁ ሲታይ ጥበበኛ
ለራሱ ከራሱ ጠበኛ

By @Yidne567

@getem
@getem
@getem
( አትፍረድ ... )
==============

እኔ ድንግሉ ሰው
ትዕዛዙን ልሽር ስወድቅ ከአልጋ
ገዳም ገባች አሉኝ
ዘማይት ያልኳት ሴት .. አምላኳን ፍለጋ

እንዲያ የረገምኳት
እንዲያ ያሻሟጠጥኳት
ድንጋይ ተንተርሳ ስትጸልይ ለኔ
ሞኙ ከዓለም ገባሁ
ለበደል መስዋእት ለኃጢአት ምናኔ

ግዴለም ምን ቢከብድ
ፍጻሜህን ሳታይ
አትፍረድ ወገኔ !!!!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
አምላኬ ባትረዳኝ ብትከዳኝ እንደሰው 
ሀጥያቴን ብትቆጥር በደሌን ብትጠቅሰው
እንኳንስ በአንተ ዘንድ አልመችም ለሰው
ክፋት ያገረሸ ተንኮል ያጠለሸ ሰውነት አዝዬ
ከፊትህ ቆሜያለሁ ዛሬም ማረኝ ብዬ
ምን ይሆን ምላሽህ አልልም በአንተ ፊት
አውቀዋለሁኛ!!
ባትምረኝ ከጥፋት ባታወጣኝ ከመዓት
አልኖርም አንድ ቀን እንኳንስ ለአመታት።

BY፦LIONEL YOHANNES

@getem
@getem
@paappii
ትናንትና ማታ እጅጉን ናፍቀሽኝ
ያ ክፉ ትዝታሽ አላስተኛህ ብሎኝ
ድምፄን ከፍ አድርጌ ስምሽን ጠራሁኝ
እንደ ደብተራ አስማት እንደ ጴጥሮስ ክህደት
በአንዴ ባይሆንልኝ ሶስቴ ደጋገምኩት
ሰልስቱም አልሆነ ሃያ አንዴ ጮኬ በማርያም ለመንኩኝ
አርባ አንድ አድርጌ ኪሪያላየሶን አልኩኝ
ጠራሁሽ በናፍቆት ጠራሁሽ በፍቅር
ወይ አንቺ ነይልኝ ወይ ትዝታሽ ይቅር

                   ዘረ-ሠናይ
                @SenayArt

@getem
@getem
@getem
🗣የሰው ወሬ🗣

መቼም ቢሆን ላይቆም ነገር

ምን ብትሰራ ላይቀየር

ላያስገኝህ ትንሽ ፍሬ

ጆሮ አትስጠው ለሰው ወሬ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
የትኛው ነሽ አንቺ



ፀደይ ነሽ መስከረም ?
ግማሽ መልክሽ አደይ ግማሽ መልክሽ አረም።
ግማሽ የሚቀጠፍ ግማሽ የሚነቀል ፣
የትኛውን ልመን ምንሽን ልቀበል፤
የተኛው ነሽ አንቺ ምህረት ወይስ በቀል?
ስምዖንን መስለሺኝ መስቀሌን ስትይዢ
ለአንድ ሠሞን ፍዳ፣
በየት ዞረሽ ሸጥሽኝ ለብቻ መከራ
ደግሞ እንደ ይሁዳ።


✍️©እስራኤል
   (@AdamuReta)

@getem
@getem
@getem
እኔ እንደናፈቅኩሽ ታውቂያለሽ አውቃለሁ
አንቺ ሌላ ወደሻል ሌላ ተላምደሻል አዎን ሰምቻለሁ
የሰማሁት ነገር ሀሰት ይሁን ብዬ
አምላክ ለምኛለሁ
ሻማውን ለኩሼ ጧፍ እያበራሁኝ ተማፅኘዋለሁ
አንቺን ያጣሁ ዕለት ጠፍቷል የኔ ብርሃን
እንደ አምላክ ስቅለት ያውም በእኩለ ቀን
ይሄን ሁሉ መዓት እያየሽው ባይንሽ 
ነገ የተሻለ ነው ለምን ትይኛለሽ ?
የኔ ፀሐይ ትናንት ማለፉን እያየሽ
የኔ ጀንበር አንቺ መሆንሽን እያወቅሽ ?
በርግጥ ነገ እንዳለ በልቤ አምናለሁ
ቀኑ መሽቶ ይነጋል ይህንን አውቃለሁ

ግን ታውቂያለሽ አንዳንዴም

የ ጀንበር መውጣቷ ሌሊት አያነጋም
ጎህ መቅደዱ ብቻ ጨለማ አያጠፋም
በትር የያዘ ሁሉ ባህሩን አይከፍልም
ባለ ወንጭፍ ሞልቶ ጎልያድን አይጥልም
ገባኦን ካልሆነ አትቆምም ፀሐይም
አንቺ የሌለሽበት ሁሌ ጨለማ ነው ጀንበር ባትጠልቅም

                        ዘረ-ሠናይ
               @SenayArt
@getem
@getem
@getem
ሀገር ስጠኝ...

ሀገር ስጠኝ እስቲ ወዳጄ
ማለት ሚያስችለኝ ''እዛ ሄጄ
ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ"

ሀገር ስጠኝ የምኮራበት
መልስ የሌላቸው እንቆቅልሾች የማይበዙበት
ግራ ሲገባኝ ምን አውቄልህ ማልባልበት

እስቲ ሀገር ስጠኝ አንድ ትልቅ
ከሰፈር ጎሳ ከብሄር ሚልቅ

ሀገርን ስጠኝ ሰላም ያለበት
ሰው ለፍቶ ሰርቶ የሚያተርፍበት
ካለሰቀቀን የሚኖርበት::

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
ትናንትና ጠዋት
ፀሐይ የመሰለች ቆንጆ ልጅ አይቼ
በሊቀ መልዓኩ
እንዴት ምታምሪው አልኩኝ ድምፅ አውጥቼ
ትንሽ ኮራ እያለች ጥቂት ፈገግ ብላ አለችኝ "ከላይ ነው"
ባለቤቱ የፈራው "ዉስጥሽ"ስ እንዴት ነው ?

                  ዘረ-ሠናይ
@SenayArt

@getem
@getem
@paappii
እዉነት እንዳይመስልሽ
.
.
ዛሬ ......ምን ብትደምቂ፤
ከቆነጃጅቱ እጅጉን ብትልቂ፤

ኑሮ ተመችቶሽ ያ.... ፊትሽ ቢወዛ፤
ወደድኩሽ የሚለዉ አፍቃሪሽ ቢበዛ ፤

ሴትነትሽ ማለት... መልክ ከመሰለሽ፤
ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ፤

አንቺን ሳያማክር........

የጠቆረዉ ፀጉርሽ.. በሽበት ይተካል፤
ጸአዳዉም መልክሽ በፍጥነት ይረግፋል፤

ሴትነትሽ ማለት መልክ ከመሰለሽ፤
ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ።
..........................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
ጥላሞት
(shadow
)



አንድ ጥያቄ አለ
ነብሴን ሁልግዜ
የሚያብሰለስላት
ገሀድ የማይገልጠው
ማነው የኔ ጠላት?
ማነው እንቅፋቴ
ጉድባ ለመንገዴ
ሌላ አካል አለ
ወይስ ክፉ ገዴ?

ማነው ከነብሴ ጋር
ያረገኝ ባላንጣ
ህዋው ነው ጠላቴ
ወይስ ክፉ እጣ?

ጀርባዬን ለህልሜ
ማነው ያሰጠኝ ሰብ
ወይስ አቅቶኝ ነው
ተስኖኝ ነው ማሰብ?

ማነው ማነው ማነው?

በዳይ ስጋ ችሮኝ
'ሚያስረግም ዕለቴን
ሬት ሆኖ ኑሮ
'ሚያስናፍቀኝ ሞቴን

ማነው ማነው ማነው?

ስደምር ስቀንስ
ስመትር ስለካ
እኔ ፊት የቆምኩት
ራሴው ነኝ ለካ።

ይሄን ያወቅሁኝ ቀን
ይሄ የገባኝ 'ለት
ፊት የቆመው እኔን
ገለል አረግሁለት።

አሁን ጸሐይ ወጣ።


✍️©እስራኤል


@AdamuReta

@getem
@getem
@getem

Inspiration(ንሸጣ) : psychological podcast about self sense and shadow
ልማድ ቢሆንብን ቃሉ ከአፋችን
"እንዴት ነህ?"
ስንባል ደህና ነው መልሳችን
ለሰው የማይነግሩት ቢሆን ታሪካችን
ይሸሸግ ጀምሯል በሶስት ፊደላት
ጥልቁ ህመማችን

:- "እንዴት ነህ?"
:- ደህና ነኝ!!

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
ጊዜ ደጉ 🕔

ሰው ከኔ ሲለየኝ

ያመንኩት ሲርቀኝ

መሄጃው ሲጨንቀኝ

ፍረሀት እምነቴን እየሸረሸረ

እንዴት እሆን ብዬ እሰጋ ነበረ
:
:
:
ለካ ጊዜ ደጉ ለሁሉም ይደርሳል

እምባዎች ያብሳል

ቁስል ይፈውሳል

ፈጠነም ዘገየም መከራን ያስረሳል።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
.....
እሱ እኮ.. እያሉ ባሞገሱህ ቁጥር፤
አንተን እያነሱ ባወደሱህ ቁጥር፤

ልብህን አይሙቀዉ ፍፁም ደስ አይበልህ፤
ቀን የከፋ ለታ.........
ቁልቁል ይጥሉሃል....... እላይ የሰቀሉህ።
......................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
▪️▪️አባቴ▪️▪️▪️

ምተማመንብህ ምኮራብህ አባዬ

ስወድቅ ምታነሳኝ የኔ መከታዬ

ለቤትህ ምሰሶ ትከሻህ ጠንካራ

ለልጆችህ ስትል ሳትደክም ምትሰራ።
:
:
ፍቅርህን ሳትሰስት ሰጥተህ ያሳደከኝ

መልካም ሰው መሆንን ለኔ ያስተማርከኝ

አባቴ ውለታህ እጅጉን ብዙ ነው

ከማመስገን በቀር ሌላ ምን እላለው።
:
:
ምፈልገው ቢኖር ታላቁ ምኞቴ

ደስታህን ማየት ነው ሳለው በህይወቴ

አባቴ አድምጠኝ ስማኝ ይሄን ስልህ

በጣም ወድሀለው እኔ ያንተ ልጅህ።

📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
HTML Embed Code:
2024/04/26 04:17:04
Back to Top