TG Telegram Group Link
Channel: H
Back to Bottom
Channel created
ኑሮ ለምን ተወደደ

ሞያዊ ምልከታዎች መንግስትንም ተጠያቂ የሚያደርጉ ናቸው የሚሉት አስተያየታቸው ለባላገሩ ቲቪ የሰጡ የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች መንግሥት የዋጋ ንረትን የሚያባብሱ እርምጃዎች ከመውሰድ መቆጠብ እንዳለበት አሳስበዋል። በልቶ ማደር ከበደን የሚል እሮሮ የሚያሰማው የማኅበረሰብ ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ ከሰሞኑ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃኑ ላይ ሲዘዋወር የቆየው መብላት የቸገራቸው እናት መሶባቸው ለመሸጥ አደባባይ መውጣት ለዚህ ላነሳነው ጉዳይ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡

የምርቶች ዋጋ በየዕለቱ ለእጥፍ በተጠጋ ዋጋ እየጨመረ ይገኛል። የምርቶች ዋጋ በቀናት ብቻ ሳይሆን በሰዓታት ልዩነት  የሚለዋወጥበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል፡፡ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ገበያ ላይ የዋጋ ንረት መታየት እንደ ጀመረ የጥናት ውጤቶች ያሳያሉ፤ የዋጋ ንረቱ ባለፉት ዐሥርት ዓመታት የሚያቆመው ልጎም አጥቶ ለብዙ ሕዝብ የጭንቀት ምክንያትም ሆኗል፡፡

መንግሥት የዋጋ ንረቱን ያረጋጋል ያላቸውን በርካታ እርምጃዎች እየወሰደ እንደሆነ ቢናገርም እስካሁን በመሬት ላይ የተቀየረ ነገር እንደሌለ የማእከላዊ ስታስቲክ ኤጀንሲ በየወሩ የሚያወጣውን የዋጋ ግሽበት ቁጥራዊ መረጃ መመልከት ይቻላል።

የመንግስት እርምጃዎች እና አንድምታቸው

"መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች የዋጋ ንረቱን እያባባሰው ነው" ይላሉ የምጣኔ ኃብት ባለሞያዎችም። መንግሥት ባለፉት ዓመታት የነዳጅ ፣የመዘጋጃ ቤት አገልግሎት ፣ የኤሌትሪክ ታሪፍ ላይ ጭማሪ ማድረጉ የዋጋ ንረቱን በተወሰነ መልኩ እንዳባበሰው ያነሳሉ፡፡

* የነዳጅ እና መሰል የዋጋ ጭማሬዎች

ከሰሞኑ የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉ የዋጋ ንረት  ላይ የራሱን ጫና መፍጠሩን ያነሱት የምጣኔ ሃብት ባለሞያው ዶ/ር አስፋው አድማሴ ናቸው፡፡ መንግሥት በአንድ ጊዜ የተጋነኑ የሚመስሉ የዋጋ ጭማሪዎችን ከማድረግ ይልቅ በሂደት የሚጨምርበት ሁናቴ ቢፈጠር ይተሻለ እንደሆነም  የምጣኔ ሃብት ባለሞያው ይመክራሉ፡፡

* በቃል የቀሩ ውሳኔዎች

ሌላኛው ለባላገሩ አስተያየታቸውን የሰጡት የምጣኔ ኃብት ባለሞያው አቶ አጥላው አለሙ  ናቸው፡፡ መንግሥት ከኢኮኖሚው ጋር በተያያዘ የሚሰጣቸው አስተያየቶች እና መሬት ላይ የሚታየው እውነታ የተለያየ መሆኑ ኢኮኖሚው ተገማች እንዳይሆን ፤ ነጋዴው እና ሸማቹ በመንግሥትም እምነት እንዳይጣልበት አድርጎል ይላሉ፡፡

መንግሥት ቀድሞ መውሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ሳይወስድ በመቆየቱ የዋጋ ውድነቱ  ዛሬ የደረስንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል የሚሉት ዶ/ር አስፋው ተበላሽተው የቆዩ የገበያ ስርዓቶች ሳይጠገኑ በመቆየታቸው የዋጋ ንረቱን እንዳባባሰው አንስተዋል፡፡

* ፍራንኮ ቫሎታ

"ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዶላር አንፃር የብር የመግዛት አቅም እያደከመ መጥቷል። ይህም 80 በመቶ በላይ ምርቷን ከውጭ ለምታስገባ አገር የምርት ዋጋ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል" የሚሉት የምጣኔ ኃብት ባለሞያው በቅርቡ የተፈቀደው 'የፍራንኮ ቫሉታ )'/አሰራር በትይዩ ገበያ ( በጥቁር ገበያ ) እና በባንኮች የምንዛሬ ዋጋ ላይ ሰፊ ክፍተት መፍጠሩን ያነሳሉ ይህም የዋጋ ንረቱን እንዳባባሰው ጠቁመዋል፡፡

* የአዳዲስ ገንዘብ ህትመት

ሌላኛው ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት ዋነኛ ምክንያት መንግሥት አትሞ ወደ ገበያው የሚለቀውን የገንዘብ መጠን መጨመሩ እንደሆነ የሚያነሱት ዶ/ር አጥላው በገበያው ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የገንዘብ መብዛት ገንዘብ የመግዛት አቅሙ እንዲዳከም አድርጎታል ባይ ናቸው። ይህም ሁሉም ምርት በአንድ ጊዜ  እንዲጨምር ማስገደዱን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

* ቅድሚ የሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች አለመለየት

ባለፉት ዓመታት መንግሥት በብድር እና እርዳታ የሚያገኛቸውን ገንዘቦች ፈጣን ተመላሽ በሌላቸው ፕሮጀክቶች ላይ ሲያውል እንደነበረም ዶ/ር አጥላው ያነሳሉ። እነዚህ ፕሮጀክቶች በርካታ የሥራ እድል መፍጠር በማይችሉ፣ የምርት ውጤት በሌላቸው፣ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት አስተዋፅዖ የሌላቸው መሆናቸውን በማንሳት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የማይገባው መሆኑን ያሰምሩበታል፡፡

ምን አልባት ይህ ገንዘብ በሌሎች ምርትቶች እና ውጤት ባላቸው ሥራዎች ላይ ቢያርፉ የተሻለ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡መንግሥት የዋጋ ንረቱን የሚያባብሱ እርምጃዎችን ከመውሰድ መቆጠብ እንዳለበት የሚያነሱት ባለሞያዎቹ በተቻለ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በጥንቃቄ ማየት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

via - ባላገሩ ቴሌቪዥን
ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በ300 ሚሊዮን ዶላር 500 የኔትወርክ ማዕከላትን መገንባቱን አስታወቀ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እስካሁን አዲስ አበባን ጨምሮ በ11 ከተሞች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

የኩባንያው ስራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ በአዲስ አበባ አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይ እንደተናገሩት ኩባንያው በአንድ ወር ውስጥ 200 ሺህ ደንበኞችን አፍርቷል።

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነ የተናገሩት ስራ አስኪያጁ በ300 ሚሊዮን ዶላር ወጪ 500 የኔትወርክ ማዕከላትን፣ ሁለት የዳታ ማዕከላትን እንደገነባም ተናግረዋል፡፡
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በጉዞ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ተጋጭቶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

👉 በተማሪዎቹ ላይ የደረሰው አደጋ ቀላል ሲሆን ከፈተና እንደማያስቀራቸው ተጠቁሟል

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በጉዞ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተጓጭቶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን አስታወቀ ።

አደጋው የደረሰው በምዕራብ ጎጃም ዞን በሰሜን ሜጫ ወረዳ አምቦ መስክ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በትናንትናው ዕለት 5:30 ገደማ ሲሆን ከምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ በመነሳት የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎችን በመጫን ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በጉዞ ላይ ነበረ። የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ እንደሆነ ተገልጿል ።

በትራፊክ አደጋው የተጎዱ ሌሎች ሰዎች መኖራቸውን እና በተማሪዎች ላይ ከደረሰው ጉዳት መካከል በአምስት ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱንና ከፈተና የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ የሰሜን ሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አ/ቶ መዝገቡ ስመኘው ተናግረዋል ።

የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር በመሆኑ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በተገቢው ፍጥነት ማሽከርከር እንደሚገባ አ/ቶ መዝገቡ ተናግረዋል::
#ማስጠንቀቂያ

መፈተኛ ጣቢያ ውስጥ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተፈታኞቻችን ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል፡፡ የተከለከሉ ነገሮችን ማንም ተፈታኝ ይዞ እንዳይገባ ከወረዳ ጀምሮ ገለጻ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም አካላዊ ፍተሻ ተደረጓል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን በተለይም ተንቀሳቃሽ ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ ድርጊቱ ከፍተኛ የፈተና ደንብ ጥሰት በመሆኑ ውሳኔው ከሁሉም ፈተና የሚሰረዙ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ከዚህ በኃላም የተከለከሉ ነገሮችን መፈተኛ ማዕከላት (የኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ማንኛውም ተፈታኝ ይዞ ቢገኝ ከሁሉም ፈተና የሚሰረዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ገለጻውን ባለመቀበልና አካላዊ ፍተሻዎችን በማጭበርበር ስለፈጸመው ጉዳይ ተጨማሪ ህጋዊ ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን እንደግኝቱም ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል፡፡

ፈተና የሁሉም ማህበረሰብ ሀብት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለፈተና ደህንነትና ፍትኃዊነት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
HTML Embed Code:
2024/04/24 17:03:08
Back to Top