TG Telegram Group Link
Channel: አል ሒከም 💚 Al Hikem💚
Back to Bottom
ሳቅ ከኡለሞች ጋር!
````

አንድ ሰው ሻዕቢይ ጋር መጣና እንደዚህ ብሎ ጠየቃቸው፦

ሰውዬው፦ የሆነችልን ልጅ ካገባኋት በኋላ እንደምታነክስ አወኩ… መፍታት እችላለሁ እንዴ?
ሻዕቢይ፦ ግልብያ ልትወዳደርባት ከሆነ እንደገበሀት ፍታት!

ሻዕቢይ ተጠየቀ ኢህራም ያደረገ ሰው ሰውነቱን ማከክ ይችላልን ?
ሻዕቢይ፦ አዎ!
ጠያቂ፦ እስከምን ድረስ ?
ሻዕቢይ፦ አጥንቱ እስኪታይ ድረስ!

አንድ ሰው አቡ ሃኒፋ ዘንድ መጣና ጠየቃቸው..
ጠያቂ፦ ገላዬን ለመታጠብ ወንዝ ውስጥ ስገባ ወደ ቂብላ ልዙር ወይስ ወደሌላ?
አቡሃኒፋ፦ ልብስህ እንዳይሰረቅ ወደልብስህ ዙር !

አንድ ሰው ቃዲ መሀመድ ኢብን ኢስማኢል አል-ኡምራኒን እንደዚህ ብሎ ጠየቃቸው፦
ጠያቂው፦ ያ ሼኽ ሚስቴ የማህፀን ማስወገድ ኦፕሬሽን አድርጋ ነበር እናም አሁን መውለድ ትችላለች?
ኡምራኒ፦ ልጄ ማህፀኗ ከወጣ እንዴት ብላ ነው
የምትወልደው?
ሰውየው፦ አላህ ከፈለገስ?
ኡምራኒ፦ አላህ ከፈለገማ አንተም ትወልዳለህ!

አንድ ሰው አምር ኢብን ቀይስን ጠየቀ
ሰውየው፦ አንድ ሰው መስጊድ(አፈር ላይ) ሰግዶ ሲወጣ ልብሱ ግንባሩና ኹፉ ላይ ተጣብቀው የሚያገኛቸውን ነገሮች ምን ያርጋቸው ?
አምር፦ ይወርውራቸው(ያራግፋቸው)
ሰውየው፦ መስጊድ እስኪመለሱ ድረስ ይጮሀሉ ይባላል…
አምር፦ ተዋቸው ጉሮሮዋቸው እስኪቀደድ ድረስ ይጩሁ!
ሰውየው፦ ጉሮሮ አላቸው እንዴ?
አምር፦ ታድያ እንዴት ይጮሀሉ?

አንድ ተማሪ ከሼኽ አልባኒ ጋር በመኪና እየሄደ ነበር ሼይኽ አልባኒም በፍጥነት ነበር የሚነዱት ከዛም ተማሪው እንዲህ አለ፦
ተማሪው፦ ያ ሼኽ ፍጥነታችሁን ቀንሱ ሼኽ ኢብን ባዝ እኮ ከሚፈቀደው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር እራስን ለጥፋት እንደመዳረግ ይቆጠራል ብለዋል
አልባኒ፦ ይህ መኪና ነድቶ የማያውቅ ሰው ፈትዋ ነው(ማየት የተሳናቸው ስለነበሩ)
ተማሪው፦ ያላችሁትን ለሼኽ ኢብን ባዝ ልንገራቸው?
አልባኒ፦ ንገራቸው
ተማሪውም ሼኽ አልባኒ ያሉትን ለሼኽ ኢብን ባዝ
ሲነግራቸው…
ሳቁና እንዲህ አሉ፦ ይህ ዲያ (የግድያ ካሳ) ከፍሎ የማያውቅ ሰው ፈትዋ ነው በለው!

አንድ ሰው ኢብን ኡሰይሚንን እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፦
አንድ ሰው ዱዐ አድርጎ ከጨረሰ በኋላ ምንድን ነው
የሚያደርገው?
ኢብን ኡሰይሚን፦ እጁን ያወርዳል !

ሌላኛው ጠየቃቸው፦ አንድ ሰው በካሴት ቁርዐን እያዳመጠ ሳለ ሱጁድ እሚወረድበት ቦታ ካጋጠመው ሱጁድ ይውረድ?
ኢብን ኡሰይሚን፦ አዎ ካሴቱ ሱጁድ ከወረደ!

ሌላ ግዜ ደግሞ ስለ ኒካህ ትምርት እየሰጡ ሳለ አንዱ እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው…
ጠያቂው፦ አንድን ሴት ካገባኋት በኋላ ጥርስ
እንደሌላት ባውቅ ለዚህ ዐይብ ብዬ ኒካሁን ማፍረስ ይበቃልኛል?
ኢብን ኡሰይሚን፦ ይች እንደውም ጥሩ ሴት ናት ምክንያቱም ልትነክስህ አትችልም !!!

Share&join
🙏🙏🙏🙏
@Alhikem @Alhikem
@Alhikem @Alhikem
የሚሰግዱበት መሰጂድ የላቸውም እንዲሁም ፀሀዩን የሚቋቋሙበት የሚያቀዘቅዝ ነገር የላቸውም እንዲሁም የመሬቱ ቃጠሎ ከባድ ስለሆነ የሚያነጥፉት ነገር የላቸውም .....
በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ሆነውም ሰላትን አልተዉም
😔😔በሰላትህ ላይ የደከምክ ሰው ሆይ ሰበብክ ምን ይሆን ??
@Alhikem
በዑመር (ረ.ዐ) ዘመን ሶስት ወጣቶች አንድ ስውዬን
ጎትተው በማምጣት
‹‹ያዐሚረል ሙእሚኒን ይህ ሰው አባታችንን ገድሏል ሀድ/
ቅጣት/ እንደትወስንበት እንሻለን›› በማለት በእልህና
በቁጣ
ተናገሩ፡፡
‹‹ለምን ገደልክ ?›› ሲል ዑመር ረጋ ብሎ ጠየቀ
‹‹ እኔ የግመል እረኛ ነኝ… አንደኛው ግመሌ የአባታቸው
መሬት ላይ ካለ ዛፍቅጠል ቀንጥሶ ሲበላ አባታቸው
ድነጋይ
ወርውሮ ሲመታው ግመሌ ሞተ እኔም እሱ የወረወረውን
ድንጋይ አነስቼ ስወረውር መታሁትና ሞተ››…ሲል ተናገረ፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ ቅጣት እወስንብሃለሁ!›› አለ ዑመር
(ረ.ዐ)::
‹‹እሺ ሦስት ቀናትን አቆየኝ……አባቴ ሲሞት ለኔና
ለወንድሞቼ የተወው ከንዝ/የተደበቀ ሃብት/አለ እኔ አሁን
እዚሁ ከሞትኩ ከንዙም ይጠፋል ወንድሞቼም ይጠፋሉ
(ይቸገራሉ)..ስለዚህ ፍቀድልኝና ሄጄ ልምጣ›› አለ
ተከሳሹ፡፡
‹‹ታዲያ እሰክትመለስ ዋስ የሚሆንሀ ማነው?›› በማለት
ዑመር (ረ.ዐ) ጠየቀ
ሰውዬው የተሰበሰቡትን ሰዎች ተመለከተ የሚያውቀው
የለም……የእያነዳንዱን ፊት ተመለከተና
‹‹ያ ሰውዬ እዛ ጋ የቆመው ›› አለና አንዱን ጠቆመ
‹‹ያ አባ ዘር ለዚህ ሰው ዋስ ትሆናለህ ?›› በማለት ዑመር
(ረ.ዐ) የተጠቆመውን ሰውየ ጠየቀው…
‹‹አዎን ያ አሚረል ሙእሚኒን ›› በማለት መለሰ::
‹‹ይህ ሰው ካመለጠ ቅጣቱ አንተ ላይ ተፈፃሚ
እንደሚሆን
አታውቅም እንዴ? ›› ሲል ዑመር ተገርሞ ጠየቀ
‹‹ግድ የለም ያ አሚረል ሙእሚኒን እኔ ዋስ
እሆነዋለሁ….›› ሲል አቡዘር መለሰ፡፡ሰውየው ሄደ፡፡
አንድ ቀን አለፈ….ሁለተኛው ቀን ተከተለ…በሦስተኛው ቀን
….ሰውየው ካልመጣ ቅጣቱ አቡዘር ላይ ስለሚፈፀም
ሰዎች
ተጨነቁ………ሆኖም በሶስተኛው ቀን ከመግሪብ
(ከመምሸቱ
በፊት ) በፊት …..ያ ሰው እያለከለከ መጣ…በጣም
እንደደከመው ገፅታው መስካሪ ነበር፡፡..ከዑመር (ረ.ዐ)
ፊት
ለፊት መጥቶ በመቆም
‹‹ከንዙን ለወንድሞቼ እና ለእናቴ ወንድሞች አስረክቤ
መጣሁ አሁን በቁጥጥርህ ስር ሆኛለሁ ቅጣቱን
ፈፅምብኝ››
በማለት ተናገረ፡፡
ዑመር (ረ.ዐ) ተገረመ ;
‹‹ በዚያው ማምለጥ የምትችል ሆነህ እንዴት ተመለስክ?
››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ ሰዎች ዘንድ ‹ቃል አክባሪነት ጠፋ› እንዳጥባል ፈርቼ
ነው›› በማለት መለሰ ተከሳሹ ፡፡
ዑመር ወደ አቡዘር (ወደተዋሰው ሰው ) ዙሮ
‹‹ይህን ሰው እነዴት ዋስ ሆነከው? ›› በማለት
ጠየቀ…………
‹‹እኔማ ዋስ የሆነኩት በሰዎች ዘንድ ኸይር/መልካም/
ስራ
ጠፋ እንዳይባል ፈርቼ ነው››ሲል አቡ ዘር መለሰ፡፡
በሁኔታው
የሟች ልጆች ልብ ተነካ…
‹‹በቃአፉ ብለነዋል(ምረነዋል )…ቅጣቱ
እንዳይፈፀምበት››
ሲሉ ተናገሩ…
ዑመር (ረ.ዐ) ‹‹ለምን?›› ሲል ጠየቃቸው…..
‹‹እኛ ደግሞ በሰዎች መሃል ‹ይቅር መባባል ጠፋ ›
እንዳይባል እንፈራለን›› አሉ……
እኔ ደግሞ ሰዎች የሰሙትን አያደርሱም እነዳይባል
ሰጋሁና
ነገርኳችሁ!! እናተጋ ቢቻ እንዳይቀር ሼር አድርጉት
ጀዛኩሙ ላህ!!

@Alhikem @Alhikem
@Alhikem @Alhikem
ዐሹራእ ደረሰ

አቡ ሀይደር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምሥጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

#ዐሹራእ ምንድነው?

ዐሹራእ ማለት (የሙሐረም ወር) አሥረኛው ቀን ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሙሐረም አንደኛው ወር ተብሎ ይጠራል፡፡

#ይህ ወር ክብር ያለው ወር ነው፡-

አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ከነቢያችን (ዐለይሂ ሶላቱ-ወስ-ሰላም) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- "ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው" (ሙስሊም 2812)፡፡
ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አሥረኛው የዐሹራእ ቀን በላጭ ቀን ነው፡፡

#ለምን ይጾማል?

ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው፡ እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ! በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡
ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡

#ጥቅሙስ ምንድነው?

አቢ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)፡፡
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዐሹራእን ቀን የጾሙና ሶሓቦቻቸውን ያዘዙ ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል ሲሏቸው፡ እሳቸውም፡- በቀጣዩ ዓመት አላህ ካደረሰን ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን አሉ፡፡" (ሙስሊም 2722)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ "ከ(ዐሹራእ) ቀን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድን ቀን ጹሙ" ብለዋል (አሕመድ የዘገቡት)፡፡ ሐዲሡ ዶዒፍ ነው የሚሉም አሉ ወላሁ አዕለም፡፡
ያ ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልክተኛ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ የኢስላም ሊቃውንትም ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት የሁዳዎችን ላለመመሳሰል ዘጠነኛውንም ቀን ጨምሮ መጾም ነቢያዊ ሱንና መሆኑን ገለጹ፡፡

#መጾሙ ዋጂብ ነው ወይስ ሱንና?

የዐሹራእን ቀን መጾም ሑክሙ ሱንና ነው፡፡ በሒጅራ 2ኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ላይ ስለነበር የተደነገገው የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር፡፡ ከ7 ወር በኋላ ግን በሒጅራ 2ኛው ዓመት 8ኛው ወር ሻዕባን ላይ የረመዷን ጾም ግዳጅነት ሲደነገግ፡ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰረዘ፡፡ ይህን በተመለከተ ቀጣዩ ሐዲሥ እንዲህ ይላል፡-

እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ ካዕባም የሚሸፈንበት ቀን ነበር፡፡ አላህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- የፈለገ ሰው (ዐሹራእን) ይጹመው ለመጾም ያልፈለገ ደግሞ ይተወው" (ቡኻሪይ 1489)፡፡

#መቼ እንጀምር?

የሙሐረም አስረኛው ቀን (ዐሹራእ) የፊታችን ረቡእ ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አላህ ወፍቆት ይህን ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ይጹም፡-
ሀ. ረቡእን ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ቀንነው፡፡
ለ. ማቅሰኞና ረቡእን፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭና ሱንና ነው፡፡
ሐ. ከ ማቅሰኞ-ሀሙስ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህም በላጩ ነው፡፡
መ. ረቡእና ሀሙስን፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ 9ኛውን ቀን ጁምዓህ ለመፆም ያልተመቸው 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ይችላል፡፡
አላህ ይወፍቀን፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder

@Alhikem
@Alhikem
ከ 1400 አመት በፊት አንድ ሰው እንደሚወድህ ታውቃለህ? ገና አልተወለድክም ነበር
እሳቸው ግን አለቀሱልህ አላህን ምህረት ጠየቁልህ
ለአንተ ከጀነት ያነሰ ነገር አልተመኙልህም
ሚስቶች ልጆች ጓደኞች እና ቤተሰብ እያላቸው
ያ ዑመቲ ያ ዑመቲ እያሉ በናፍቆት ለአንተ አነቡልህ
የእውነተኛ ፍቅር መገለጫ ውዱ ነብያችን ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ.
ምንም ለማያውቅህ ኳስ ተጫዋች ወይ አክተር አድናቂ አትሁን
ከ 1400 አመት በፊት አንተን በመናፈቅ
ላለቀሱልህ የነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ አድናቂ ተከታይ ሁን
የእናት አባቴ ፍቅር ያረሱለላህ ሰ.ዐ.ወ ስላንቱ ትሰዋ ፊዳ ትሁኖት ሩሄ
ያማረ ጁምዐ ይሁንልን

@Alhikem @Alhikem
@Alhikem @Alhikem
ከሞትክ በኋላ ሰው አንተን የሚረሳበትን ፍጥነት ብታውቅ

የጌታህን ውዴታ ፍለጋ እንጂ ለሰው ልጅ ዉዴታ ባልኖርክ ነበር

@Alhikem
@Alhikem
የፈጅር ሰላት

👉ለፊት ብርሃን
👉ለልብ እርካታ
👉ለነፍስ መረጋጋት ነች፤

የሰገዳት ሰው
፦ እሱ በአላህ ጥበቃ ውስጥ ሆኖ ያመሻል።

" لا تنسوا سنة الفجر فهي خير من الدنيا ومافيها "

«የፈጅርን ሱና አትርሱ፣ እሷ ከዱንያ እና በውስጧ ካሉት በሙሉ በላጭ ናት።»

ምነኛ አማረ እሷን ጠብቆ የሚሰግድ ❤️

@Alhikem @Alhikem
@Alhikem @Alhikem
ከቁርአን ከሰላት ከዚክር የራቀ ሰው አይደለም አኼራው ዱንያውም ጭንቀት ነው

ቃለ ረሱል ሰ.ዐ.ወ

@Alhikem
@Alhikem
ወላሂ የኛ የሰው ልጆች ተግባር ግርም ነው የሚለው
ጀነት ያስገባል የተባለውን ስራ ትተን ጀሀነም በሚያስገቡ ስራዎች ተጠምደናል
አላህ ጀነት በሚያስገቡ ስራዎች ምንጠመድ ያድርገን😭😭
@Alhikem @Alhikem
@Alhikem @Alhikem
ሁሉም የአደም ልጆች ተሳሳቾች ናቸው ከተሳሳቾችም በላጮቹ ስተታቸውን አውቀው የሚመለሱ ናቸው።😭😭

አላሁ (ሱ.ወ) ስህተታቸውን አውቀው ከሚመለሱት ያድርገን
🍂ዶክተር ካሊድ አልጅበይር እንዲህ አለ!

☞6 ቀላል መንገዶች ከሞት ቡሃላ አጅርን ለማግኘት ።

1.በመስ ጂድ ላይ አንድ ቁርአን መተው ስዎች እንዲያነቡት ማመቻቸት!

2.በሆስፒታል ተንቀሳቃሸ ወንበር(ጋሪ) ለበሸተኞች መቀበያ ማስቀመጥ!

3.በመሰጊድ ግንባታ በአንድ ስሚንቶ ከረጢትም ቢሆን መሳተፉ!

4.በብዙሃን ህዝብ መገልገያ መሃከል የውሃ መጠጫ ጋን ማስቀመጥ!

5.ዛፉ መትከል በዛፏ የተጠቀመበት ሁላ አጅር ታገኝበታለህ !

6.ከዚህ ሁላ የሚቀለው ግን ይህንን ሜሴጅ ለሌላው ማስተላለፉ በስሩበት ልክ አጅሩን እዲያገኙ።
ውብ ምሽት ተመኘሁ😊

𝐉𝐨𝐢𝐧 ➪ @Alhikem
𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 ➪ @Alhikem
አምላኬ ሆይ በሌሎች ላይ የማየውን አስቀያሚ ነገር በራሴ ላይ ከመፈፀም ጠብቀኝ ።
@Alhikem
@Alhikem
የስልካቸውን የጥሪ ድምፅ
ስለሚወዱት ሲደወልላቸው ዘግይተው
የሚያነሱ ሰዎች አጋጥመዉኛል።

#አላህም ዱዓህን በቶሎ
የማይመልስልህ ያንተን ጥሪ ደጋግሞ
መስማት ፈልጎ እንደሆነ አስብ !!
በጣም ወደምትፈልገው ሰው ስትደውል
ስልኩ ዝግ ቢሆንብህና ጥሪ ባይቀበልም
……ኔትዎርክ ቢያስቸግርህም ተስፋ
ባለመቁረጥ ደጋግመህ ትሞክራለህ!

እንደዚሁ ሁሉም ከምንም ከማንም በላይ
ለሚያስፈልግህ ጌታህ ተደጋጋሚ የጥሪ
ሙከራህን አታቁም።

@Alhikem
@Alhikem
☞የሠዉ ልጂ ሁለት ግዜ አሏህ ፊት ይቆማል

①:::የመጀመርያዉ በዱንያ ላይ እያለህ የምትሠግደዉ ሷላት ነዉ

②::::የሁለተኛዉ የዉመልቂያማ ነዉ።

▼☞ የሁለተኛዉ አሏህ ፊት አቋቋምህ ያማረ እዲሆን ከፈለክ የመጀመርያዉን ☞አቋቋምህ አሳምር።

ኢብኑል ቀይም☞
@Alhikem @Alhikem
@Alhikem @Alhikem
📖:::::::ቁርአንን ስትቀራ::::::::📖

☞የአላህ እዝነት ይዘንብብሃል

☞ መላኢኮች ይከቡሃል

☞አላህ እርሱ ዘንድ ባሉት መላኢኮቹ ያወሳሃል

🤲 የአላህ ከቁርኣን ሰዎች አድርገን🤲

🍀🍀 ይህንን እድል ለማግኘት ኑ ከኛ ጋር ቁርኣንን በ 3 ወር ያኽትሙ🍀🍀


#ሼር......share

@Aliifquran
@Aliifquran
#ወሎ

#በአሁኑ ሰዓት ኢትዮ ውስጥ ላሉ ሙስሊሞች በተለይ በተለይ ለውሎ ሙስሊሞች ልናደርገው የሚገባ ዱዓእ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ በማለት ዱዓእ ያደርጉ ነበር
"አላህ ሆይ
ደካማ የሆኑ ሙስሊሞችን
ነፃ አድርጋቸው !!!!"
አሚንንን
---
#በዱዓ_ላይ_እንበርታ
~~~~
ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ
ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላል
" አጋሪዎች(ሙሽሪኮች) ጭንቅ በገጠማቸው ጊዜ አላህን ለምነው(ዱዓእ ) አድርገው ዱዓቸው ተቀባይነት ያገኝ ከነበር
➧አማኝ (ሙወሂድ) ከሆነ
(የበለጠ ተቀባይነት አለው።)

#ምንጭ [ጃሚዕ አልመሳኢል 1/71]
..🖋አቡ ዐብደላህ

በጭንቅ ላይ ላሉ ወንድሞቻችን በሙሉ ከሚያሰጨንቃቸው ከሚያሳስባቸው ነገር አላህ ነጃ ይበላቸው ።

#አደራችሁን በዱዓቹ እንዳትረሷቸው

@Aliifquran
@Aliifquran
አሊፍ ዘመናዊ የቁርኣን ንባብና የተጅዊድ ት/ቤት
አሊፍ ዘመናዊ የቁርኣን
ንባብና የተጅዊድ ት/ቤት

“እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር ቁርኣንን ቅዱሱ መንፈስ እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው።”

ኑ! ቁርኣንን በ 3 ወር ያኽትሙ!!!
አድራሻ፦ አዳማ
0962082444
0940221366
0937065664
https://hottg.com/Aliifquran
Forwarded from Ibnu seid
🎊 #ታላቅ_የምስራች 🎊

📿የተከበረውና የተወደደው የረመዷን ወር ሊገባ የቀሩት ትንሽ ቀናቶች ናቸው።

‼️ ረመዷንን ቁርኣን አኽትመው መቀበል ይፈልጋሉን?
‼️ አቀራርዎን በተጅዊድ አስተካክለው መቀበልስ?


▶️📶 እንግዲያውስ ወደ 👇
#አሊፍ_የቁርኣን_ንባብ_ማዕከል ጎራ ይበሉ።

‼️ከዚህ በፊት በማዕከሉ ብቻ ይሰጠው የነበረውን የቁርአንና የተጅዊድ ትምህርት 🏠 ከስራዎ ወይም ከትምህርቶ ሳይነፈናቀሉ ባሉበት ቦታ ሆነው በፈለጉት ሰዓት ......
#በኦንላይን አማካኝነት ትማሩ ዘንድ ብቅ ብሏል።
🔎አድራሻ ፦ 🏢አዳማ
#ከፖስታ ወደ መብራት በሚወስደው መንገድ አንበሳ ባንክ ያለበት ህንፃ 3ኛ ፎቅ

📞☎️ ለበለጠ መረጃ
                0962082444
                0940221366
                0937065664

አላማችን የቁርኣን አነባበብን ቀላል ማድረግ ነው።

📲ፈጥነው ይመዝገቡ

ለመመዝገብ👇👇👇
@Yebasitbariyanegh
@Slanchi

አሊፍ ዘመናዊ የቁርኣን ንባብና የተጅዊድ ት/ቤት
ሴት ልጅ የማትፈልገውን እንድታገባ ማስገደድ⁉️

🌐ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።
የትኛዋም ሴት የማትፈልገውን ሰው እንድታገባ ከተገደደች ኒካሁ ውድቅ (ተቀባይነት የሌለው) ነው። ያስገደዳት አካል ወንድሟም ይሁን አጎቷ፣ አባቷም ይሁን አያቷ ያው ነው። ማንኛውም ሰው አንድን ሴት የማትፈልገውን አካል እንድታገባ ማስገደድ አይችልም። ልክ እንደዚሁ አቻዋ የሆነና የምትፈልገው ሰው ከመጣ ወልዮቿ መከልከል እንደማይችሉ ሁሉ "የማትፈልገውን እንድታገባ" ማስገደድም አይችሉም።
📘(فتاوى اللقاء الشهري [20] /فتاوى المر
https://hottg.com/mewedaagencey
http://hottg.com/mewoda
HTML Embed Code:
2024/04/16 21:52:10
Back to Top