TG Telegram Group Link
Channel: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Back to Bottom
ኒካሕ ከመታሰሩ በፊት ከእጮኛው ጋር ዝሙት ፈጸመ። ከሱ ስታረግዝ ጊዜ ነፍሰ ጡር ሆና ሳለች ኒካሕ አሰሩለች። ፅንሱንም ወደ ሱው አስጠጉት። ነፍሰ ጡር እያለች ኒካሕ ማሰር ሑክሙ ምንድን ነው? ፅንሱንስ ወደሱ ማስጠጋት ይቻላል?

መልስ፦
ፅንሱ የሱ በመሆኑ ላይ እርግጠኝነት ከተገኘ ኒካሑን ከሷ ጋር ቢያስሩለት እና እሱንም እሷንም በዚህ ጉዳይ ላይ ቢሸፍኗቸው ችግር የለውም። ነገር ግን ከዚህ ጥፋት የሚገታቸው ትችትና እርምት ሊሰጣቸው ይገባል። የሆነ ሆኖ በትክክለኛው የዑለማእ አቋም ኒካሑ ልክ ነው። በጉዳዩ ላይ የሃሳብ ልዩነት ተከስቷል። ትክክለኛው ኒካሑ የፀና ሲሆን ፅንሱም ወደሱው ነው የሚጠጋው። ፅንሱ የራሱ መሆኑ ከተረጋገጠም ከሷ ጋር ግንኙነት መመስረቱም የሚፈቀድ ነው።

ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም
በቴሌግራም ከቀረበ ፈትዋቸው የቀረበ። https://hottg.com/ibnhezam/15997
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://hottg.com/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
ኺላፍ ያለባቸው የፊቅህ ርእሶች ላይ እኛ ከምናምንበት የተለየ ሃሳብ ሲነሳ አቅሙ ያለው በመረጃ ሃሳብ ያንሸራሽራል እንጂ ነገሮችን ያላግባብ ማክረርና ጉዳዩን ወደ ንትርክ መውሰድ አይገባም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://hottg.com/IbnuMunewor
በዑለማእ መካከል የሃሳብ ልዩነት የተንፀባረቀባቸው ብዙ የፊቅህ ርእሶች አሉ። ከፍ ከፍ ያሉ ሹሩሓትን የተመለከተ ሰው ይህንን በሰፊው ያውቃል። በመሰል ጉዳዮች ላይ እኛ ከያዝነው የተለየ አቋም ሲገጥመን ምን ማድረግ ነው ያለብን? አቋማችን በጠንካራ መረጃ የተደገፈ ከሆነ መረጃችንን አቅርበን የሳተውን አካል መመለስ ነው። ይህንን ስናደርግ ምናልባት ከጠበቅነው በተለየ መረጃ ያለው በዚያኛው በኩል ከሆነም ለመቀበል መዘጋጀት ያስፈልጋል። አንዳንዴ ደግሞ ጉዳዩ ላይ እኩል ድምዳሜ ላይኖረን ስለሚችል ሆደ ሰፊ ሆኖ መተላለፍ ነው። እንጂ "ምን ሲባል የተለየ ነገር ተነስቶ?" አይነት ቅሬታ ልናንፀባርቅ አይገባም።
ልብ በሉ! የማነሳው ስለ ፊቅሃዊ የኢጅቲሃድ ርእሶች ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://hottg.com/IbnuMunewor
"የፈለግከውን መልካም ስራ ብትሰራ በስራህ አትደነቅ። ባንተ ላይ ካለው የአላህ ሐቅ አንፃር ስራህ ትንሽ ነው።"
ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን
[ሸርሑ ሪያዲ አስሷሊሒን: 1/575]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://hottg.com/IbnuMunewor
Forwarded from የለተሞ መንጋን በመረጃ ማፈራረስ (أبو عبدالرحمٰن الأثري)
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
🟣 የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች!!

👆 እነዚህ በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ሁለቱ ሰዎች : አንደኛው የለየለት የአህባሽ አቀንቃኝ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሼይኽ አብዱልሀሚድ አል-ለተሚ አለኝታ የቅርብ ተማሪ የሆነው ቃሲም ሱልጣን የተባለ ግለሰብ ነው።

ይህ ግለሰብ በቅርቡ በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ በተደረገው የመጅሊስ አደረጃጀት ውሰጥ ገብቶ በአባልነት ተመርጧል , ከመመረጡም በፊት መጅሊስ ውስጥ ለመግባት ደብዳቤ ፅፎ በማስገባት ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ሰው ነው!

በምስሉ ላይ እንደተመለከታችሁ ቃሲም ሱልጣን ከአህባሹ ጋር ከመቀማመጥም አልፎ በአንድ ሳህን ላይ አብሮ እየበላ ነው!

በሶሻል ሚድያ ላይ የሚጮኸው ሳይሆን መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ይህ ከሆነ!!

👉 ለተሚዮች ሆይ : በእናንተ ቃዒዳ መሠረት ከሄድን ቃሲም ሱልጣን ከአህባሽ ጋር ተደምሯል አይደል!?

👉 በነሸምሱ ጉልታ ገለፃ መሠረት ተሽከርካሪ የስልጣን ወንበር ቃሲም ሱልጣንን አቋም አስቀይራ የኋልዮሽ አጡዘዋለች አይደል!!
ቃሲምን ብቻ ሳይሆን ዋና አለቃቸውን ሸይኽ አብዱልሃሚድን ጭምር ወንበሯ ጉድ ሰርታለች! ምክኒያቱም እሱም ብሆን መጅሊስ ውስጥ ገብቶ በአባልነት ተመርጧል !!

👉 ለተሚዮች ሆይ! ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥና መጅሊስ ውስጥ መግባት ከቢድዓ ሰዎች ጋር መደመር ከሆነ!  መጅሊስ ውስጥ ስለገቡ , ከሙብተዲዖች ጋር - አህባሽ ስሩሪይ- ጋር አብሮ እስከመብላት ድረስ ስለተቀማመጡ, ለሆዳቸው ሲሉ ተምር ፍለጋ ኢኽዋኖች ናቸው ከሚሏቸው ሰዎች ጋር ስለምላላሱ የእናንተ ሰዎች ምን እንበል?! እነርሱም ተደምረዋል ማለት ነው?!
ወይስ ለናንተ ስሆን ሁሉም ነገር ፍቁድ ሆኖ ለሌላ ሀራም ነው?!!
ሁለት መስፈሪያ ነው ያላችሁት?!

ለተሚዮች ባለፈው ሀዋሳ ላይ በግለሰብ ግቢ ላይ ድንኳን ጥለው ባካሄዱት ፕሮግራም ላይ ሼይኽ አብዱልሀሚድ የሚሾፍረው ሼይኽ ተብየው ሀሰን ገላው 20 የሙመይዓዎች መገለጫ በማለት ሀዋሳ ያሉ የሱና ወንድሞች እሱ የገለፃቸው ባህሪያት እንዳለባቸው በማስመሰል አጭበርብሮ ከሄደ በኋላ በወቅቱ የመድረሳ ስርዓትን ጥሶ ከተገኙ ልጆች ጋር ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት ተከትሎ ሀዋሳ ያሉ የለተሞ ጭፍሮች ከተብሊጎች ጋር ተሰብስበው እኛ እስካለንበት መስጂድ ድረስ መጥተው ሁከት በመፍጠር ከሙብተዲኦች ጋር መደመራቸውን በተግባር አሳይተውናል።

ስለዚህስ የተግባር መደመር ምን ትላላችሁ?! ወይስ የእናንተ ተዓውን እንጂ መደመር አይደለም?!

አቡ ሰህለህ ነኝ
https://hottg.com/Menhaje_Selef
መሪጌታዎች አጭበርባሪ ደጋሚዎች ናቸው። ድግምት ከኢስላም የሚያስወጣ ቆሻ ሻ ተግባር ነውና ልንርቀው ይገባል። ፌስቡክ ላይ ስታገኟቸው ብሎክ አድርጓቸው። በቴሌግራም ግሩፖቻቸው ውስጥ እንዳያስገቧችሁ setting አስተካክሉ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://hottg.com/IbnuMunewor
"ሁሉም ሰው በፖለቲካ ተጠምዷል። ፖለቲከኞች ሲቀሩ። እነሱ ግን በንግድ ነው የተጠመዱት።"
* ዐብዱል መሊክ አልኢብቢ *
·
·
መሪር ሐቅ!! አብዛኞቻችን የፖለቲካው ማእበል ወስዶን ከዚያ ከዚህ እያላጋን ነው። አንዳንዱማ ከሃይማኖቱ በላይ ዘሩን እያስቀደመ የቆሻሻ ፖለቲካ ጎርፍ ወስዶታል።
ፖለቲከኞቹስ? አብዛኞቹ የሞቀ ንግድ ላይ ናቸው። እንጀራቸውን ሊያበስሉ ተፍ ተፍ እያሉ ነው። ከመንግሥት በተቃዋሚ ስም፣ ከህዝብ በነፃነት ትግል ስም፣ ከውጭ በሰብአዊ መብት ቅስቀሳ ስም ከያቅጣጫው ይዘርፋሉ። ለምስኪን ተፈናቃዮች የተሰበሰበን እርዳታ ይነጥቃሉ።
በነሱ የፖለቲካ ጦስ የሚሞተው፣ የሚፈናቀለው፣ የሚጎዳው ግን ፖለቲከኞቹ ሳይሆኑ ህዝቡ ነው። ለዘመናት ተዋልዶ፣ ተጋምዶ የኖረ ህዝብ የፖለቲከኞች ድግምት ከተደገመበት በኋላ ፍፁም በማይታሰብ መልኩ አንዱ ሌላውን ያርዳል፤ ይሰቅላል፤ ያቃጥላል፤ ይወግራል፤ በጅምላ ያፈናቅላል። ፖለቲከኞቹ ግን በህዝብ እልቂት ገበያቸው ይደራል። በህዝብ መፈናቀል ንግዳቸው ይደምቃል። በኛ ስም በጮሁ ቁጥር ለኛ የተቆረቆሩ እየመሰለን ጆሯችንን እንሰጣቸዋለን። "ማንም በክፉ አይንካቸው" እንላለን። ፎቷቸውን አሳትመን እንለብሳለን፤ እንለጥፋለን፤ እንሰቅላለን። ግና ህዝብ እየከሳ እነሱ ይደልባሉ። ህዝብ እየተፈናቀለ እነሱ ለአይን ከሚያሳሳ ሰገነት መግለጫ ይሰጣሉ። የህዝብ ልጅ ወደ ትግል፣ የነሱ ልጆች ወደ ውድ ትምህርት ተቋማት። ህዝብ ወደ ታች እነሱ ወደ ላይ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 9/2011)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://hottg.com/IbnuMunewor
ከመግሪብ በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ።
የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል፡- https://hottg.com/IbnuMunewor
Live stream finished (1 hour)
Riyadh #152
Ibnu Munewor
ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣5️⃣2️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://hottg.com/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 457፣ ሐዲሥ ቁ. 1307
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://hottg.com/IbnuMunewor
ማስተማር ላይ እንበርታ
~
ዐብዱላህ ብኑል ሙባረክ ረሒመሁላህ "ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ነበር የምትሰራው?" ተብለው ቢጠየቁ "ሰዎችን አስተምር ነበር" ብለው መለሱ።

[አልመድኸል፣ ሊልበይሀቂይ፡ 2/45]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://hottg.com/IbnuMunewor
ሰሞኑን በአማራ ክልል ሙስሊሞች ላይ እየደረሱ ስላሉ ጉዳዮች ለምን ዝም አልክ ይለኛል አንዱ በውስጥ። በርግጥ ብዙ ነገሮችን እየሰማሁ ነው ዝም ያልኩት። ቢሆንም ስለ ሁለቱ ክልሎች ... ጉዳይ ከዚህ በኋላ ከነ ጭራሹ ምንም ላለማለት እያሰብኩ ነው። በሆነ ምክንያት ካልተቀየረ ቢያንስ ጊዜያዊ ስሜቴ ይሄ ነው። የሃገሪቱ ነገር እንደሆነ የሚጠበቅ ነው። አላህ ይሁነን እንጂ ገና ብዙ ግፍ ይሰማል። ብቻ በገዳዩ ፍቅር የተለከፈውን ነሆለል አላህ ያንቃው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://hottg.com/IbnuMunewor
ኹጥባ በተቻለ መጠን፡

* ቃላቱ የተከሸነ፣
* መጠኑ የተመጠነ፣
* መልክቱ ወቅቱን ያማከለ፣
* አቀራረቡ ታዳሚውን ያልዘነጋ ቢሆን መልካም ነው።
ኸጢቦች ሆይ! ሌላው ቢቀር ቢያንስ ሰዎች ውጭ ላይ ከባድ የቀትር ፀሐይ ቃጠሎ ሲያንቃቃቸው ወይም ዝናብ ሲዘንብ እንኳ ርህራሄ ቢኖራችሁ መልካም ነው። ሰዎች እየተከፉ ዒባዳቸውን እንዲፈፅሙ አታድርጉ። "ከናንተ ውስጥ አስበርጋጊዎች አሉ" የሚለውን ሐዲሥ አስታውሱ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://hottg.com/IbnuMunewor
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ጓደኛህ ማነው?
~
ጓደኛህ ወደ ተሻለ የምትወስደው ወይም ወደተሻለ የሚወስድህ ይሁን። ካልሆነ ግን ወይ ያጠፋሀል። ወይ ታጠፋዋለህ። ወይ ተያይዛችሁ ትጠፋላችሁ።
ሰው ውሎውን ይመስላል። ውሎህ የት ነው? ከማን ጋር? ሰዎች ጠጪ የሚሆኑት በጓደኛ ሰበብ ነው። ቃሚ፣ አጫሽ የሚሆኑትም በጓደኛ ተፅእኖ ነው። ያለ ምክንያት አይደለም "ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ" የሚባለው።
ከመጥፎ ሱስ መውጣት፣ ባህሪህን መግራት ትፈልጋለህ? ከልብህ ከሆነ ውሎህን አስተካክል። ልጅህ ከመጥፎ አዝማሚያ እንዲመለስ፣ መስመር እንዲይዝልህ ትፈልጋለህ? ሰበብ ሳታደርስ ጠዋት ማታ አትጨቃጨቅ። ይልቁንም ውሎው ላይ አጥብቀህ ስራ። ካልሆኑ ጓደኞች ጋር ገጥሞ ከሆነ የምትችለውን ሁሉ መስዋእትነት ከፍለህ ለየው።
ለብዙዎች በዲንም ይሁን በዱንያ መቃናት መልካም ጓደኛ ትልቅ ድርሻ አለው። እስኪ በህይወት ጉዟችሁ ላይ አነሰም በዛ ላገኛችሁ ስኬት ወይም መልካም ለውጥ አስተዋፅኦ ያላቸውን ጓደኞቻችሁን ለአፍታ አስቧቸው። በተቻለ መጠን ውለታ መላሽ ሁኑ። እሱ ቢቀር አመስጋኝ ሁኑ። ከዚያም በላይ በዱዓእ አስታውሷቸው።
ጓደኝነት ኣኺራን ከነጭራሹ ሊያጨልም፣ ኩ. ፍ. ር ላይ ሊጥል ይችላል። በጓደኛ ሰበብ ስንቶች ለተረዱት እውነት እጅ መስጠት አቅቷቸዋል?! በጓደኛ ሰበብ ስንቶች ውስጣቸው እያወቀ እምነት ቀይረዋል? ስንት ወንዶች ሴት ተከትለው፤ ስንት ሴቶችም ወንድ ተከትለው ዘላለማዊ ህይወታቸውን አጨልመዋል?! የተሰጠን እድል ከእጃችን ሳያፈተልክ፣ ነፍሳችን ሳትሾልክ በፊት ሳይመሽ እናስብበት። እንወስን በጊዜ። ነገ ፀፀት እንዳይበላን። ጌታችን እንዲህ ይላል:-
{ وَیَوۡمَ یَعَضُّ ٱلظَّالِمُ عَلَىٰ یَدَیۡهِ یَقُولُ یَـٰلَیۡتَنِی ٱتَّخَذۡتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِیلࣰا (27) یَـٰوَیۡلَتَىٰ لَیۡتَنِی لَمۡ أَتَّخِذۡ فُلَانًا خَلِیلࣰا (28) لَّقَدۡ أَضَلَّنِی عَنِ ٱلذِّكۡرِ بَعۡدَ إِذۡ جَاۤءَنِیۗ وَكَانَ ٱلشَّیۡطَـٰنُ لِلۡإِنسَـٰنِ خَذُولࣰا (29) }
{በዳይም፡ «ምነው ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ ዋ ምኞቴ!» እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)። «ዋ ጥፋቴ! ምነው እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ። (የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ» (ይላል)። ሰይጣንም ለሰው በጣም ለውርደት አጋላጭ ነው።} [አልፉርቃን፡ 27-29]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 2/2016)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://hottg.com/IbnuMunewor
ከመግሪብ በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ።
የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል፡- https://hottg.com/IbnuMunewor
Live stream finished (58 minutes)
HTML Embed Code:
2024/06/01 02:40:07
Back to Top